የፀጥታው ምክር ቤት መግለጫ :
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በክልሉ ላለው ቀውስ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቋል፡፡
መግለጫው እንደሚገልፀው ፣ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ ዕርዳታን ለማቅረብ እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል፡፡
ነገር ግን የምክር ቤቱ አባላት የሰብዓዊ ችግሮች አሁንም መኖራቸውን እንደሚገነዘቡ እና በክልሉ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸውም ነው መግለጫው ያመለከተው፡፡
ከምግብ ዋስትና ጋር በተያያዘ የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር እንዳለበት እና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ለሁሉም የተቸገሩ ወገኖች ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ አስቸኳይ እርዳታ መርሆዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ሰብዓዊነትን ፣ ገለልተኛነትን እና ነፃነትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች እንዲቀጥሉ የፀጥታው ም / ቤት አባላት ጥሪ አቅርበዋል።
በትግራይ የተፈጠረው ፀጥታ ችግር ለቀጣይ የሰብአዊ አገልግሎቶች እንቅፋት መሆኑን በመግለጽ መደበኛ ሁኔታው እንዲመለስም አባላቱ መጠየቃቸው በመግለጫው ተካቷል ፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/UNSC-04-23
ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#UNHCR
የተመድ የስደተኞች ተቋም (UNHCR)፥ ከስድስት ወር በፊት በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የነበሩ 2 የስደተኞች ጣቢያዎች ከአገልገሎት ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ የስደተኞች መጠለያ ሊገነባ መሆኑን ለቢቢሲ አስታውቋል።
ተመድ (UNHCR) ከስደተኞችና የስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር በመሆን በትግራይ ክልል እንዲዘጉ በተደረጉት ሁለት የመጠለያ ጣብያዎች ምትክ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ ለመገንባት ቦታ የመለየት ስራ መከናወኑን ገልጿል።
ተመድ በስፍራው ላይ ለኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ለመገንባት ሕጋዊ ሰነዶች እስኪሟሉ እየጠበቀ ነው።
እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ የክረምቱ ወራት ከመጀመሩ በፊት ግንባታውን ለማካሄድ እና ስደተኞቹን በቦታው ለማስፈር እቅድ መያዙን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የፀጥታው ምክር ቤት መግለጫ : የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በክልሉ ላለው ቀውስ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቋል፡፡ መግለጫው እንደሚገልፀው ፣ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ ዕርዳታን ለማቅረብ እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እያደረገ…
የUN የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ያወጣውን የፕሬስ መግለጫ በተመለከተ በተመድ የኢፌድሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈ ቤት መግለጫ ሰጠ።
* ሙሉ የመግለጫው ሀሳብ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
* ሙሉ የመግለጫው ሀሳብ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Bahirdar
ባህር ዳር ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ፥ "ከተማችን ሰላም ናት ወደመደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች" ነው ያለው።

በአሶሳ አንድ ተሣቢ መኪና ሙሉ የጦር መሣሪያ ተይዟል ?
ትናንት በአሶሳ ከተማ "ባለቤቱ ያለታወቀ አንድ ተሣቢ መኪና የጦር መሣሪያ ተይዟል" በሚል ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተናፈሰው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
"በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው መረጃ ማንነታቸውን በደበቁ እና ድብቅ አጀንዳ ባነገቡ አካላት ነው" ያለው ፖሊስ ህብረተሰቡን በማደናገር እና በከተማው ያልተፈለገ ግርግር ለመፍጠር የታሰበ እንደሆነ ተረድቻለሁ ብሏል።
ወደ ከተማው ገባ የተባለው ተሽከርካሪ የንብረቱ ባለቤቶች ባሉበት ፍተሻ ሲያደርግ በመኪናው ውስጥ የነበረው በህጋዊ መንገድ እና ህጋዊ ሰውነት በፌደራል ተሰጥቶት የገባ የ"ወርቅ ማሽን" ነው ፤ ግለሰቦቹ የማሽኑን ህጋዊነት የሚያሳይ ሰነድ ይዘው መገኘታቸውም ተረጋግጧል ሲል አሳውቋል።
ህብረተሰቡ ምንጩ የማይታወቅ እና ያልተረጋገጠ መረጃዎች ይዘው ለማወናበድና የከተማውን ነዋሪ ወደ አልተፈለገ ሽብር ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን በመለየት እራሱን እንዲጠብቅ ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ አሳስቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#WorldBank
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩ ሶስት ፕሮጀክቶች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ አድርጓል።
ዛሬ አርብ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ናቸው የፈረሙት።
ስምምነቱ ሶስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ይወላል ተብሏል ፦
- የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።
- የ500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በሀገሪቱ ለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ካፒታል ተሳትፎንና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት የሚያስችል ነው ፤ ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚውለው የግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው፡፡
- የ207 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል ነው።
Via Ministry of Finance -Ethiopia

በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ላይ ያለ ህንጻ ተደርምሶ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ !
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ አንድ ህንፃ ተደርምሶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ካዛንቺስ ጁፒተር ሆቴል ፊት ለፊት በግንባታ ላይ የነበረ ህንፃ በመደርመሱ ነው የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።
የአዲስ አበባ አተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ፥ ከሟቾች በተጨማሪ በአደጋው ሶሰት ሰዎች ቀላል አንድ ሰው ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
አደጋው የተከሰተው ዛሬ ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በግንባታ ላይ የነበረ አንድ ህንፃ በመደርመሱ መሆኑንም ተናግረዋል።
በወቅቱ ከአደጋው ሰዎችን ለመታደግ 35 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፣ 3 ከባድና 4 ቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም 3 አምቡላንሶች መሰማራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በወቅቱ በቦታው ስራ ላይ የነበሩ 109 ሰዎችን ከአደጋው መታደግ መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBOT

#BREAKING የቻድ ፕሬዜዳንት ተገደሉ። ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡ ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው…
#update
“...ቻድን ማንም እንዲያስፈራራት አልፈቅድም” - የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት
የቀድሞ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ቀብር ስነስርዓት ዛሬ በትውልድ አካባቢያቸው አቅራቢያ ተፈፀመ።
የቀብር ስነስርዓቱ በትውልድ አካባቢያቸው ከመፈፀሙ ቀደም ብሎ በኒጃሚን በነበረ ስነስርዓት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቺሲዲኬ እና ሌሎችም ተገኘተው ነበር ፤ ምንም እንኳን አማፂያን የሀገራት መሪዎች በደህንነት ምክንያት በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳይገኙ ቢያስጠነቅቁም።
ፕሬዜዳንት ማክሮን ፥ በስነስዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ “ቻድን ማንም እንዲያስፈራራት አልፈቅድም” ሲሉ ተደምጠዋል።
ለቻድ መረጋጋት እና አንድነት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀው፥ ነገር ግን ወታደራዊ ተተኪዎቹ ወደሲቪል አስተዳደር በሰላም እንዲመለሱ አሳስበዋል።
የቀድሞ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ባለፈው ሰኞ ዕለት በሃገሪቱ ሰሚናዊ ክፍለ ግዛት ከአማጽያኑ ጋር የሚዋጉትን ወታደሮች በውጊያው ግንባር ተገኝተው በመጎብኘት ላይ ሳሉ ቆስለው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

#NEBE
ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ከሃገሪቱ የምርጫ ህግና የስነ ምግባር አዋጅ በተጻረረ መልኩ "ለአመጽ የሚጋብዝና በግለሰቦች ወይም ቡድኖች ላይ ስጋትን የሚያጭር ቋንቋ" ን የሚጠቀሙ ፓርቲዎች እና እጩዎችን አሳስቧል።
ፓርቲዎች እና እጩዎች ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮች እና ድርጊቶች እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡ ህጉ የማይከበር ከሆነ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳስቧል።
* የምርጫ ቦርድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ።
የመራጮች ምዝገባ መራዘምን አስመልክቶ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጥቷል።
ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ቀን ማጠናቀቂያ ዛሬ መሆኑን ተከትሎ የስራ ሂደቱን ያጋጠሙትን ችግሮች መመርመሩን ገልጿል።
በዚህም መሰረት ፦
1. የመራጮች ምዝገባ በግማሽ የአገሪቱ ክፍሎች ዘግይቶ በመጀመሩ
2. በጊዜው በተጀመረባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ መረጃዎች እጦት እና በሌሎች ምክንያቶች ለመመዝገብ ጊዜ በመውሰዱ
3. የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቁ በቀሩት ጥቂት ቀናት በአንድ ምርጫ ጣቢያ 1500 ሰው ብቻ መመዝገብ በመቻሉ የተነሳ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በሚገኙ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ በመቋረጡ እና ተጨማሪ ምርጫ ጣቢያዎች በመክፈት ሂደት ክፍተት በመፈጠሩ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወስኗል።
በዚህም መሰረት ፦
1. የመራጮች ምዝገባ እጅግ ዘግይቶ በጀመረባቸው በአፋር እና በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ለሶስት ሳምንት ተራዝሟል ። ይህም ማለት የመራጮች ምዝገባ ግንቦት 06 ቀን 2013 የሚጠናቀቅ ይሆናል።
2. የመራጮች ምዝገባ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በተስተጓጎለባቸው ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ለሁለት ሳምንት ተራዝሟል ይህም ማለት የመራጮች ምዝገባ ሚያዝያ 29 ቀን 2013 የሚጠናቀቅ ይሆናል።
3. የመራጮች ምዝገባ እስካሁን ድረስ ባልተጀመረባቸው እና የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ እና ቄለም ወለጋ የመራጮች ምዝገባን የማስጀመር እንቅስቃሴዎችን እየተደረገ ይገኛል።
4. 1500 ሰዎቸን መዝግበው በጨረሱ ምርጫ ጣቢያዎች ተጨማሪ ንኡስ ምርጫ ጣቢያዎችን መክፈት የሚቀጥል ይሆናል።
* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

ምን ያህል ዜጎች ለምርጫ ተመዘገቡ ?
እንደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እስከ ትላትንና ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 18 ሚልዮን 427 ሺህ 239 ዜጎች (18,427,239) የተመዘገቡ ሲሆን በ41,659 ምርጫ ጣቢያዎች ነው መራጮች እየተመዘገቡ የሚገኙት።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
እንደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እስከ ትላትንና ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 18 ሚልዮን 427 ሺህ 239 ዜጎች (18,427,239) የተመዘገቡ ሲሆን በ41,659 ምርጫ ጣቢያዎች ነው መራጮች እየተመዘገቡ የሚገኙት።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ETHIOPIA😷
ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ወደ 250 ሺህ ተጠግቷል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 6,581 የላብራቶሪ ምርመራ 1, 303 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 249,292 ደርሰዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,511 ደርሷል።
ትላንት 2,973 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ያገገሙ 188,080 ደርሰዋል።
አሁን ላይ 968 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia

"...የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ የስራ ገበያን መሰረት ያደረገ ይሆናል" - MoSHE
በመጀመሪያ ዲግሪ በሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች ከአቅርቦት እና ገበያ አንፃር ያለባቸውን ችግር የሚዳስስ የስራ ገበያ ሁኔታ ጥናት እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት በ2014 የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ገበያን መሰረት ያደረገ የተማሪዎች ቅበላ ይደረጋል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።
ይህ የተገለፀው ዛሬ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት ነው።
ምክር ቤቱ ከ200 በላይ የሙያ ማህበራትን ያካተተ ሲሆን በትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ አተኩሮ ይሰራል ነው የተባለው።
የም/ቤቱ መመስረት ለትምህርት ጥራትና አግባብነት ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው ከመሆኑ ባለፈ ከስርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ ተማሪዎችን ለማብቃት በጋራ መስራት እንደሚያስችል ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በገለልተኝነት የሚሰራ ቢሆንም የትምህርት ጥራት እና አግባብነትን ለማረጋገጥ ከMoSHE ተባብሮ እንደሚሰራ ተገልጿል።
ም/ቤቱ የምሩቃን ምዘና፣የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያና የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ሲመዘን ሚናውን እንደሚወጣ ተገልጿል።
ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር በመጀመሪያ ዲግሪ በሚሰጡ 211 የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ከአቅርቦትና ገበያ ጋር ያላቸውን ችግር ለመዳሰስ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
በቅድመ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች የስራ ገበያ ሁኔታ ጥናት መሰረት በቀጣዩ የ2014 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅበላ የሚከናወን ይሆናል። ~ ENA

የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦
[ በ Purpose የቀረበ ]
- ትላንት በመላው ዓለም 891,268 ሰዎች ለቫይረሱ ታጋላጭ መሆናቸው ሲረጋገጥ ፤ 14,247 ሰዎች ሞተዋል።
- ህንድ ትላንት ብቻ 345,147 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች፤ በ24 ሰዓት 2,621 ሰዎች ሞተዋል።
- በብራዚል በ24 ሰዓት 2,866 ሰዎች ሲሞቱ፥ 65,971 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች።
- በ24 ሰዓት በርካታ ሰዎችን ከሞቱባቸው ሀገራት መካከል : አሜሪካ 790 ፣ ፖላንድ 539 ፣ አርጀንቲና 556፣ ኢራን 380፣ ፔሩ 408፣ ዩክሬን 434፣ ሩሲያ 398 ፣ ፈረንሳይ 332 ፣ ጣልያን 342 ፣ ቱርክ 343 ፣ ኮሎምቢያ 420 ፣ ሜክሲኮ 498 ይጠቀሳሉ።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች 146,277,103 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 3,100,405 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል 124,075,915 አገግመዋል።
- በአፍሪካ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 4,525,278 የደረሰ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ በማስመዝገብ ደቡብ አፍሪካ በ1,572,985 ቀዳሚ ናት፣ ሞሮኮ በ508,530 ፣ ቱኒዝያ በ296,343 ፣ ኢትዮጵያ በ249,292 ይከተላሉ።