TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...ታጣቂዎች የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተቆጣጥረውታል" - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፣ ከማሺ ዞን የሚገኘውና ከ25 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙበት የሴዳል ወረዳ "ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ "፣ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ/ም. ጀምሮ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የደረሱት መረጃዎች እንዳመለከቱ አሳወቀ።

ኢሰመኮ ይህን ያሳወቀው ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ነው።

ኮሚሽኑ ፥ በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች መሸሻቸውን እንደተረዳ ገልጿል።

ታጣቂ ቡድኑ የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችን ማቃጠሉን ፤ ነዋሪችን፣ የወረዳውን እና የዞን አመራሮችን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን መግደሉን እና ማገቱም ተገልጿል።

ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በአቅራቢያው ያለው የፀጥታ ኃይል ከአቅሙ በላይ እንደሆነና ተጨማሪ የተላከው ኃይልም ወደ አካባቢው እንዳልደረሰ ገልፀዋል።

ይህ ክስተት በክልሉ የቆየው የጸጥታ ችግር እየተባባሰ እና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት የሚያሳድር ነው ብሏል ኢሰመኮ።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን በመግለፅ ፥ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን አሳውቋል።

ኢሰመኮ መንግስት በአፋጣኝ የአካባቢውና የክልሉን የፀጥታ ኃይል እንዲያጠናክርና እና ተጨማሪ የሰዎች ሞት እና የከፋ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Update

አራተኛ ቀኑን የያዘው የአማራ ክልል የተቃውሞ ሰልፍ አድማሱን አስፍቶ ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል።

በአማራ (አጣየና አካባቢው) እንዲሁም ከአማራ ክልል ውጭ በኦሮሚያ (ወለጋ)፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ (መተከል) ፣ በደቡብ (ጉራ ፈርዳ) የአማራ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ይቁም በሚል የሚደረጉት ሰልፎች ከቀን ወደ ቀን አድማሳቸው እየሰፋ መጥቷል።

ዛሬ በአራተኛ ቀን የተቃውሞ ሰልፍ ፥ ጎንደር ፣ መራዊ ፣ መርሳ ፣ አዴት ፣ ደብረብርሃን (ለሁለተኛ ቀን) ፣እንጅባራ፣ ኮምቦልቻ ፣ ሞጣ ፣ ደብረታቦር ፣ ቆቦ በርካቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን ለማውቅ ተችሏል።

ተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊዎች ጥያቄ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ሰልፎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የሚፈፀሙት ግድያዎች፣ ማሳደዶች፣ ማፈናቀሎች፣ ንብረት ማውደሞች ይቁሙ የሚል ነው።

በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ መንግስትን የዜጎቹን በሰላም የመኖር ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱት የሚያወግዙ የተለያዩ መልዕክቶች እየተላለፉ መሆኑን ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
#Update

ባለፉት ቀናት የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፎችን ያስተናገደችው የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ዛሬ የእንቅስቃሴ አድማ ውስጥ መሆኗን የባህር ዳር ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ስራ ቆሟል፣ እንቅስቃሴም የለም ፤ ትላንት በከፊል ነበር ዛሬ ግን የለም፤ ከተማው ጭር ብሏል ሲሉ አሳውቀዋል።

የስራ ማቆም አድማ የሰልፎቹ ተከታይ ሲሆን ዋነኛው ዓለማው ደግሞ የሚፈፀሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎች መቃወም እና መፍትሄ እንዲፈለግ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምን ይላል ?

የባህር ዳር አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ፥ በኦሮሚያ [ወለጋ ዞን] ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ [መተከል] ፣ አማራ [ሰሜን ሸዋ ዞን] በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በደረሰው ህይወት መጥፋት ፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት ሃዘን እንደተሰማው ገልጾ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ተወለጆችን ሰርተው ለመለወጥ በሚታትሩበት ወቅት በማንነታቸው እየተለዩ መገደል አረመኔነት ነው ብሎታል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በከተማው ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን አሳውቆ ፥ ነገር ግን የሰልፉ አላማ ሞት እና መፈናቀል ይቁም የሚል ቢሆንም "አንዳንድ ፅንፈኞችና የወቅቱን የክልሉን እና አማራን ህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ያልተረዱ ሰላማዊ ሰልፉን ለማበላሸት ሙከራ ሲያደርጉ ነበር" ብሏል።

"በሰልፉ ላይ የክልሉን እና የከተማውን ህዝብ የማይመጥኑ ንግግሮች ፣ ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን የሚያሸማቅቁ መፈክሮችና የክልሉ አመራሮች ስብዕና የሚነኩ መፈክሮች እና ንግግሮች ፣ በፀጥታ አካላት ላይ የታዬ ማንጓጠጥ እና ማመናጨቅ ፣አመራሩን ለመከፋፈል አንዱን በማኮሰስ ፣ሌላውን በማጀገን የተደረገው ቅስቀሳ ፍፁም ስህተት ነው" ሲል ገልጿል።

More : telegra.ph/Tikvah-Bahirdar-04-22

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ለፀጥታ ስጋት አጠራጣሪ ለሆኑ ጉዳዮች ጥቆማ መስጫ ስልክ ቁጥሮች ፦

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህብረተሰቡ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮችን በሚመለከትበት ወቅት ከታች በተዘረዘሩት የስልክ ቁጥሮች አማካኝነት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

- ልደታ ክፍለ ከተማ - 0118578492
- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ- 0118578501
- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ - 0118578499
- ቦሌ ክፍለ ከተማ - 0118578509
- የካ ክፍለ ከተማ - 0118578491
- ቃለቲ ክፍለ ከተማ - 0118578507
- ላፍቶ ክፍለ ከተማ - 0118578503
- ጉለሌ ክፍለ ከተማ - 0118578505
- አራዳ ክፍለ ከተማ - 0118578511
- ኮልፌ ክፍለ ከተማ - 0118578508

ሀገር አቀፍ የ24 ሰዓት መረጃ መቀበያ ፦

- 0115526302
- 816, 987
- 0115526303
- 0115524077
- 0115543678
- 0115543681

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም ተጠቆመ።

በምርጫው ሂደት አስካሁን የነበሩትን ክንውኖች በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ “የኢትዮጵያ ጠላቶች ምርጫውን ለማስተጓጎል፣ ደካማና የሚያዙት መንግስት ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል” ብለዋል።

የዘንድሮው 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ “ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየሠራን ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

በውይይቱ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በምርጫው ሂደት የእስካሁኑን ክንውን ሪፖርት አቅርበዋል። በእስካሁኑ ሂደት የመራጮች ምዝገባ ተሳትፎ በጥሩ ሁኔታ የተከናወነባቸው ክልሎች መኖራቸው ተመልክቷል።

በሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የመራጮች ምዝገባ “ከ80 በመቶ በላይ” አፈፃፀም መኖሩን አብራርተዋል።

በሌሎች ክልሎችም የመራጮች ምዝግባ አፈፃፀም ከ50 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመራጮች ምዝገባ እንደሚራዘም ጠቁመዋል።

ተጨማሪው ቀን ምን ያክል እንደሚሆን ግን ቦርዱ ተወያይቶ የሚወስን እና የሚያሳውቅ መሆኑን ሰብሳቢዋ መገለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የጭልጋና አካባቢው የፀጥታ ችግር :

በአይከል እና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ነዋሪዎቹ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል።

አይከል ከተማ ውስጥ ከሁለት ሳምንት በላይ መብራት የለም፣ ኔትዎርክ የለም ፣ ውሃ የለም።

ችግር የተፈጠረው በአይከል ብቻ ሳይሆን በዙሪያ ባሉ አካባቢዎችም ጭምር ነው።

አንድ ቤተሰቦቹ እዛው የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ በሳርጥያ፣ ወርቀየ ፣ እያሁ ማይርያ ቀበሌዎች ሰዎች ተገድለዋል። ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸዋል።

አይከል ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

ይኸው የቤተሰባችን አባል ፥ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጆች ፣ አያቱ በእሳት እንደተቃጠሉ እንደተነገረው ነግሮናል።
ከእሱ ቤተሰቦች ብቻ በርካቶቹ እንደሞቱበት ገልጿል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ ኃይል መጥቶ በከባድ መሳሪያ ጥቃት እንደፈፀመ፥ ከሟቾቹ መካከል ደግሞ ህፃናት እንደሚገኙበት አስረድቷል።

ምንም ጉዳዩን የማያውቁ ንፁሃን ጭምር የጥይት እራት ሆነዋል፤ ያለው ነገር እጅግ የሚያሳዝን ነው ብሏል።
ከምንም በላይ ደግሞ ህዝቡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ እየታወቀ ምንም ሚዲያ አለማውራቱ ልብ ይሰብራል ሲል ተናግሯል።

https://telegra.ph/Tikvah-Chilga-04-29

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአብን እጩ ተገደሉ። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበሩት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) አባል አቶ በሪሁን አስፈራው በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ እንደተፈፀመባቸው ፓርቲው አስታውቋል። አቶ በሪሁን ግድያ የተፈፀመባቸው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያሉ ልዩ ቦታው "ካርባር" በሚባል ቦታ ላይ መሆኑ ተገልጿል። ፓርቲው በተፈፀመው…
የአብን ፓርቲ አባል ተገደሉ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የወጣቶች አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አማኑኤል ጥሩነህ ትላንት ሚያዚያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በጥይት ተመተው ሕይወታቸው ማለፉን ፓርቲው ዛሬ አሳውቋል።

አብን በአባሉ ግድያ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ በየደረጃው በሚገኙ አባሎቹ እና አመራሮቹ ላይ የሚፈፀመውን ግድያ፣ ወከባ እና እስር አውግዟል።

አብን ፥ መንግስት በፓርቲው አባሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ ለህዝብ እንዲሰጥ ጠይቋል።

በሌላ በኩል ፦

አብን ከአሁን ቀደም ፥ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበሩት አባሉ አቶ በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመባቸው መሆኑን መግለፁን አስታውሶ ፥ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ለጠየቀው ጥያቄ እስከአሁን ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና እያሳደረው ያለው ጫና ፦

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ እያሳደረ ያለው የኢኮኖሚ ጫና እየበረታ ነው።

ከታማሚዎች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞም የህክምና ግብአቶች እጥረት እያጋጠመ ነው።

1 የጤና ባለሞያ ለታካሚዎቹ በሚሰጠው አገልግሎት ለብሶ የሚገባው አልባሳት ከአንድ ጊዜ በላይ የሚለበስ ባለመሆኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ ከ160,000 ብር በላይ የሚገመቱ የጤና አገልግሎት መስጫ አልባሳት በሚሊኒየም የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ወጪ ይደረጋል።

በሚሊኒየም ማዕከል የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ናኦል አሉላ ፥ ያለውን ጫና ለ #አዲስ_ቴሌቪዥን አስረድተዋል።

በፅኑ ህሙማን ክፍል /በማሽን እየተነፈሱ ያሉ ታማሚዎች ጋር የሚገቡ የጤና ባለሞያዎች የሚያደርጓቸው የ coverall ሂሳብ የአንዱ ብቻ ከ3500 እስከ 4000 ብር ይደርሳል።

ICU ክፍል /ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገባ ሁሉ coverall አድርጎ ነው የሚገባው።

በተጨማሪ face shield፣ N95 ማስክ (ከሰርጂካል ማስክ ተጨማሪ) ፣ ቡትስ ያደርጋል። መመሪያው እና ፕሮቶኮሉም የሚያዘው ይህንኑ ነው።

በቀን ውስጥ ወደ 200 - 400 ሰው የሚገባ ሲሆን የአንዱ coverall ዋጋ ከ3,500 - 4000 ብር ሌሎችም መከላከያዎች ተዳምረው በትንሹ 4 ሺህ ብር ይጠጋል ፥ ይህም በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 160,000 ብር ወጪ እንዲሆን ያደርጋል።

የታማሚዎች ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሚወጣው ወጪ በዛው ልክ እየጨመረ ይመጣል፣የቁሳቁስ እጥረትም ይከሰታል ብለዋል አቶ ናኦል አሉላ።

ዜጎች ያለውን ሁኔታ በመገንዘብ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንደሀገር፣ እንደተቋም እየወጣ ያለውን ወጪ ለመቀነስ እራሱን እና ቤተሰቡን ከበሽታው መጠበቅ አለበት።

ሚዲያዎችን እንደ ቀድሞ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
ከጤና ተቋማት ተምረውና ተመርቀው የሚወጡ የጤና ባለሙያዎችን ወደሥራ ለማስገባት አማራጭ መንገዶች መለየታቸው ተገለፀ !

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ ከተለያዩ የጤና ተቋማት ተምረውና ተመርቀው የሚወጡ ባለሙያዎችን ወደሥራ ለማሰማራትና ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት ሶስት ዋና ዋና አማራጭ መንገዶች መለየታቸውን አሳወቁ።

ዶ/ር ሊያ ይህን ያሳወቁት ዛሬ ጤና ሚኒስቴር ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረመበት ወቅት ነው።

ከተለያዩ የጤና ተቋማት ተምረውና ተመርቀው የሚወጡ ባለሙያዎችን ፦

- በአገር ውስጥ ሥራ ማስያዝ፣
- የውጭ ሀገራት የሥራ ዕድሎችንና አማራጮችን ማመቻቸት - አዳዲስ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴሎች ላይ መሰማራት እንዲችሉ የማመቻቸት ሥራዎችን በመሥራት ባለሞያዎች በተናጠል ሆነ በጋራ ተቋም መስርተው እንዲሰሩ ማድረግ ዋና ዋና አማራጭ ተብለው የተጠቀሱ ናቸው።

አዳዲስ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሞዴሎች እንዲፈቀዱ በማድረግ ለመተግበር እንዲቻል የተለያዩ አገራትን ልምድ በመቀመር የጤና ባለሞያዎች በተናጠል ሆነ በጋራ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችሉ መመሪያዎች የማዘጋጀት ሥራ የተጠናቀቀ መሆኑን ዶ/ር ሊያ አሳውቀዋል።

የቤት ውስጥ የጤና አገልግሎት (Homebased Care) እና በስልክ ጥሪ የሚደረጉ የጤና ድጋፎች (Telemedicine) መመሪያ ክለሳ መደረጉን ገልፀዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
"...ይህ ሁሉ ውድመት ሲከሰት የጸጥታ ኃይላችን የት ነበር ? የመረጃ እና የደኀንነት መዋቅራችን የት ነበር ? የሚለውን እያጣራን ነው" - አቶ አገኘሁ ተሻገር

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሰሞኑን በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰው ጥፋት ጥቃት ፈፃሚዎችን ለሕግ ለማቅረብ ከፌዴራል የጸጥታ ኀይል ጋር በጋራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

አቶ አገኘሁ ይህን ያሉት ዛሬ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ፕሬዝዳንቱ ፥ በሁለቱ ዞኖች በተፈፀመው ጥቃት የመንግሥት መዋቅር ጭምር መሳተፉን ገልፀዋል።

"እኛም መዋቅራችንን እየፈተሽን ነው ፣ ይህ ሁሉ ውድመት ሲከሰት የጸጥታ ኀይላችን የት ነበር፣ የመረጃ እና የደኀንነት መዋቅራችን የት ነበር የሚለውን እያጣራን ነው" ብለዋል።

አቶ አገኘሁ ፥ ማንነትን መሰረት አድርጎ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት በሰላማዊ እና በሰለጠ መንገድ መግለጹ ተገቢ መሆኑን ተናግረው፤ ሰላማዊ ሰልፎች በአብዛኛው ሰላማዊ እንደነበሩ ተናግረዋል።

ሰልፎቹ ላይ ግን የተሳሳተ መልዕክት ለማስተላለፍ ጥረት መደረገን ዛሬ ደግሞ በባህር ዳር ከተማ የዝርፊያ እና የንግድ ተቋማትን የመዝጋት ሙከራዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

አሁን ላይ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደነበረበት እንደተመለሰ ነው ብለዋል።

More : https://telegra.ph/AMC-04-22

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,041 የላብራቶሪ ምርመራ 1,505 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,175 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 247,989 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,496 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 185,107 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 999 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ሙሃመድ ዴክሲሶ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቅ ይገባል" - ኢሰመኮ ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 1 ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኘውን ሙሃመድ ዴክሲሶ በተመለከተ የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋስ እንዲለቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ከእስር አለመለቀቁ እንዳሳሰበው ገልጾ፣ ሙሃመድ ዴክሲሶን ጨምሮ ሌሎችም በፍርድ ቤት የዋስትና…
'መሀመድ ዴክሲሶ ያለበት አይታወቅም'

• "...የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው ስድስት ሆነው መጥተው ነው በፓትሮል የወሰዱት ከዛ ቀን ጀምሮ እዚህ ነው የሚል ተጨባጭ መረጃ የለንም።" - አቶ ሱልጣን ዴክሲሶ

• "... እኛም ያለበትን ቦታ ማወቅ አልቻልንም" - ኢሰመኮ

የካቲት 6/2013 ዓ/ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሚያስመርቅበት መድረክ ላይ እነ አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች ከእስር እንዲፈቱ የጠየቀው መሃመድ ዴክሲሶ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥሯል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ከተመሰረተበት ወዲህ ከእስር አልተለቀም።

የመሀመድ ቤተሰቦች ፥ ፍርድ ቤት ከአንድም ሁለት ጊዜ ቢያሰናብተውም እስካሁን ሳይለቀቅ ቀርቷል ብለዋል።

የመሀመድ ዴክሲሶ ወንድም አቶ ሱልጣን ዴክሲሶ ለጀርመን ድምፅ እንደተናገሩት ከሆነ ፥ አሁን ላይ መሀመድ ዴክሲሶ ያለበትን ቤተሰቦቹ አያውቁም።

አቶ ሱልጣን ፥ " ... በምርቃት ቀኑ እዛው በመድረክ ላይ ድምፁን ካሰማ በኃላ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው፤ ከዛም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነው የተወሰደው ፤ ከዛ ፍርድ ቀርቦ ነበር፤ ከዛ በኃላ ባልታወቀ ምክንያት ልዩ ኃይል በሚባለው ተወሰደ ፤ ከተወሰደ ወዲህ ዛሬ 3 ሳምንት አልፎታል ፤ እዚህ ነው ያለው፤ በዚህ ሁኔታ ነው ያለው የሚለውን እንደቤተሰብ እኛ ምንም የምናውቀው ነገር የለም" ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢስመኮ) የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አማካሪ ኢማድ አብዱልፈታህ እንደተናገሩት፥ መሀመድ ዴክሲሶ አሁን ያለበትን ስፍራ ለማወቅ የተለያዩ የመንግስት መዋቅሮችን ጠይቆ ለመረዳት ቢሞከርም ይህ ከኮሚሽኑ አቅም በላይ መሆኑን ነው የገለፁት።

ያንብቡ : telegra.ph/Mohaammad-Deeksisoo-04-22

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia