TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrTedrosAdhanom

የWHO ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለምን የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት ለራሳቸው ብቻ የሚሰበስቡ ሃገሮች አጥብቀው ነቅፈዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ፥ በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፋቸው ክትባቱን ማግኘት ለሚቸግራቸው ሃገሮች ለማቅረብ በዓለም የጤና ድርጅት አሰባሳቢነት በተቋቋመው በኮቫክስ አማካይነት የሚደረገውን ጥረት “ክትባት ለራስ ሃገር ብቻ መሰብሰብ" ሲሉ በገለጹት አድራጎት ጥረቱ እየተዳከመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ጥቂት ከበርቴ ሃገሮች የሚመረቱ ክትባቶችን የበለጠ ዋጋ ለሚከፍላቸው ከሚሸጡ ኩባኒያዎች ላይ ተቀራምተው በመግዛት የሚያግበሰብሱበት ሌሎች ትርፍራፊው የሚቃርሙበት ሁኔታ እየታየ ነው ብለዋል።

አያያዘውም ወረርሽኙን ለመዋጋት መፍትሄው ቀላል ነው ፣ ያም ማካፈል ወይስ አለማካፈል ከሁለት አንዱን የመምረጥ ጉዳይ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አስከትለውም በዚያ ደግሞ የሚፈተነው ሳይንስ ወይም የኢኮኖሚ እና የኢንዱስትሪ አቅም ሳይሆን የሚፈተነው ማንነታችን ነው" ማለታቸውን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ምርጫ2013 አጭር ቁጥራዊ መረጃ ፦

[ በ www.ethiopiaindider.com የቀረበ ]

- እስከሚያዝያ 14 ቀን 2013 ድረስ ባለው ጊዜ 18,427,239 መራጮች ተመዝግበዋል። 41,659 ምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን እየመዘገቡ ይገኛሉ።

- በአዲስ አበባ ከተማ ይመዘገባል ተብሎ የሚጠበቀው ሰው 1,405,650 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1,234,802 ያህሉ መመዝገቡን ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል። (ከሳምንት በፊት ምርጫ ቦርድ ባወጣው መረጃ በአ/አ ለመራጭነት የተመዘገቡ ሰዎች 200,903 እንደሆነ መግለፁ አይዘነጋም)

- በአማራ ክልል ከ5 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አቶ አገኘሁ ተባገር ተናግረዋል ፤ በአማራ እስካለፈው ሳምንት የተመዘገበው መራጭ ብዛት 1 ሚሊዮን እንኳን የማይሞላ ነበር ብለዋል።

- በኦሮሚያ ይመዘገባሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰዎች ብዛት 16 ሚሊዮን 500 ሺ ሲሆን እስካሁን የተመዘገቡት 12,347,537 መሆናቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል። ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ውጭ ባሉ 17 ዞኖች ውስጥ ለመራጭነት ይመዘገባሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ 85 በመቶ ያህሉ መመዝገባቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ፣ የደህንነት እና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT
#UnitedStates

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትላንት ጄፍሪ ፌልትማን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ተደርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል።

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ላይ አገልግለዋል።

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

አዲሱ የኃላፊነት ስፍራ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተፈጠረ ነው።

- በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ
- በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል ያለውን አለመግባባት በቅርበት ለመከታተል የታለመ መሆኑ ታውቋል።

አንቶኒ ብሊንከን ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " አሁን ላይ አሜሪካን የሚያሳስበው ነገር ቢኖር የትግራይን ግጭትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያለው ተለዋዋጭ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለው የመጣ የድንበር ውጥረት እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ውዝግብ ነው" ብለዋል።

ጄፍሪ ፌልትማን ፤ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውም የባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተያያዥ የሆኑትን ፖለቲካዊ፣ የደኅንነትና የሰብአዊ ጉዳዮች ምፍትሔ እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት አስታውቀዋል።

Via Al ALIN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...የፀጥታ ኃይሎች የጸጥታ ችግር ያለበት ቦታው የሚደርሱት ህይወት ከጠፋና ረብሻ ከተነሳ በኋላ ነው" - ዶክተር ራሄል ባፌ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የጸጥታ ሀይሎችና የደህንነት ተቋማት የሰው ህይወት ከጠፋ በኋላ የሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ስራ ሊታረም ይገባል ሲል አሳሰበ፡፡

ም/ቤቱ በወቅታዊ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ላይ፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ተቋም ወቅቱን የጠበቀ የቅድመ ማስጠንቀቂያ የሁኔታ ትንተና ለሚመለከተው አካል የማድረስና ከችግሮች ቀድሞ የመገኘት ግዴታና ኃላፊናቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌ፥ ለአሐዱ 94.3 ሬድዮ እንደተናገሩት የመከላከያ ሰራዊት ፣ ፌደራል ፖሊስ እና ሚሊሻዎችም የጸጥታ ችግር ያለበት ቦታው ላይ ቢደርሱም ህይወት ከጠፋና ረብሻ ከተነሳ በኋላ ነው ብለዋል፡፡

የመረጃ መረብ ደህንነት ኃላፊነት ችግሮች ሳይፈጠሩ ቀድሞ የመለካለል ስራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጸጥታ አላካትም ሆነ የሚመለከታቸው የደህንነት ተቋማት ግዴታና ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አለመሆናቸው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የጸጥታ ኃይሎች እና የሚመለከታቸው ተቋማት የሰው ህይወት ከጠፋ በኋላ የሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ስራ እና ችግሩን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ሊታረም እንደሚገባ ማሳሰቡን አሀዱ ሬድዮ 94.3 ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Attention😷

"ከወደ ህንድ ሃገር በየ5 ደቂቃው 1 ሰው በ ኮቪድ 19 ምክንያት ህይወቱ ያልፋል" - አልጀዚራ

ሆስታሎች ሞልተው እድለኛ የሆኑት በየጎዳናው ኦክስጅን ታቅፈው የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማሉ::

እድል ያልቀናው ደግሞ ቤቱ ሆኖ የሞቱን ቀን እና ሰዓት ይጠባበቃል::

አሁን ላይ በሃገሪቱ የቫይረሱን በከፍተኛ ፍጥነት መዛመት ተከትሎ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መስጠት አልቻሉም። ከእንደዚህ አይነቱ ክስተት ካልተማርን እና እርምጃ ካልወሰድን የህንድ እጣ ፈንታ ነገ እኛ ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለንም::

ዛሬም በእጃችን ያለው መድሃኒት "መጠንቀቅ" ብቻ ነው።

እባካችሁ ሃላፊነት በመውሰድ ቀን ሳለማድረግ የሚገባንን ጥንቃቄ እንፈፅም።

ቤታችን እስኪንኳኳና የምንወዳቸውን እስኪነጥቀን አንጠብቅ፤ ካለተጠነቀቅን የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሁላችንም ቤት መንኳኳቱ አይቀሬ ነዉ።

የመጀመሪያውን ፍርሃታችንን እና ጥንቃቄያችንን ልንመልሰው ይገባል። ኮሮና ቫይረስን በምናብ የተሳለ ተረት አናድርገው ፣ ሲደርስብን ብቻ ለመንቃት አንሞክር።

በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ የፊት ጭንብል እና ሳኒታይዘር አይለየን።

ነገን ለማየት ዛሬን እንጠንቀቅ፤ ብልህ ሰው ከሌላው ይማራል::

(በዶክተር ኃይለልኡል መኮንን)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የማህበር ቤት ምዝገባ ተጠናቀቀ።

ባለፉት 25 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበር ቤት ምዝገባ 12 ሺህ 609 ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የማህበር ቤት ምዝገባ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ቢሮው በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ነዋሪዎች በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር በማደራጀት የራሳቸውን ቤት እንዲገነቡ ምዝገባ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።

በምዝገባ ሂደትም ችግር የገጠማቸው ተመዝጋቢዎች ካሉ ቅሬታቸውን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለቢሮ ማቅረብ ይችላል።

መረጃው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ አለፈ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 8,869 የላብራቶሪ ምርመራ 1,663 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 250,955 ደርሰዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት 20 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,531 ደርሷል።

ትላንት 1,933 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ያገገሙ 190,013 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 987 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

እንደሚታወቀው ይህ ፕላትፎርም በመላው ኢትዮጵያ ከክልል እስከ ቀበሌ ፣ በውጭ ሀገር እንዲሁ ያሉ የቲክቫህ አባላት የእርስ በእርስ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት [የሚተገጋገዙበት] ነው።

ባለፉት 3 ዓመታት ሁሉም አባላት በያሉበትበመሆን የሚያዩትን የሚመለከቱትን እያሳወቁ ፤ ያሳሰባቸውን ጉዳይ እያስገነዘቡ/እያስጠነቀቁ ቆይተዋል።

በየጊዜው ሰላም ሆናል፣ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ግድያ ይቆማል ፣ መፈናቀል ያበቃል ፣ የደቦ ፍርድ ዳግም አናይም ፣ ሁሉም አካላት ያለባቸውን ችግር በሰላም ይፈታሉ ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች ሁሉ እየተባባሱ ዛሬ ደርሰዋል።

ጭራሽ ሁሉን በሚያስደነግጥ መልኩ ሚሊዮኖች በሚኖሩበት ትግራይ ክልል ሙሉ ጦርነት ተደርጎ ይህ ትውልድ በአይኑ አይቷል፤ ከ5 ወራት በላይ ኢንተርኔት ባለመኖሩ አብዛኛው የትግራይ ክልል ቲክቫህ አባላት በህይወት ይኑሩ ይሙቱ አናውቅም ፤ ሪፖርትም የለን፤ ዛሬ ጨለማ ውስጥ ነን።

በተለይ ባለፈው 2 ዓመት የቲክቫህ አባላት ለሀገር ሰላም እና ለእርስ በእርስ ግጭት እና እልቂት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ አድርገው መልዕክት ሲያጋሩ ቆይተዋል ፤ ይህም በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ይፈታል ብለው በማሰብ ነበር።

ከዓመታት በፊት በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ሲቀርቡ የነበሩ መልዕክቶች የእርስ በእርስ ግጭት ይዘት ያላቸው ሳይሆን/የብሄር ጉዳይ የተካረረበት ሳይሆን ቀጥታ ከመንግስት ጋር የሚያላትም ነው ፤ ይህም አንድም ሳይጓደል መንግስት ሲፈፅም የነበረውን ግፍ አንዱ አካባቢ ያለው የቲክቫህ አባል ለሌላው ሲያሳውቅ ነበር።

ያ ሁኔታ ዛሬ እንደሌለ ሁላችሁም የምታውቁት ነው።

1/4
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የብሄር ጉዳይ እጅግ ተካሮ እጅግ አስፈሪ በሆነ ድባብ ውስጥ ከቶናል (ለዚህ ደግሞ መንግስት ፣ ተቃዋሚዎች፣ አክቲቪስቶች ፣ ተው ይሄ ነገር ወዳልተፈለገ አቅስጣጫ እየሄደ ነው ብለን ያልገሠፅን ካለን እኛም እንደ ዜጋ ኃላፊነቱን መውሰድ አለብን)።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚታየው የብሄር እና አንዳንዴ ደግሞ የሀይማኖት ጉዳይ መካረር ፥ አንዳንድ የቲክቫህ አባላት መልዕክት ሲልኩ ይህን ብናገር ሌላው ወገኔ እንዴት ይሆን እያሉ ስለሚሰጉ ጉዳዩን በዝምታ ያልፋሉ/በውስጥ አውርተው ይጨርሳሉ።

እያንዳንዱ ነገር ከብሄር እና ከዘር ጋር በመገናኘቱ ለመረጃ ልውውጥ አስጊ ፣ ለንግግር እና ሀሳብ ማቅረብ ጠንቅ ፥ሁሉም ነገር አስከፊ ሆኗል።

የብሄር ጉዳይ እጅግ በተካረረበት ፣ ሁሉም አቅጣጫ ተበደልኩ፣ ታፈንኩ፣ ጩኸቴ ተቀማ የሚለው ፖለቲከኛ እና ግለሰብ ባለበት ሀገር ላይ ስለሀገራዊ ስሜት ማውራት በራሱ የሚያስወግዝ ሆኗል።

የአንዱ ቦታ ቀውስ /ግድየ ጭፍጨፋ፣ ወደሌላው ተዛምቶ በዚህ ላይ የፖለቲከኞች ሴራ ተጎንጉኖ አሁን ካለው በላይ የእልቂት ምድር እንዳይፈጠር አባላቶቻች የቻሉትን ሁሉ ሲያደርጉ ሲጠነቀቁ ነበር።

ዛሬም ግን ግድያው ፣ ጭፍጨፋው፣ የዜጎች መፈናቀሉ ቀጥሏል። ሁሌም ደግሞ ተጎጂዎቹ ምንም የማያውቁ ንፁሀን ናቸው። የፖለቲካው መቆመሪያ እነሱ ንፁሃን ነብሶች ናቸው።

ፖለቲካው ምን ላይ እንዳለ እንኳን የማያውቁ ገበሬዎች፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ እናቶች ናቸው የሚሞቱት ፤ የነሱን ሞት ደግሞ አንዱ ሲያቃልል ፥ ለማድበስበስ ሲሞክር፣ ወይም ሁኔታውን ለማብራራት ሲሞክር (ግፍን ማብራራት ከየት እንደለመድነው አናውቅም) ፤ አንዱ ደግሞ ሆን ብሎ ተቆርቋሪ በመምሰል ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ሲያውል እያየም ነው።

ይይህ የሀገሪቱ ሁኔታ መቼ ነው ማብቂያው ? የሚለው የሁሉም አባላት ጭንቀት ነው።

2/4
ውድ አባላት ያለውን ሁኔታ እየተረዳችሁ መልዕክት ለሌሎች እየላካችሁ ስለሆነ ልትመሰገኑ ይገባል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጡት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ አባላት የተሳሳተ እይታ እንዳይኖራቸው። እንዴት መረጃ መለዋወጥ እንደሚችሉ እንደሚከተለው በአጭሩ እንገልፃለን።

- ቲክቫህ የሚመራውም ሆነ ባለቤቶቹም አባላቱ ብቻ ናቸው፤ መልዕቶችን ለማደራጀት እና ለሌሎች ለመላክ እንዲሁም ሚዲያዎች ለመዳሰስ ካሉ አስተባባሪዎች ውጭ ሌላ አካል የለውም።

- ቲክቫህ ቋሚ የመደበኛ ሚዲያዎች ይዘት የለውም (እንደዛ አስፈላጊ ከሆነ በአባላት ምክክር ወደፊት ይደረግ ይሆናል)

- ቲክቫህ ውስጥ የገባ እንደ የቤተሰቡ አንድ አባል/አካል/ባለቤት ነው የሚቆጠረው።

- የቲክቫህ አባላት ጋዜጠኞች፣ አመራሮች፣ የሚዲያ ባለቤቶች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ተማሪዎች፣ በተለያየ የስራ መስክ ያሉ ፣ የመንግስት ሹማምንት፣ የተቃዋሚ አመራሮች ያሉበት ነው።

- ለአባላት በስልካቸው በቴሌግራም የሚላክላቸው መልዕክት የትኛውንም ወገን የሚወግን ፣ የፖለቲካ ትርፍ ሆነ አላማ የሌለው ነገር ግን በየአቅጣጫው ያለውን ሁኔታ አባላት እንዲያውቁት የሚያደርግ ነው።

- በየአባላት ስልክ በቴሌግራም በኩል የሚላከው መልዕክት ለጋዜጠኞች ፣ ለሚዲያዎች ግብዓት እንዲሆን እነሱም ለሌላው እንዲያሳውቁ የሚያደርጉ ናቸው።

- አባላት በቻሉት አቅም ግጭት የማያባብስ ፣ ለሌሎች ጉዳት መንስኤ የማይሆን፣ እሳት የማይሎክስ መረጃ ለሌሎች መካፈል ይችላሉ።

- አባላት መረጃቸውን ይፋ ሲያወጡ፥ ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ ነው፤ ምላሽ መስጥ የሚፈልግ አካልም በተቀመጠው ስልክ ወይም አድራሻ ምላሽ መስጠት ይችላል።

- ሁሉም አባል የመጀመሪያ ምንጭ በመሆን መልዕክቱን ለሌሎች መላክ (ቲክቫህ ውስጥ ላሉ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች) መላክ ይችላል።

3/4
- አባላት መረጃ ስታካፍሉ ከማህበራዊ ሚዲያ እየወሰዳችሁ ሳይሆን በቀጥታ ጉዳዩን የምትከታተሉ ሊሆኑ ይገባል፤ ይህ ለምን እንደሆነ ለናተ የሚጠፋ አይደለም።

- እንደሚታወቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገራችን ሚዲያዎች በተካረረው የብሄር ግዳይ እና በፖለቲካ ውስጥ ገብተው ቦታ ቦታቸውን ይዘው ስላለ ሚዲያዎችን ዋቢ ስታድርጉ በጥንቃቄ ይሁን።

- በቲክቫህ ውስጥ የሚያስተባብሩ ደግሞ ሚዲያዎችን እየተከታተሉ ፣ ከአባላት የተላኩትን መልዕክቶች እያደራጁ ኃላፊነት ባለው መልኩ፣ በሁሉም አቅጣጫ ለሌሎች ያደርሳሉ።

- አባላት መረጃ ለሰዎችን ለመላክ ስትፈልጉ እውነተኛ ያልተደበቀ ማንነት ሊኖራችሁ ግድ ነው፤ አስፈላጊ ከሆነ ስልክ፣ ተጎጂዎችን አነጋግራችሁ ከሆነም የተጎጂዎችን አድራሻ ማያያዝ አለባችሁ። በተደበቀ ማንነት የሚላኩ መልዕክቶች በቀጥታ ለአባላት ለመላክ አይቻልም።

- የፀጥታ ስጋት እንዳለ በማንኛውም ጊዜ ስትጠቁሙ /ለአባላት ስትልኩ፤ ትክክለኛ መሆኑን እና እዛው ሊፈታ እንደማይችል ስታምኑበት መሆን አለበት።

- በየቦታው ካለው ውጥረት ጋር በተያያዘ ጥቆማ ስታካፍሉ ኃላፊነት ባለው መልኩ ሌላ ቦታ ችግር በማይፈጥር መልኩ መሆን አለበት።

ከዚህ በተጨማሪ የቲክቫህ አባላት ይህ ፕላትፎርም የናተው የመረጃ መለዋወጫ ስለሆነ አሁን ካለው እና ከተባባሰው ቀውስ እንድንወጣ በየአካባቢው ያሉ ችግሮችን በኃላፊነት ለሌሎች አጋሩ።

እንደአንድ ዜጋ መፍትሄ የምትሉትን በውስጣችሁ ያየዛችሁትን ሃሳብ ካለ እያካፍሉ።

ምናልባት ስለቲክቫህ ቤተሰባዊ ግንኙነት በቅጡ ሳትረዱ የመጣችሁ/የራሳችሁን ዓላማ ለማስፈፀም የምትፈልጉ አካላት የተሳሳተ ቦታ እንደመጣችሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

መልዕክት ማስቀመጫ ፥ @tikvahethiopiaBOT / 0919743630 /

ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
ቲክቫህ "ተስፋ" ኢትዮጵያ
''...ጊዜያዊ መጠለያችን እየፈረሰብን ፤ መኝታችንና አልባሳቶቻችን በጎርፍ እየተዋጡብን ነው'' - ተፈናቃዮች

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ቻግኒ ከተማ ራንች አካባቢ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከዚህ ቀደም ከደረሰባቸው እንግልት እና በደል በተጨማሪ <<ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ >> እንዲሉ አሁን ላይ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ጊዜያዊ መጠለያቸው እየፈረሰ ፤ ምኝታቸውና አልባሳቶቻቸዉ በጎርፍ እየተዋጠ ፤ አንዳንድ መጠለያ ውስጥ እንደ አጋጣሚ የተገኘች እፍኝ ሙሉ ስንቅ ሳትቀር እየተበላሸ ይገኛል።

በመሆኑም መንግስት የክረምት ወር ከመግባቱ በፊት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው ፤ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችና መላው ህዝቡ በማንነታቸው ምክንያት ብቻና ብቻ ከሞቀው ቤታቸው ወጥተው ሜዳ ላይ በጊዜያዊ ሸራ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከጎናቸው ይቁም ሲል የቻግኒ ኮሙዩኒኬሽን ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ ከባህር ዳር ወደ እንጅባራ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሲዘዋወር ነበር የተባለ ፦

- 900 የብሬል፣
- 120 የክላሽ ጥይቶች፣
- አንድ የቱርክ ሽጉጥ እና 43 የተለያዩ ስለታማ ነገሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።

ከፋግታ ኮሚኒኬሽን እንዳገኘነው መረጀ ከሆነ ከህገወጥ መሳሪያው ጋር የተያዙ ተጠሪጣሪዎችን ላይ ፖሊስ የማጣራት ስራ እየሰራ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"... በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነት እና መስፋፋት የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከልና ዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ ሚጠቁም ነው" - ኢሰመኮ

ኢሰመኮ በጅማ ሊሙ ኮሳ ወረዳ ፣ ቀጮ ክርክራ እና ጋሌ ቀበሌ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም በታጠቁ ኃይሎች ጥቃት መድረሱን ገልጾ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

በተመሳሳይ በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ፣ ዳኖ ቀበሌ በሚያዚያ 14 ታጣቂዎች 6 ሰዎች እንደገደሉ የአካባቢው አስተዳደር ማሳወቁን ገልጿል።

በኮሳ ወረዳ የደረሰውን አደጋ ተከትሎም በእለቱ የክልል እና የፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው መሰማራታቸውን ኢሰመኮ መረዳቱን አሳውቋል።

ኢሰመኮ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና ክልል አካላት ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ በቅርበት እናት ነጋጋረ መሆኑ ገልጾ ፤ የክትትል ተግባሩን እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኮሚሽኑ ፥ ነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳትና የሰዎች ሞት ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ያሳሰበ ሲሆን በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነት እና መስፋፋት የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከል እና ዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ የሚጠቁም ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia