TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአ/አ የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የጣምራ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ አሰራር ሊዘረጋ ይችላል ተብሏል !

በአዲሰ አበባ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የተለያዩ እቅዶችን አቅዶ ወደ ተግባር ለመግባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑን የከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ጅሬኛ ሄርጳ #ለFBC (ኤፍቢሲ) ተከታዩን ብለዋል ፦

- የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች በስራ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት የጣምራ ማለትም 3 ሰውና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው አሸከርካሪዎች የጣምራ ትራንሰፖርት ካልሰጡ ጠዋት ከ1 እሰከ 3 ሰዓት እና ምሸት ከ11 እሰከ ምሽት 1 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ አይችሉም።

- የጣምራ ትራንስፖርት አገልግሎት የኮድ 2 እና ኮድ 3 ተሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቁን ለመቀነስ በፈቃደኝነት ለሌሎች ተሳፋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡበት መንገድ ነው።

- ህብረተሰቡ የብዙሃን ትራንሰፖርትና የጣምራ ትራንሰፖርትን በመጠቀም የመዲናዋን የትራፊክ መጨናነቅ እንዲቀንስ የበኩሉን አሰተዋጾ ሊያደርግ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia