TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌቤላ ዘይት ወደ አ/አ መግባት ጀመረ።

ንብረትነቱ የአቶ በላይነህ ክንዴ የሆነው የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ የሚያመርተውንዘይት ወደ አዲስ አበባ መግባት መጀመሩን ኤፍ ቢ ሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የፌቤላ የፓልም ዘይት ፋብሪካ ለአዲስ አበባ ከፋብሪካው ምርት በወር 3 ሚሊየን ሊትር ዘይት ለማቅረብ ስምምነት የተፈጸመ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ ተናግረዋል።

ከስምምነቱ 3 ሚሊየን ሊተር ዘይት ውስጥም እስካሁን 120 ሺህ ሊትር ዘይቱን ቢሮው መረከቡንም ገልጸዋል።

በኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት መጋዘን ባለ 20 ሊትር የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ ምርት የሆኑ ዘይቶች መግባታቸውን ኤ ፍ ቢሲ በአካል ማረጋገጡን በድረገፁ ላይ የገለፀ ሲሆን በቀጣይ የሚገቡት ዘይቶች ለህብረተሰቡ ምቹ እንዲሆኑ ባለ 3 እና ባለ 5 ሊትር እሽጎች እንደሚሆኑ ስምምነት መፈጸሙን ተነግሯል።

Via ኤፍ ቢ ሲ ፣ ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia😷

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከተደረገው 6,212 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 878 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 169 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 156,112 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,321 ሰዎች ሞተዋል፤ 133,607 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 387 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቃሊቲ አዛዥ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተላለፈ! የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነአቶ ጃዋር መሃመድ ህክምና ላይ አስተላልፎ የነበረውን ውሳኔ ለምን እንዳልፈፀመ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አዣዥ ረዳት ኮሚሽነር ግርማ አደሬ በአካል ቀርበው መልስ እንዲሰጡ ቢያዝም አዛዡ ዛሬም ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ፖሊስ አዛዡን ከነገ በስቲያ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ/ም አስሮ እንዲያቀርብ…
ረ/ኮሚሽነር ግርማ አደሬ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ዛሬ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ግርማ አደሬ ችሎት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠበቃ ከድር ቡሎ እንዳሉት ኃላፊው ለፍርድ ቤት እንደገለፁት ተከሳሾቹን የግል ዕክምና ተቋም ያልወሰዷቸው ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን አንስተዋል።

ችሎቱ እንዴት የፍ/ቤት ትዕዛዝ ሊከበር እንዳልቻለ/የበላይ አካል ያዘዛችሁን ነው ወይስ ፍርድ ቤት ያዘዛችሁን ነው የምትፈፅሙት የሚል ጥያቄ እና ፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡ ሲያዞት ለምን አልቀረቡም የሚሉ ጥያቄዎችን ለረ/ኮሚሽነር ግርማ አቅርቦ ለዚህ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም።

ጠበቆች ላንድ ማርክ ሆስፒታል የሚገኝበት ሜክሲኮ አካባቢ የፀጥታ ችግር እንደሌለ አንስተው ተከራክረዋል።

https://telegra.ph/UpdateDW-02-25
የትግራይ ጊዜያዊ አመራሮች በወሰን እና አስተዳደር ጉዳይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ምላሽ መስጠታቸውን ገለፁ !

የትግራይ ወሰን እና አስተዳደር ወደነበረበት በመመለስ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አካባቢውን በቅርቡ ማስተዳደር እንደሚጀምር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ምላሽ መስጠታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ገለፁ።

አመራሮቹ የክልሉ የወሰን እና አስተዳደር ጉዳይ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ቁልፍ የፖለቲካ ጥያቄ ሆኖ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ጦርነቱ የህግ ማስከበር ነው ? ወይስ ግዛትን ማስፋፋት ? የሚል ጥያቄ አሁንም በትግራይ ህዝብ ዘንድ እየተነሳ ነው ብለዋል።

የትግራይ ክልልን ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ አለመመለስ ማለት በቀጣይ ክልሉ እንዳይረጋጋ፣ ክልሉ ከፌዴራል መንግስት ጋር ምናልባትም ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ጋር ከነአካቴው አብሮ እንዳይቀጥል ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አለ ብለዋል አመራሮቹ።

በተጨማሪ የህዝቡ ጥያቄ አለመመለስ ሌላ ፖለቲካዊ ጥያቄ ፤ ሌላ የትግል ስልት ይዞ መጥቶ ምናልባትም #የኤርትራ ዕጣ ፈንታ ይዞ ሊመጣ ይችላል ብለዋል።

https://telegra.ph/Tigray-Interim-Administration-02-25
#NationalExam

"...በፈተናው ዙሪያ ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም አካል አንታገስም" - የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የካቲት 29/2013 በሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ዙሪያ በክልሉ ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም አካል አንታገስም አሉ።

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ይህን ያሉት ዛሬ በባህርዳር በነበረ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ ላይ ነው።

ኮሚሽነሩ የክልሉን ሰላም የማይፈልጉ አካላት ፈተናውን እንዳያደናቅፉ በቅንጅትና በልዩ ትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

በተጨማሪ ተማሪዎች የረጅም አመት ውጤታቸውን የሚያዩበት ጊዜ በመሆኑ የፀጥታ መዋቅሩ በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይም የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ የፀጥታ ሀይል ስምሪት ይደረጋል ያሉ ሲሆን የፀጥታ ተቋሙ ችግሮች ሲፈጠሩ ፈጣን ውሳኔዎችን መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

ፈተናውን የሚያውኩ ማንኛውም መረጃ ፈጥኖ ለፖሊስ አካላት መስጠት ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው የምክክር መድረክ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱና ትክክለኛ ምንጫቸው ከማይታወቁ መረጃዎች ራሳቸውን በመጠበቅ የተዘጋጁበትን ፈተና እንዲፈተኑ ጥሪ ቀርቧል።

በ2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሰጥ የቀረው የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሊሰጥ 10 ቀናት ብቻ ቀርቶታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሪፖርት ፦

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች በኅዳር ወር በሁለት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸውን ትላንት በወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

አምነስቲ ያናገራቸው 41 ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች የተገደሉ ናቸው ያሏቸውን ከ200 በላይ ሰዎች ስም ሰጥተዋል።

በኅዳር 19 እና 20/2013 ዓ.ም የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ ገልጿል።

በተፈጸመው ግድያ በየመንገዱ አስከሬኖች ለቀናት ሳይነሱ መቆየታቸውን ገልጸው በርካቶቹ በጅብ መበላታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

የአምነስቲን ኢንተርናሽናል ሪፖርት በተመለከተ መንግሥታዊው የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳለው ምንም እንኳን ያልተጠናቀቀ ቢሆንም በአክሱሙ ክስተት ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

የኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቱ ጥቂት ነዋሪዎችና የህወሓት ታጣቂዎች ለፈጸሙባቸው ጥቃት የኤርትራ ወታደሮች በወሰዱት የበቀል እርምጃ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰላማዊ ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ተገድለዋል ሲል አመልክቷል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመው የህወሓት ወታደሮች አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኋላ መሆኑንም ኢሰመኮ ገልጿል።

https://telegra.ph/Amnesty-International-02-26
The_Massacre_of_Axum_-_AFR_25.3730.2021.pdf
1.1 MB
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ፦

- 41 ከጥቃት የተረፉ ሰዎች ተገደሉ ያሏቸው 200 በላይ ሰዎችን ስም ዝርዝር ለአምነስቲ ሰጥተዋል።

- የኤርትራ ወታደሮች በመንገዶች ላይ ወደወደቁ አስክሬኖች ማንም እንዳይቀርብ ከልክለው ነበር፤ ለመቅረብ የሚሞክሩት ላይም ይተኩሱ ነበር።

- የ29 እና 14 ዓመት የቅርብ ዘመዶቿ የተገደሉባት አንዲት ሴት "መንገዶች በእስክሬን ተሞልተው ነበር" ስትል ቃሏን ሰጥታለች።

- የአካባቢው ሽማግሌዎች እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ጣልቃ ከገቡ በኋላ የተገደሉትን ሰዎች ለቀናት መቅበር ተጀመረ።

- ነዋሪዎች በአንድ ጊዜ አስከ 10 የሚደርሱ አስከሬኖችን በፈረስና በአህያ በሚጎተቱ ጋሪዎች በመጫን እያመላለሱ የበርካታ ሰዎች ቀብር የተፈጸመው ኅዳር 21 ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SidamaRegionalState

በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የ12 ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ መደረጉን የክልሉ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ የመንግስት እና የህዝብ ንብረት የሆነ 7.8 ሚሊዮን ብር ከምዝበራ ማዳኑንም ገልጿል።

ኮሚሽኑ ለኢዜአ በሰጠው መረጀ ከቀረቡለት 56 አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥያቄዎች ውስጥ 54ቱን ተቀብሎ ምላሽ ሰጥቷል።

በዚህም የ81 ሰዎች ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እና የ12 ሰዎች ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ መደረጉን ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ከሁለት ቦታ ደመወዝ ሲበሉ የነበሩ እና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች በህግ እንዲጠየቁ ሰነድ በማደራጀት ለሚመለከተው የህግ አካል እንዲተላልፈ መደረጉንም ገልጿል።

በሀሰት ለተደራጁ 9 የአረንጓዴ ፓርክ ልማት እና የኮብል ስቶን ማህበራት ክፍያ ሊፈጸም የነበረውን ጨምሮ 2 ሚሊዮን 367 ሺህ ብር በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ከተለያዩ ተቋማት ተመዝብሮ የነበረ 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በኦዲት ግኝት ተረጋግጦ ተመላሽ እንዲደረግ መስራቱንም ለኢዜአ በሰጠው መረጃ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአንድ የሰርግ መልስ ዝግጅት ላይ የፈነዳ ቦንብ አንድ ሰው ሲገድል 15 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ !

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በአንድ የሰርግ መልስ ዝግጅት ላይ የፈነዳ ቦምብ በ15 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ አንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (FBC) ዘግቧል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ፍንዳታው የደረሰው ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ ላም ዋሻ በሚባል ቀበሌ መሆኑን አሳውቋል።

ለሰርግ መልስ ተጠርተው የነበሩ ታዳሚዎች በዝግጅቱ ቦታ ላይ እየጨፈሩ እያሉ ከአንድ ግለሰብ ኪስ የወደቀ የጭስ የእጅ ቦምብ በእግር ተነካክቶ ፈንድቷል።

በፍንዳታው የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ፥ ሌሎች 15 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት ደርሶባቸው በደነባ ሆስፒታል እና በደብረ ብርሃን ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ፥ ቦንቡን ይዞ በስፍራው የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ17 ዓመቷን ወጣት የደፈረው ግለሰብ በ8 ዓመት እስራት ተቀጣ።

አዛኝና ተባባሪ መስሎ በመቅረብ የ17 ዓመቷን ወጣት የተከራየው ቤት ወስዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 ዓመት ጽኑ እስራት መቅጣቱን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የ18 ዓመቱ ወጣት ተከሳሽ ዳንኤል ጥር 28 ቀን 2013 ከምሽቱ 10፡00 ሰዓት ላይ ወጣት ብርትኳን ሀሰንን በወቅቱ በሚዛን ከተማ የደቡብ ክልል የባህል ስፖርት ውድድር በሚካሄድበት ወቅት አብዛኛው የከተማዋ መኝታ ቤቶች በስፖርተኞች መያዙን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ወንጀሉን መፈፀሙ ተገልጿል።

ተከሳሹ የ17 ዓመቷን ወጣት ብርትኳን ለስራ ከሄደችበት ቤሮ ወረዳ ለዕረፍት ወደ ቤሰቦቿ ጂማ ለመጓዝ ሚዛን ስትደርስ አልጋ ያለበት ቦታ ላሳይሽ በሚል ከተግባባ በኋላ ወዲያው ሀሳቡን በመቀየር ወደእኔ ቤት ሂደን ከእህቴ ጋር ትተኚያለሽ በማለት አታሎ በኪራይ ወደሚኖርበት ቤት ከወሰደ በኋላ በሀይል በማስገደድና ግለሰቧ ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ ከደፈረና ደጋግሞ ግብረስጋ ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ አውጥቶ ጎዳና ላይ መጣሉን በቀረበበት ክስ ተመላክቷል፡፡

ተከሳሽ ዳንኤል በዐቃቤ ህግ የተመሰረተበትን ክስ በችሎቱ ካዳመጠ በኋላ ወንጀሉን መፈጸሙን በማመኑ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃና መረጃ ሳያቀርብ በ8 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደሰጠበት የቤንች ሸኮ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ3 አመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪነቱ ሳንጃ ከተማ ቀበሌ 01 የሆነው የ42 ዓመት ጎልማሳ በጋሸው በላይ የ3 አመት ህፃን መድፈሩን የታች አርማጭሆ ወረዳ ፍርድ ቤት ገልጿል።

ግለሰቡ ወ/ሮ ሚሚ አበበ መኖሪያ ቤት ተገኝቶ የግል ተበዳይ የሆነችውን የ3 ዓመት ህፃን አስቴር አይቸውን በመድፈሩ የታች አርማጭሆ ወረዳ ፍርድ ቤት በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

የታች አርማጭሆ ወረዳ ወላጆች ልጆቻቸው በጥንቃቄ መያዝ እና መቆጣጠር እንዳለባቸው፤ ለማያውቁት ሰው ልጃቸውን አምነው መስጠት እንደሌለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OrangeDigitalCenterEthiopia ኦሬንጅ የዲጂታል ማዕከል (ኦዲሲ) የምረቃ ስነስርዓት ዛሬ በአይሲቲ ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል። አዲስ አበባ በ "አይሲቲ ፓርክ" ውስጥ በ500 እስኩዌር ሜትር ላይ የሰፈረው ኦሬንጅ የዲጂታል ማዕከል (ኦዲሲ) በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን ኦሬንጅ እየሰራ ከሚገኝባቸው 32 ሀገራት ማለትም በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና አፍሪካ አህጉራት አንዱ አካል…
#OrangeDigitalCenter

አዲስ አበባ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ በ500 እስኩዌር ሜትር ላይ የሰፈረው የኦሬንጅ ዲጂታል ማዕከል ለወጣቶች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ስልጠናዎችን በመስጠት፤ ሥራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ እና አነስተኛ ድርጅቶችን በማነቃቃት እና የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት የሚያግዝ ማዕከል ነው።

አገልግሎቱ የሚሰጠውም በነጻ እንደሆነ በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል።

ማዕከሉ በውስጡ አራት መሰረታዊ ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ፦

- የኮዲንግ ት/ቤት( Coding School)፤
- ''FabLab Solidaire'' የተሰኘ የዲጂታል ማኑፋክቸሪንግ ላብራቶሪ፤
- ለጀማሪ የንግድ ድርጅቶች ድጋፍ የሚያደርግ ማዕከል (Orange Fab) እንዲሁም - የኢንቨስትመንት ሰጪ (Orange Ventures Africa) ማዕከላት ናቸው።

https://telegra.ph/ODC-02-25
#AddisAbaba

"የወጣቶች ተሳትፎ ለብሄራዊ መግባባት እና ለመጪው ምርጫ" በሚል እዕስ ነገ ቅዳሜ ጥዋት 3 ሰዓት በብሄራዊ ትአትር መዘጋጀቱ አዘጋጆቹ ገልፀውልናል።

የመግቢያ ካርዱ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ መደብሮች ማግኘት እንደሚቻል የተነገረ ሲሆን በመድረኩ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ፣ ዶ/ር መስከረም ገስጥ፣ ፓስተር ፃድቁ አብዶ ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ይገኛሉ።

ይህን መድረክ ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ማነቃቃት አገልግሎት ነው።

በሌላ መረጃ ፦

አፍሪካን ሞዛይክ ኤዲት (EDIT) የተሰኘ ትኩረቱን በፋሽን ላይ ያደረገ መጽሔት ታትሞ ለንባብ ሊበቃ መሆኑን አዘጋጆቹ በላኩልን መልዕክት ገልጸውልናል። መጽሔቱ ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆን በእንግሊዝኛ እና አማርኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለንባብ የሚበቃ ነውም ተብሏል።

76 የገጽ ብዛት ያሉት መጽሔቱ በአመት ሁለት ጊዜ በሦስት ሺ ቅጂ (1500 አማርኛ 1500 እንግሊዝኛ) ታትሞ ለገቢያ እንደሚቀርብ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

ላለፉት 2 አመት ዝግጅት የተደረገበት መጽሔቱ የፊታችን ቅዳሜ የሚመረቅ ሲሆን የመጽሔቱን ምርቃት ተከትሎ እሁድ ለገጣፎ በሚገኘው የአፍሪካ ሞዛይክ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ዝግጅቶች ተሰናድተዋል።

ለበለጠ መረጃ 0970231639 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ስብሀት ነጋ በግል ሀኪማቸው እንዲታከሙ ፍርድ ቤት አዘዘ!

(በዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ)

የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ተሰይም የእነ ስብሀት ነጋ እና ሌሎች 2 መዝገቦችን ተመልክቷል።

አቶ ስበሀት ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት ጠበቆች ከዚህ ቀደም በፖሊስ ሆስፒታል ቢታከሙም ከህመማቸው አንፃር የሚመጥን እንዳልነበር አስረድተዋል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት ክትትል ያደርጉበት በነበረው አዲስ ህይወት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲፈቅድ ችሎቱን ጠይቀዋል።

የህገመንግስቱ አንቀፅ 21/2 መሰረት ተጠርጣሪው በግል ሀኪም ቢታከሙ የሚከለክል ሁኔታ አላየሁም ያለው ችሎቱ የግል ሀኪማቸው የህክምና መሳሪያዎቹን ይዞ ባረፉበት ቦታ እንዲያክማቸው አዟል።

የህመማቸው ሁኔታ ከፍተኛ መሳሪያውችን የሚጠይቅ ከሆነ ደግሞ ሀኪማቸው በችሎት ቀርቦ ቃለመሀላ ከፈፀመ በኋላ አስፈላጊው እጀባ ተደርጎላቸው በሆስፒታል ሆነው እንዲታከሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ይህ የማይሆን ከሆነ የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውም የተጠበቀ መሆኑን ችሎቱ አሳስቧል።

በሌባ በኩል የፌደራል ፖሊስ ባለፉት የምርመራ ቀናት የ85 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን እና የጦር መሳሪያዎችን ማሰባሰቡን ለችሎቱ ገልጿል።

ሆኖም ተጨማሪ የምርመራ ስራዎች ስለሚቀሩት 14 ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ምርመራው በጅምላ መሆን የለበትም በማለት ተቃውመዋል።

ይህን ሁሉ ጊዜ ለምርመራ ከተሰጠ በኋላ አሁንም በጅምላ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ የለበትም ብለዋል።

ማን ምን አይነት ወንጀል እንደፈፀመ በግልፅ ሊቀመጥ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። ፖሊስ የእያንዳንዱን ወንጀል ለይቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠው ችሎቱ ተጨማሪ 13 ቀን ፈቅዷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ !

ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ስርጭትን አስመልክቶ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ( ዶ/ር ኢንጂነር) ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲከናወን ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት እና ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦተሬ በበኩላቸው ፈተናው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄና ቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከየካቲት 21 - 26/2013 ድረስ የመፈተኛ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ሥራ እንደሚጠናቀቅም በውይይቱ ተገልጿል።

በመሆኑም ፈተናው በሚፈለገው አግባብ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት፣የትምህርት ማህበረሰቡና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (MoE)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መገለጫ ፦

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለኑሮ ውድነት ምክንያት ናቸው የተባሉ ከ30 ሺህ በላይ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዱን አሳውቁ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች በ200 ሺ መጋዘኖች ላይ ብርበራ ተደርጎ 30 ሺ ያህሉ ላይ ምርት አከማችተው በመገኘታቸው ርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል። በተጨማሪ 2 ሺህ 800 ሚዛን ቤቶችም ሚዛን ሲያዛቡ ተገኝተው ርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጿል፡፡

ም/ከንቲባዋ በሰጡት መግለጫ የሚስተዋለው የኑሮ ውድነት ዋነኛ ምክንያቱ ከምርት መሸሸግ እስከ ግብይት ማስተጓጎል የደረሱ አሻጥሮች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ክትትልና እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ተብሏል።

ከዚህ ባሻገርም የሸማች ሕብረት ሥራ ማሕበራት ያለውን አቅም ለማጎልበት የ500 ሚሊዮን ብር ድጎማ እንዲያገኙ መደረጉም ተገልጿል። - (ኤፍ ቢ ሲ፣ ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
The_Massacre_of_Axum_-_AFR_25.3730.2021.pdf
ትግራይ አክሱም ፅዮን ቅድት ማሪያም ቤተ ክስርቲያን ውስጥ 750 ሰዎች ተገድለዋል ?

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማህበራዊ ሚዲያ በአክሱም ጽዮን ያለውን ጽላት የኤርትራ ወታደሮች ለመውሰድ ሲሞክሩ በተፈጠረ ግርግር የሰው ህይወት ጠፍቷል በሚል ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ የሚያረጋግጥ መረጃ እንዳላገኘ ለቢቢሲ አሳውቋል።

ነገር ግን ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2013 ዓ/ም በአክሱም አስከፊ የተባለ ጭፍጨፋ መካሄዱን አረጋግጫለሁ ብሏል።

እንደ አምነስቲ ገለፃ ኅዳር 19 የተወሰኑ የህወሓት ሚሊሻዎች አክሱም ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ካለች አንድ ተራራ ወይም ጉብታ ላይ ወደ ኤርትራ ወታደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር።

ይህ ካበቃ በኋላ እዛው የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ሌላ ተጨማሪ ኃይል እና የጦር መሳሪያ ተጨምሮ (ታንኮችን ጭምር) ጥቃት ሰነዘሩ። በመንገድ ላይ ያገኙትን እና በየቤቱ እያገቡ ያገኙትን ጎረምሳ ወንዶች ሲገድሉ እደነበረ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ብሏል ተቋሙ።

በማግስቱ ህዳር 20 ይህ ድርጊት ቀጥሎ ነበር የሚለው አምነስቲ አስከሬን ማንሳንትም አይቻልም ነበር ፤ ኅዳር 21 2013 ዓ.ም. በአክሱም ጽዮን ክብረ በዓል ዕለት ነው እንዲቀበሩ የተደፈቀደው ብሏል።

አምነስቲ በ21 ትልቅ ግድያ እንደነበረ የሚያስረዳ ነገር የለም ፤ ይልቁንም አስከሬን መቅበር የተጀመረውም በእዛው ዕለት ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎችን ውድቅ የሚያደርግ መረጃ ሰጥቷል።

#AmnestyInternational #Ethiopia #Tigray #Axum

https://telegra.ph/Amnesty-International-02-26-2
የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ለአምነስቲ ሪፖርት ፦

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “አክሱም ከተማን በተመለከተ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው ሪፖርት የተጠቀመው የመረጃ ምንጭ ፍትህን ለማስፈን ዓላማ አይጠቅምም” ሲል ገለጸ።

ተቋሙ ለመረጃ ምንጭነት የተጠቀመውም በምስራቅ ሱዳን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሰዎችን እንዲሁም ውስን የአክሱም ነዋሪዎችን በስልክ ቃለ መጠይቅ ማድረጉ የተሟላ ምስል ለመያዝ እንደማያስችል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

https://telegra.ph/Ethiopia-02-26-2