'መስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት'
ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለው የመስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት 90 በመቶ መጠናቀቁ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማሳወቃቸውን ኢዜአ አስነብቧል።
ምክትል ከንቲባዋ ይህን ያሳወቁት በግንባታ ስራ ላይ ለተሳተፉ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት በተዘጋጀ የምስጋና መርሃ ግብር ላይ ነው።
የመስቀል አደባባይ የፓርኪንግ ፕሮጀክት 1,400 ተሽከርካሪዎችን ማቆሚያ ፣ 24 የመገልገያ ሱቆች ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እና ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Ethiopia😷
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 6,562 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 788 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ13 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 723 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 147,092 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,194 ሰዎች ሞተዋል፤ 128,742 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 291 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
#Purpose #Tikvah

የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦
- የመቐለ ዓይደር ክፍለ ከተማ ቀጠና 7 ነዋሪዎች በችግር ላይ ላሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸው
- መቐለ በቀጠና 6 ፖሊስ ኮሚኒቲ በሁለት ክፍል ውስጥ የተጠለሉ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ (ነፍሰጡሮች ችግር ላይ መሆናቸው፣ ለበሽታ እየተጋለጡ መሆኑ)
- በትግራይ ከተሞች ከማክሰኞ ጀምሮ የነበረው አድማ/ተቃውሞ አብቅቶ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መጀመሩ
- EU ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች ትግራይ ክልል ውስጥ “ጥሩ ሥራ” እየሰሩ ነው ማለቱ
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የላከው የትምህርት ቁሳቁስ የመቐለ ከተማ አስተዳደር መረከቡ
- የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ወላጆችን፣ አጠቃላይ ማህበረሱን ይቅርታ መጠየቁ
- ከነገ የካቲት 8 ጀምሮ በትግራይ ክልል የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ መባሉ
[ለቲክቫህ አባላት የቀረበ]
(Tikvah - Family የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ/ም)
https://telegra.ph/TikvahFamily-02-14-2

Telegraph
#TikvahFamily
የመቐለ ዓይደር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ድጋፍ : በትግራይ ጦርነት ከምዕራባዊ ዞን ተፈናቅለው መቐለ ለሚገኙ ዜጎች የመቐለ ዓይደር ክፍለ ከተማ ቀጠና 7 ነዋሪዎች 40 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ አደረጉ። ተፈናቃዮቹ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ህፃናት፣ ሽማግሌዎች፣ በከባድ መሳሪያ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆኑ በክፍለ ከተማው ፖሊስ ኮሚኒቲ ተጠልለው ነው የሚገኙት። በዓይደር ክ/ከተማ ነዋሪዎች የተደረገው ድጋፍ ነዋሪው…
#Russia #Ethiopia #Switzerland
ትላንት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከሩሲያ አምባሳደር (Mr. Vladimir Zheltov) እና ከስዊዘርላንድ አምባሳደር (Mr. Christian Winter) ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የነበረው በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግንብ (GERD) የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ ነበር ተብሏል።
በውይይቱ አምባሳደር ይበልጣል ስለተጠቀሱት ጉዳዮች ወቅታዊ ሁኔታና ስለ ኢትዮጵያ አቋም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የሩሲያ አምባሳደር፥ ሩሲያ ችግሮች ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፈታት አለባቸው ፣ የአገሮች ሉዓላዊነት መከበር አለበት እና ጉዳዮችን Politicized መደረግ የለባቸውም የሚል የፀና አቋም ያላት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የስዊዘርላንድ አምባሳደር በአምባሳደር ይበልጣል የተሰጣቸው ማብራሪያ ሰፊ ግንዛቤ እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡
Via Ethiopia Embassy Sudan

#EthiopiaElection
- በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
- በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር
- በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና
- በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከዛሬ የካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩ ምዝገባ ይከናወናል።
በሌላ በኩል ፦
- በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
- በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት እና
- በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከየካቲት 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለዕጩዎች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች እየተጓጓዙ ሲሆን እስከ የካቲት 14 ድረስ የዕጩዎች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ተሰጥቶ ይጠናቀቃል።
ከየካቲት 15 ጀምሮ እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ ነው።

#EthiopiaElection2013
እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው።
በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
የአቶ በላይነህ ክንዴ የዘይት ፋብሪካ በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ተመረቀ ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በአማራ ክልል በቡሬ ከተማ የተገነባውን የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ዛሬ መርቀው ከፍተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ…
#PhiBela
ንብረትነቱ የባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የሆነው ፊቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በተመረቀ በቀናት ውስጥ ምርቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለተጠቃሚዎች በማጓጓዝ ማከፋፈል መጀመሩ ተገልጿል።
በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ እንደሆነ የሚነገርለት የፊቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ምርቱን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተጠቃሚዎች እያሰራጨ ይገኛል። (Tewachew Derso)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ንብረትነቱ የባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የሆነው ፊቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በተመረቀ በቀናት ውስጥ ምርቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለተጠቃሚዎች በማጓጓዝ ማከፋፈል መጀመሩ ተገልጿል።
በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ እንደሆነ የሚነገርለት የፊቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ምርቱን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተጠቃሚዎች እያሰራጨ ይገኛል። (Tewachew Derso)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ዶክትር አቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ዛሬ ይፋ አደረጉ።
የፓርቲው ፕሬዜዳንት የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና ይፋዊ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ ያደረጉት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ በሚገኝ መርሃግብር ላይ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የመወዳደሪያ ምልክት እየበራ ያለ አምፖል ነው። (EPA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በምርጫ 2013 እንደሚሳተፍ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲያ ለአልዓይን ዜና ማሰራጫ ድረገፅ ከቀናት በፊት አረጋግጠዋል።
መንግስት ካላስወጣን በስተቀር ከምርጫ አንወጣም ብለዋል።
ነገር የኦፌኮ በምርጫው መወዳደር ሁኔታ በመንግስት እንደሚወሰን ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።
ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ ይሆን ዘንድም ፓርቲው የሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉት ፦
- በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቶቹ ፣ ደጋፊዎቹ እና አመራሮቹ ከእስር እንዲፈቱለት።
- የተዘጉ ቢሮዎቹ እንዲከፈቱ።
- የምርጫ ቦርድ ለአስመራጭነት የመረጣቸው አካላት ብቃት፣ አቅም እና ገለልተኝነት ላይ ቅሬታ አለው።
* ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምርጫ ቦርድ በአስመራጭነት የመረጣቸውን አካላት ዝርዝር ለፓርቲው ተልኮለት መመልከታቸውን አሳውቀዋል። በዝርዝሩ ኤሌክትሪሽያን፣ተላላኪ፣ እንጨት አውራጅ፣ ስራ አጥ በሚል የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መካተታቸውን ገልጸው “ኢትዮጵያውያኑን መናቄ ሳይሆን ምርጫ ለማስፈጸም መንግስትን የሚመርጥ አካል እንዴት ታሰማራለህ?” ሲሉ የምርጫውን ተዓማኒነት ተጠየቅ ውስጥ የሚከት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ቦርዱ ዳግም እንዲዋቀር እና ከአሁን ቀደም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈው ጉልህ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ሲያደርጉ በነበሩ ሰው እንዲመራ መደረጉንም ለምርጫው ነጻና ፍትሓዊነት ዋስትና አድርጎ መውሰዱ እንደሚቸግራቸው ፕሮፌሰሩ አስረድተዋል።
የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ በፓርቲዎች ለሚነሳ ቅሬታ የሰጠው ዝርዝር መገለጫ በዚህ ይገኛል : https://telegra.ph/NEBE-02-15 ~ [AlAIN]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

Photo
#Update
በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት መመረቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ መገኘታቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት መመረቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ መገኘታቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaElection2013 እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው። በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ /የምርጫ ዘመቻ የሚጀምርበት ቀን ነው።
ፖርቲዎች እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ደውለን ጠይቀናል።
• ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ) ፦
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ የደወለ ሲሆን አመራሮቹ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመሩ ገልፀዋል።
ነገር ግን ፓርቲው ምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለመጀመር ሰፋ ያለ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።
በዚህ ሳምንት የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምር ተገልጾልናል።
• የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ፦
የፓርቲውን አመራሮች በስልክ አግኘተን ያነጋገርናቸው ሲሆን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ እንዳልጀመረ ገልፀውልናል።
ነገር ግን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ቅድመ ሁኔታዎችን የማመቻቸት እንዲሁም ሌሎች ሰፊ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥም ወደቅስቀሳ ይገባል።
• የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲት ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፦
በቅርቡ ከመድረክ በይፋ ለተለያየው ኢሶዴፓ የምርጫ ቅስቀሳውን በተመለከተ ጥያቄ አቅርበን ነበር ዛሬ ምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመር ገልጾልናል።
ፓርቲው ወደፊት ቀስ ብሎ የምርጫ ቅስቀሳውን እንደሚጀምር አሳውቆናል።

የቀጠለ ...
• አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፦
የኢትፓ ፓርቲ ዛሬ በተለያዩ ቦታዎች ቢሮዎቹን እየከፈተና እግረ መንገዱንም የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።
ፓርቲው በአ/አ ፣ አማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ክልል እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል።
• ከክልላዊ ፓርቲዎች መካከል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ፦
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እንዳልጀመረ አሳውቆናል። አሁን ላይ በእጩዎች ምዝገባ ስራ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፆልናል። ዛሬ የፓርቲው አመራሮች ስብሰባ ያላቸው ሲሆን የእጩዎች ጉዳይ የደረሰበት ደረጃ ከተገመገመ በኃላ ቅስቀሳው መቼ ይጀመር በሚለው ላይ ውሳኔ ይተላለፋ ተብሎ ይጠበቃል።
• የባልደራስ እውነተኛ ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ባልደራስ) ፦
ፓርቲው ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ ለመጀመር እቅድ የነበረው ቢሆንም በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች መዘግየቱን አሳውቋል።
ፓርቲው በአዲስ አበባ ከተማ መኪናዎችን በመከራየት በየክ/ከተማ ቅስቀሳ ለመጀመር ቢያስብም በቴክኒካል ጉዳዮችን ለእሁድ አራዝሞታል። ፓርቲው ሰፋ ያለ የምርጭ ቅስቀሳ እንደሚያደርግ አሳውቋል። (ከሸገር ኤፍ ኤም ተገኘ)

• የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፦
ኢዜማ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ በይፋ መጀመሩን አሳውቋል።
ፓርቲው በከተማዋ በሁለት አቅጣጫዎች በትልልቅ ባሶች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በባሱ ውስጥ የፓርቲው ምክትል መሪ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ፣ ዋና ፀሀፊው በመገኘት ከህብረተሰቡ ጥያቄ በመቀበል ምላሽ በመስጠት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጿል። ይህ ስራ በዚህ ሳምንትም ይቀጥላል ብሏል።
ኢዜማ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን የምርጫ ቅስቀሳ ምን ገጠመው ?
ከሽሮ ሜዳ በተነሳው የቅስቀሳ መኪና ጋር ተያይዞ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይቻል ክልከላ አድረገዋል።
ፓርቲው ለምን ቅስቀሳ ማድረግ እንደተከለከተ የፖሊስ አባላቱን የጠየቀ ሲሆን የፖሊስ አብላቱ የምርጫ ቅስቀሳ እንደተጀመረ እንደማያውቁ ገልፀዋል።
የፖለስ አባላቱ ለኃላፊዎቻቸው ደውለው ኃላፊዎቹ በሰጡት ምላሽ ዛሬ የእጩ ምዝገባ ቀን እንጂ የቅስቀሳ ማስጀመሪያ ቀን ባለመሆኑ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም ብለው ከልክለዋል። ፓርቲው ከዛ አካባቢ ውጭ ባሉ ሌሎች ቦታዎች ግን ቅስቀሳ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።
ቅዳሜ በይፋ የምርጫ ክንውን የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እንደሚኖረውም አሳውቋል።
ከዚህ በኃላ በክልል ያሉት አባላቱ ቤት ለቤት እየሄዱ አጫጭር ፅሁፎችን እየሰጡ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ብሏል። (ከሸገር ኤፍ ኤፍ)
• የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፦
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የምርጫ ቅስቀሳውን ዛሬ አልጀመረም። ፕ/ር መረራ ጉዲና እንዳሉት ፓርቲው መንግስትን ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠቱ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ እየጠበቀ መሆኑን አሳውቋል። (ከሸገር ኤፍ ኤም የተገኘ)

ኢዜማ አባሉ በጥይት ተመተው መገደላቸውን አሳወቀ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ትላንት እሑድ ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳወቀ።
ኢዜማ አባሉ በማን እንደተገደለ/በግድያው ዙሪያ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
ፓርቲው የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያወገዘው ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች አሰባስቦ እንደጨረሰ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

"በ6 ወር 449 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞተዋል" - የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት መምሪያ
በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት መምሪያ የትራፊክና ስታስቲክስ ባለሙያ ም/ኢንስፔክተር ሰጠኝ አለሙ የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ገለፁ።
ባለፉት 6 ወራት አንድ ሺህ እንድ መቶ ሃያ አንድ የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን አሳውቀዋል፡፡
በዚህም ፦
- 449 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል
- 461 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት
- 487 ሰዎች ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል
- ከ28 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡
ለአደጋዎች መከሰትም ከ29 በላይ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች ተለይተዋል፡፡ ይሁን እንጅ በቀዳሚነት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ብቻ 234 አደጋ ደርሷል፡፡
ለእግረኞች ቅድሚያ ባለመስጠትም 206 አደጋዎች ደርሰዋል፡፡
ይህ ደግሞ ከምንም በላይ የአሽከርካሪዎችን የማሽከርከር ብቃት እና ሥነ ባህሪ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ሰጠኝ አለሙ ገልፀዋል፡፡
አደጋውን ለመቀነስ ተደጋጋሚ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ቢከናወንም አጥጋቢ ውጤት አለመገኘቱን ነው ያስረዱት፡፡
አደጋው እየተባባሰ በመምጣቱም የጋራ መፍትሔ እንደሚሻ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

#Mekedonia
ትላንት የደቡብ ክልል የዞን እና የከተማ አመራሮች የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎብኝተው ነበር።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት ለማዕከሉ መስራች እንዲሁም ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ የመሬት ካርታ አስረክበዋል።
የመሬት ካርታ ያስረከቡ ከተሞች/ዞን ፦
- የዲላ ከተማ 30 ሺህ 400 ካሬ ሜትር
- የጉራጌ ዞን 20 ሺህ ካሬ፣
- ካራት ከተማ 10 ሺህ ካሬ እና የሶዶ ከተማ 8 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ካርታ ለአቶ ቢኒያም አስረክበዋል::
የተርጫ ከተማ አስተዳደር ደግሞ በቅርቡ የመሬት አቅርቦት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል::
ሌሎችም ክልሎች ይህንን "ተምሳሌታዊ ተግባር" ከደቡብ ክልል በመማር ለማዕከሉ የቻሉትን ያህል ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ቢኒያም ጥሪ ማቅረባቸውን የደቡብ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

"4 የታጠቁ ሰዎች መኪናችንን ዘረፉን" - የቲክቫህ አባላት
መነሻውን ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ያደረገ የታርጋ ቁጥር 22984 "ሀይሮፍ መኪና" በ4 መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች እንደተዘረፈባቸው የመኪናው ባለቤቶች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።
አራቱ ሰዎች መኪናውን ኮንትራት ይዘው ይጓዙ የነበረ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ሹፌሩ እና ረዳቱን በመደብደብ መኪናውን ሰርቀው ጠፍተዋል።
መኪናው የተዘረፈባቸው አባላቶቻችን ጉዳዩን ለፖሊስ ያሳወቁ ሲሆን ከላይ በተገለፀው የታርጋ ቁጥር መኪና ያየ ካለ 0949908233 ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል።