TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ_19_ወረርሽኝን_ለመከላከልና_ለመቆጣጣር_በወጣ_መመሪያ_1.pdf
ጤና ሚኒስቴር እና EPHI ፦

"ለልደት ፣ ለምረቃ ፣ ለማህበር ፣ ሀዘንን መሰረት የሚያደርጉ ዝግጅቶች (ከቀብርና ከቀብር መልስ ያሉ ስነስርዓቶች ውጭ) እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበሪዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆነ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለ ነው።

ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ የሰርግ ስነስርዓት በተመለከተ ማንኛውም ሰው ከ50 በላይ የማይበልጡ ሰዎች በመሆን እና ሁለት ሜትር ተራርቆ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የሰርግ ስነስርዑት ማካሄድ ይችላል፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ከ100 አለፉ!

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አንድ መቶ አንድ (101) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት የ3 ሰዎች ሞት መመዝገቡን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 12,647 ደርሰዋል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ከ 512 የላብራቶሪ ምርመራ 120 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

ጥንቃቄ አይለየን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ_19_ወረርሽኝን_ለመከላከልና_ለመቆጣጣር_በወጣ_መመሪያ_1.pdf
የጤና ሚኒስቴር እና EPHI ፦

"እንደ ካፌዎች ፣ ካፌ እና ሬስቶራንቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ ይገባል።

አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

የሚስተናገዱ ሰዎች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጭ የአፍ እና አፍንጫ መሽፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮች እንዳልተሳተፉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለBBC አረጋግጠዋል። በተጨማሪም አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ ህወሓት በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱ ፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር…
#UPDATE

ህወሓት ከዛሬ ጀምሮ በፌዴራል ደረጃ ኃላፊነቶች እና ውክልና የነበራቸው የድርጅቱ አመራር እና የፌደራል ፓርላማ አባላት ሀላፊነታቸው በማስቆም ወደ ድርጅታቸው (ህወሓት) ሪፖርት እንዲያደርጉ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ያላቸውን ኃላፊነት በማስቆም ሪፖርት እንዲያደርጉ የተባሉት በፌዴራል ደረጃ ህወሓትን ወክለው ሲሰሩ የነበሩ አመራሮችና የፓርላማ አባላት ስም ዝርዝር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አውጥቷል፤ ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

በነገራችን ላይ የፌዴራል ኃላፊነታቸውን በማስቆም ወደ ድርጅቱ (ህወሓት) ሪፖርት እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ካስተላለፈላቸው አመራሮች መካከል ዶ/ር አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።

ዶ/ር አርከበ እቁባይ የህወሓት ነባር ታጋይ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አማካሪ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,062 የላብራቶሪ ምርመራ 618 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 956 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 79,437 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,230 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 34,016 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ህወሓት ከዛሬ ጀምሮ በፌዴራል ደረጃ ኃላፊነቶች እና ውክልና የነበራቸው የድርጅቱ አመራር እና የፌደራል ፓርላማ አባላት ሀላፊነታቸው በማስቆም ወደ ድርጅታቸው (ህወሓት) ሪፖርት እንዲያደርጉ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። ያላቸውን ኃላፊነት በማስቆም ሪፖርት እንዲያደርጉ የተባሉት በፌዴራል ደረጃ ህወሓትን ወክለው ሲሰሩ የነበሩ አመራሮችና የፓርላማ አባላት ስም ዝርዝር ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ፓርቲው…
ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ በዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ !

ዛሬ በነበረው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ብቸኛዋ ትግራይ ክልል ተወካይ ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ ተገኝተው ነበር።

ትግራይ ክልል በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት ሰላሳ ስምንት (38) ተወካዮች መካከል ሰላሳ ሰባቱ (37) ሳይገኙ ቀርተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ጌታ በ102 ዓመታቸው አረፉ!

በወሎ እና አካባቢው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ጌታ በ102 ዓመታቸው አርፈዋል።

ሼህ ሀጅ ሙሀመድ ከሃይማኖት አባትነታቸው ባሻገር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ሕሙማን በሚሰጡት የባህል ሕክምና ታዋቂ ነበሩ፡፡

መስጅዶችን ማስገንባታቸው ፣ የተቸገሩ መርዳታቸው ፣ በተለይ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር እንዲኖር ያለመሰልቸት መሥራታቸው በጉልህ ይጠቀስላቸዋል፡፡

ሀጅ ሙሀመድ ጌታ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የፌዴራልና የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን ከአብመድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፕ/ር መስፍን የቀብር ስነ-ሥርዓት ማክሰኞ ይፈፀማል! የታዋቂው ምሁር እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የቀብር ስነ-ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 26/ 2013 ዓ/ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ተገልጿል። ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ጠዋት ከ2:30 እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ልደት አዳራሽ የሽኝት ዝግጅት ይደረጋል። ከሽኝቱ…
#UPDATE

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስክሬን ሽኝት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ እንደሚገኝ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ በሚገኘው ልደታ አዳራሽ ሽኝት ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የልደታ አዳራሽ ሥነ-ስርዓቱ እንደተጠናቀቀ የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም አስክሬን ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚያመራና ከቀኑ 6 ሠዓት እስከ 7 ሠዓት በካቴድራሉ በሚካሄድ ሥነ-ስርዓት ቀብራቸው ይፈፀማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ ከሆስፒተል ወጥተዋል!

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ህክምናቸውን በቤተ መንግሥታቸው ፣ ዋይት ሃውስ ለመቀጠል ከሆስፒታል መውጣታቸውን BBC አስነብቧል።

ዶናልድ ትራምፕ ፥ " በጣም በጥሩ ስሜት ላይ ነኝ። ኮቪድን አትፍሩት። ህይወታችሁን እንዲቆጣጠረው አትፍቀዱለት " በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ባስተላለፉት የትዊተር መልዕክታቸው ፥ "በአሁኑ ወቅት ከሃያ አመታት በፊት ከነበረው ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፤ በቅርቡ ወደ ምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻዬ እመለሳለሁ" ብለዋል ።

እንደ BBC መረጃ በኮቪድ-19 ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ 7.4 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ፣ 210 ሺህ ዜጎቿም ህይወታቸውን አጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ በአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ !

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ 2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክፍት የስራ መደቦች ላይ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ዝርዝር መረጃው ከላይ ባሉት ፎቶዎች ተመልከቱ።

ማሳሰቢያ ፦

• ማስታወቂያው የሚቆይበት ጊዜ - ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት

• ምዝገባው የሚካሄደው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ድረስ ከጥዋቱ 2:30 - 11:30 ሰዓት

• የትምህርት ማስረጃ እና የስራ ልምድ ዋናውና የማይመለስ ኮፒ

• የግል፣ የቤተክህነት እና የሚሲዮን ትምህርት ቤቶች የስራ ልምድ ተቀባይነት አይኖረም

• ከግል የትምህርት ተቋም የሚቀርብ የትምህርት ማስረጃ ቀድሞ በወጣው የሰራተኞች የቅጥር መመሪያ መሰረት ይሆናል

• የስራ ቦታው አዲስ አበባ (10ሩም ክፍለ ከተሞች)

ለተጨማሪ መረጃ : 011-869-83-76

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በ40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ስኬትን የተጎናፀፉት አትሌቶቻችን ዛሬ መስከረም 26/2013 ዓ.ም ከማለዳው 1:45 ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በስፍራው ተገኝተው የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል የተከሰሱት ፦

- 1ኛ ጥላሁን ያሚ ባልቻ፣
- 2ኛ ከበደ ገመቹ መገርሳ፣
- 3ኛ አብዲ አለማሁ እና
- 4ኛ ላምሮት ከማል መሃመድ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ክሱ ተነቦላቸዋል፡፡

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ የማቆም አቅም እንደ ሌላቸው ተናግረዋል፡፡

4ኛ ተከሳሽ የሆነችው ላምሮት ከማል ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላት ገልጻ ሆኖም የሚቆምልኝ ጠበቃ አጥቻለው በማለት ለፍርድ ቤት አስረድታለች፡፡

ፍርድ ቤቱ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው አዟል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተነበበላቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመመልከት ለጥቅምት 4 /2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ሽንዲ ከተማ ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

አድራሻቸው ከሰከላ ወረዳ እና ከቡሬ ከተማ የሆኑ 2 ግለሰቦች በወምበርማ ወረዳ በሚገኙ ለንግድ ተቋማትና ለህብረተሰቡ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

2ቱ ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ የብር ኖቱን ከባህር ዳር እንዳመጡት ፖሊስ ገልጿል። ብሩን በወምበርማ ወረዳ ሊያሰራጩትም ነበር ተብሏል።

የጸጥታ ሃይል ክትትል እንዳለ ሲያውቁ ወደ ቡሬ ከተማ ተመልሰው በመሄድ ለማሰራጨት ሲሞክሩ ፖሊስ ወደ ቡሬ አብሮ በመሄድና ክትትል በማድረግ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዳደረጋቸው ተገልጿል።

የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት በክትትል እና ስምሪት ላይ ለነበሩት የፖሊስ አባላቱ ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ፦ የወምበርማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia