TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የህክምና ተማሪው የቴክኖሎጂ አሰልጣኝ !

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪ ነው። በቅርቡ አስራ ዘጠኝ (19) ወጣቶችን 'ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ' ላይ ያተኮረ ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በራሱ ጥረት በውጭ ከሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመነጋገር በአከባቢው (አሰላ) የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ (STEM) ማዕከል አቋቁሟል።

ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት መለያ ማሽን፤ የደን ውስጥ ቃጠሎ ማሳወቂያ እና መቆጣጠሪያ፤ የግቢ መብራቶችን በመጠቀም የጸጥታን ሁኔታ መቆጣጠር የሚያስችል እና በረካታ ሥራዎችን ሰርተዋል።

ከወጣት አልዓዛር አለማየሁ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገናል ያንብቡ : telegra.ph/የህክምና-ተማሪው-የቴክኖሎጂ-አሰልጣኝ-01-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው። • አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል። • በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ…
#Metekel

1ኛ. ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ዳለቺ" ጥር 4/ 2013 ዓ/ም ከ80 ሰዎች በላይ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ኮሚሽኑ ለቢቢሲ በሰጠው መረጃ ህይወታቸው የተቀጠፈው እድሜያቸው ከ2-45 ነው ብልሏል።

2ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ብሏል።

በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ጥር 4 ቀን ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ በተፈፀመው ጥቃት 82 ሰዎች መገደላቸውን አንድ አይን እማኝ አሳውቋል።

እንደ ኢሰመጉ በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ከ100 ሊበልጥ እንደሚችልና በአብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ብሏል።

ከ24 ሰዎች በላይ ቆስለው ጋሊሳ ጤና ጣቢያ ቡለን ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው።

በተጨማሪ ፦ ከጥር 2-3 በቡለን ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜላ እና አይነሽመስ በተባሉ ቦታዎች በታጣቂ ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 ሰዎች ተገድለዋል፤ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። (ሙሉ መግለጫቅ ከላይ ተያይዟል)

3ኛ. የቲክቫህ መተከል ዞን አባላት ከትላንት በስቲያ በድባጤ ወረዳው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ100 እንደሚበልጡ ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት ተናገረዋል።

ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት እና እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከጥቃቱ በኃላ የነበረውን ሁኔታ በፎቶ እንዲሁም በቪድዮ ቀርፀው ለማስረጃነትም አቅርበዋል።

⚠️ ይህ የመተከል ዞን አሁንም ከስጋት ቀጠናነት ያልተላቀቀ መሆኑን ነዋሪዎች እያሳወቁ ይገኛል ፤ የሚጨመር ኃይል ተጨምሮ አካባቢው ከስጋት እናቶች እና ህፃናትን ከሞት መታደግ እንደሚገባ እያስገነዘቡ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TransEthiopia

179 የትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ተወካይ የ179 የጭነት መኪናዎችን ቁልፎች ከጅቡቲ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀብሏል።

የጭነት መኪናዎቹ ጅቡቲ PK 12 የመኪኖች ማቆሚያ የቆሙ ነበሩ።

14 አሽከርካሪዎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ ፍቃደኛ ሲሆኑ ቀሪዎቹ አሽከርካሪዎች በጅቡቲ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ።

የትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት መኪናዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዘዙ ይታወሳል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOR
#NetBlocks

ዛሬ ምርጫ በምታካሂደው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ።

ኢተርኔት የተቋረጠው ከትላንት ጀምሮ ነው።

ብሎክስ በትዊተር ገፁ ፥ ከትናንትና ምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ በመላው አገሪቱ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብሏል።

ይህ የባለስልጣናቱ ኢንተርኔት የማቋረጥ ውሳኔ በቅርቡ የትኛውም የትኛውም አይነት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ የተላለፈውንም ይከተላል።

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኑ እንዳሉት ፌስቡክ የፓርቲያቸውን ደጋፊዎች አካውንት እንዲታገድ በማድረጉ ይህ ውሳኔ እንደተላለፈ አስታውቀዋል።

በአፍሪካ ውስጥ ለረዥም ዘመናት ስልጣን ከተቆጣጠሩት አንዱ በሆኑት ዩዌሪ ሙሴቪኒና በታዋቂው ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል።

ሙዚቀኛው እና ለእጬ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው ቦቢ ዋይን፥ የኢንተርኔት መቋረጥ ምርጫውን የማጭበርበር አካል እንደሆነ ገልጿል።

"የኡጋንዳ ህዝብ በከፍተኛ ፅናትና ውሳኔ ላይ ነው። ይህንን ጨቋኝ መንግሥት ከስልጣን ለማውረድ የሚያግደው ኃይል አይኖርም።" ብሏል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሱዳን እና የኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብ ...

በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ ና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ ባሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና የጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አምባሳደሩ ይህን ያሳሰቡት ትላንት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ድንበር ኮሚሽን ተቀማጭነታቸው በሱዳን ለሆኑ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ ቆንስላዎች እና የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ባዘጋጁት የገለጻ መድረክ ላይ ነው።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያሰራጨውን ዘርዘር ያለ መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ telegra.ph/Ethio-Sudan-01-14 ተቀምጧል።

በሌላ በኩል፦

ትላንት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊትር ገፁ 'የኢትዮጵያ የጦር ጀት የሱዳንን ድንበር ጥሶ ገብቷል፤ ይህም አደገኛ ዉጤት ሊያስከትል የሚችልና በድንበር አካባቢ ያለውን ውጥረት የሚያባብስ ነው" ብሏል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 'በኢትዮጵያ በኩል ያለውን ሁኔታ የማባባስ' ያለውን ድርጊት እንደሚያወግዝና በ2ቱ ሀገራት መካከል ባለው ግንኙነትና በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ አደገኛ የሆነ ውጤት ስለሚያስከትል ይህ  “ትንኮሳ” መደገም የለበትም ብሏል፡፡

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ጄት ድንበሬን ጣሰ ያለችው በቅርቡ በወታደራዊ ሃይል የተቆጣጠረችውን የኢትዮጵያ ግዛት ይሁን አይሁን መግለጫው ላይ አልተገለፀም።

በተጨማሪ፦

ትላንትና በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰከሰው የሱዳን የጦር ሄሊኮፕተር ምክንያቱ ባይታወቅም አልጀዚራ ግን የሄሊኮፕተሩ መከስከስ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር አይገናኝም ብሏል።

ምንጭ፦ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ አል ዓይን፣የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አልጀዚራ
@tikvahethiopia
አየር ኃይል ሰልጣኞቹን አስመረቀ።

የኢፌዴሪ አየር ሀይል በተለያዩ የሙያ አይነቶች በደረጃ ሰባት (7) ያሰለጠናቸውን ቴክኒሺያኖች ማስመረቁን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ሚዲያው አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#China

የዓለም ጤና ድርጅት የተመራማሪዎች ቡድን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ለማጥናት በቻይናዋ ከተማ ውሃን መግባቱ ተገለፀ።

ቡድኑ ሐሙስ ጠዋት ቻይና የገባው በዓለም ጤና ድርጅትና በቻይና መካከል የወራት ድርድር በኋላ ነው።

10 ተመራማሪዎችን የያዘው ቡድኑ እአአ በ2019 ለወረርሽኙ መነሻ ናቸው ከተባሉ የምርምር ተቋማት፣ ሆስፒታሎች እና የባህር ምግቦች የገበያ ቦታዎች ለሰዎች ቃለ መጠይቅ ከማድረጉ በፊት ተመራማሪዎቹ ለሁለት ሳምንት ራሳቸውን ለይተው ይቆያሉ ተብሏል።

ቻይናመጀመሪያ ላይ ቫይረሱ ሲከሰት ግልፅ ባለመሆኗ በተለይ በአሜሪካ ትችት ይቀርብባታል። ~ BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። ጦራ ከተማ 'ኑርቴ ነዳጅ ቤት' አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደገ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ሙሉበሙ በቁጥጥር ስር ውሏል። የእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም። በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የከተማው ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Tora

ትላንትና በጦራ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ በግምት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጦራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ሳጅን ሪዱዋን ደኑር ዛሬ ገልፀዋል።፡

በአደጋው 21 የንግድ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በአንድ የነዳጅ መሸጫ ቤትና የዱቄት መሸጫ ላይ ከፍተኛ ጉደት የደረሰ ሲሆን በውስጡ የነበሩ ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡

@tikvahethiopia
" ... በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው" - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ታህሳስ 18 አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ 6 ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት ፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ውስደውባቸዋል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች እንደያዛቸው ገልጿል።

ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ስፍራው በጣም ሰፊ እንዲሁም ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል ጠቁሞ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ ነው ብሏል።

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ግን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በ'ስማ በለው' ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማውን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

አብዛኛዎቹ በማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃውን ያሰራጩት አካላት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የጉዞ ማስጠንቀቂያ ክፍልን ዋቢ አድርገው ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬው ከቀኑ 10፡30 ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ለተለያዩ በዓላት ማክበሪያ ተብሎ በመጋዘን የተቀመጠ መጠነኛ ርችት በድንገት ፈንድቶ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች ፣የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በቦታው ተገኝተው ሰራተኛው ወደ መደበኛ ስራው መመለስ እንደሚችል ያሳወቁ ሲሆን የከንቲባ ጽ/ቤት እና የህንጻው እድሳት ስራም እንደቀጠለ ይገኛል ተብሏል፡፡

ህብረተሰቡ ከላይ የተጠቀሰውን እውነታ ተገንዝቦ ከተሳሳቱ መረጃዎች እራሱን እንዲያርቅ የከተማ አስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ኢትዮጵያ ከአዙሪት ወደ እረፍት : የስልጣኔና የጥበብ መስመርን ማስቀጠል" በሚል ርዕስ የፊታችን ቅዳሜ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፐብሊክ ሴሚናር ሊካሄድ ነው።

የፐብሊክ ሴሚናሩ መግቢያ 200 ብር እንደሆነ ነው አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለፁት።

በዕለቱ የሚገኙ አቅራቢዎች ባለቅኔ፣ ፀሐፌ-ተውኔት እና መምህር አያልነህ ሙላቱ እንዲሁም ደራሲና የማዕከለ-ሰብ ጥበባት ተመራማሪ ጤንነት ሰጠኝ እንደሆኑ የፐብሊክ ሴሚናሩ አዘጋጆች አሳውቀዋል።

የሰሚናሩ አላማ ነፃ የዕይታ አማራጮች እንዲሰፉ መደላድል በመፍጠር፣ ሀገር-በቀል የሆኑ ሐሳቦችን በማስተዋወቅ የራሱ አቋም ያለው ህብረተሰብ እንዲፈጠር የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 5,848 የኮሮና ቫይረስ ላብራቶሪ ምርመራ 467 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት የሁለት ሰው ሞት ሲመዘገብ ፤ 182 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን እስካሁን ከተደረገው ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የላብራቶሪ ምርመራ 129,922 ሰዎች ላይ ኮቪድ-19 ተገኝቷል ፥ ከነዚህ መካከል 2,008 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ፥ 114,749 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በግጭት ምክንያት ህይወታቸው ፣ ንብረታቸው ማህበራዊ ኣገልግሎትችን ላጡ፣ ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሱ ላለ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምፅ እንሁን !

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአስቸኳይ የእርዳታ ትብብር ፣ ግጭቶች እና ጥቃቶች መቆም የዘላቀፍትሄ ጥሪ አቅርበዋል

በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱትን አስጊ ሁኔታዎች እና ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን ከመኖሪያው የተፈናቀለ ህዝብ ከግምት በማስገባት በስርዓተ ፆታ እኩልነት እና ሴቶችን የማብቃት ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች በጉዳዩ ላይ ለመንግስት ፣ ለዓለም አቀፋዊ የእርዳታ ድርጅቶች ፣ ለግሉ ዘርፍ እንዲሁም ለሚዲያ አካላት አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ መገለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia