TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 7557 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ 1,704 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 19 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 531 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 179,812 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,592 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,019 ሰዎች አገግመዋል።

ወረርሽኙ በሀገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 597 ተመዝግቧል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ሰበር_ዜና

የታንዛኒያው ፕሬዜዳንት ጆን ማጉፉሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ፕሬዜዳንቱ በ61 ዓመታቸው ነው ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፈው።

የፕሬዜዳንት ማጉፉሊን ህልፈት ያሳወቁት ምክትል ፕሬዜዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሲሆኑ ህልፈታቸው ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሰሞኑን ፕሬዜዳንት ማጉፉሊ ለሳምንታት ያህል ያለመታየታቸው መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል ፤ አንዳንዶችም በኮቪድ-19 ተይዘው በውጭ ሀገራት (ኬንያ እና ህንድ) ህክምና ላይ ናቸው ሲሉ ነበር።

ለመጨረሻ ጊዜ በህዝብ ፊት የታዩት የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ/ም ነው።

ፕሬዜዳንቱ በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በሽታውን ሲያናንቁት፣ ለበሽታው ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው የሚልና ሌሎችም አነጋጋሪ አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ።

አንዳንዶች ህልፈታቸውን ከኮቪድ-19 ጋር ቢያገናኙትም ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ የህልፈታቸው ምክንያት "የልብ ህመም" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ሱዳን በግድቡ ጉዳይ ወደ 2ኛ አማራጭ እየተሸጋገረች ነው" - ኦስማን ማርጋኒ ሱዳን ከታለቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች መሆኑን ሱዳናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኦስማን ማርጋኒ ተናገሩ። ኦስማን ማርጋኒ በዛሬው እለት የሕዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በአዲስ አበባ በተካሔደው ሲምፖዚየም ላይ ከተነሱ ሀሳቦች ጋር በማያያዝ በስካይ ኒውስ ቀርበው አስተያየታቸውን…
#GERD🇪🇹

አሜሪካ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ በ3ቱ ሀገራት ጥሪ ካልቀረበላት በስተቀር እጇን እንደማታስገባ ገለፀች !

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ ሀገራቸው ዓባይ ለግብፅ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ሱዳንም ወሳኝ ወንዝ እንደሆነ እንደምታምን አስታውቀዋል፡፡

ሶስቱም ሀገራት አሜሪካን ለውይይት ካልጠሯት ለመሳተፍ እንደማትችልም ቃል አቁባዩ ገፀዋል።

አዲስ አበባ፤ ካርቱምና ካይሮ ፤ ዋሸንግተን ታደራድረን የሚል ጥሪ ካላደረጉ በስተቀር በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ጣልቃ የምትገባበት ሁኔታ እንደማይኖር አስታውቀዋል፡፡

ይሁንና ሶስቱም ሀገራት ግብዣ የሚቀርቡ ከሆነ ለውጤታማነቱ አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗንም ቃል አቀባዩ ይፋ አድርገዋል፡፡

ቃል አቀባዩ "ቴን" ከተባለ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የሕዳሴ ግድብ ድርድር መፍትሄ የሚገኘው በሶስቱ ሃገራት መካከል በሚደረግ ንግግር እንደሆነ አሜሪካ እምነት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲም ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ለሶስትዮሽ ድርድር ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ ባለፈ ሱዳን እና ግብጽ ፤ የአውሮፓ ሕብረት ፤ አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአደራዳሪነት እንዲገቡ ያቀረቡት ሀሳብ በይፋ እንዳልቀረበ ገልጸው ነበር፡፡

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ድርድር በአፍሪካ ሕብረት ብቻ መሆን እንዳለበት ጽኑ አቋም እንዳላት መገለጹ ይታወሳል፡፡

ምንጭ : አል አይን ኒውስ (am.al-ain.com)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
"ሙሃመድ ዴክሲሶ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቅ ይገባል" - ኢሰመኮ ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 1 ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኘውን ሙሃመድ ዴክሲሶ በተመለከተ የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋስ እንዲለቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ከእስር አለመለቀቁ እንዳሳሰበው ገልጾ፣ ሙሃመድ ዴክሲሶን ጨምሮ ሌሎችም በፍርድ ቤት የዋስትና…
ወጣት ሙሃመድ ነፃ ቢባልም ከእስር አልተፈታም።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከየካቲት 06 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውን የወጣት ሙሃመድ ዴክሲሶ እና በሱ መዝገብ የተከሰሱትን ሁለት ሰዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በቅርበት በመከታተል ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ተከሳሾቹን በነጻ አሰናብቶ ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም አሁንም በእስር ላይ ናቸው።

ኮሚሽኑ እስረኞቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአስቸኳይ ከእሰር እንዲለቀቁ የጠየቀ ሲሆን የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እንዲከበርም ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
አብን እና ባልደራስ ስምምነት ተፈራረሙ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

2ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ትብብር ፈጥረው ለመስራት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia
ባለስልጣኑ ተገደሉ።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የሄበን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በሪሶ ቡልዬ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በየተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

አቶ በሪሶ ትላንት ምሽት 1:30 ነው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው።

የሄበን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አቶ በሪሶ ለህዝቡ ሰላም እና እድገት ቀን እና ማታ ሲለፉ የነበሩ የህዝብ አገልጋይ መሆናቸውን አውስቶ በህልፈታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ፦

የተመድ (UN) ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊ ሚሼል ባሽሌት በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን በተመለከተ ለሚደረገው ማጣራት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከስምምነት መደረሱን መግለፃቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል።

የኮሚሽኑ ቃለ አቀባይ ጆናታን ፈውለር ኃላፊዋ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አማካኝነት የቀረበውን የ ’አብረን እናጣራ’ ጥሪ በበጎ መልኩ ተቀብለውታል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባዩ አክለው ፥ “የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሁን ላይ ተፈጸመ የተባለውን ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል እቅድ ነድፈው ፣ ተልእኮቸቸውን በተቻለ ፍጥነት ለመፈጸም በመስራት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ሰቆጣ እና አካባቢው ምን ተፈጥሯል ?

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን "የሰቆጣ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከአሉባልታ እና ሽብርን ከሚነዙ ሀይሎች ራሱን በመጠበቅ ከጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አካባቢውን ይጠብቅ" ሲል መግለጫ አውጥቷል።

የአስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ፥ "በመከላከያ፣ አማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የህወሓት ቡድን የፃግብጅ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን #የፃታ_ከተማ ላይ ዛሬ መጋቢት 9/2013 ዓ.ም ወረራ ፈጽመዋል" ሲል አስታውቋል።

ነገር ግን መግለጫው ስለፃታ ከተማ ወረራ/አሁን ላይ ስላለው ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አይገልፅም።

የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ "በብሄረሰብ አስተዳደሩና በአካባቢው ትክክለኛ ያልሆኑ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሳይሸበር ራሱን ከአሉባልታ በመጠበቅና አሉባልታ የሚያሰራጭቱን በማጋለጥ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን እንዲሰለፍ" ሲል በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

እስካሁን ድረስ በሰቆጣ እንዲሁም አካባቢዋ ምንም የተከሰተ የጸጥታ ችግር አለመኖሩ የተገለፀ ሲሆን ማህበረሰቡ መደበኛ የእለት ከእለት ተግባሩን እያከናወነ ከጸጥታ ኃይል ጋር በመሆን አካባቢውን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Alert😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 600 ደረሰ።

ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,055 የላብራቶሪ ምርመራ 2,057 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 181,869 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,602 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 145,349 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ መጋቢት 9 ሁኔታ ፦

- 600 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች

- በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ 2,057 ይህ 26% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ ነው (#እስካሁን_ከፍተኛው) በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት እንኳን ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበን አናውቅም ፤

- 10 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 8 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦

1. ሲዳማ-45%
2. ድሬዳዋ-40%
3. አዲስ አበባ-26%
4. ኦሮሚያ- 31%
5. ደቡብ- 20%
6. አማራ- 20%
7. ቤንሻንጉል-29%
8. ሐረር- 23%

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ የሚረዳ "ምርጫዬ" የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ !

ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዲሁም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን ለህዝቡ እንዲሸጡ የሚያስችል ምርጫዬ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያና ድረ ገጽ ማዘጋጀቱን እውነት ኮሚኒኬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

በአሁኑ ወቅት መራጮች ስለሚመርጡት ፓርቲ እና ተመራጭ የመረጃ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ይህንን ፍላጎት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ መሸፈን ይቻል ዘንድ ይህ መተግበሪያና ድረ-ገጽ መዘጋጀቱ ነው ያስታወቁት።

በተለይ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ለማድረግ ቴክኖሎጂውን እንደ ትልቅ አቅም መጠቀም እንደሚገባ የጠቀሱት አዘጋጆቹ ሁሉንም ፓርቲ ያለምንም ክፍያ በእኩል ለማሳተፍ የሚያስችል መድረክ መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

በምርጫ መተግበሪያው/ ድረ ገጹ ላይ የፓርቲዎች መግለጫ፣የሲቪክ ማህበራት እና የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድ መረጃ፣ ለፓርቲዎች ድጋፍ የሚደረግበት የእርዳታ ወይም የልገሳ ፎርም፤ ሰነዶች እና ተቀሳቃሽ ምስሎች ማጋሪያ፣ ዜና፣ ወደ ማህበራዊ ገጽ ማጋሪያ እንዲሁም ኩነቶችን ማስተዋወቂያ በውስጡ አካቷል።

እውነት ኮሚኒኬሽን ኃ/የ/የግ/ማኅበር በወጣቶች የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን ይህንን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን፤ በተለይ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን አስመልክቶ በሙያቸው በበጎ ፈቃደኝነት ሥራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

ወደፊት ትልልቅ ለውጥ የሚፈጥሩ የቴከኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ገቢያው ለማምጣት በሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልናል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ትላንት ምሽት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ በትግራይ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጨማሪ የ52 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቀዋል።

አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ከተፈጠረ አንስቶ ያደረገችው ድጋፍ 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

ሚኒስትሩ አሁንም ቢሆን አሜሪካ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

በስቴት ዲፐርትመንት በኩልን በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ ተደራሽነት በማሳደግ የሰራቸውን ስራዎች አሜሪካ እውቅና እንደምትሰጥ ገልፃለች።

በመግለጫው ላይ ያለ ፖለቲካዊ መፍትሄ በትግራይ የሰብዓዊ ሁኔታው እየተባባሰ ሊቀጥል እንደሚችል ይገልፃል ፤ ግጭት ቆሞ በአስቸኳይ የኤርትራ ወታደሮች እና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያሰፈራቸውን የአማራ ክልል ኃይሎች እንዲነሱ ማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብሏል።

ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ግፎች በኢትዮጵያ መከላከያ ውስጥም ሆነ በህወሓት፣ በኤርትራ ኃይል ወይም በአማራ ክልል ኃይል ተጠያቂ አካል መኖር አለበት ይላል የስቴት ዲፓርትመት መግለጫ።

www.state.gov

ብሊንከን ከዚህ ቀደምም ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የአማራ ኃይል ይውጣ ሲሉ ማናገራቸው እና ፥ የአማራ ክልል መንግስትም ትግራይ ውስጥ እንደሌለ እና የአማራ ኃይል አሁን ያለበት ቦታ "በታሪክም የትግራይ እንዳልሆነ" ፤ የአማራ ኃይል ትግራይ ውስጥ አለ እየተባለ የሚገለፀውም ስህተት እንደሆነ የሚገልፅ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በዚህ ጉዳይ ሉአላዊነትን የሚጋፋ ፣ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልጋ የመግባትና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል መግለጫ እንደሰጠበት ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ትላንት ምሽት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ በትግራይ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጨማሪ የ52 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቀዋል። አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ከተፈጠረ አንስቶ ያደረገችው ድጋፍ 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ሚኒስትሩ አሁንም ቢሆን አሜሪካ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባት ገልፀዋል። በስቴት ዲፐርትመንት…
#Tigray

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ፍፁም አረጋ የአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ በኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ በመወሰናቸው ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እኤአ ከ1903 ጀምሮ የዘለቀ ነው ብለዋል።

አሁኑ አሜሪካ ያደረገችው ድጋፍ ሌሎችም የልማት አጋሮች ተመሳሳይ የሆነ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማበረታታት ተምሳሌት ይሆናል ሲሉ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopia
በርበሬና ሽሮ ውስጥ የከለር ኬሚካል ፉርሽካና ሰጋቱራ ቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ግለሰብ ተያዘ !

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ባእድ ነገሮችን ከምግብ እህል ጋር በመቀላቀል ለገበያ ያቀርብ የነበረ ነጋዴ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።

የጤና ቢሮው ምክትል የቢሮ ሀላፊ እና የጤና እና ጤና ነክ አገ/ግ/ጥ/ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ እንደገለጹት በሀይቅ ዳር ክ/ከተማ አሮጌ ገበያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ወፍጮ ቤት በርበሬ ሽሮ እና እርድ በማለት የተለያዩ እንደሰጋቱራና ጥራጊ ያሉ ነገሮችን በመፍጨት እና የተለያዩ ከለር ያላቸው ኬሚካሎችን በማደባለቅ ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበርና አሁንም ከ200 ኩንታል በላይ ለገበያ የተዘጋጀ በቁጥጥር ስር መዋሉንገልጸዋል።

ቢሮው ተጠርጣሪው በፍጥነት ለህግ ቀርቦ ተገቢውን የሆነ ቅጣት እንደሚያገኝ አሳውቋል።

ለገበያ የተዘጋጀው የእህል አይነት ላይ በተደረገው ምርመራ ባእድ ነገር የተቀላቀለበት መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የሚጨመረው የከለር ኬሚካል በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰውን የጉዳት መጠን ለማጣራት የላቦራቶሪ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

ህብረተሰቡ እንዲህ ባለጉዳይ የተለየ ጥርጣሬ ሲያጋጥመው ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልጸው ሸማቹም ቢቻል በቤት ውስጥ አዘጋጅቶ እንዲጠቀም አልያም የታወቁ እና ህጋዊ ከሆኑ ተቋማት እንዲገበያይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አሳስቧል።

Via Tariku Dubale
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT