TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

ዛሬ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ከመላው ኢትዮጵያ በመመልመል ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ምልምል ወታደሮች አስመርቋል።

ምልምል ወታደሮቹ ሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።

ሰልጣኞቹ በፍላጎታቸው ወደ መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀልና መስፈርቱን በሟሟላት በዛሬው ዕለት በየማሰልጠኛ ተቋሙ ተመርቀዋል።

ተመራቂ ምልምል ወታደሮቹ የአካል ብቃት ፣የተኩስና የስልት ስልጠናዎችን በመውሰድ ከፍተኛ አቅም መገንባታቸውን በተግባር ማሳየታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኬንያዊው የቀድሞ ረጅም ርቀት ሯጭ ፖል ቴርጋት በ20ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በክብር እንግድነት እንደሚገኝ ተገለጸ።

20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዘንድሮው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች አንደኛ ለሚወጡ 100 ሺህ ብር፣ ለሁለተኛ 30 ሺህ እና ሶስተኛ ለሚወጡ 12 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ እስከ 10ኛ የሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን በአጠቃላይ ለተወዳዳሪዎች የ306 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል። ~ ENA

@tikvahethiopiaBot
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ/ም በአማራ ክልል የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 96.85 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል።

በዚህ አመት የተሻለ ውጤት የተመዘገበት መሆኑ ተገልጿል።

የፈተናዉ ውጤት ማለፊያ ነጥቡን በተመለከተ ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች የተላለፈ ሲሆን ተማሪዎችም በየትምህርት ቤታቸው ውጤታቸውን በማየት የ9ኛ ክፍል ምዝገባ ከታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲያካሂዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ? (በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ) © #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13…
የቀድሞ የደረግ ባለስልጣናት ከጣልያን ኤምባሲ ወጡ።

በጣልያን ኤምባሲ ውስጥ ቁም እስር ላይ የነበሩት የደርግ ባለስልጣናት (የ77 ዓመቱ ሌ/ጄነራል አዲስ ተድላ እና የ85 ዓመቱ ሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ) መለቀቃቸዉን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ም/ፕሬዚዳንት ፍስሃ ደስታ ጣልያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩ ጓዶቻቸው ኤምባሲውን ለቀው ቤታቸዉ መግባታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TrainingAnnouncement

ስቴም ፓወር ከቪዛ ጋር በመተባበር የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረ የሦስት ወር ነጻ ሥልጠና ሊሰጡ ነው።

አጠቃላይ ስልጠናው ለቀጣይ ሦስት (3) ዓመታት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚሰጥ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስልጠናው ተደራሽ ይሆን ዘንድ አብሮ የሚሰራ ይሆናል።

ጥር 24 የሚጀምረው አንደኛው ዙር ስልጠና አዲስ አበባ እና አከባቢዋ ላሉ የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ስልጠናን መውሰድ ለሚፈልጉ 200 ሰልጣኞች ያለምንም ክፍያ የተመቻቸ ነው።

ዝርዝር መስፈርቶች እንዲሁም የምዝገባ አድራሻ ይመልከቱ በዚህ ተመልከቱ : telegra.ph/TRAINING-ANNOUNCEMENT-01-04

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Harari

ዛሬ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 88.3 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ 9ኛ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን የተሻለ ውጤትም ተመዝግቧል ብሏል ቢሮው።

የፈተናዉ ውጤት በቀጣይ ቀናት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰራጭ እንደሆነ ተገልጿጻ።

ተማሪዎች ከሰኞ ጥር 3 ጀምሮ ውጤታቸውን በየትምህርት ቤታቸው በመመልከት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ት/ቤት ምዝገባ እንዲያከናውኑ መልዕክት ተላልፏል። ~ የሀረሪ ክልል ት/ት ቢሮ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,934
• በበሽታው የተያዙ - 322
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 203

አጠቃላይ 126,241 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,963 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 112,813 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

245 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#LemiKura

1.8 ሚሊዮን ብር የሚገመት ለገና በዓል የሚዉል ቁሳቁስ ለአቅመ ደካማ ወገኖች በስጦታ መልክ ተበረከተ።

ድጋፉ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ነው የተደረገው።

ድጋፉ በክፍለ ከተማው እና በወረዳዉ ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞችን በማስተባበር የተደረገ መሆኑ ፅ/ቤቱ ለቲክቫህ ገልጿል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፤ የወረዳ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው የገና በዓል ስጦታው የተበረከተው።

@tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የገና በዓል በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ “የመዲናዋን ሠላምና ጸጥታ ለማስከበር ከወጣቶች ጋር እየሰራሁ ነው” ብሏል።

ኅብረተሰቡ በዓሉን በሠላማዊ ሁኔታ እንዲያከብር ለማድረግ ከሃይማኖት አባቶችና ከወጣቶች ጋር ውይይት እንደተካሄደ አሳውቋል።

ፖሊስ የወቅቱን የፀጥታ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ጥበቃ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቆ ፥ ሕዝቡ በዓሉን ለማክበር ሲንቀሳቀስ ስጋት እንዳይገባው እየሰራን ነው ብሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በዓሉ በሠላም እንዲከበር ከፖሊስ ጋር መተባበር ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ~ ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለራያ ዩኒቨርስቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ተደረገ።

የራያ ዩኒቨርስቲ ጥር 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚያካሂድ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ተገኝተው ምዝገባ እንዲያካሂዱ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን መደበኛ ትምህርት ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#Egypt #Sudan

በግብፅ እና ሱዳን ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የገቡት የአሜሪካው የግምጃ ቤት ኃላፊ ስቴቨን ምኑቺን ካርቱም መግባታቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

ስቴቨን ምኑቺን ካርቱም ሲደርሱ በሱዳን የገንዘበና ኢኮኖሚ ዕቅድ ሚኒስትር ዶ/ር ሂባ መሐመድ አሊ እና በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር አቀባበል እንደተረገላቸው ተገልጿል፡፡

ምኑቺን ትናንት ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተወያይተዋል።

በካርቱም ቆይታቸው ከሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ (ዶ/ር ) ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ምኑቺን ትናንት በግብፅ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየሰራችው ባለው የሕዳሴ ግድብ ሰሞነኛ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ገልጿል።

ምኑቺን በሱዳን ቆይታቸውም እንዲሁ በግብፅ እንዳደረጉት ሁሉ ስለ ሕዳሴ ግድብ ድርድርና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

ስቴቨን ምኑቺን የሕዳሴ ግድብ ድርድር በአሜሪካ ሲደረግ ፣ ከታዛቢነት ሚናቸው አልፈው ፣ ድርድሩን በሦስተኛ ወገንነት ሲመሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡

በአሜሪካ ግምጃ ቤት የተዘጋጀውን ሰነድም ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንፈርምም ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ~ ኣል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
የትላንት ለሊቱ የእሳት አደጋ ...

አደጋው የደረሰበት ቦት እና ሰዓት ፦

• አ/አ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 መኮንኖች ክበብ በሚባለው አካባቢ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ።

የደረሰው ጉዳት ፦

• 2 ሚልዮን 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል። አደጋው በአንድ እንጨት ቤት፣ ጋራዥ ቤት እና በቶርኖ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በጋራዡ ውስጥ ከነበሩት 5 መኪኖች መካከል ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ 3ቱ ከፍተኛ ጉዳት ደረሶባቸዋል።

በእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

እሳቱን ለጥፋት የተደረገው ስራ ፦

እሳቱን ለማጥፋት በተደረገ ርብርብ 26 ሚልዮን ብር የሚገመት ንብረት ለማዳን ተችሏል።

አደጋውን ለመቆጣጠር 9 የእሳት ማጥፊያ መኪኖች አገልገሎት ሰጥተዋል።

የአደጋው ምክንያት ፦

የእሳት አደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ ነው።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፣ ኢዜአ

PHOTO : COSTA (Tikvah Family)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አሁንም ስደተኞች ወደ ሱዳን እየገቡ ነው።

UNHCR አሁንም ስደተኞች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወደ ሱዳን እየገቡ ነው አለ።

በቅርቡ ወደ ሱዳን ከተሰደዱት ሰዎች መካከል ደግሞ የመጀመሪያዎቹን ወደ አዲስ የስደተኞች ማቆያ ማዘዋወሩን ገልጿል።

2021 በገባ ጥቂት ቀናት 800 የሚደርሱ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ምሥራቃዊ ሱዳን የገቡ መሆኑን ድርጅቱ አሳውቋል።

ከኅዳር ወር ጀምሮ ከ56 ሺህ በላይ ስደተኞች ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን መሰደዳቸውንም UNHCR አስታውሷል።

በቅርቡ የደረሱት ስደተኞች በጦርነት መካከል መንቀሳቀስ ሳይችሉ የቆዩ ፣ በተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት የደረሰባቸው እና ቤታቸው የተዘረፈ ፣ ያለፈቃዳቸው ለውትድርና የተመለመሉ አዋቂ ወንዶች እና ልጆች እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃት ያጋጠማቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ይገኙባቸዋል።

ድርጅቱ መግለጫ ላይ እንዳለው ወደ ሱዳን የደረሱት አዲሶቹ ስደተኞች ከያዟቸው ጥቂት ልብሶች ውጪ ምንም የሌላቸው ናቸው።

ለቀናት ባደረጉት ጉዞ የተጎሳቆሉና የደከሙ ናቸው ሲልም ገልጿል።

ከመካከላቸው ከ30 በመቶ የሚበልጡት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ሲሆን 5 በመቶው ደግሞ ከ60 ዓመት በላይ ናቸው።

ኡምራኩባ የስደተኞች ጣቢያ ሊሞላ መቃረቡን የገለጸው UNHCR ከአጋሮቹ ጋር በመሆን በድንበር ላይ ካሉ የመቀበያ ቦታዎች ስደተኞቹን ከገዳሪፍ ከተማ 136 ኪሎ ሜትሮች ርቆ ወደ የሚገኘው አዲስ ወደ ተከፈተው @ቱናይድባህ በፍጥነት ለማዘዋወር እየጣረ መሆኑን ገልጿል።

የስደተኞች መቀበያ ቦታዎቹ በበርካታ ሰዎች የተጨናነቁና ለድንበር ቅርብ በሆኑ ቦታዎች ላይ ስላሉ የስደተኞቹ ደኅንነትን ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ናቸው ብሏል። ~ BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ከአቻ (ባቻቸው) ጋር ጥሪ እንዲደረግላቸው ተባለ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ከአቻ (ባቾቻቸው) ጋር ጥሪ ይደረግላቸው ዘንድ ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች አሳስቧል። ~ EHEISU

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT