TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሪፖርት ፦

- በትግራይ አክሱም ከተማ ህዳር 19 እና 20፣ 2013 ዓ.ም በነበረው ውጊያ የኤርትራ ወታደሮች 110 ንጹሃን ሰዎች ገድለዋል።

• 70 ሰዎች በአክሱም ከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንገድ ላይ እያሉ ተደገድለዋል ከሟቾቹ ውስጥ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ነበሩ።

• 40 ንጹሃን ሰዎች የኤርትራ ወታደሮች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሰሳ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው እና በቤታቸው ውስጥ ተገድለዋል።

- በከተማዋ በርከት ያሉ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ደርሷል፥ ከእነዚህም ውስጥ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ብራና ሆቴል ይገኙበታል።

- ጠቅላይ አቃቤ ህግ በትግራይ በንጹሃን ግድያና በጾታ ጥቃት ላይ ትኩረት በማድረግ ባካሄደው ምርመራ፣ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የኢትዮጵያ ወታሮች ላይ ክስ መስርቷል።

- የጾታ ጥቃት እና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮች ክስ ተመስርቶባቸዋል።

* ሙሉ የአቃቤ ህግ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

#አል_ዓይን #የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል ተባሉ የመብት ጥሰቶችን በይፋ መመርመር እንደሚጀምር ገልጿል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን ምርመራ ፥ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሥራውን በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው።

በዚህም መሰረት በትግራይ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላም የጎረቤት ሀገራትን ሁኔታ ለማየት ይሞክራል።

ኮሚሽኑ ለ3 ወራት ሁኔታውን እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ የ3 ወራት ጊዜውም ሊታደስ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት እንዳለው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተናጠል ምርመራ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃውሟል።

መንግስት ተቃውሞውን የገለፀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ ፥ ኮሚሽኑ ብቻውን በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን እመረምራለሁ ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡

ነገር ግን ኮሚሽኑ ምርመራውን ማድረግ ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ማካሄድ ይችላል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት፤ የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ብቻዬን አካሂዳለሁ ያለውን የምርመራ ሂደት በአስቸኳይ #እንዲያቋርጥ ጠይቋል፡፡

#አል_ዓይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
#USA

አምባሳደር ሳተርፊልድ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ እኤአ ከጥር 17-20 ባሉት ቀናት ነው ሃገራቱን የሚጎበኙት፡፡

በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ አብረዋቸው ወደ ሃገራቱ እንደሚጓዙ ተገልጿል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ በሪያድ ቆይታቸው በሱዳን ያለውን ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁትን የለውጥ ኃይሎችን እንደሚያገኙና በመንግስታቱ ድርጅት አመቻችነት ለማካሄድ ስለታሰበው ሃገራዊ ውይይት እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡፡

ወደ ካርቱም ተጉዘው ከተለያዩ የለውጥና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር እንዲሁም ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር ይወያያሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

መንግስት የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል እንዲያጠናክር፣ የአየር ጥቃቶችን እንዲያቆም እና ሌሎችም መቃቃሮች እንዲያበቁ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩም ነው የተገለጸው፡፡

ተኩስ እንዲቆም፣ እስረኞች አሁንም እንዲለቀቁና ሰብዓዊ እርዳታዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲቀርቡ ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡

መረጃውን #አል_ዓይን_ኒውስ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ነው በድረገፁ ላይ ያስነበበው።

@tikvahethiopia