TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ካርታ ይፋ ማድረጊያ ቀንን ከመጋቢት 01 ቀን 2012 ወደ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ማዘዋወሩን አስታወቀ።

ምርጫ ቦርዱ የምርጫ ክልሎች ካርታ ዝግጅትን ያጠናቀቀ ቢሆንም ሂደቱ መከናወን ያለበት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መሆን ስላለበት እና በጉዳዩ ላይ ባለሞያዎች ማብራሪያ መስጠት ስላለባቸው ቀኑን መቀየር ማስፈለጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት የምርጫ ክልሎች ካርታ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 05 ቀን 2012 ዓ.ም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ይፋ የሚደረግ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#election2012

ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ/ም እንዲካሄድ ቀን የተቆረጠለት የዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ 170 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል ካርታን ዛሬ ይፋ ያደርጋል። በዛሬው ስነ ስርዓት ላይ የሀገር አቀፍ ፣ የዘጠኙ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ካርታዎች ለዕይታ ይበቃሉ።

#ETHIOPIAELECTION
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፥ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረገው የምርጫ ክልልን እንደገና ማካለል ወይም ማሻሻል አይደለም ብለዋል። ቦርዱ ተበታትኖ የነበረውን የቃላት የካርታ መረጃ በዘመናዊ መልክ አሰናድቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ካርታነት መለወጡን ነው ለመድረኩ ተሳታፊዎች ያስረዱት።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የደቡብ፣ የጋምቤላ፣ የሶማሌ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የሀረሪ ክልል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና አፋር የምርጫ ክልል ካርታዎች!

#EthiopiaElection2012
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

ሲዳማ በክልልነት ለምን አልተካተተም ?

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የምርጫ ክልልን ይፋ ማድረጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ለምን 'ሲዳማ በክልልነት' እንዳልተካተተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረሱ አቶ በቀለ ገርባ ጠይቀው ነበር።

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

"የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ ስራውን ጨርሷል። የስልጣን ርክክቡ ተፈጽሞ ፤ ሲዳማ ክልል መሆኑ formalize ካልተደረገ ፤ ለፓርላማ መቀመጫ ቆጥረን ማቅረብ አይጠበቅብንም። ብናደርግም ስህተት ነው"

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቀረበ።

“ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ መሰረት እስከ ነሃሴ ወር ማለቂያ ድረስ አጠቃላይ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ቢኖርባትም የኮቪድ19 ወረርሽኝ ምርጫን ማከናወን የማያስችል ደረጃ ላይ በማድረሱ ምክንያት ህግና እውነታውን አጣጥሞ መሄድ አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንዳሉት ችግሩን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማያፋልስ መልኩ ለመቅረፍ አራት የመፍትሄ አማራጮች ተቀምጠዋል።

1. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን

2. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ

3. ህገ መንግስት ማሻሻል

4. የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ናቸው ብለዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia