በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ ነው፤ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር፣በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እና በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ በእጅጉ እያሻቀበ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ12 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከተደረገው 6,089 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 977 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 387 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 155,234 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,316 ሰዎች ሞተዋል፤ 133,438 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 386 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#MinistryOfHealthEthiopia
ጤና ባለሙያዎች ከምረቃ በኋላ የሙያ ፍቃድ ከማግኘታቸው አስቀድሞ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንዲፈተኑ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።
ይህ የተባለው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በአገሪቱ ውስጥ ካሉ የጤና ሙያ ማህበራት ጋር ባካሄደው ምክክር ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ ከሙያ እድሳት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ማንኛውም የጤና ባለሙያ በሙያው ሲያገለግል ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ እድሳቱን እንደሚከውን ተጠቁሟል፡፡
አሁን ላይ አንድ ባለሙያ እድሳት ለመፈጸም የተለያዩ የሙያ ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለመውሰድ እንደሚገደድና በቂ ስልጠና ጊዜን ማሳለፉም መረጋገጥ እንዳለበት ተገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ በአሁኑ ግዜ ተመርቀው ስራ እያጡ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና በዚህም ላይ ከጤና ሙያ ማህበራቱ ጋር መፍትሄ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል፡፡
ምንጭ፦ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን

ኤርትራ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውጥረት የለሁበትም አለች።
ሱደን ፥ "... የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መከላከያ መለዮን ለብሰው አብረው ድንበር ላይ እንደሚገኙ መረጃ አለን" ማለቷን ተከትሎ የኤርትራው ፕሬዝደንት ለሱዳን ጠ/ሚ መልዕክት መላካቸውን አል ዓይን ዘግቧል።
ትላንት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል ያሲር አል አታ ከአል አረቢያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ “የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መከላከያን መለዮ ለብሰው አብረው ድንበር ላይ እንደሚገኙ መረጃ አለን” ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህን ተከትሎ የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የጽሁፍ መልዕክት ልከዋል።
መልዕክቱን ያደረሱት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አማካሪ የማነ ገበረአብ ናቸው።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት በመልዕክታቸው ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር ባለው ሁኔታ ስጋታቸውን በመግለፅ ሀገራቸው ከድንበር ውጥረቱ ጋር ምንም የሚያገናኛት ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል፡፡
የቀጣናውን ሰላም ፣ መረጋጋት እና ደህንነት በሚያረጋግጥ መንገድ ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለው ውጥረት በሰላም እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል ፦
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አማካሪ የማነ ገበረአብ ዛሬ በሱዳን ካርቱም በነበራቸው ቆይታ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን ጋር ተገናኝተው ነበር በወቅቱም የኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነትን በሚመለከት ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል።
Via AlAin , Yemane G. Meskel

ከዋጋ ንረቱ በተጨማሪ የሚዛን ጉድለት ለሸማቹ ትልቅ ፈተና መሆኑ ተገለጸ !
ምክንያታዊ ያልሆነ የሸቀጦችና የምግብ ነክ ዋጋ ጭማሪ ከሚዛን ጉድለት ጋር ተደምሮ ህብረተሰቡን እያማረረ መሆኑን የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቋል፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፥ አሁን እየተስተዋለ ያለው የዋጋ ግሽበት በአመዛኙ ሰው ሰራሽ ነው ብሏል። እራሱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ዙሪያ በቅንጅት ባለመስራታቸው ችግሩ እየተባባሰ መጥቷልም ብሏል።
ከዋጋ ንረቱ በተጨማሪ በጣም ያልዘመኑ /አናሎግ/ ሚዛን ላይ ከፍተኛ የማጭበርበር ሥራ እንደሚሰራ ባለስልጣን መ/ቤቱ በጥናት እንደተረጋገጠ አሳውቋል።
አንዳንድ ነጋዴዎች የኪሎውን መያዣ ብረትና ከኪሎው ስር የሚወተፈው ማግኔት በማውጣት በእያንዳንዱ ሸቀጥ ላይ ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ግራም እንደሚያጨበረብሩ በጥናቱ መለየቱን ተገልጿል።
የጥናቱን ውጤት ተከትሎ በተደረገ ክትትል ችግሩ በተገኘባቸው ወፍጮ ቤቶችና ሱቆች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን መስሪያ ቤቱ ጠቁሞ ሚዛኖች ዲጅታል እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሶ አንዳንድ ስጋ ቤቶችና አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ሱቆች ተግባራዊ ቢያደርጉም የነበረው ቅንጅታዊ አሰራር በመላላቱ ምክንያት አሁን ላይ ሚዛን ላይ የሚደረገው ክትትል ያለበት ደረጃ ለመግለጽ ያስቸግራል ተብሏል።
ምንም እንኳ በአንዴ ሁሉን ሚዛኖች ወደ ድጅታል መቀየር አስቸጋሪ ቢሆንም ያለውን ሚዛን መከታተልና ቁጥጥር ማድረግ በንግድ ላይ የሚታየውን የሚዛን ጉድለት ህገ ወጥነት ለመከላከል በጋራ መሰራት እንደሚገባ መስረያ ቤቱ አመልክቷል። (ኢፕድ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

"ሙሃመድ ዴክሲሶ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቅ ይገባል" - ኢሰመኮ
ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 1 ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኘውን ሙሃመድ ዴክሲሶ በተመለከተ የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋስ እንዲለቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ከእስር አለመለቀቁ እንዳሳሰበው ገልጾ፣ ሙሃመድ ዴክሲሶን ጨምሮ ሌሎችም በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተከብሮላቸው በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ አሳስቧል።
የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የተማሪዎች የምረቃ መርኃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ በመሆኑ ታዳሚ የነበረው ሙሃመድ ዴክሲሶ፣ በዝግጅቱ ላይ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን እና አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በማስመልከት መፈክሮችን ማሰማቱን ተከትሎ በፌደራል ፖሊሶች ተይዞ በጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ሙሃመድ ዴክሲሶ ለኢሰመኮ አስረድቷል።
* ዝርዝር የኢሰኮ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Attention😷
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊነቱ እየጨመረ እንደሚገኝ EPHI አሳውቋል።
ባለፉት 7 ቀናት (ከየካቲት11 - የካቲት17) 47,204 ናሙና ከሰጡት ግለሰቦች ውስጥ 5,927 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፡፡ በእነዚህም 7 ቀናት (ከየካቲት11 - የካቲት17) ከተመረመሩት ከመቶ 13 ግለሰቦች (13%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ማለት ነው።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥርም ከእለት ወደ እለት እያሻቀበ ይገኛል።
እስከ ትላንትናው እለት ብቻ 386 ሰው በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 61 ህሙማን በ መተንፈሻ ማሽን ላይ ይገኛሉ፡፡
በቫይረሱም ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ ሲሆን እስካሁን 2,316 ግለሰቦች በኮቪድ -19 ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በዚህ 7 ቀናት ብቻ የ79 ግለሰቦች ህይወት አልፏል፡፡
ሕብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ይህንን እውነታ በመገንዘብ አሁንም የጥንቃቄ መንገዶችን በሚገባ መተግበር እንዳለባቸው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስገንዝቧል።

#OrangeDigitalCenterEthiopia
ኦሬንጅ የዲጂታል ማዕከል (ኦዲሲ) የምረቃ ስነስርዓት ዛሬ በአይሲቲ ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል።
አዲስ አበባ በ "አይሲቲ ፓርክ" ውስጥ በ500 እስኩዌር ሜትር ላይ የሰፈረው ኦሬንጅ የዲጂታል ማዕከል (ኦዲሲ) በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን ኦሬንጅ እየሰራ ከሚገኝባቸው 32 ሀገራት ማለትም በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና አፍሪካ አህጉራት አንዱ አካል ነው።
ማዕከሉ ለወጣቶች ነፃና ክፍት የሆኑ ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ፣ ሥራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ እና የንግድ ሐሳባቸውን እንዲያጎለብቱ በማድረግ ብቁ የሆኑ ሐሳቦች ላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ የሚደግፍ ይሆናል ተብሏል።
በውስጡም የኮዲንግ ማሰልጠኛ ማዕከል ፣ የኦሬንጅ ፋውንዴሽን ፋብላብ ሶሊዴር፣ ስታርትአፕ አክሲለሬተር እንዲሁም ኦሬንጅ ቬንቸር አፍሪካ የመዋዕለ ንዋይ ድጋፍ የሚመቻችበት ፕሮግራሞችን አቅፎ የያዘ ነው።

የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝና ታሰሩብኝ ክስ የመንግስት ምላሽ ፦
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከአስራ አንድ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውንአስታውቋል።
ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ ተሰርዞ ምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ በተያዘለት ጊዜ ሲደረግ ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ ከማድረግ ተቆጥቦ ሰልፉ ከተካሄደ በኃላ ነው ወደ ቅስቀሳ የገቡት ከዚህ በኃላ ነው እስርና ድብደባው በአባላቶቻችን ላይ የደረሰው" ብለዋል።
የፓርቲው አባላት ሲታሰሩ የኢዜማን አርማ መያዛቸውን፣ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት ያለበት ቲሸርትም ለብሰው እንደነበር በኮንሶ ዞን የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።
ምክትል ሊቀመንበሩ ፥ የአካባቢው ፀጥታ አካላት የኢዜማን ቲሸርት የለበሱ አካላትን እየቀጠቀጡ እና እየደበደቡ ነበር ብለዋል ፤ አንደኛው የኢዜማን ቲሸርት የለበሰ ሃኪምም በሳንጃ ሁሉ ተወግቷል ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት በኢዜማ አባላት ላይ በማህበራዊ ኑሮ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጫና እያዳደረ መሆኑንም አብራርተዋል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ አሳውቀዋል።
"እነሱ በየአዳራሹ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ፣ ቀበሌዎች ላይም በመንግስት ሃብት (ሞተር እና መኪና) እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ ያደርጋሉ እኛ ግን በራሳችን ፅ/ቤታችን እንኳን እንዳንሰበሰብ ሊያደርጉን ነው" ብለዋል።
የታሰሩት የኢዜማ አባላት ማክሰኞ እለት ተፈተዋል።
የኮንሶ ዞን የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ ፥ በኢዜማ ምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ብለዋል። ነገር ግን መንግስት ፈርሷል እያሉ ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በአደባባይ ሲያውጁ/ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ሲጥሩ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ ገልፀዋል።
#EthiopiaElection2013
https://telegra.ph/EZEMA-02-25

Telegraph
#EZEMA
የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝ እና ታሰሩብኝ ክስ እና የመንግስት ምላሽ ፦ ኢዜማ ከ11 በላይ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አስታውቋል። ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ…
የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ እንቅስቃሴ ፦
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል።
ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል።
በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን ላይ የእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው። በየክልሉ ያሉት የፓርቲው አደረጃጀቶችን ሰፊ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ የሚገኙት በዚሁ በእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ ነው።
ጎን ለጎን እንዲሁም ምዝገባው እንዳለቀ ነፃነት እና እኩብነት ፓርቲ በሰፊው የምርጫ ቅስቀሳ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የአዲስ አባባ ቅስቀሳ እንዴት ነበር ?
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በጀመረበት አዲስ አበባ ይሄ ነው ተብሎ የሚገልፅ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመው አሳውቆናል።
ቅስቀሳው በሁሉም ክ/ከተማ በሰላማዊ እና በተሳካ ሁኔታ ነው የተካሄደው።
ነገር ግን ፓርቲው ከወዲሁ ወደክልል በሚወርድበት ጊዜ ችግር ይገጥመኛል የሚል ስጋት አለው ይህም የመነጫው አሁን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ችግር እየገጠመን ነው በማለት ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ነው።
በሌላ በኩል ፦
በርከት ያሉ የቲክቫህ አባላት ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምንድነው በስፋት በሚዲያዎች ላይ የማናገኘው ? የሚል ጥያቄ አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል ፤ ለዚህም የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድርን ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናል።
ዶክተር አብዱልቃድር፥ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባሉት የሚዲያ አማራጮች እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ፓርቲው በሚዲያ ወጥቶ ወደህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት በህዝብ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።
#EthiopiaElection2013 #TikvahEthiopia
https://telegra.ph/Freedom--Equality-Party-02-25

Freedom & Equality Party
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ፦ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ በይፋ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል። ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል። በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል። ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን…
ኢትዮጵያ እንቁላል ከዩክሬን ልታስገባ ነው ?
ዩኬሬን ኢንፎርም የተባለ ድረገፅ ኢትዮጵያ ከዩክሬን እንቁላል ልታስገባ ነው ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ከዩክሬን አቅራቢዎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲል አስነብቧል።
በግብርና ሚኒስቴር ወደ ውጭ ሀገራት የሚላኩ እና ከውጭ የሚገቡ እንስሳት ደህንነት በተመለከተ የተቋቋመው ዳይሬክተር ኃላፊ ዶ/ር ወንድማገኝ ደጀኔ ፥ ኢትዮጵያ ከዩክሬን እንቁላል ልታስገባ ተስማምታለች ስለመባሉ ግብርና ሚኒስቴር የሚያውቀው ነገር የለም ብለዋል።
ዶክተር ወንድማገኝ ደጀኔ ፥ ከዚህ ቀደም ከዩክሬን የዶሮ ስጋ ለማስገባት እንቅስቃሴ ነበር ይህም ኢትዮጵያ ያሉ ሆቴሎች ፍላጎት ስላሳደሩ ነበር ብለዋል። በወቅቱ የዩክሬን መንግስት የማስገቢያ መስፈርቶችን ጠይቆ እንደነበርም አስታውሰዋል። ነገር ግን ከዛ በኃላ ምንም የተከናወነ ነገር በኢትዮጵያ መንግስት በኩልንም የተፈቀደ ነገር የለም ብለዋል።
ዶ/ር ወንድማገኝ አክለው፥ "...ምናልባት የሚያጠራጥረኝ ምግብ በሚል ስም በጤና ሚኒስቴር በኩል እየሄዱበት ያለው ነገር ካለ እርግጠኛ አይደለሁም እንደ ግብርና ሚኒስቴር ግን ከዩክሬን ጋር የተገናኘ ምንም መረጃ የለንም" ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሚሊዮን በበኩላቸው በጉዳዩ ዙሪያ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ/እንዳላረጋገጡ ተናግረዋል።
More : https://telegra.ph/ShegerFM-02-25
Via Sheger FM 102.1

በትግራይ የእርዳታ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ !
የፌዴራል መንግስት ለሽሬ ከተማ እና ለአካባቢዋ ነዋሪዎች ዕርዳታ እንዲውል የላከው ከ800 ኩንታል በላይ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት ማስታወቁን ኢዜአ ዘገበ።
የኢዜአ ዘገባ እህሉ ወዴት ሊጓጓዝ እንደነበር ግን አይገልፅም።
ከዚህ ህገ-ወጥ የሆነ ድርጊት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 10 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡
ለትግራይ ተልኮ ወደ ሌላ ቦታ ሊጓጓዝ የነበረው እህል በቁጥጥር ስር የዋለው ለመከላከያ ሃይል በተሰጠው ጥቆማ መሰረት መሆኑን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት ሃላፊ ሻለቃ አብርሃም አረሩ ተናግረዋል።
ከወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦችንና ሶስት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ላምሮት ከማል በነፃ እድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወሰነ !
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከነበሩት መካከል አንዷ የሆነችው ላምሮት ከማል በነጻ እንድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወሰነ።
በግድያው ተጠርጥረው መዝገብ ከተከፈተባቸው አራት ግለሰቦች ውስጥ ላምሮት ከማል ግድያውን በማመቻቸት ተጠረጥራ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ ተሳትፎዋን የሚያረጋግጥ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ዐቃቤ ሕግ አለመቅረቡን በመግለጽ ነው እንድትለቀቅ የወሰነው።
ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ወንጀል ሁለተኛ ምድብ ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ማስረጃና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ነው ብይን የሰጠው።
ፍርድ ቤቱ አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ መፈፀሙን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ማረጋገጡን ገልጿል።
የዛሬው የችሎት ውሎ : telegra.ph/BBC-02-25
Via BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB

ጥናት ፦
በፋይዘር እና ባዩንቴክ የተሰራው የኮቪድ-19 ክትባት ፣ እየተከተቡ ባሉ ሰዎች ላይ ቀደም ብሎ በሙከራው ወቅት ያስመዘገበውን ዓይነት ውጤታማነት እያሳየ መሆኑን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።
የእስራኤል "ክሌሊት የምርምር ተቋም" ተመራማሪዎች ባካሄዱት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ያሳተፈ ጥናት እንደገለጠው ሁለት ጊዜ የሚሰጠው የፋይዘር ክትባት በማናቸውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ የህመም ስሜት በሚያመጣ ደረጃ እንዳይጠቁ በማድረግ ረገድ 94 ከመቶ ውጤታማነት አሳይቷል።
አንዷን ብቻ ክትባት ለወሰዱ ሰዎች፤ 57 ከመቶ ቫይረሱን የመከላከል ዓቅም ሰጥቷቸዋል።
በአቻ ተመራማሪዎች ተገምግሞ 'በኒው ኢንግላንድ የህክምና መጽሄት' ላይ የወጣው ይህ የእስራኤሉ ጥናት በሃገር አቀፍ የኮቪድ19 ክትባት መርሃ ግብር ላይ ያተኮረ ግምገማ ሲካሄድ የመጀመሪያ መሆኑን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

የፊታችን ቅዳሜ ፐብሊክ ሴሚናር በአ/አ ይካሄዳል።
"ኢትዮጵያ በእምነትና በእውነት መንገዶች" በሚል ርዕስ የፊታችን ቅዳሜ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፐብሊክ ሴሚናር ማዘጋጀታቸውን አድሜሽ መፅሃፍትና ኢቨንት ኦርጋናይዘር እና ማህበረ-ሰብዓዊ አሳውቀውናል።
ሴሚናሩ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የሚደረግ ሲሆን መግቢያ 200 ብር መሆኑ ነው የተገለፀው።
በዚህ ፐብሊክ ሴሚናር ላይ የተለያዩ ቁልፍ የውይይት ሃሳቦች ይነሳሉ የተባለ ሲሆን አበባው አያሌው (የታሪክ ምሁርና መምህር) ፣ ጤንነት ሰጠኝ (ደራሲና የማዕከለ-ሰብ ጥበቦች ተመራማሪ) በአቅራቢነት ይሳተፉበታል ተብሏል።
የሴሚናሩ አላማ ነፃ የዕይታ አማራጮች እንዲሰፉ መደላድል በመፍጠር፣ ሀገር-በቀል የሆኑ ሐሳቦችን በማስተዋወቅ የራሱ አቋም ያለው ህብረተሰብ እንዲፈጠር የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ ነው ብለዋል አዘጋጆቹ።