#EthiopiaElection2013
እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው።
በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ዶክትር አቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ዛሬ ይፋ አደረጉ።
የፓርቲው ፕሬዜዳንት የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና ይፋዊ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ ያደረጉት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ በሚገኝ መርሃግብር ላይ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የመወዳደሪያ ምልክት እየበራ ያለ አምፖል ነው። (EPA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በምርጫ 2013 እንደሚሳተፍ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲያ ለአልዓይን ዜና ማሰራጫ ድረገፅ ከቀናት በፊት አረጋግጠዋል።
መንግስት ካላስወጣን በስተቀር ከምርጫ አንወጣም ብለዋል።
ነገር የኦፌኮ በምርጫው መወዳደር ሁኔታ በመንግስት እንደሚወሰን ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።
ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ ይሆን ዘንድም ፓርቲው የሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉት ፦
- በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቶቹ ፣ ደጋፊዎቹ እና አመራሮቹ ከእስር እንዲፈቱለት።
- የተዘጉ ቢሮዎቹ እንዲከፈቱ።
- የምርጫ ቦርድ ለአስመራጭነት የመረጣቸው አካላት ብቃት፣ አቅም እና ገለልተኝነት ላይ ቅሬታ አለው።
* ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምርጫ ቦርድ በአስመራጭነት የመረጣቸውን አካላት ዝርዝር ለፓርቲው ተልኮለት መመልከታቸውን አሳውቀዋል። በዝርዝሩ ኤሌክትሪሽያን፣ተላላኪ፣ እንጨት አውራጅ፣ ስራ አጥ በሚል የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መካተታቸውን ገልጸው “ኢትዮጵያውያኑን መናቄ ሳይሆን ምርጫ ለማስፈጸም መንግስትን የሚመርጥ አካል እንዴት ታሰማራለህ?” ሲሉ የምርጫውን ተዓማኒነት ተጠየቅ ውስጥ የሚከት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ቦርዱ ዳግም እንዲዋቀር እና ከአሁን ቀደም በተቃዋሚ ጎራ ተሰልፈው ጉልህ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ሲያደርጉ በነበሩ ሰው እንዲመራ መደረጉንም ለምርጫው ነጻና ፍትሓዊነት ዋስትና አድርጎ መውሰዱ እንደሚቸግራቸው ፕሮፌሰሩ አስረድተዋል።
የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑን በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ በፓርቲዎች ለሚነሳ ቅሬታ የሰጠው ዝርዝር መገለጫ በዚህ ይገኛል : https://telegra.ph/NEBE-02-15 ~ [AlAIN]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaElection2013 እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው። በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013
ዛሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ /የምርጫ ዘመቻ የሚጀምርበት ቀን ነው።
ፖርቲዎች እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ደውለን ጠይቀናል።
• ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ) ፦
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ የደወለ ሲሆን አመራሮቹ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመሩ ገልፀዋል።
ነገር ግን ፓርቲው ምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለመጀመር ሰፋ ያለ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።
በዚህ ሳምንት የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምር ተገልጾልናል።
• የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ፦
የፓርቲውን አመራሮች በስልክ አግኘተን ያነጋገርናቸው ሲሆን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ እንዳልጀመረ ገልፀውልናል።
ነገር ግን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ቅድመ ሁኔታዎችን የማመቻቸት እንዲሁም ሌሎች ሰፊ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥም ወደቅስቀሳ ይገባል።
• የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲት ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፦
በቅርቡ ከመድረክ በይፋ ለተለያየው ኢሶዴፓ የምርጫ ቅስቀሳውን በተመለከተ ጥያቄ አቅርበን ነበር ዛሬ ምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመር ገልጾልናል።
ፓርቲው ወደፊት ቀስ ብሎ የምርጫ ቅስቀሳውን እንደሚጀምር አሳውቆናል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።

በምርጫ 2013 ክልሎች የሚኖራቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) የውክልና መቀመጫ፦
- የሲዳማ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖረው መቀመጫ 19
- የደቡብ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና 104 ደቡብ ክልል ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና ወይም መቀመጫ 123 ነበር፤ ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ከቻለ በኃላ ፣ ደቡብ የሚኖረው መቀመጫ ብዛት 104 ሆኗል።
- ኦሮሚያ ክልል በነበረበት 178፣
- አማራ ክልል በነበረበት 138፣
- ሶማሌ ክልል በነበረበት 23፣
- አዲስ አበባ ከተማ በነበረበት 23፣
- ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበረበት 9፣
- አፋር ክልል በነበረበት 8፣
- ጋምቤላ ክልል በነበረበት 3፣
- ሐረሪ ክልል በነበረበት 2 እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ በነበረበት 2 ሆነው ይቀጥላሉ።
6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በትግራይ ክልል እንደማይከናወን ምርጫ ቦርድ ቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሰሞኑ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የክልሎች የፓርላማ ውክልና ድርሻ ውስጥም የትግራይ ክልል አልተገለጸም።
ይሁን እንጂ ላለፉት አሥርት ዓመታት የትግራይ ክልል የፓርላማ ውክልና 38 እንደሆነ ይታወቃል።
ይህንን ከግምት በማስገባት ሥሌት ሲደረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጠቃላይ መቀመጫ ብዛት ከነበረበት 547 አልተለወጠም።
(ከሪፖርተር ጋዜጣ)

#EthiopiaElection2013 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ…
#EthiopiaElection2013🗳
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ አካሂዷል።
አብን ከአ/አ ከተማ በተጨማሪ በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ፣ ደብረብርሃን ከተሞች የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻውን ዛሬ በይፋ እያስጀመረ ይገኛል።
አብን በአዲስ አበባው የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ ከዋና ጽህፈት ቤቱ በመነሳት መድረሻውን መስቀል አደባይ ያደረገ መርሃ ግብር አካሂዷል።
ይህ መርሃ ግብር አብን በአዲስ አበባ አብሯቸው ለመስራት ስምምነት ካደረገባቸው ፓርቲዎች ጋር በመሆን ያከናወነው ነው።
በመስቀል አደባባይ ንግግር ያደረጉት የአብን ሊቀመንነር ረ/ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ አብን ከእህት ድርጅቶች ጋር በመሆን የሕዝብን አመኔታና ይሁንታ ወደ ፖለቲካ ውክልና የሚቀይርበትን ትልም ነድፎ ወደስራ ገብቷል ብለዋል።
ማንኛውም ዜጋ በሰላም እና በደኅንነት ወጥቶ የሚገባባት ፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ፣ ሰብአዊ መብቶች ፣ ፍትህ እና ርትዕ የተከበረባት፣ ያለልዩነትና መድልኦ በነፃነት መንቀሳቀስ፣ መኖርና ሰርቶ መበልፀግ የሚቻልባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቆርጦ ተነስቷል ሲሉም ተናግረዋል።

በመተከል ዞን በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያዎች መከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።
የፀጥታ ችግር በነበረበት የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ላይ በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መክፈቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በመተከል ዞን በሚገኙት 7 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መከፈቱን ያስታወቁት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ናቸው፡፡
ምርጫ ቦርድ በዛሬው እለት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚሁ ውይይት ላይም በስድስት ክልልሎች ላይ የእጩ ምዝገባ መጀመሩን ዋና ሰብሳቢ አስታውቀዋል።
የእጩ ምዝገባው የተጀመረባቸው ቦታዎች አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሆኑ በተቀሩት ክልሎች ደግሞ ከዛሬው እለት ጀምሮ የእጩ ምዝገባ ሂደቱን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝና ታሰሩብኝ ክስ የመንግስት ምላሽ ፦
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከአስራ አንድ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውንአስታውቋል።
ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ ተሰርዞ ምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ በተያዘለት ጊዜ ሲደረግ ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ ከማድረግ ተቆጥቦ ሰልፉ ከተካሄደ በኃላ ነው ወደ ቅስቀሳ የገቡት ከዚህ በኃላ ነው እስርና ድብደባው በአባላቶቻችን ላይ የደረሰው" ብለዋል።
የፓርቲው አባላት ሲታሰሩ የኢዜማን አርማ መያዛቸውን፣ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት ያለበት ቲሸርትም ለብሰው እንደነበር በኮንሶ ዞን የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።
ምክትል ሊቀመንበሩ ፥ የአካባቢው ፀጥታ አካላት የኢዜማን ቲሸርት የለበሱ አካላትን እየቀጠቀጡ እና እየደበደቡ ነበር ብለዋል ፤ አንደኛው የኢዜማን ቲሸርት የለበሰ ሃኪምም በሳንጃ ሁሉ ተወግቷል ሲሉ ገልፀዋል።
መንግስት በኢዜማ አባላት ላይ በማህበራዊ ኑሮ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጫና እያዳደረ መሆኑንም አብራርተዋል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ አሳውቀዋል።
"እነሱ በየአዳራሹ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ፣ ቀበሌዎች ላይም በመንግስት ሃብት (ሞተር እና መኪና) እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ ያደርጋሉ እኛ ግን በራሳችን ፅ/ቤታችን እንኳን እንዳንሰበሰብ ሊያደርጉን ነው" ብለዋል።
የታሰሩት የኢዜማ አባላት ማክሰኞ እለት ተፈተዋል።
የኮንሶ ዞን የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ ፥ በኢዜማ ምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ብለዋል። ነገር ግን መንግስት ፈርሷል እያሉ ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በአደባባይ ሲያውጁ/ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ሲጥሩ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ ገልፀዋል።
#EthiopiaElection2013
https://telegra.ph/EZEMA-02-25

Telegraph
#EZEMA
የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝ እና ታሰሩብኝ ክስ እና የመንግስት ምላሽ ፦ ኢዜማ ከ11 በላይ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አስታውቋል። ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ…
የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ እንቅስቃሴ ፦
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል።
ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል።
በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን ላይ የእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው። በየክልሉ ያሉት የፓርቲው አደረጃጀቶችን ሰፊ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ የሚገኙት በዚሁ በእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ ነው።
ጎን ለጎን እንዲሁም ምዝገባው እንዳለቀ ነፃነት እና እኩብነት ፓርቲ በሰፊው የምርጫ ቅስቀሳ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የአዲስ አባባ ቅስቀሳ እንዴት ነበር ?
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በጀመረበት አዲስ አበባ ይሄ ነው ተብሎ የሚገልፅ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመው አሳውቆናል።
ቅስቀሳው በሁሉም ክ/ከተማ በሰላማዊ እና በተሳካ ሁኔታ ነው የተካሄደው።
ነገር ግን ፓርቲው ከወዲሁ ወደክልል በሚወርድበት ጊዜ ችግር ይገጥመኛል የሚል ስጋት አለው ይህም የመነጫው አሁን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ችግር እየገጠመን ነው በማለት ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ነው።
በሌላ በኩል ፦
በርከት ያሉ የቲክቫህ አባላት ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምንድነው በስፋት በሚዲያዎች ላይ የማናገኘው ? የሚል ጥያቄ አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል ፤ ለዚህም የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድርን ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናል።
ዶክተር አብዱልቃድር፥ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባሉት የሚዲያ አማራጮች እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ፓርቲው በሚዲያ ወጥቶ ወደህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት በህዝብ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።
#EthiopiaElection2013 #TikvahEthiopia
https://telegra.ph/Freedom--Equality-Party-02-25

Freedom & Equality Party
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ፦ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ በይፋ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል። ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል። በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል። ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን…
#EthiopiaElection2013
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሀይማኖት መምህርነታቸውና በሚሰጧቸው ማህበራዊ ሂሶች የሚታወቁት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግላቸው እንደሚወዳደሩ አሳውቁ።
ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵየ ቼክ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ "...በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እወዳደራለሁ" ብለዋል።
"ሀሳብ ከመስጠት ባለፈ በሂደቱ ተሳታፊ መሆን ይገባል ብዬ ስላመንኩ በምርጫው ለመሳተፍ ወስኛለሁ" የሚሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 12/13 ምርጫ ክልል በግል ተወዳዳሪነት ዕጩ ሆነው አስረድተዋል።
ለምን በግል ለመወዳደር ፈለጉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፥ "...ከፓርቲ ፖለቲካ ይልቅ ግላዊ ፖለቲካ የተሻለ ነው ብየ ስለማምን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ምንጭ፦ www.ethiopiacheck.org

አብን በተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማደረጉን ገለፀ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።
አብን በም/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግንደወይን ከተማ እና በማቻከል ወረዳ ደጋሰኝና ደብረቀለም ታዳጊ ከተሞች ፣ እና በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት «ታሪክ እየጠበቅን ታሪክ ለመስራት ድምጻችንን ለአብን እንስጥ!» በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳካሄደ አሳውቋል።
አብን ከየካቲት 14/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።