TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

ትላንት የተደገደሉትን የህወሓት ቡድን አመራሮች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው መውሰድ እንደሚችሉ ብ/ጄ ተስፋዬ አያሌው በቪኦኤ ቀርበው ተናገረዋል።

አመራሮቹ የተገደሉበት ቦታ ሩቅ እና በረሃ በመሆኑ መከላከያ የሁሉንም አስክሬን መልቀም እንደማይችልም አሳውቀዋል።

ሰራዊቱም በእግሩ እየተጓዘ መሆኑ ገለፀዋል።

በዚህ ተገቢ ባልሆነ ጦርነት ህይወታቸው እያለፈ የሚገኘውን አካላት ገበሬዎች እየቀበሯቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ብ/ጄ ተስፋዬ ፥ "የአመራሮችን አስክሬን ብንችል ብናመጣው ደስ ይለን ነበር" ብለዋል።

በተጨማሪ ፥ ትላንት የተገደሉት አመራሮች ፎቶ እና ቪድዮ እንደሚደርሳቸው ገልፀው ካስፈለገ ይህን መስጠት ፣ በሚዲያ ማስተላለፍ ይቻላል ነገርግን በሚዲያ ሰው ገደልን ብሎ ማሳየት ከኢትዮጵያ ባህል አንፃር የማይሄድ እና የእርስ በእርስም ስለሆነ ይህን ማድረጉ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሓት አመራሮች በእልህ እና በአልሸነፍም ባይነት እርሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ፣ በማያውቀው ጉዳይ ከነሱ ጋር የተሰለፈውን ወጣት ጠባቂዎቻቸውን እየጎዱ ነው ብለዋል።

ብ/ጄነራል ተስፋዬ ፥ "የአመራሮቹ አስክሬን እዛው ነው ያለው (ከተከዜ ወንዝ ዳርቻ) ፥ ቤተሰቦቻቸው ከፈለጉ እና እንሄዳለን ካሉ ከመቐለ ጀምሮ እስከ ቆላ ተንቤን ያለው ሰራዊት ስላለ ከነሱ መረጃ መቀበል እና አስክሬኑን መውሰድ ይችላሉ።" ሲሉ ገልፀዋል።

ትላንት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍን ፣ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ፣ አቶ ኣስመላሽ ወልደስላሴ፣ ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ መደምሰሳቸውን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa

11 አባላት ያሉት የሀዋሳ ከተማ የከተማ ልማት አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ።

በዚህም መሰረት :

1ኛ. አቶ አባተ ኪሾ:-የከተማ ልማት አማካሪ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ ቱፋ ዶይቻ :- ም/ሰብሳቢ
3ኛ. አቶ ካሳሁን ቡሪሶ :- ፀሀፊ
4ኛ. አቶ ዱካሌ ዋቃዮ :- አባል
5ኛ. አቶ ያሬድ ፈይሳ :-አባል
6ኛ. አቶ ፍትህ ወ/ሰንበት :- አባል
7ኛ. ወ/ሮ ሰናይት ዳኜ :-አባል
8ኛ. ዶ/ር ግርማ አባቢ :-አባል
9ኛ. አቶ አንድነት ጌታቸው :-አባል
10ኛ. አቶ ወሌ አበጋዝ :-አባል
11ኛ. አቶ አስቻለው አድማሱ :-አባል ሆነው ተመርጠዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ፥ ምክር ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት በመስራት መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ በጋራ በመለየትና የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ የከተማው አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ጉልህ ድርሻ ይጫወታል ብለዋል።

Via Hawassa City Communication
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Afar

አቶ ሙሳ አብደላ የአፋር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

አቶ ሙሳ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ከጥር 5 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት በተጠናቀቀው ክልሉ ም/ቤት 6ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ነው።

በተጨማሪ አቶ አብዱሠላም አህመድ የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና አቶ አህመድ መሀመድ የክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
ኬንያ ውስጥ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ተገኘ።

በኬንያ "አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ" መገኘቱን ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው የሕክምና የምርምር ተቋም ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት ማመልከቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

ለኬንያ አዲስ የሆነው ዝርያው ከሰኔ ወር እስከ ጥቅምት ድረስ የተሰራን ጥናት ተከትሎ በደቡብ ምስራቅ የአገሪቷ ክፍል መገኘቱን የምርምር ተቋሙ አስታውቋል።

አዲሱ ዝርያ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለማወቅ ተጨማሪ ምርምሮች እንደሚያስፈልጉም ተቋሙ ገልጿል።

በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በሶስት አፍሪካ አገራት መገኘቱ ተረጋግጧል።

እነዚህም ቦትስዋና ፣ ዛምቢያና ጋምቢያ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ~ BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተባለለት ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያ ተመሰረተ!

ኢቴክ አክስዮን ማህበር በአለም ዙሪያ የሚገኙ በቴክኖሎጂ እና የንግድ ሥራ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ችሎታ ባላቸው ኢትዮጵያዊ ባለሞያዎች በሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጅ ድርጅት ሆኖ መመስረቱን በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫና የምስረታ መርኅግብር ላይ አስታውቋል።

በአስራ አንድ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ለመስራት አቅዶ የተነሳው ኩባንያው በሦስት ዘርፎች ላይ ማለትም በሶፍትዌር ማበልጸግ ፣ በሳይበር ደኅንነት ምርትና ማማከር አገልግሎት እና በቴሌኮም መሰረተ ልማት ምርትና አገህግሎት ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ሥራ መጀመሩን ገልጿል። በፋይናንስ ቴክኖሎጂ (Fin Tech) ላይም ለመሰማራት ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ብሏል።

ተጨማሪ : telegra.ph/TIKVAH-ETHIOPIA-01-15

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
መቅደላ አምባ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ሊያስመርቅ ነው።

በ2010 ዓ/ም የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን ለማስመረቅ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በ2012 ዓ/ም በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የፊታችን ነገ ጥር 8 ያስመርቃል፡፡

Via Mekedela Amba University
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በግጭት ምክንያት ህይወታቸው ፣ ንብረታቸው ማህበራዊ ኣገልግሎትችን ላጡ፣ ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሱ ላለ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምፅ እንሁን ! የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአስቸኳይ የእርዳታ ትብብር ፣ ግጭቶች እና ጥቃቶች መቆም የዘላቀፍትሄ ጥሪ አቅርበዋል በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱትን አስጊ ሁኔታዎች እና ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን ከመኖሪያው የተፈናቀለ ህዝብ ከግምት በማስገባት በስርዓተ ፆታ እኩልነት…
"...በትግራይ ሴቶች እና ህፃናት እየተደፈሩ ነው" - የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች

በቅርቡ ከመንግሥት እንዲሁም ከሌሎች ምንጮች እንደተገኘው መረጃ በትግራይ ክልል መንግስት ያደረገውን የህግ ማስከበር ስራ ከተከናወነ በኃላ ሴቶች እና ህፃናት ላይ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት በሰፊው እየደረሰ ነው።

በተጨማሪ በትግራይ ክልል ዝርፊያ እና ሌሎች ግጭትን ተገን አድርገው የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መኖራቸውን ማወቅ ተችሏል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋትም ከችግር የተነሳ በመጠለያ ጣቢያዎች ተፋፍገው የተቀመጡ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።

በጊዜያዊነት የተቋቋሙ የመጠለያ ጣቢያዎችም መሰረታዊ የሚባሉ የኮቪድ-19 መከላከያ መሳሪዎች እና የንፅህና አገልግሎቶች የተሟሉላቸው አይደሉም።

ይህም የሴቶች የጤና እና የንፅህና ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ጤንነታቸውንም ሆነ ሰብዓዊ ክብራቸውን ለመጠበቅ አዳጋች ሁኔታ ፈጥሯል።

* ትላንት ምሽት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተላከልን መግለጫ ከላይ (በReply ተቀምጧል) ማንብበ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"የኛ የሁላችንም ታሪክ"

በሴቶች ብቻ በተመራ ቡድን የተሰራው "የኛ የሁላችንም ታሪክ" አራተኛ ምዕራፍ የታዳጊ እና ወጣቶች የቲቪ ድራማ ጥር 16/2013 ዓ.ም. እንደሚጀምር 'ገርል ኢፌክት' በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

16 (አስራ ስድስት) ክፍሎች ያሉት ይህ ምዕራፍ በአገር አቀፍ ደረጃ ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ 'ቃና' በተሰኘው ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚተላለፍ ተገልፆልናል።

በሴት ደራሲያን ተፅፎ በሴቶች ዳይሬክት የተደረገው ይህ ድራማ በኢትዮጵያ በሴቶች ብቻ ተመርተው ከተስሩ ጥቂት ስራዎች አንዱ ነው።

በ4ኛው ምዕራፍ ድራማው አዳዲስ ገፀ-ባህሪያትን አካቶ ሁሉም ታዳጊዎች ሊጋሯቸው የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ማለትም እንደ ጤናማ አመጋገብ፣ እርግዝና እና የስራ አለምን መቀላቀል የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስስ ይሆናል።

በተጨማሪም በዚህ ምዕራፍ ከኢትዮጵያ በስደት ለጉልበት ስራ ወደ ሌላ ሃገር ሄደው ተመላሽ የሆኑ ሴቶች የሚያልፉበት ውጣ ውረድ ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ይህ ምዕራፍ ለአለም አቀፉ ተከታታይ (አድማጭ ተመልካች) ከታህሳስ 18/2013 ጀምሮ በኦንላይን ሲስተም ጥራት እና ተደራሽነት ያላቸውን አለም አቀፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ስራዎችን በሚያስተላልፈው ሀበሻ ቪው ላይ በመታየት ላይ ይገኛል።

* ከ 'ገርል ኢፌክት' የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"በትግራይ የፀጥታ ችግር መድሃኒት ማቅረብ አልተቻለም"

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የመድሃኒት ክፍል አስተባባሪ ኣቶ ገ/እግዚአብሔር ገ/ጊዮርጊስ ለቪኦኤ የሰጡት መረጃ ፦

- በክልሉ ያሉ የጤና ተቋማት ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል፤ በአንድ ወረዳ እስከ 5 የሚደርሱ ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ አዳጋች ሆኗል።

- በተለያዩ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ለ3 ወር ደሞዝ አልተከፈላቸውም። ቢሯቸውን ትተው ተበታትነው ይገኛሉ።

- አሁን ላይ ጥቂት የጤና ተቋማት ስራ የጀመሩ አሉ፤ በሽረ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ መቐለ፣ ኣብይ ዓዲ የሚገኙ ናቸው። በደቡባዊ ዞንም አንዳንድ ተቋማት ስራ ጀምረዋል።

- በፀጥታው ችግር ምክንያት ስራ ወደ ጀመሩ ተቋማት መድሃኒት ለማቅረብ እንቅፋት ሆኗል። እንዲሁም ስራ በጀመሩት እና ባልጀመሩት ተቋማት ላይ ዳሰሳ ለማድረግ ከባድ ሆኗል።

- ጤና ሚኒስቴር ለጤና ተቋማት በነፃ መድሃኒት እንዲወስዱ ቢያመቻችም የተቋማቱ መኪናዎች በመዘረፋቸው መድሃኒት ለማምጣት ተቸግረዋል። ይህን ችግር ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ለመፍታት እየተሰራ ነው።

- ህብረተሰቡ መድሃኒት ማግኘት ስለሚገባው የፀጥታው ችግር በአቸኳይ ቢፈታ፣ የጤና ተቋማት ሰራተኞችም ደመወዝ ቢከፈላቸውና ወደስራቸው እንዲመለሱ ቢደረግ ብለዋል።

* የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ለመንግስት ሰራተኞች (የጤና ተቋማት ሰራተኞችን ጨምሮ) ደመወዝ መከፈል እንደተጀመረ ተናግረዋል። ከሌሎች የትግራይ ክፍሎች ወደ መቐለ የገቡ ግን ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ከፍተኛ ችግር ላይ እንደሆኑ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Via ሙልጌታ ኣፅብሃ
@tikvahethiopia
በመተከል ዞን የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከትናንት ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የሰዓት እላፊ ገደብ እንደተጣለ ተገለፀ።

በዚህም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድም።

ይህን ገደብ ተላልፎ የሚገኝ እግረኛም ሆነ ተሽከርካሪ ካለ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑ በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Metekel

በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀው ግብረ ሃይል አባል ብ/ጄነራል ኣለማየሁ ወልዴ ከ2 ቀን በፊት በመተከል 74 ንፁሃን መገደላቸውን አሳውቀወል።

ግድያውን "ኦነግ ሸኔ እና የህወሃት ተላላኪ ታጣቂ ቡድን አባላት" ነው የፈጸሙት ብለዋል።

የታጣቂውን የሽፍታ ቡድን እንቅስቃሴ በመከታተል የተቀናጀ የህግ ማስከበር እርምጃ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

በዚህም በርካታ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን ጠቅሰዋል።

በታጣቂ ሃይሉ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ባልተገባ መንገድ የሚገልጹ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
እነ አቶ ስብሃት ነጋ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

አቶ ስብሃት ነጋና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከቀረቡት አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል።

ተጠርጣሪዎቹ ሰሜን ዕዝ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 15 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደረገ።

ይህ ቁጥር ከባለፉት ሃያ (20) ቀናት በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር መሆኑን መረዳት ችለናል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 5,625 የላብራቶሪ ምርመራ 404 ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው ተረጋግጧል። ትላንት 679 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በ130,326 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ መካከል 2,023 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 115,428 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
እነ አቶ ስብሃት ነጋ ፍርድ ቤት ቀረቡ። አቶ ስብሃት ነጋና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።  ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከቀረቡት አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል። ተጠርጣሪዎቹ ሰሜን ዕዝ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ…
የአቶ ስብሃት ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ ፦

"ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል" ተብለው ፍርድ ቤት ቀረቡት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች 20 ናቸው።

አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ ኣባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ይገኙበታል።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪዎቹ ፈፅመዋቸዋል ያላቸውን የወንጀል ተግባራት ለፍርድ ቤት አቅርቧል ፦

- በትግራይ ክልል ህገ ወጥ ቡድን አደራጅተው ሰሜን ዕዝ እንዲጠቃ አድርገዋል።

- የክልሉ ወጣቶች ለጦርነት እንዲዘመቱ ቀስቅሰዋል።

- የነዳጅ ዴፖ እንዲዘረፍ አድርገዋል።

- በጥቅምት 24 ጥቃት በርካታ የሰራዊቱ አባላት ህይወት እንዲጠፋ አስደርገዋል።

- ባልተሰጣቸው ስልጣን ከተለያዩ ሀገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለጦርነቱ ገንዘብ ሰብስበዋል።

- በጎንደር እና ባህር ዳር ኤርፖርቶች ሮኬት እንዲወረወር እና የንፁሃን ህይወት እንዲጠፋ አድርገዋል የሚሉና በሌሎች ወንጀሎች እንደጠረጠራቸው ገልጿል።

ፖሊስ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንፃር ለተጨማሪ ምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

የፖሊስን ማመልከቻ ተከትሎ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን አልፈፀምንም ብለዋል።

አቶ ስብሃት፣ ወ/ሮ ሙሉን ጨምሮ አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከነበርንበት ጉድጓድ ውስጥ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውለናል ብለዋል።

በእነ ኣቶ ስብሃት ነጋ መዝገብ ከተከሰሱት ተጠርጣሪዎች አቶ ስብሃትን ጨምሮ አብዛኞቹ ጠበቃ አቁመው እንደሚከራከሩ ገልፀዋል ፤ 2ቱ መንግስት ጠበቃ ያቁመልን ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፦
- በቂ ህክምና ይሰጠን
- ከቤተሰቦቻችን እና ከጠበቆቻችን ጋር እንድንገናኝ ይታዘዝልን
- ልብስና ምግብ እንዲቀርብልን ይደረግልን የሚሉ አቤቱታዎችን አሰምተዋል።

@tikvahethiopia