TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል ተባሉ የመብት ጥሰቶችን በይፋ መመርመር እንደሚጀምር ገልጿል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን ምርመራ ፥ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሥራውን በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው።

በዚህም መሰረት በትግራይ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላም የጎረቤት ሀገራትን ሁኔታ ለማየት ይሞክራል።

ኮሚሽኑ ለ3 ወራት ሁኔታውን እንደሚመረምር የገለጸ ሲሆን፤ የ3 ወራት ጊዜውም ሊታደስ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት እንዳለው ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተናጠል ምርመራ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃውሟል።

መንግስት ተቃውሞውን የገለፀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ ፥ ኮሚሽኑ ብቻውን በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን እመረምራለሁ ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡

ነገር ግን ኮሚሽኑ ምርመራውን ማድረግ ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ማካሄድ ይችላል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት፤ የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ብቻዬን አካሂዳለሁ ያለውን የምርመራ ሂደት በአስቸኳይ #እንዲያቋርጥ ጠይቋል፡፡

#አል_ዓይን_ኒውስ

@tikvahethiopia