TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኤርትራ ምላሽ ፦

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል ዛሬ ከሰዓት በኋላ በትዊተር ባሰፈሩት ጽሁፍ የአገራቸው ወታደሮች አክሱም ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለመግደላቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት እንዳጣጣሉት ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ሚኒስትሩ ኤርትራ በሪፖርቱ መቆጣቷንና የተሳሳተ ነው ያሉትን ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደማትቀበለው በመግለጽ ሪፖርቱ በአብዛኛው መሰረት ያደረገው ሱዳን ውስጥ ባለው "ሐምዳይት የስደተኞች መጠለያ" ውስጥ ያሉ 31 ግለሰቦችን ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አቶ የማነ ጨምረውም ፥ "በዚህ መጠለያ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በተገደሉበት የማይካድራው ጭፍጨፋ ተሳታፊ ሆነው የሸሹ የህወሓት ሚሊሻዎች መሆናቸው ይታወቃል" በማለት በትዊተር ገጻቸው ላይ ስፍረዋል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከእውነት የራቀ መሆኑን በመግለጽ አገራቸው እንዳማትቀበለው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት የ19 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከተደረገው 6,659 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 935 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ትላንት 954 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 157,047 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,340 ሰዎች ሞተዋል፤ 134,561 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 375 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ፦

በትግራይ ክልል የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ኢንጅነር አስቴር ይትባረክ ዛሬ እንዳስታወቁት በክልሉ 12 ሺህ ያህል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይገኛሉ። 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 29/2013 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጠው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች በትግራይ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተው ፈተና እንዲወስዱ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ አክሱም፣ በዓዲግራትና ራያ ዩኒቨርስቲዎች እስከ የካቲት 23/2013ዓ.ም. ድረስ በአካል ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት ወራት የመማር ማስተማር ሂደት ባይኖርም ተማሪዎች ቀደም ባሉት ዓመታት የትምህርት ዝግጅት እያደረጉ በመምጣታቸው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንዲቀመጡ ያስችላችዋል ብለዋል።

ተማሪዎቹ ቀደመው በዩኒቨርሲቲዎቹ በመገኘት ለአስር ቀናት ያህል ዝግጅት እንዲያደርጉ እድል መሰጠቱን ኢንጅነር አስቴር ማስታወቃቸውን ኢዜአ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ጊዜያዊ አመራሮች በወሰን እና አስተዳደር ጉዳይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ምላሽ መስጠታቸውን ገለፁ ! የትግራይ ወሰን እና አስተዳደር ወደነበረበት በመመለስ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አካባቢውን በቅርቡ ማስተዳደር እንደሚጀምር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ምላሽ መስጠታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ገለፁ። አመራሮቹ የክልሉ የወሰን እና አስተዳደር ጉዳይ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ቁልፍ የፖለቲካ…
የቀጠለ...

የትግራይ ጌዚያዊ አመራሮች ከጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በነበረው ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ወታደሮች ስለመግባታቸው አምኗል ወይ ተብለው ተጠይቀዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገ/ህይወት ፥ ይህ "አልተካደም" ሲሉ መልሰዋል።

በውይይቱ ወቅት በትግራይ ችግሮች እንዳሉ ታምኗልም ብለዋል። 

አቶ አበበ ገ/ህይወት ፥ "በትግራይ የህግ ማስከበሩ ሂደት ከግዛት ማስፋፋት ጋር ተያይዞ መሄዱ ይታወቃል የህግ ማስፈፀሙ ጉዳይ ከዚህ ጋር መገናኘት አልነበረበትም ፤ እንዲሁም የሀገር ሉኣላዊነት ተደፍሯል" ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ አበበ ይህ የተፈጠረበትን ምክንያት እና ሁኔታ ላይ ትንታኔ መስጠት እንደማይፈልጉም ገልፀዋል።

ነገር ግን በትግራይ ችግሮች እንደተከሰቱ ግልፅ ነው ፤ የሚካድም አይደለም ፤ በራያ ፣በምዕራብ በኩል ያለውም ነገር ይታወቃል፣ እንደዚሁም የሰሜኑ ትግራይ ክፍል የደረሰው ነገር ይታወቃል ብለዋል።

በትግራይ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እየተሄደበት ያለው ሂደት ላይ እንቅፋ አለ ያሉ ሲሆን እንቅፋቶቹ የመጡትም የመከላከያ ሰራዊቱ ሆነ የፌዴራሉ መንግስት በብዙ ነገሮች ተወጥሮ ስላለ ነው ብለዋል።

https://telegra.ph/Tigray-Interim-Administration-02-26
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው !

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርስቲው እያስመረቃቸው ያሉ ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቋርጠው የነበሩና በተያዘው አመት ያጠናቀቁ ናቸው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴራል እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Via ENA , Haramaya University
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ተመድ በፍትሃዊ የኮቪድ-19 ክትባት ስርጭት ዙሪያ የውሳኔ ሀሳብ አጸደቀ !

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት ግጭት ባለባቸው ቀጣናዎችና በድሃ ሀገራት የኮቪድ19 ክትባት አቅርቦት እንዲስተካከል የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ማጽደቁ ተዘግቧል፡፡

ምክርቤቱ በኮቪድ19 ዙሪያ የውሳኔ ሃሳብ ሲያጸድቅ ከባፈው አመት ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤አዲሱ የውሳኔ ሃሳብ በሁሉም የምክርቤቱ አባላት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ፍትሀዊ የክትባት ስርጭት በጣም አስፈላጊና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ነገርግን በተግባር የተደገፈ እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

Via AlAIN
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በ69 ሚሊዮን ዶላር በድሬደዋ እየተገነባ የሚገኘው የደረቅ ወደብ ግንባታ 50% መድረሱ ተገለፀ !

በድሬዳዋ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ የተመራ ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን በድሬደዋ እየተገነባ የሚገኘውን ደረቅ ወደብ ያለበትን ሁኔታ መጎበኘቱ ተሰማ።

ከንቲባው በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ግንባታ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል፤ ግንባታው ተጠናቆ ሲራ ሲጀምር ከዚህ በላይ የስራ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

በተጨማሪም ደረቅ ወደቡ የድሬዳዋና የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለውጥ በመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሎጂስቲክ ዘርፍ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረትዓብ ተኽሉ ደረቅ ወደቡ በ69 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ34 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ ገልፀዋል፤ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር እስከ 4 ሺ ኮንቴነር ማስተናገድ እንደሚችል አሳውቀዋል።

የድሬዳዋው ደረቅ ወደብ ግንባታ በአውሮፓውያኖቹ አቆጣጠር ጁን 20 / 2020 ግንባታው የተጀመረ ሲሆን በ15 ወራት ለማጠናቀቅ ነው ውል የተገባው አሁን ግንባታው 50% መድረሱን ተገልጿል።

መረጃው የድሬዳዋ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በእድሳት ምክንያት ተዘግቶ የቆየው "አምባሳደር ፓርክ" ተመረቀ !

የአ/አ "አምባሳደር ፓርክ" በ49 ሚሊየን ብር እድሳት ተደርጎለት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በ1 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የአምባሳደር ፓርክ የእድሳት ስራ በ25 ወራት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በ4 ሄክታር ቦታ ላይ በ101 ሚሊየን ብር የተገነባውና በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ ስም የተሰየመው የቢትወደድ ወልደፃዲቅ ጎሹ መታሰቢያ ፓርክም በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በሁለቱም ፓርኮች ምርቃት ላይ ላይ የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ተገኝተዋው እንደነበር ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photo : Abbas Shah (File)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የእጩዎች ምዝገባ ለ4 ቀናት ተራዘመ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ እንዳለ የሚታወቅ ነው።

• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
• የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር
• የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል
• የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል
• የጋምቤላ ብሔራዊ ክልል
• ሃሪሪ ብሔራዊ ክልል ለእጩዎች ምዝገባ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የካቲት 08- 21 ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ምዝገባም መካሄድ መጀመሩ አዘነጋም።

ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም የምርጫ ክልል ቢሮዎች ለመከፈት በመዘግየታቸው ፣ የትራንስፓርት መጓተት የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ የምዝገባ ቀንን በማራዘሙ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች እጩዎችን ለመመዝገብ ችግር ስላጋጠመን ይራዘምልን ብለው መጠየቃቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች አሳማኝ ናቸው ያለ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በጀመሩት ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ላይ የሚካሄደው የእጩዎች ምዝገባ ለ4 ቀናት ያህል እስከ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ዛሬ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ሽጉጥና ከ5 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች ተያዙ።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል ከጭነት ጋር ተመሳስሎ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን ፣ ሽጉጥ ፣ ከ5ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች እንደተያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡

መነሻውን ጎንደር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 99483 አይሱዙ ተሽከርካሪ በጉሌሌ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መንደር ሰባት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት መያዙ ነው የተገለጸው።

በተደረገው ክትትልም 2 ብሬን ፣ 2 ስናይፐር ፣ 38 ትልቁ እና 25 ትንሹ ኢኮልፒ ሽጉጦች ፣ 5992 የክላሸ ኮቭ ጥይት ፣ 892 የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣ 5 የስናይፐር ጥይት ፣ የብሬን እግር እና ሁለት የብሬን ዝናር ህገወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያዘዋወሩ ከተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ 2 ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EthiopiaElection2013

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሀይማኖት መምህርነታቸውና በሚሰጧቸው ማህበራዊ ሂሶች የሚታወቁት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግላቸው እንደሚወዳደሩ አሳውቁ።

ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵየ ቼክ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ "...በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እወዳደራለሁ" ብለዋል።

"ሀሳብ ከመስጠት ባለፈ በሂደቱ ተሳታፊ መሆን ይገባል ብዬ ስላመንኩ በምርጫው ለመሳተፍ ወስኛለሁ" የሚሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 12/13 ምርጫ ክልል በግል ተወዳዳሪነት ዕጩ ሆነው አስረድተዋል።

ለምን በግል ለመወዳደር ፈለጉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፥ "...ከፓርቲ ፖለቲካ ይልቅ ግላዊ ፖለቲካ የተሻለ ነው ብየ ስለማምን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ www.ethiopiacheck.org
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወልርድ ቪዥን በትግራይ ከልማት ስራ ከሚሰራበት ገንዘቡ ቀንሶ በችግር ላይ ላሉ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል !

ወርልድ ቪዥን የሰሜን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በትግራይ የልማት ስራዎችን ከሚያከናውንበት በጀት 19 ሚሊዮን ብሩን በጦርነቱ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ስራውን ጀምሯል።

ወርልድ ቪዥን ባለፉት ቀናት በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ ዜጎች 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በውቅሮ ኽልተ አውላዕሎ ለሚገኙ 590 የተቸገሩ ዜጎች ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዝብ ድጋፍ አድርጓል።

ለአንድ ሰው 2,200 ብር ነው ወርልድ ቪዥን እየሰጠ የሚገኘው።

በአጠቃላይ በትግራይ ድርጅቱ በ7 ወረዳዎች ላይ የሚሰራ ሲሆን ለዚህ ድጋፍ 19 ሚሊዮን ብር መድቧል፤ በቀጣይ ወደ ሽረ፣ አላማጣ፣ ዓዲግራት እና ሌሎች ያልደረሰባቸው ቦታዎች በመድረስ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ድርጅቱ እያደረገ ያለው ድጋፍ በቂ በለመሆኑ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ባለሀብቶች አፋጣኝ እርዳት ለትግራይ ህዝብ ማድረስ ይገባቸዋል ብሏል። ያለው ችግር መጠነ ሰፊ በመሆኑ ሁሉም ሊተባበር ይገባል ብሏል።

የወልርድ ቪዥን የሰሜን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ተስፋይ አስፋ ፥ እንደድርጅት ሰራተኞች ከ10-15 ፐርሰንት ከደሞዝ ላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል እንደገቡ ገልፀዋል፤ ከደሞዛቸው ተቆርጦ ለትግራይ እገዛ ለማድረግ የወሰኑት በትግራይ ክልል ብቻ የሚሰሩ የወልድ ቪዥን ሰራተኞች ሳይሆኑ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ ሰራተኞች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ባለሃብቶችን በማስተባበር ድጋፍ እንዲያደርጉ ገንዝብ የማሰባሰብ ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia