TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ ፦

• እስከ ትላንት ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት ወስደዋል
• 35 ያህል ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል

በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት የፍቃዱን የአፈፃፀም መመሪያ መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የክትባቱ ደህንነት ለመከታተል እና በሚፈለገው ፍጥነት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

እስከትናንት ድረስ ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት የወሰዱ ሲሆን 35 ያህል ሰዎች ላይ ነው የሚጠበቅ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት የተደረገው ተብሏል።

ክትባቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያግዝ በመሆኑ በጎንዮሽ ጉዳቱ መደናገጥ እንደማያስፈልግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መግለፁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
👍1👎1
የኢትዮጵየ መንግስት ከህወሓት ቡድን ጋር ይተባበራሉ ላላቸው አካላት #የመጨረሻ ማሳሰቢያ ዛሬ ሰጠ።

ከመግለጫው ላይ የተወሰደ፦

"...በወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩ እና በዚህም መናሻ የፍርድ ቤት መያዣ ከወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካ አመራሮች በስተቀር ሌሎች ዜጎች ያለ ስጋት ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደቀያቸው እና መኖሪያቸው በመመለስ ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ያቀርባል። በዚህ መንገድ ከአጥፊው ቡድን ተለይተው ወደሰላማዊ ኑሯቸው የሚመለሱ የክልሉ ተወላጆች ዜጎች፣ የትኛውም የህግ ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው ፣ ከአጥፊ ተግባራት ተቆጥበው ወደ ስራቸው እና ኑሯቸው በሰላም መሰማራት ይችላሉ፤ እነዚህን ዜጎች በመልካም ሁኔታ ለመቀበል እንዲተባበሩ እና የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ለየሚመለከታቸው የፀጥታ፣ የአስዳደር እና ህግ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊው መመሪያ ተሰጥቷቸዋል" - የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵየ መንግስት ከህወሓት ቡድን ጋር ይተባበራሉ ላላቸው አካላት #የመጨረሻ ማሳሰቢያ ዛሬ ሰጠ። ከመግለጫው ላይ የተወሰደ፦ "...በወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩ እና በዚህም መናሻ የፍርድ ቤት መያዣ ከወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካ አመራሮች በስተቀር ሌሎች ዜጎች ያለ ስጋት ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በአንድ ሳምንት…
መንግስት ላልተያዙ የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ ፦

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ያልተያዙ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች በሰላም እጃቸውን ለህግ አስከባሪ ተቋማት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

ከዛሬው መግለጫ የተወሰደ ፦

"...የፍ/ቤት መያዣ የወጣባቸው ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች በሰላም እጃቸውን ለህግ አስከባሪ ተቋማት እንዲሰጡ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።

እነዚህ አመራሮች እስከዛሬ ከደረሰው ሀገራዊ ጥፋት እና ጉዳት በመማር ለፍትህ ራሳቸውን በማቅረብ ፣ ተጨማሪ ሀገራዊ ኪሳራ እንዳይደርስ እና በከንቱ የዜጎች ደም እንዳይፈስ የበኩላቸውን በጎ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።

ይሄንን የሚያደርጉ ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና የፖለቲካዊ አመራሮች ራሳቸውን ከከፋ ቅጣት ፤ ወገናቸውን ከመጎሳቀል ይታደጉታል።

ይሄ የመጨረሻ ጥሪ ተጠቅመው ራሳቸውን ለፍትህ በማያቀርቡ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ ህግ በሚፈቅደው ሁሉም ዓይነት መንገድ ፣ ህግ ለማስከበር ሲባል አስፈላጊው ሁሉ የሚፈፀም መሆኑን ቀድመን እንገልፃለን።" - የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

* ሙሉ የመግለጫውን ሃሳብ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የትግራይ የተፈናቃዮች ሁኔታ ፦

• "እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች በኃይል ተፈናቅለዋል። የዞኑ ነዋሪዎች በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና አንዳንድ ሊህቃን በሚፈፅሙት ተግባር ነው እየተፈናቀሉ የሚገኙት" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን

• "750 ሺ የትግራይ ተወላጅ ተፈናቀለ የተባለው ነጭ ውሸት ነው፤ የዚህን ያህል የትግራይ ተወላጅ ቦታው ላይ አይኖርም፥ የአማራ ተወላጆች ናቸው በብዛት የሚኖሩት፤ ወልቃይት እና ራያ አካባቢን በምዕራብ ትግራይ ስም መጥራት ተገቢና ወቅታዊ አይደለም፤ ጊዜው ያለፈበት ነው" - የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን

https://telegra.ph/Tigray-03-19
TIKVAH-ETHIOPIA
ባለስልጣኑ ተገደሉ። በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን የሄበን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በሪሶ ቡልዬ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በየተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። አቶ በሪሶ ትላንት ምሽት 1:30 ነው በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ህይወታቸው ያለፈው። የሄበን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አቶ በሪሶ ለህዝቡ ሰላም እና እድገት ቀን እና ማታ ሲለፉ የነበሩ የህዝብ አገልጋይ…
"...ገዳዮችን ለመያዝ የዞኑ ፖሊስ መርማሪ ቡድን አዘጋጅቶ ወደ ስራ አሰማርቷል" - አቶ አበራ ቡኖ (የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ)

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ባልታወቁ ታጣቂዎች የተገደሉት የሔባን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ የቀብር ሥነ-ስርዓት ዛሬ መፈፀሙ ተገለፀ።

የሔባን አርሲ ወረዳ አስተዳዳሪ በሪሶ ቡሊዬ ባለፈዉ ረቡዕ ምሽት ነው በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተመተው የተገደሉት።

የ3 ልጆች አባት የሆኑት በሪሶ ቡሊዬ በሻሸመኔ በስብሰባ ላይ ውለው በአርሲ ነጌሌ ከተማ 01 ቀበሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ለመግባት ከተሸከርካሪ ሲወርዱ ነው በሶስት ጥይት ተመትተው የተገደሉት።

የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ፥ "ገዳዮችን ለመያዝ የዞኑ ፖሊስ መርማሪ ቡድን አዘጋጅቶ ወደ ስራ አሰማርቷል" ብለዋል።

ለ9 ወራት ብቻ ወረዳውን ያስተዳደሩት የአቶ በሪሶ ቡሊዬ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰቦቻቸውና የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተፈፅሞአል።

ባለፈው ቅዳሜ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከቀድሞ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በወረዳው የተሰራውን የበጋ ስንዴ ምርት ሲጎበኙ አቶ በሪሶን አበረታተውት እንደነበር የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ አሳውቋል። (ዶቼ ቨለ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ ፦ • እስከ ትላንት ከ1,400 በላይ ሰዎች ክትባት ወስደዋል • 35 ያህል ሰዎች ላይ የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል በኢትዮጵያ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 ክትባት የፍቃዱን የአፈፃፀም መመሪያ መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። የክትባቱ ደህንነት ለመከታተል እና በሚፈለገው ፍጥነት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ…
ቀላል የጎንዮሽ ጉዳት የተባሉት የትኞቹ ናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ እስከትላንት የኮቪድ - 19 ክትባት ከወሰዱ ከ1,400 በላይ ሰዎች 35 ሰዎች ላይ ቀላል የጐንዬሽ ጉዳት ሪፖርት ተደርጓል።

ይህ ማለት ልክ እንደሌሌች ክትባቶች ሁሉ የእራስ ምታት፣ ድካም እና የክትባት መስጫ አካል ላይ መቅላት ሲሆኑ እነዚህ ደግሞ በጥናቱም ወቅት የታዩ እና የሚጠበቅ ቀላል የጐንዮሽ ጉዳት ነው።

እስካሁን በክትባቱ ምክንያት የ "ከፋ ጐንዬሽ ጉዳት" ሪፖርት አልተደረገም ፤ በሌሎች ሀገራት አጋጥሟል የተባለው የደም መርጋት ችግርም አላጋጠመም።

ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተላከልን መልዕክት።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOt
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

የዛሬ የኮቪድ19 ሪፖርት ምን ይመስላል ?

- 624 ከፍተኛ ክትትል እና ፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች
- 24% ሀገራቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ
- 16 ሕይወታቸው ያጡ ዜጎች

በዛሬው ቀን ከተመረመሩት ዉስጥ 6 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት ታይቶባቸዋል ፦
1. ሲዳማ-48%
3. ድሬዳዋ-22%
3. አዲስ አበባ-25%
4. ኦሮሚያ- 25%
5. ደቡብ- 21%
6. አማራ- 24%

በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል።

በፍጥነት የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ አስገዳጅነት እንዲገባ ካላደረግን እና ሁላችንም በሚገባ ካልተጠነቀቅን የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ከእነዚህ ቁጥሮች በላይ ምስክር የለም::

ሁላችንም የበሽታውን ስርጭት በመግታት የራሳችን እና የምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ሕይወት እናድን።

ያዕቆብ ሰማን
ጤና ሚኒስቴር
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር

@tikvahethiopia
😢1
የዓለም አገራት ህዝቦች የደስተኝነት ደረጃ ፤ የኢትዮጵያ ስንተኛ ?

በተመድ በሚደገፈው በዓመታዊ የዓለም አገራት ሕዝቦችን ደስተኝነት በሚለካው ጥናት ፤ ከ149 አገራት ሕዝቦችን የደስተኝነት ደረጃ #ኢትዮጵያ 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከዓለም አገራት በተለያዩ መለኪያዎች ደስተኛ ሕዝብ ያላት ቀዳሚዋ አገር ፊንላንድ ስትሆን ዴንማርክ ሁለተኛ ፣ ስዊትዘርላንድ ሦስተኛ ፣ አይስላንድ አራተኛ እና ኔዘርላንድስ አምስተኛ በመሆን ተከትለዋታል።

ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ከያዙት አገራት ውስጥ አውሮፓዊ አገር ያልሆነችው ኒውዚላንድ ብቻ ናት።

ይህ ውጤት የተገኘው ጋሉፕ በተባለው የመረጃ ተንታኝ አማካይነት ደስተኛነታቸውን ለማወቅ ከ149 የዓለም አገራት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ነው።

ይህ የሰዎች የደስተኝነት ሁኔታ የተለካው የሚያገኙት ማኅበራዊ ድጋፍ፣ ግለሰባዊ ነጻነት፣ ጠቅላላ አገራዊ ምርት (ጂዲፒ) እና በአገራቱ ውስጥ ባለው የሙስና መጠንን ጨምሮ ሌሎችንም መመዘኛዎች በመመልከት ነው።

በዚህ ዓመቱ ጥናት ከዓለም አገራት ውስጥ ደስተኛ ያልሆኑ ሕዝቦች ይኖሩባቸዋል የተባሉት አፍጋኒስታን፣ ሌሶቶ፣ ሩዋንዳ እና ዚምባብዌ ናቸው።

የጥናቱ አዘጋጆች እንዳሉት ዓለምን ባጠቃት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ አንድ ሦስተኛ በሚሆኑ አገራት ውስጥ "አሉታዊ የሆኑ ስሜቶች በተደጋጋሚ የመከሰታቸው ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል።

የእስያ አገራት ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ደረጃ መሻሻልን ሲያሳዩ ቻይና ቀደም ባለው ዓመት ከነበራት የ94ኛ ደረጃ ወደ 84ኛ ከፍ ብላለች።

Via BBC
@tikvahethiopia
#AstraZeneca አጫጭር መረጃዎች ፦

- WHO የክትባት ደህንነት አማካሪ ኮሚቴ የአስታራዜኔካ ክትባት ተጠቂነትን ለመከላከል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞትን ይቀንሳል ብለዋል። አማካሪ ኮሚቴው እንዳለው ተገኘው መረጃ የደም መርጋት መጨመርን አያሳይም ብሏል፡፡

- የአውሮፓ የመድሃት ኤጀንስ ክትባቱ እንደተባለው የጎላ የደም ማርጋት ችግር እንደሌለበት እና ክትባቱ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ውጤታማነት እንደሆነ አሳውቋል።

- ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና ጀርመን ያቋረጡትን የአስትራዜኔካ ክትባት መስጠት እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

- የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትላንት አርብ የአስትራዜኔካ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ተከትበዋል።

- የ55 ዓመቱ የፈረንሳይ ጠ/ሚ ዣን ካስቴክስ የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ትላንት ተከትበዋል፤ ፈረንሳይ 55 እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ዜጎቿ ክትባቱን መስጠት እንደምትቀጥልም ተገልጿል።

- Africa CDC የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን መስጠት እንዲቀጥሉ ብሏል።

Source : France 24, Sky News , Al Ain, Africa CDC, WHO

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
“ነእፓ ለጣምራ መንግስት ምስረታ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር እየሰራ አይደለም”- ነእፓ

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር የጣምራ መንግስት ለመመስረት ምንም አይነት ውይይት ወይም ምንም ስምምነት አለማድረጉን አስታውቋል።

በትላንትናው እለት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነእፓ ከእናት ፓርቲ ጋር የጣምራ መንግስት ለመመስረት እየሰራ እንደሆነ የሚገልፅ ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ ነው ፓርቲው ይህንን ያስታወቀው።

“የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነእፓ የጣምራ መንግስት ለመመስረት ከእናት ፓርቲ ጋር እየሰራ እንደሆነ ያሰራጨውን የተሳሳተ ዜና እንዲያስተካክል እንጠይቃለን” ሲል ጠይቋል።

ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሚዲያ ተቋማት ምርጫ ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን ከመዘገባቸው በፊት የመረጃውን ትክክለኝነት በማረጋገጥ ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እና የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

የምርጫው ውጤት በኢትዮጵያ ውስጥ የጣምራ መንግስት የሚቋቋምበትን ሁኔታ ከፈጠረ የሚመሰረተው የጣምራ መንግስት ፓርቲዎች በሚያገኙት የህዝብ ድምጽ መሰረት በፓርቲዎች መካከል በሚደረግ ድርድር የሚፈጸም እንደሚሆን ፓርቲው ገልጿል፡፡

@tikvahethiopia
የእናት ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ታሰሩ።

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ጋሞ ዞን፣ከምባ ወረዳ፣ ከምባ ምርጫ ክልል የእናት ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጬ ተወዳዳሪ የሆኑት መምህር በድሉ አለባቸው "ግርግር አስነስተዋል" በሚል ምክንያት ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት መታሰራቸውን ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ፓርቲው ፥ "ጉዳዩ በቀላሉ ይፈታል የሚል ግምት የነበረን ቢሆንም እስከአሁን ቃላቸውን ተቀብለን እንላቀቸዋለን በሚል ሽንገላ የከምባ ከተማ ፖሊስ እስካሁን ድረስ አስሮ ይዟቸዋል" ብሏል በመግለጫው።

"በዚህ ጊዜ የሚደረግ እንዲህ ያለ መሠረተ ቢስ ክስ የእጩዎቻችንን መልካም ስምና ዝና ሆን ተብሎ ለማጉድፍ፣ እና ለሌሎች እጩዎችም የማስፈራሪያ መልዕክት ለማስተላለፍ ያሰበ እንጂ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዳልሆነ እንረዳለን" ሲል ገልጿል።

እናት ፓርቲ ፥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ገልጾ እስሩ ፖለቲካዊ እንድምታ ያለው እሥር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
አጣዬ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጀምሮ የፀጥታ መደፍረስ ተከስቷል።

ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን በዝርዝር ማወቅ አልተቻለም።

የቲክቫህ አጣዬ አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ አካባቢው በተኩስ እሩምታ ሲናጥ እንደነበር ገልፀው የሚመለከተው አካል እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬም በአካባቢው ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ሲሆን ወደ ደሴ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እና መንገደኞች መንገድ ላይ ለመቆም ተገደዋል።

በአካባቢው ለፀጥታው መደፍረስ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን በጣዬ የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መረጃ አቀናጅተን ወደበኃላ የምናቀርብ ይሆናል።

አሁን ላይ ህዝቡ በሰላም መደፍረስ ከፍተኛ ችግር ላይ ሰለወደቀ አካባቢውን የማረጋጋት ስራ እንዲሰራ አባላቶቻችን ጠየቀዋል።

ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት አጣዬ አካባቢ በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚሄዱ መኪናዎች ደብረ ሲና ላይ መቆማቸውን የሚያሳይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ የታጠቁ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ በፅፅቃ ከተማ አከባቢ 8 አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።

"አስር (10) ማንነታቸው አልታወቀም" የተባሉና ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎችን ነው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት የገለፀው

ግለሠቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑን ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአጣዬ እና አካባቢው አለመረጋጋት የሰው ህይወት አልፏል።

ከትላንት አርብ ምሽት ጀምሮ በተኩስ እሩምታ ስትናጥ በነበረው አጣዬ የሰዎች ህይወት አልፏል።

ትላንት አርብ ምሽት በነበረው ተኩስ አንድ ሰው ሲሞት 2 ሰው መቁሰሉ ተሰምቷል።

የኤፍራታና ግድም ወረዳ የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አልታየ እስከ ረፋድ ድረስ የ4 ሰዎችን ሞት መመልከታቸውን ለቢቢሲ አሳውቀዋል።

የተከፈተውን ተኩስ ተከትሎ የአጣዬ ከተማ የ01 ቀበሌ "ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎች መያዙን" ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከለሊት ጀምሮ ደግሞ በማጀቴ የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው ሰዎች መጎዳታቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል። የተጎጂዎች ቁጥር በውል አይታወቅም።

አሁንም በአካባቢው ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ሲሆን ተጨማሪ የፌዴራል/ክልል ኃይል ወደ አካባቢው እንዲገባ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲያረጋግጥ እየተጠየቀ ነው።

የባንኮች እና የሰዎች ንብረት ተዘርፏል።

በሰላም መደፍረስ ምክንያት ተሸከርካሪዎች አሁንም በመንገድ ላይ እንደቆሙ ይገኛሉ። መንገደኞችም በሁሉም አቅጣጫ እየተንገላቱ ነው።

ለአካባቢው የፀጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት መነሻ አሁንም በተለያዩ ወገኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየቀረቡ ነው።

የክልሉ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።

ከዚህ ቀደምም በተለያየ ጊዜ በአጣዬ እና አካባቢው በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሰዎች ህይወት እንዳለፈ/ንብረት እንደወደመ የሚዘነጋ አይደለም።

PHOTO : MUSI (Tikvah-Family Dbersina)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
👍1
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ.pdf
95.5 KB
#UPDATE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛዉን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ለሲቪል ማህበራት እውቅና የመስጠት ስራውን እንዳጠናቀቀ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው 134,109 የአገር ውስጥ ታዛቢዎች ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- በሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሰሩ 8 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረቡ 61,851 ሴት ታዛቢዎች (46%) ሲሆኑ፣

- በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ስር የታቀፉ 7 ማህበራትን ያካተተ 244 ታዛቢዎች እና

- በሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ሂደትን ለመታዘብ በተመረጠ 1 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የቀረቡ 100 ታዛቢዎች እና በስሩ 37 ያህል ሲቪል ማህበራትን ያቀፈ የሲቪል ማህበረሰብ ኔትወርክ ይገኙበታል።

@tikvahethiopia
በደቡብ ጎንደር ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን እና የመገበያያ ገንዘቦችን የያዙ ግለሰቦች በተደረገ የፖሊስ ፍተሻ አንዳቤት ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።

ግለሠቦቹ ከጎንደር ጭነው ሲመጡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አንዳቤት ከተማ ላይ በተደረገ ፍተሻ ፦

- ከ1 ሽህ 500 በላይ ጥይቶች፣
- 3 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ፣
- 1 ካዝናና 37 ሽህ700 ብር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ፖሊስ አሳውቋል።

መሳሪያውን ሲያዘዋውሩ የተያዙት 3 ግለሰቦች እና የመኪና አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ግለሰቦቹ የሃሰት መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል ተብሏል።

የአንዳቤት ወረዳ የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሲሳይ እንየው ግለሰቦቹ የያዙት ህገ ወጥ ጥይት #ከመንግስት_ካዝና ጭምር የወጡ እንደሆነ መረጃው የሚያመላክት መሆኑን በመጥቀስ ግለሰቦቹም ህጋዊ ነን በማለት ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል ብለዋል፡፡

መንግስት እንደዚህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ የሆነ ርምጃ መውሰድ እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን
የሚመለከተው አካል የፍተሻና የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል።

አሽከርካሪዎች የሚጭኑትን እቃ በደንብ በመፈተሸ ከተጠያቂነትና ከህገ ወጥ ስራዎች ራሳቸውን መቆጠብ አለባቸው ተብሏል።

መረጃውን ከአንዳቤት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
👍1