የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ለፕ/ር ክንደያ የእውቅናና ምሥጋና ሰርተፊኬት አበረከተ !
ዛሬ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ለቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በአገልግሎት ዘመናቸው ለሰሯቸው ተግባራት የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት አበርክቷል።
በተጨማሪ የEITM ስታፍ ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በስራ ዘመናቸው ላከረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ልዩ ስጦታም አበርክተውላቸዋል።
በሌላ በኩል የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በቀጣይ 2 ሳምንት ውስጥ ለፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት የምስጋና ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል።
Via Mekelle University
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#COVID19Ethiopia
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,101 የላብራቶሪ ምርመራ 959 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 735 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 78,819 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,222 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 33,060 ደርሷል።

TIKVAH-ETHIOPIA
“ለክብራቸው በሚመጥን መልኩ ይሸኛሉ” - ኮሚቴው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የቀብር ስነ ስርዓትን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ቪኦኤ ዘግቧል። የቀብር ስነ ስርዓታቸው ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ እንዲከናወን ዝግጅት ተጀምሯል። ውጭ ሀገር ያሉት 2ቱ ልጆቻቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በያዝነው ሳምንት መጨረሻ እንደሆነ ስለሚጠበቅ ሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያዎቹ ላይ…
የፕ/ር መስፍን የቀብር ስነ-ሥርዓት ማክሰኞ ይፈፀማል!
የታዋቂው ምሁር እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የቀብር ስነ-ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 26/ 2013 ዓ/ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ተገልጿል።
ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ጠዋት ከ2:30 እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ልደት አዳራሽ የሽኝት ዝግጅት ይደረጋል።
ከሽኝቱ ዝግጅት በኃላ ከቀኑ 6:30-7:30 ባለው ጊዜ ስርዓተ - ቀብራቸው የሚፈጸም መሆኑን የቀብራቸው አስፈፃሚ ኮሚቴ አሳውቋል። (Ahadu Radio)

በአ/አ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ አሰራር ሊዘረጋ ይችላል ተብሏል !
በአዲሰ አበባ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የተለያዩ እቅዶችን አቅዶ ወደ ተግባር ለመግባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑን የከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ጅሬኛ ሄርጳ #ለFBC (ኤፍቢሲ) ተከታዩን ብለዋል ፦
- የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት የጣምራ ማለትም 3 ሰውና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው አሸከርካሪዎች የጣምራ ትራንሰፖርት ካልሰጡ ጠዋት ከ1 እሰከ 3 ሰዓት እና ምሸት ከ11 እሰከ ምሽት 1 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ አይችሉም።
- የጣምራ ትራንስፖርት አገልግሎት የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቁን ለመቀነስ በፈቃደኝነት ለሌሎች ተሳፋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡበት መንገድ ነው።
- ህብረተሰቡ የብዙሃን ትራንሰፖርትና የጣምራ ትራንሰፖርትን በመጠቀም የመዲናዋን የትራፊክ መጨናነቅ እንዲቀንስ የበኩሉን አሰተዋጾ ሊያደርግ ይገባል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ቀደም ብሎ የአ/አ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ጅሬኛ ሄርጳን አናግሮ ያወጣውን ዘገባ ከይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አንስቶታል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለምን / በምን ምክንያት መረጃውን ከገፁ ላይ እንዳነሳው ምንም የገለፀው ነገር የለም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለምን / በምን ምክንያት መረጃውን ከገፁ ላይ እንዳነሳው ምንም የገለፀው ነገር የለም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
የአ/አ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ጅሬኛ ሄርጳ 'ከኢትዮጵያ ቼክ' ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ቼክ : ይህ የአሰራር ሀሳብ እንዴት መጣ ?
አቶ ጅሬኛ : ዋናው ሀሳቡ ትራፊክ በሚጨናነቅባቸው ሰአቶች ፍሰቱን ማቃለል ነው፣ በተለይ አሁን ትምህርት ለመጀመር እንቅስቃሴዎች ስላሉ እንደ ምክረ ሀሳብ የቀረበ ነው ፣ ግን ገና ህግ ሆኖ አልወጣም፣ ብዙ ውይይት ይደረግበታል።
ኢትዮጵያ ቼክ : በአሁን ሰአት ካለው የኮሮና ቫይረስ እና የፀጥታ ስጋት (በተለይ ከመኪና ዝርፊያ ጋር) ይህ እንዴት ይታያል?
አቶ ጅሬኛ : እኛ እንደ ትራፊክ ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ምን ብናደርግ ችግሩ ሊቃለል ይችላል ብለን ነው ያሰብነው ፣ በዚህ ላይ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት አንፃር እና ከፀጥታ ሁኔታ ጋር ገና ውይይት እና ምክክር ይደረግበታል። እኛ ህግ ማውጣት አንችልም፣ አሰራሩን ገና እንደ ምክረ ሀሳብ ብቻ ነው ያቀረብነው።
ኢትዮጵያ ቼክ : አሽከርካሪዎች ተጨማሪ ሰው ከየት አግኝተው እና በምን መልኩ ሊጭኑ እንደሚችሉ አስባችሁበታል?
አቶ ጅሬኛ : ለምሳሌ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲሄዱ በአንድ ቤተሰብ መኪና ቢሄዱ ፣ ሰራተኞች ወደ አንድ ስፍራ ሲሄዱ ትርፍ ቦታ ካለ ቦታ ቢጋሩ የሚል ሀሳብ አለ። ካልሆነ ግን ወይ ከጠዋት 1 ሰአት በፊት ወይም ምሽት ከ1 ሰአት በሗላ እንዲንቀሳቀሱ ነው። ግን ቅድም እንዳልኩት ይህ ገና ምክረ ሀሳብ ነው።
ኢትዮጵያ ቼክ : ከዚህ ውጪ የቀረቡ ሌሎች ምክረ ሀሳቦች አሉ?
አቶ ጅሬኛ : አዎ ፣ ለምሳሌ ብዙ ሰው የጫኑ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ አግኝተው እንዲጓዙ የሚል ሌላ ሀሳብ አለ ፣ ይህ ውጪም የተለመደ ነው።
[የኢንተርኒውስ ፕሮጀክት-ኢትዮጵያ ቼክ]
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#DonaldTrump በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል የገቡት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደህና መሆናቸውንና ቀጣዮቹ ቀናት ለጤንነታቸው ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ጤንነታቸውን አስመልክቶ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎችን ተከትሎ ትላንት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ነው። "እዚህ ስመጣ ደህና አልነበርኩም ፤ አሁን ላይ ግን እየተሻለኝ ነው" ብለዋል ትራምፕ። የሚቀጥሉት…
ትራምፕ ነገ ከሆስፒታል ሊወጡ ይችላሉ ተብሏል!
ፕሬዜዳንት ትራምፕ ከሆስፒታል ወጥተው በዋይት ሀውስ ሆነው ህክምናቸውን ሊከታተሉ እንደሚችሉ ሃኪሞቻቸው መግለፃቸውን #ቪኦኤ ዘግቧል።
የፕሬዚደንት ትራምፕ ዋናው ሃኪማቸው ዶክተር ሻን ኮንሊ ዛሬ በነበረ መግለጫ ላይ "እንደዕውነቱ ከሆነ በጣም በጎ ናቸው" ብለዋል።
የመተንፈሻ አካላት አጠቃላይ ጤና ሃኪም የጦር ሰራዊቱ ኮሎኔል ዶ/ር ሻን ዱድሊ የዛሬ ጠዋት የፕሬዚደንቱ የጤና ይዞታ ምልክቶች (የደም ግፊት ፥ የልብ ምት ፥ የሰውንት ሙቀት እና አተነፋፈስ) በደህና ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸዋል።
"ወዲያ ወዲህ ይራመዳሉ ፥ የትንፋሽ ማጠርም ይሰማኛል አላሉም ፥ ሌላ የመተንፈሻ አካላት ችግር አልታየባቸውም" ሲሉ አብራርተዋል።
ዶክተር ብራያን ጋሪባልዲ (ከJHU)፥ "እንደ ዛሬ ይዞታቸው ከቀጠሉ እና ደህንነት ከተሰማቸው ነገም ቢሆን ከሆስፒታሉ ወጥተው ዋይትሃውስ ሆነው ህክምናቸውን የሚቀጥሉበትን ዕቅድ ማዘጋጀት እንችላለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

ዛሬ በ8:00 ሰዓት 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ጉባኤ ይካሄዳል።
ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ የሚካሄደው ሲሆን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ይገኛሉ።
የ2ቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር ይከፈታል።
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የመክፈቻ ንግግር በ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸው ተግባራት ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኤፍ ቢ ሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተማሪዎቹን እንደሚጠራ አስታወቀ!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮቪድ-19ን በመከላከል ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቁመና የሚገመግም ቡድን ወደየተቋማቱ መላኩ ይታወቃል፡፡
የግምገማ እና ክትትል ቡድኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዝግጁነት በተለያዩ መለኪያዎች መዝኖ ግብረ መልሱን ለመካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አቅርቦ በስጋትና መልካም አጋጣሚዎች ውይይት እና ምክክር ተደርጓል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅትና የጤና ሚኒስቴርን መመሪያ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማሩን እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚገኝ በቡድኑ ግምገማ ውጤት #ተረጋግጧል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ ትምህርቱን የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
መስከረም25/2013 ዓ.ም

ከዛሬ ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝግጁነት ይገመገማል ተብሏል !
(በSHEGER FM 102.1 የቀረበ)
የከፍተኛ ትምህርት ጥራት አግባብነት ኤጀንሲ ከዛሬ ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እንደሚጎበኝ አሳውቋል።
ጉብኝቱ ተቋማቱ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጁ ስለመሆናቸው ምልከታ የሚደረግበት እንደሆነ ተገልጿል።
በጉብኝቱ ወቅት የኤጀንሲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።
የተቋማቶቹን ዝግጅት ለመገምገም የሚያስችል ስልሳ (60) መስፈርቶች ያሉት መጠይቅ በMoSHE ተዘጋጅቷል።
በተቋማቱ ጉብኝት ወቅት ዋነኛው ትኩረት የሚሰጣቸው ነጥቦች ተለይተዋል። እነዚህም፦
• የአመራርና የሰው ኃይል አደረጃጀት ዝግጅት
• በመማር ማስተማር በኩል በቂ የመሰረተ ልማት አገልግሎት ግብዓት ዝግጅት
• የህግና እቅድ ማዕቀፍ ዝግጅት ናቸው።
ግምገማው ሲጠናቀቅ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ይጠበቃል።
ኤጀንሲው 250 በሚደርሱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክትትል እና ቁጥጥር የሚያደርግ ይሆናል።
ተቋማቱ በአጠቃላይ ከ1,000 በላይ ቅርንጫፎች አሏቸው በሁሉም የተቋማቱ ቅርንጫፎች በመገኘት ግምገማው እንደሚካሄድ ተገልጿል። በ10 ቀናት ውስጥ የግማሾቹን ግምገማ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ ከሆስፒታል ወጣ ብለው መታየታቸው አግራሞትን ፈጥሯል !
ከሰዓታት በፊት ዶናልድ ትራምፕ ባልተጠበቀ ሁኔታ በጥቁር መኪናቸው የኋላ መቀመጫ ሆነው ከሆስፒታል ውጭ ታይተዋል፡፡
ፕሬዜዳንት ትራምፕ ከሆስፒታል የወጡት ጤና እንዲሆኑ የሚመኙላቸው ደጋፊዎቻቸውን ሰላም ለማለትና አድናቆታቸው ለመግለጽ ነው ተብሏል።
ይህ የዶናልድ ትራምፕ ያልተጠበቀ ድርጊታቸው አንዳንድ ተቺዎቻቸውን አስቆጥቷል፡፡
ዶናልድ ትራምፕን ከሆስፒታል በመኪና ይዘዋቸው የወጡት ሾፌራቸው እና ጠባቂዎቻቸው ሁሉም ራሳቸውን ማግለል ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡
ትራምፕ ዛሬ ሰኞ ማምሻውን ድረስ ሙሉ በሙሉ ከተኙበት ከዋልተር ሪድ ሆስፒታል ወጥተው ወደዋይት ሐውስ ቤታቸው ሊያመሩ እንደሚችሉ BBC አስነብቧል።

#ATTENTION
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከ100 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር ቅያሬ ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም እንደሚጠናቀቅ አሳውቋል።
በቀሩት 11 ቀናት ውስጥ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኝ ባንክ የብር ቅያሬውን እንዲፈጽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ሚኒስቴርን የ3 ወር የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ተከታዩን ብልዋል ፦
- መንግስት ለተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማቅረብ ስራ እየሰራ ነው።
- ትምህርት ሲጀመር ማስክ ያላደረገ ማንኛውም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት አይገባም።
- የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ማቆያ ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች የኬሚካል ርጭት ሳይደረግላቸው ትምህርት አይጀምሩም።
- በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የኬሚካል እርጭቱን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፤ በቀጣይ ሳምንታት ርጭቱ ይከናወናል።
- ይህንን አስቸጋሪ ወቅት በድል ለመወጣት መምህራን እና ወላጆች ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል።
#MoE

#UPDATE ዛሬ በ8:00 ሰዓት 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ጉባኤ ይካሄዳል። ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ የሚካሄደው ሲሆን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ይገኛሉ። የ2ቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር ይከፈታል። …
#UPDATE
5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን መከፈቱን በይፋ አብስረዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን መከፈቱን በይፋ አብስረዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TPLF
ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮች እንዳልተሳተፉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለBBC አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ ህወሓት በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱ ፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን ለBBC ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው፥የፓርላማው የስልጣን ዘመን ማክተሙን በመግለጽ ፣ ከፓርላማው በተጨማሪ ፓርላማው ያቋቋመው መንግሥም ፣ ካቢኔም የተመረጡት ለ5 ዓመት መሆኑን ጠቅሰው የሰልጣን ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።

#UPDATE 5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን መከፈቱን በይፋ አብስረዋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዘንድሮ የሚካሄደው ምርጫ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ እና እውነተኛ ዴሞክራሲ በተግባር የሚገለጽበት ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ባለፉት አስር (10) ዓመታት የተካሄዱ ምርጫዎች ከክርክር አንፃር እውነተኛ ፉክክር ያልተካሄደባቸውና ፖለቲካዊ ምህዳሩ ያልተመጣጠነ ነበር ብለዋል።
በዘንድሮው ምርጫ ፓርላማው የተለያዩ ፓርቲዎች ሃሳባቸወና ድምጻቸውን የሚያሰሙበትና እውነተኛ ውክልና የሚያገኙበት እንዲሆን እንደሚሠራ አስረድተዋል። (ENA)

የኮቪድ_19_ወረርሽኝን_ለመከላከልና_ለመቆጣጣር_በወጣ_መመሪያ_1.pdf
108 KB
#SHARE #ሼር
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአዋጅ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጣር የሚያግዝ መመሪያ አውጥተዋል፡፡
ያወጡት መመሪያ ስሙ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ፤ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ሲሆን 10 ክፍሎች እና 31 አንቀፆች አሉት።
#ይነበብ