TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ቡናው ታዋቂ ደጋፊ ጥቃት ተፈፅሞት ህይወቱ አለፈ። በኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊነቱ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አበባው ወይም ደግሞ በቅፅል ስሙ "ቴዲ ቡናማው" ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ አልፏል። ቴዎድሮስ ላይ እነማን ጥቃት እንደሰነዘሩ እና ህይወቱን እንዳጠፉ አልታወቀም። ጥቃት አድራሾቹ ስለመያዛቸውም የተባለ ነገር የለም። ኢትዮጵየ ቡናዎች እንዲህ ይላሉ ፦ "ቴዎድሮስ ክለቡ በሚፈልገው ቦታ ሁሉ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቴዎድሮስ አበባው ገዳዮች ዙሪያ ምርመራ እየተደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ በሆነውን ቴዲ ቡናማው ገዳዮች ዙሪያ መንግስት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጓደኞቹ ተናግረዋል።
እንደ ጓደኞቹ ገለፃ ቴዲ ቡናማው የትራንስፖርት ሰራ እየሰራ እያለ ሶስት ሰዎች ናቸው ጥቃት ፈፅመው የገደሉት።
ጓደኞቹ እንደተናገሩት ይህን የትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት ስራ ከጀመረ አንድ ወር እንኳን አልሞላውም።
የቴዲ ሞት የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎችን ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰቦችን ያስደነገጠ፣ ያሳዘነ እና በቁጭትም ያንገበገበ ነው።
ሁሌም በተጠራበት የሚገኘው ፥ የታመሙት ለማሳከም የሚሮጠው፣ ሰዎችን ለመርዳት ዘውትር የማይደክመውን ቴዲን በዚህ አሳዛኝ ግድያ በማጣታቸው ጓደኞቹ እና የክለቡ ደጋፊዎች ልብ ተሰብሯል።
ቴዲ ኑሮውን ሊቀልስ እየተዘጋጀ እያለ ነው ህይወቱን የተቀጠፈው።
በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ምሽት ላይ ተገደሉ/ተዘረፉ የሚሉ ወሬዎች በተለያየ ጊዜ ይሰማሉ ፤ አምሽቶ መስራትም እጅግ አደገኛ እንደሆነ አገልግሎት ሰጪዎቹ የሚያነሱት ጉዳይ ሲሆን በማንኛውም ሰዓት የዜጎች በሰላም ወጥቶ የመግባት ደህንነት ሊረጋገጥ ይገባል ይላሉ።
Video : Nahoo Television (16 MB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"አሜሪካ በሰላም መተኛት ካሻት ከጦርነት ጨዋታዎች እራሷን ታቅብ" - ሰሜን ኮሪያ
አሜሪካ በሰላም መተኛት ካሻት ከጦርነት ጨዋታዎች እራሷን ታቅብ ስትል ሰሜን ኮሪያ አስጠነቀቀች።
የሰሜን ኮሪያ መሪ እህት ኪም ዮን ጆንግ የአሜሪካ አስተዳደር እንቅስቃሴን በኮሪያ ድንበር አካባቢ "የሚሰነፍጥ የባሩድ ሽታ ነው" ሲሉ ኮንነዋል።
እንቅስቃሴው በአካባቢው ሰላም ለማምጣት የሚረዳ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።
ኪም ዮ ጆንግ ይህን ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ወደ ደቡብ ኮሪያ ሄደው ለመወያየት መወሰናቸውን ካሳወቁ በኃላ ነው።
2ቱ የአሜሪካ ከፍተኛ ከፍተኛ ባለስልጣናት የፓሲፊክ ተሻጋሪ አጋርነትን ለማጠናከር በታለመ ጉዟቸው ጃፓንን እየጎበኙ ናቸው።
የመጀመሪያቸው በሆነው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጉዞ፣ በቶኪዮ ከጃፓን አቻዎቻቸው ጋር ተነጋግረዋል።
የጉዟቸው ዓላማ "ቻይና አቋሟን እያፈረጠመች ባለችበት እና ሰሜን ኮሪያ ጠብ አጫሪነቷን እያባባሰች ባሉበት በዚህ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስን ፓሲፊክ ተሻጋሪ አጋርነት ይበልጡን አስረግጦ ለማሳየት" መሆኑ ተገልጿል።
ሁለቱ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶሽሚትሱ ሞቴጊ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ኖቡ ኮሺ ጋር የተወያዩ ሲሆን ነገ ደግሞ ለተመሳሳይ ተልዕኮ ወደደቡብ ኮሪያ ሶል እንደሚያመሩ ታውቋል።
ምንጭ፦ Deutsche Welle & Voice Of America
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Alert😷
በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 591 ደረሰ።
ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።
ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,338 የላብራቶሪ ምርመራ 1,490 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሰዎች ሞተዋል።
ትላንት 660 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 178,108 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,573 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 144,488 ሰዎች አገግመዋል።
#Purpose #Tikvah

#BREAKING አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች 'በጥይት ተመትቶ' ህይወቱ አልፏል። አርቲስት ሃጫሉ በዛሬው ዕለት ምሽት 'ገላን ኮንዶሚኒየም' አካባቢ በጥይት መመታቱንና ህይወቱ ማለፉን በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን 'ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር' #አረጋግጠዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግራሚ አዋርድ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አስታውሷል።
Grammy Award እ.አ.አ 2020-2021 የዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ካጣቸው አርቲስቶች እና የሙዚቃ ሰዎች ዝርዝር ዉስጥ የሀገራችንን ድምፃዊ አርቲስት ሃጫሉን ሀንዴሳን አካቷል።
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ያለፈው ዓመት ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትቶ መገደሉ አይዘነጋም።
አርቲስት ሃጫሉን ሚሊዮኖች እንደ ድምፃዊ ብቻ ሳይሆን እንደነፃነት ታጋይ ፣ እንደጭቁን ህዝቦች ድምፅ፣ እንደሰብዓዊ መብት ተሟጋችም ጭምር ነው የሚያዩት።
በህይወት እያለ ለህዝብ ያቀረባቸው ሙዚቃዎቹ በሀገሪቱ ውስጥ ሲደረግ ለነበረው የፖለቲካ ፣ የነፃነት ትግል እና ጥያቄ ሚሊዮኖችን ለለውጥ እንዳነሳሳ ይታመናል።

ፆታዊ ጥቃቶች በትግራይ ፦
- እንደ ሆስፒታል ምንጮች በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል ሪፈራል ሆስፒታል በየቀኑ በአማካኝ ከ3 የማያንሱ ሴቶች በተለያዩ አካላት ተደፍረው መጥተው ሪፖርት ያደርጋሉ።
- የትግራይ ክልል ሴቶች ቢሮ ከታህሳስ እስከ የካቲት ወር ባለው 3 ወራት 524 ሴቶች መደፈራቸውን በመቐለ እና ዓዲግራት ጤና ተቋማት ሪፖርት ተደርጓል።
- ከመቐለ ፣ እና ለመቐለ በቅርብ ርቀት ላይ ካሉ ወረዳዎች ፣ ከዓዲግራት ከተማ እና አካባቢው የተሰበሰበው ሪፖርት ውጭ በአብዛኛው የትግራይ ክፍል ስለተፈፀመው ጥቃት በተለያየ ምክንያት ሪፖርት ማግኘት አልተቻለም።
- በአይደር ሆስፒታል ብዙ ጥቃት ተፈፅሞባቸው አልጋ ይዘው የተኙ ሴት እህቶቻችን አሉ።
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ነው ብሏል።
- የትግራይ አስተዳደር ፆታዊ ጥቃቶቹን እንደሚቃወም፣ አጥብቆ እንደሚኮንን ፤ ድርጊቱን የፈፀሙ ለህግ መቅረብ አለባቸው የሚል አቋም መያዙን አሳውቋል።
ሰፋ ያለውን ሪፖርት ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/Tigray---Ethiopia-03-16

Telegraph
Tigray - Ethiopia
ፆታዊ ጥቃቶች በትግራይ ፦ በትግራይ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በስፋት ከሚታዩ ችግሮች አንዱ የሴቶች ጥቃት መሆኑ ተገልጿል። እንደ ሆስፒታል ምንጮች በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል ሪፈራል ሆስፒታል በየቀኑ በአማካኝ ከ3 የማያንሱ ሴቶች በተለያዩ አካላት ተደፍረው መጥተው ሪፖርት ያደርጋሉ። እነዚህ ጥቃት ከሚፈፅምባቸው መካከል እጅግ ጥቂት ናቸው ተብሎ ይታመናል። መቐለ ውስጥ "ስራወት" በሚባል አካባቢ ምግብ…
Audio
"...የትግራይ ህዝብ በታሪኩ እንደዚህ ያለ ውስብስብ ነገር ገጥሞት አያውቅም"-ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል (የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ)
በቅርቡ በነበረ አንድ የትግራይ ድጋፍ ማድረጊያ መድረክ ላይ ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል ባደረጉት ንግግር በግጭቱ የትግራይ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ ነው ብለዋል።
ጄነራሉ የትግራይ ህዝብ በታሪኩ አሁን እንደገጠመው ያለውስብስብ ታሪክ ገጥሞት አያውቅም ሲሉ ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ ሁኔታ ገልፀዋል።
አሁን ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ እንደጥሩ አጋጣሚ ሊወስደው የሚፈልግ ኃይል አለ የሚሉት ጄነራል ዮሐንስ ነገር ግን ይህ የትም አያደርስም ሲሉ ተደምጠዋል።
መንግስት በትግራይ ያለውን ችግር አስተባብሮ ለማቆም ኃላፊነት አለበት የሚሉት ጄነራሉ በትግራይ ጦርነት የጫረው ወንጀለኛ ተጠያቂነት ይኖረዋል ብለዋል።
በዚህ መኃል ግን ህዝቡን የማዳን ስራ የሁሉም ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
በትግራይ ካለው ግጭት አፍታት ጋር በተያያዘ ጄነራል ዮሐንስ፥"የግጭት አፈታትን በተመለከተ የዓለም ታሪክ የሚያስተምረን በጦርነት ከተጀመረ በጦርነት ያልቃል የሚባል ነገር የለም። አምልጦ ከተጀመረ በሂደት ደግሞ አቁመህ፣ተኩስ አቁም ብለህ ምህረት ሰጥተህ አጀንዳ ያለው ቁጭ ብሎ እንዲነጋገር አርገህ ለህዝቡ ሰላም ሲባል እንደዚህ ነው መቋጨት ያለበት" ብለዋል።
በተጨማሪ ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ አመራሮች ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር በነበራቸው መድረክ አንድ አምባሳደር በትግራይ ያለው ሁኔታ ማብቂያ እንዲኖረው ምን አይነት መንገድ ትከተላላችሁ ሲሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር።
በወቅቱ ጄነራል ዮሐንስ፤ በመንግስት፣በTPLFና በነሱ በኩል ግልፅ የሆነ ተጨማሪ የመፍትሄ ሃሳብ እንደሌለ ገልፀው በግላቸው ግን ወታደራዊ አማራጭ ብቻ ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia

ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ተጠየቁ ! ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችቸውን የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ጠየቁ። ዶ/ር ፋውቺ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትራምፕ "በሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ዘንድ በጣም ታዋቂ ነው" በማለት የፕሬዝዳንቱ ቃል የበርካቶችን ሃሳብ እንደሚለውጥ ተናግረዋል። ትራምፕ ወጥተው…
ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ክትባት እንዲወስዱ መልዕክት አስተላለፉ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ክትባት እንዲወስዱ ጥሪ አደረጉ፡፡
ትራምፕ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ክትባቱ አስተማማኝና ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ ይህ ያሉት ጽንፈኛ እና አክራሪ ደጋፊዎቻቸው በኮሮና ዙርያ የተዛባ አመለካከት ይዘው መቆየታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።
በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች የኮሮና ቫይረስ መኖርን የማያምኑ ናቸው ፤ ክትባቱም ሌላ ዓላማ አለው ብለው ያስባሉ፡፡
በርካታ የዶናልድ ትራምፕ ነጭ አክራሪ ደጋፊዎች ክትባት አንከተብም ሲሉ የሚፎክሩ እንደነበሩ ዘገባዎች ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

በጎንደር 600 የክላሽ ጥይት እና የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በጎንደር ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 600 የክላሽ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከመሰል ጥይቶች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።
በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረው የክላሽ ጥይትና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር የዋለው መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በማራኪ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሽዋ ዳቦ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ አራት ሥዓት ተኩል ላይ ነው፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ህዘዝብ ደህንነት መምሪያ ፣ፖሊስ እና ሚኒሻ በመተባበር ነው ህገ ወጥ ጥይቶችና መሳሪያዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው።
በእለቱ የጦር መሳሪያውን ሲገበያዩ የነበሩ ሁለት ግለሶችና አንድ ደላላ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሰላምና ህዝብ ደህንነት መምሪያ አሳውቋል።
በተመሳይይ መረጃ በዞብል ክፍለ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ ከመሰል ከ195 ጥይት 252 የብሬን ጥይት አራት ባዶ የጥይት ካዚና ሶስት የወታደር ኮዳ አራት ባዶ የጥይት ሳጥን አንድ አዲስ የመከላከያ ሬንጀር ከነ ሙሉ አልባሳት ሁለት የፖሊስ የዝናብ ልብስ በቁጥጥር ስር መዋሉን መምሪያው ገልጿል።
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፖሊስ ምርመራ እየተጣራ ነው።
መረጃው የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

#GERD🇪🇹
"2ተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ አይራዘምም" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ዶክተር ስለሺ በቀለ ፥ በቀጣዩ ክረምት ቀጠሮ የተያዘለት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማይራዘም ገለፁ።
ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ዛሬ የህዳሴ ግድብን 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኝ የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ ፣ የሶስትዮሽ ድርድሩ የደረሰበት ደረጃ ለመግለፅ እና ግብዓት ለመሰብሰብ ባለመ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የህዳሴው ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ እንደደረሰ ኢንጂነር ዶክተር ስለሺ በቀለ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የቴዎድሮስ አበባው ገዳዮች ዙሪያ ምርመራ እየተደረገ ነው። የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ በሆነውን ቴዲ ቡናማው ገዳዮች ዙሪያ መንግስት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጓደኞቹ ተናግረዋል። እንደ ጓደኞቹ ገለፃ ቴዲ ቡናማው የትራንስፖርት ሰራ እየሰራ እያለ ሶስት ሰዎች ናቸው ጥቃት ፈፅመው የገደሉት። ጓደኞቹ እንደተናገሩት ይህን የትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት ስራ ከጀመረ አንድ ወር እንኳን አልሞላውም። የቴዲ…
የአዲስ አበባ ፖሊስ የቴዎድሮስን ገዳዮች ለመያዝና ለማወቅ ክትትል እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ !
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ የቴዎድሮስ አበባው (ቴዲ ቡናማው)ን ህይወት የቀጠፉትን ተጠርጣሪዎች ለማወቅ እና ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑ አሳውቋል።
በአጭር ቀናት ውስጥ ውጤቱ ለህዝብ ይገለፃል ብሏል።
እንደ ፖሊስ መረጃ ቴዎድሮስ አበባው (ቴዲ ቡናማው) መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ/ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት (7) ቤተል አዲስ ተስፋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ነው ባልታወቁ ሰዎች በተፈፀመበት ጥቃት ህይወቱ አልፎ የተገኘው።
ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ግለሰቦች ላይ ተመሳሳይ የሆኑ ወንጀሎች ተፈፅመው በተደረገ ክትትል ፈፃሚዎቹን በአጭር ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህዝብ ይፋ ማድረጉን አስታውሷል።
በተለይ የግል ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ አሽከርካሪዎች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ላይ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 8 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ/ም መረጃ ማሰራጨቱን ጠቅሷል፡፡
የግል ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ስራ ላይ የተሰማራው ቴዎድሮስን (ቴዲ ቡናማው) ህይወት ያጠፉ ተጠርጣሪዎችን ለማወቅና ለመያዝ ፖሊስ በሚያደርገው ጥረት ለሚያስፈልጉ መረጃ እንዲሁም ማስረጃዎች ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የቴዎድሮስን ገዳዮች ለመያዝና ለማወቅ ክትትል እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ ! የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ የቴዎድሮስ አበባው (ቴዲ ቡናማው)ን ህይወት የቀጠፉትን ተጠርጣሪዎች ለማወቅ እና ለመያዝ ክትትል እያደረገ መሆኑ አሳውቋል። በአጭር ቀናት ውስጥ ውጤቱ ለህዝብ ይገለፃል ብሏል። እንደ ፖሊስ መረጃ ቴዎድሮስ አበባው (ቴዲ ቡናማው)…
የቴዎድሮስ አበባው የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።
የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ የሆነው ቴዎድሮስ አበባው የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ በደብረ- ቀራኒዮ መድሐኒያለም ቤተክርስቲያን ስር በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ዛሬ ተፈፅሟል።
በቦታው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የክለቡ አመራሮች ፣ አሰልጣኞች ፣ ተጫዋቾች የተገኙ ሲሆን ፣ እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የፋሲል ከነማ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ጅማ አባጅፋር፣ መከላከያ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ....ደጋፊዎች በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በማህበራዊ ሚዲያ የአ/አ ፖሊስ የ "ቴዲ ቡናማው"ን 8 ገዳዮች ያዘ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው።
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ጥዋት ያወጣው መረጃ ከዚህ ቀደም በተለይ የግል ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 8 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የሚገልፅ እንጂ የቴዲ ቡናማው ገዳዮች መያዛቸውን የሚገልፅ አይደለም።
Photo : Ethiopia Coffe Sport Club , Dr Behaielu

የሲሚንቶና የብረት እጥረት ፦
የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር በሲሚንቶ እና ብረት እጥረት ምክንያት በግንባታ ሥራዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አሳወቀ።
ሥራ ተቋራጮች ሰራተኞቻቸውን የመበተን ስጋት ውስጥ መግባታቸውን አመልክቷል።
ማህበሩ በግንባታ ኢንዱስትሪ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ሥራ ተቋራጮች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ ለመክፈል መቸገራቸውን አመልክቷል።
ለግንባታ ወሳኝ የሆኑ የሲሚንቶና ብረት አቅርቦት እጥረት ጎልቶ ይታያል ተብሏል።
በግብዓቶቹ እጥረት ሳቢያ ፕሮጀክቶችን ለማቋረጥ እየተገደድን ነው ብሏል ማህበሩ ፤ በዘርፉ የተሰማራው የሰው ኃይል እንዳይበተን መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።
የብሔራዊ ባንክ ፤ ባንኮች ለተቋራጮች ቅድሚያ ክፍያ እንዳይፈጽሙ የጣለው እገዳ አሉታዊ ጫና ማሳደሩንም ማህበሩ ገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከ22 ሺ በላይ የሥራ ተቋራጮች እንዳሉ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክት ኢዜአ ዘግቧል።

እነሜ/ጄኔራል ገ/መድህን ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት አዘዘ!
እነ ሜጀር ጄኔራል ገ/መድህን ፍቃዴ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።
ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ የታዘዘው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረሽብርና ህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ዐቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተባቸው 21 ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ውስጥ ሰባቱ በትናንትናው እለት ችሎት ተገኝተው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ዋስትና እንዲፈቀድላቸው የጠየቁ ሲሆን ከሳሽ ዐቃቤ ህግም የተፈጸፀመው ወንጀል የሰው ህይወት ያለፈበትመሆኑን በመጥቀስ ዋስትና ሊሰጥ አይገባም ሲል ተከራክሮ ነበር።
ፍርድ ቤቱ የዋስትና ክርክሩን መርምሮ በዛሬው ችሎት ውድቅ በማድረግ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ማዘዙን ኤፍቢሲ አስነብቧል: telegra.ph/FBC-03-17

"...ከዚህ በኃላ ውሳኔ፣ ማዕቀብ፣ ተፅእኖ የሚባለው ባዶ መዝሙር ነው" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በአሜሪካ ይቀርቡ የነበሩት ቅሬታዎች መፍታት እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባዳደር ዲና ሙፍቲ በትላንት መግለጫቸው ተናግረዋል።
እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ ይቀርቡ ከነበሩ ቅሬታዎች መካከል የመጀመሪያው ወደትግራይ እንዳንገባ በሩን ዘግታችሁብናል/አልተፈቀደልንም፣ ህዝቡ ተቸግሯል ፣ ተፈናቅሏል ፣ ተርቧል ፣ ሱዳን የገባ አለ ገብተን እንዳንረዳ ተደርገናል ሲሉ ነበር ፤ ግቡ ተብሎ በር ተከፍቷል/ፍቃድም ተሰጥቷል ሲሉ ገልፀዋል።
በሁለተኛ ደረጃ ሰብዓዊ መብት ጥሰት አለ ፣ የሴቶች መደፈር አለ፣ ግድያ አለ ፣ ዘረፋ አለ ፣ ቃጠሎ አለ ብለዋል ይሄንንም ነፃ በሆነ አካል ጭምር ማጣራት ይቻላል ብሎ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃደኝነቱን ገልጿል ብለዋል።
ሶስተኛው ደግሞ የሰብዓዊ ድጋፍ ጠንክሮ ይቀጥል የሚል ሲሆን ብቻውን መንግስት 70% እየረዳ ነው ፥ ማንኛውም ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልግም በሩን ክፍት አድርጓል ብለዋል አምባሳደሩ።
"ይህ በተደረገበት ሁኔታ ከዚህ በኃላ ውሳኔ ፣ ማዕቀብ ፣ ተፅእኖ የሚለው ባዶ መዝሙር ነው" ሲሉ ተናግረዋል ፤ ሲቀርቡ የነበሩት ምክንያቶች ስለሌሉ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ተፅእኖ የሚባለው ነገር ሊኖርም አይችልም፤ እየቀለለ ይሄዳል ነው ያሉት።

"...ኮቪድ የለም ፣ ጠፍቷል ፣ ፖለቲካ ነው የሚለውን እንተወው ፤ ኮቪድ አለ ፤ በበሽታው መጀመሪያ ከነበረው የበለጠ ችግር እያጋጠመ ነው" - የጤና ባለሞያዎች
በህበረተሰቡ መዘናጋት ምክንያት በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው ኮቪድ-19 በህምክና ባለሞያዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነው።
ለአዲስ ቴሌቪዥን ሲናገሩ የተደመጡ የሚሊኒየም የኮቪድ-19 ማዕከል የጤና ባለሞያዎች ባለፉት 2 ወራት የተማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል።
የታማሚዎች ቁጥር መጨመር ብቻ ሳይሆን ታማሚዎች የሚያስፈልጋቸው የድጋፍ መጠን እየጨመረ ነው፤ይህ ደግሞ በጤና ባለሞያዎች ላይ ስራዎችን ተደራራቢ እያደረገው ይገኛል ብለዋል።
የኮቪድ ወረርሽኝ የለም፣ ጠፋቷል፣ ኮቪድ ፖለቲካ ነው የሚለውን እንተትው የሚሉት የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ባለ መረጃ ኮቪድ-19 አለ መጀመሪያ ሲገባ ከነበረው የበለጠ እየከፋ መጥቷል ሲሉ አስረድተዋል።
ወረርሽኙ ኢትዮጵየ ከገባ ጊዜ አንስቶ ከፊት መስመር የሚዋጉ በርካታ የጤና ባለሞያዎች በቫይረሱ እየተጠቁ ከስራ እንዲስተጓጎሉ ሆነዋል።
አሁንም እያንዳንዱ ሰው የእጆቹን ንፅህና በመጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ፣ በመራረቅ ፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታ ባለመገኘት እራሱን በመጠበቅ እናት አባቱን፣ ማህበረሱቡን እንዲጠብቅ/ከወረርሽኙ እንዲያተርፍ የጤና ባለሞያዎች አደራ ብለዋል።
ፎቶ : ከአቤል ጋሻው

#GERD🇪🇹 "2ተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ አይራዘምም" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ዶክተር ስለሺ በቀለ ፥ በቀጣዩ ክረምት ቀጠሮ የተያዘለት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማይራዘም ገለፁ። ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ዛሬ የህዳሴ ግድብን 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኝ የግድቡን አጠቃላይ…
"ሱዳን በግድቡ ጉዳይ ወደ 2ኛ አማራጭ እየተሸጋገረች ነው" - ኦስማን ማርጋኒ
ሱዳን ከታለቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች መሆኑን ሱዳናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኦስማን ማርጋኒ ተናገሩ።
ኦስማን ማርጋኒ በዛሬው እለት የሕዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በአዲስ አበባ በተካሔደው ሲምፖዚየም ላይ ከተነሱ ሀሳቦች ጋር በማያያዝ በስካይ ኒውስ ቀርበው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከሰጡት መግለጫ በመነሳት “ካርቱም አሁን ላይ በግድቡ ግንባታ እና የድርድር ሂደቱ ላይ የአዲስ አበባን የቆየ እና የማይለዋወጥ አቋም እንደምትረዳ ተስፋ አድርጋለሁ” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ የአፍሪካ ሕብረት እና አሜሪካ በአደራዳሪነት ይግቡ የሚለውን ሀሳብ ውድቅ ካደረገች በኋላ ሱዳን አዲስ የዲፕሎማሲ ዘዴን ትጠቀም ይሆን ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “እኔ አይመስለኝም” የሚል መልስ ሰጥተዋል ፤ ለዚህም ምክንያት “ካርቱም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ጀምራለች” የሚል ነው፡፡
ሱዳን የድርድሩ ጉዳይ እንደማያዛልቃት ተረድታ አሁን ላይ ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ “ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም አማራጭ ሱዳን የውሃ ብክነትን ለማካካስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ እና ውሃ ቀድማ የመያዝ እቅድ እንደምትከተልም አስታውቀዋል።
በአል አይን ኒውስ - የተዘጋጀ👇
telegra.ph/Grand-Ethiopian-Renaissance-Dam-03-17

Grand Ethiopian Renaissance Dam
“ሱዳን ከሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች ነው” ሱዳናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኦስማን ማርጋኒ ሱዳን ከኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገረች መሆኑን ሱዳናዊው የፖለቲካ ተንታኝ ኦስማን ማርጋኒ ተናገሩ። ኦስማን ማርጋኒ የፖለቲካ ተንታኝ እና የአል-ታይያር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከስካይ ኒውስ…
#Alert😷
በአ/አ እና በተወሰኑ ክልሎች የኦክስጅን እጥረት አጋጠመ።
በኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት በ "ጽኑ የሚታመሙ" ሰዎች ቁጥር እጅግ በመጨመሩ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙ ተሰማ።
አሁን ላይ 597 ከፍተኛ ክትትል እና የፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ያዕቆብ ሰማን ገልፀዋል።
ትላንት የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 591 የነበረ ሲሆን ዛሬ 597 ደርሷል።
ዳይሬክተሩ ያዕቆብ፤ በፍጥነት የወረሽኙን የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ #አስገዳጅነት እንዲገባ ካልተደረገ እና ሁሉም በሚገባ ካልተጠነቀቀ የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል አስገንዝበዋል።