TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጤና ባለሞያዎች ተጋላጭነት!

እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የጤና ባለሞያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው እንደተረጋገጠ ወይም በንክኪ ሳቢያ እራሳቸውን አግልለው የተቀመጡ ምን ያህል እንደሆኑ አይታወቅም። መንግስትም በዚህ ላይ መረጃ አልሰጠም።

የጤና ባለሞያዎች ባላቸው ተጋላጭነት ላይ እያነሱ ያሉትን ጥየቄ በተደጋጋሚ ስናቀርብ ነበር። አሁንም ጥንቄው አልተቋረጠም። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ እየጠየቁ ነው።

በተለይ ከፊት ለፊት ለሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች #PPE ማግኘት እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ። መንግስት ችግሩን ለመፍታት እየሰራ እንደሆ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

በዚህ ሳምንት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ያነሱትን ቅሬታና ከ9 ቀናት በፊት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ያጋጠማቸውን እና ያነሱትን ቅሬታ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው።

የጤና ባለሞያዎች ደህንነት መጠበቅ ካልተቻል ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል። እንደምሳሌ እንኳን በሁለቱ ሆስፒታሎች ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የጤና ባለሞያዎች ባላቸው ተጋላጭነትና ንክኪ ከስራ ገበታቸው ገለል ብለዋል ይህን የሚፈጥረውን ጫና ማሰብ ከባድ ነው።

ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ አንድ ሰው (የጤና ባለሞያ ፣ የፅዳት ሰራተኛ፣ ጥበቃ ሊሆን ይችላል) ይህን ወረርሽኝ ለመግታት በሚደረገው ጥረት ያላቸው ድርሻ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መበራከቱን ተከትሎ ምርመራው በስፋት እየተካሄደ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአዲስ አበባ #በኅብረተሰቡ ውስጥ መሰራጨቱ በመረጋገጡ የምርመራ አድማሱን በማስፋት በተለይም በሥራቸው ባህሪይ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የኀብረተሰብ ክፍሎች ላይ ምርመራው ተጠናክሯል።

በተለይም የቫይረሱ ስርጭት በስፋት በተስተዋለባቸው የአዲስ አበባ ልደታና አዲስ ከተማ ከፍለ ከተሞች እና አካባቢዎች የምርመራ ስራው እየሰፋ መሆኑን ነው ዶክተር ሊያ የተናገሩት።

በከተማዋ የሚደረውን እንቅስቃሴ መዝጋት ሁነኛ መፍትሄ አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ ቫይረሱን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን መተግበር ከተቻለ ስርጭቱን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል።

በተጓዳኝም ቫይረሱ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለበትን ደረጃ ማወቅ የሚያስችል የአንቲ ቦዲ ቴስት ወይም ከደም ናሙና በመውሰድ የመመርመር ሥራ በቅርቡ ይጀመራል ብለዋል።

https://telegra.ph/DrLiaTadesse-05-31

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ሕሙማንን እያገለገሉ ለሚገኙ 1 ሺህ 750 የጤና ባለሙያዎች ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኮቪድ-19ን ለመከላከል ለሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ሠራተኞች የሚውሉ የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑንም የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ለኮቪድ-19 ሕሙማን አገልግሎት ለሚሰጡ 1,750 የጤና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ ጊዜያዊ መኖሪያዎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ በሁሉም ክልሎች ለጤና ባለሞያዎች ጊዜያዊ መኖሪያዎችን ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጠቁመዋል።

https://telegra.ph/DrLiaTadesse-05-31-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,836 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠኝ (109) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,172 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 61 ወንድ እና 48 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ5 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 99 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 2

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 13

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 94

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው 1 ሰው ከትግራይ ክልል ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 209 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 11 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ ተጨማሪ የሶስት (3) ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

አንደኛዋ የ29 ዓመት በትግራይ ክልል የሰቲት ሁመራ ነዋሪ ፣ ሁለተኛ የ75 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪና ሶስተኛ የ55 ዓመት በደቡብ ክልል ካፋ ዞን (በቅርቡ አዲስ አበባ የመጣ) ሲሆኑ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አንድ (11) ደርሷል።

የመጀመሪያ ሁለቱ ግለሰቦች በሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ሶስተኛው ህይወቱ ያለፈና 'ለአስክሬን ምርመራ' ወደ ሆስፒታል የመጣና በተደረገለት ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ዕለታዊ መግለጫ (ግንቦት 23/2012 ዓ/ም በCARD እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀረሪ ክልል!

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 154 የላብራቶሪ ምርመራ ነው ሶስት (3) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በአጠቃላይ በሐረሪ ክልል ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አስራ አንድ(11) ደርሷል፡፡

የእለቱ ታማሚዎች ተጋላጭነት ሁኔታ ከታወቀ ታማሚ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እና የውጪ ጉዞም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላት።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላት።

ታማሚ 3 - የ29 አመት ኢትዮጵያዊ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 320 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ የገላን ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #ያለው

ታማሚ 2 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 3 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሱሉልታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 4 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሱሉልታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 5 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊት፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም። የሱሉልታ ነዋሪ፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)

#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrYohannesChala 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 23/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 817 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አራት መቶ ስልሳ ስምንት (468) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ (100) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 52 ሰዎች
• ልደታ - 8 ሰዎች
• ጉለሌ - 16 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 11 ሰዎች
• ቦሌ - 1 ሰው
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 3 ሰዎች
• አራዳ- 5 ሰዎች
• ቂርቆስ- 0
• አቃቂ ቃሊት - 3
• የካ - 0
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 1 ሰው

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ስምንት መቶ አስራ ሰባት (817) ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 223 ሰዎች
• ልደታ - 151 ሰዎች
• ጉለሌ - 119 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 80 ሰዎች
• ቦሌ - 65 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 34 ሰዎች
• አራዳ - 33 ሰዎች
• የካ - 32 ሰዎች
• ቂርቆስ - 23 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 16 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 41 ሰዎች

[የጤና ሚኒስቴር መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 99 እንደሆነ ይገልፃል። ይህ የቁጥር መዛባት እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ የሚመለከታቸውን አካላት ጠይቀን እናሳውቃችኃለን]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኬንያ፣ ጅቡቲና ሱማሊያ የኮቪድ-19 ሪፖርት!

- በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 74 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ1 ሰው ህይወት አልፏል። እንዲሁም 14 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ በኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 1,962 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የ64 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 478 ሰዎች አገግመዋል።

- በጅቡቲ ተጨማሪ 164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል። እንዲሁም 218 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 3,354 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 24 ሰዎች ሞተዋል፥ 1,504 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

- በሱማሊያ ተጨማሪ 60 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል። እንዲሁም 21 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 1,976 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 78 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 348 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ (ግንቦት 23/2012 ዓ/ም በCARD እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AtoAknawKawza በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 8 መሆናቸው ተገልጿል! ባለፉት 24 ሰዓት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት 100 ያህል የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል። በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ስምንት (8) ነው። አንድ ግለሰብ ከአዲስ አበባ ቤት ለቤት በተደረገው ምርመራ ፖዘቲቭ ሆኖ ወደ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ከገባ በኃላ ሲያዝ በዛሬው ዕለት የጤና…
#AtoAknawKawza

ትላንት ከተገለፀው 1 ሰው በተጨማሪ ሌሎች አምስት (5) ሰዎች ከአዲስ አበባ ውጤታቸው ሳይገለፅ ወደ ሲዳማ ዞን መግባታቸውን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አሳውቋል።

እነዚህ 5 ግለሰቦች ትላንት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ከተረጋገጠ 95 ሰዎች መካከል ናቸው።

እስካሁን ባለው መረጃ ከአምስቱ (5) ግለሰቦች መካከል ሶስቱ (3) ተይዘዋል። ሁለቱ (2) ወደመኖሪያ አካባቢያቸው ከገቡ በኃላ አንደኛው ጥቁር ውሃ ላይ ነው የተያዘው።

በአሁን ሰዓት ሁለቱ (2) ይርጋለም ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ፤ አንደኛው ሀዋሳ ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ነው የሚገኘው።

ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተለዩ ሰዎች ተይዘዋል። በንሳ ላይ 141 ሰዎች፣ ይርጋለም ላይ 180 ሰዎች፣ ሀዋሳ ከተማ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 411 ሰዎች ተይዘዋል።

ሁለቱ ያልተገኙት ሰዎች እስካሁን እየተፈለጉ ነው። አንደኛው ሽፋ ወረዳ ዕድሜው 18 የሆነና ሌላኛው በንሳ ዳዬ ዕድሜው 23 የሆነ ወጣት ናቸው #እየተፈለጉ የሚገኙት።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#DrMengistuBekele

በኦሮሚያ ክልል ትላንት ግንቦት 22/2012 እና ዛሬ ግንቦት 23/2012 በቫይረሱ መያዛቸው ስለተረጋገጠው ሰዎች የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ ተጨማሪ መረጃዎችን አካፍለውናል።

ትላንት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 22 ሰዎች ፦

- በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ 22 ሰዎች መካከል ሃያዎቹ (20) የኢትዮ-ጅቢቲ መስመር ላይ የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ናቸው።

- ከሃያ ሁለቱ (22) ሰዎች አስራ ስምንቱ (18) የተገኙት አንድ ቦታ ነው። የተቀሩት መተሃራ ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኙ ናቸው።

- የውጭ ሀገር ጉዞ ያላቸው 20 ናቸው። ሁለት ሰዎች ደግሞ ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው፤ ከሁለቱ አንደኛዋ ሴት ከምዕራብ ሸዋ ጊንደ በረት ወረዳ ነው በቫይረሱ መያዟ የተረጋገጠው።

አንድ ቦታ እንደተገኙ ከላይ የገለፅናቸው 18 ሰዎች ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ (ምዕራብ ሸዋ ዞን) የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ቦታው ድረስ ሄዶ ከወሰዳቸው ናሙናዎች መካከል ነው የተገኙት። ግለሰቦቹ ምንም እንኳን ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራዎችን ቢሰሩም የድርጅቱ #ተቀጣሪ ሰራተኞች አይደሉም።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 5 ሰዎች፦

ሶስቱ (3) ከሱሉልታ ናቸው፤ እነዚህ ግለሰቦች ለህክምና አገልግሎት በመጡበት ናሙናቸው ተወስዶ ሲመረመሩ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

አንደኛው ከሰንዳፋ ሲሆኑ እኚህ ግለሰብ ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው እየታከሙ የሚገኙ ናቸው፤ ናሙናቸው ተወስዶ ሲመረመር ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

አንደኛው የገላን ነዋሪ ሲሆን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው ነው። መተሃራ ላይ ነው ናሙናው የተወሰደው በምርመራ ውጤት መሰረት በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

#ቲክቫህ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተጠነቀቀ ይህን የከፋ ጊዜ ይሻገራል!

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሩቅ ሀገር በሽታ ነው ሲባል እንዳልነበር ዓለምን አዳርሶ ዛሬ ሀገራችንን እያመሰ ነው።

በአዲስ አበባ አሁንም መደበኛ ህይወት የሚመራባቸው አካባቢዎች እንዳሉ ተመልክተናል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነው።

በአ/አ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ቢገኝም አሁንም ከክልሎች ጋር 'የህዝብ ትራንስፖርት' አልቆመም ይህ ሁኔታ መላው የሀገሪቱን ህዝብ አደጋ ላይ እየጣለ ነው።

የክልል ከተሞች ላይ የሚታየው መዘንጋት ደግሞ ችግሩን የከፋ ሊያደርገው ይችላል። ጊዜው ሳይረፍድ መፍትሄ ቢፈልግ መልካም ነው።

የክልል ነዋሪዎች ጋር ቫይረሱ በስፋት ያለው አዲስ አበባ #ብቻ ነው እኛ ጋር አይደርስም በሚል የተሳሳተ አመለካከት ካለ አሁን መታረም አለበት።

የውጭ ሀገር ነው ሲባል የነበረው በሽታ ዛሬ ሀገራችን ፣ ሰፈራችን ደርሷል፤ #ካልተጠነቀቅን የእያንዳንዳችንን ቤት ማንኳኳቱ አይቀርም።

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከያ መንገዶች እጅግ በጣም ቀላል ሆነው ሳለ ለምን የማይገባ ዋጋ እንከፍላለን ?

• የእጆቻችንን ንፅህና እንጠብቅ! /መታጠብ/

• ቤት ውስጥ እንቀመጥ! /መቀመጥ/

• የስራችን ሁኔታ ከቤት የሚያስወጣና አስገዳጅ ጉዳዮች ኖረውን ከቤት ከወጣን የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ እናድርግ! /መሸፈን/

• በሁሉም ቦታ አካላዊ ርቀት እንጠብቅ! /መራራቅ/

የኢትዮጵያ መንግስት የቫይረሱን ከፍተኛ ስርጭት ከግምት ውስጥ ሊያስገባና በህዝብ ትራስፖርቶች ላይ ያለውን ሁኔት ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ሊፈልግለት ይገባል። ካልሆነ በሀገር ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ5,000 በለጠ!

ትላንት ምሽት የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሀገሪቱ ተጨማሪ 226 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 24 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 151 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

በአጠቃላይ 5,026 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ ውስጥ ከ262 ሰዎች ህይወት አልፏል። 1,423 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 11 ደረሰ! ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ ተጨማሪ የሶስት (3) ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል። አንደኛዋ የ29 ዓመት በትግራይ ክልል የሰቲት ሁመራ ነዋሪ ፣ ሁለተኛ የ75 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪና ሶስተኛ የ55 ዓመት በደቡብ ክልል ካፋ ዞን (በቅርቡ አዲስ አበባ የመጣ) ሲሆኑ በአጠቃላይ በሀገራችን…
በኮቪድ-19 የህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ካለፈ 11 ሰዎች መካከል አንደኛው ከካፋ ዞን እንደሆነ ይታወቃል።

ግለሰቡ የ55 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በዴቻ ወረዳ በሃ ቀበሌ ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲሆን በኃላም በተደረገው የአስክሬን ምርመራ ነው በቫይረሱ መጠቃታቸው የተረጋገጠው።

እስካሁን ከሟቹ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 34 ሰዎች ተለይተው ወደ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል።

ግለሠቡ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ፣ የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴያቸውም (2009-2010) በሃ ቀበሌ ቦቃ በተባለ መንደር ውስጥ ያደረጉ ነበሩ።

2011 ላይ በልመና ከቦንጋ - ዴቻ እየተመላለሱ የሚተዳደሩ መሆናቸውና በቅርብ ጊዜ (8/9/2012) ቦንጋ ከተማ መስጊድ አካባቢ እንደነበሩ ነገር ግን በዛው ዕለት ወደ ዴቻ ወረዳ እንደተመለሱ ተገልጿል።

የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ህብረተሰቡ በሁኔታው ሳይደናገጥ የጤና ባለሞያዎችን ምክር በማዳመጥ ፣ የሚተላለፉ መመሪያዎችን በማክበር እራሱን፣ ቤተሰቡን እና ወገኑን ከዚህ ወረርሽኝ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,257 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 51 ወንድ እና 34 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 ወር እስከ 65 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 72 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 19

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 18

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 48

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው 8 ሰዎች (3 ከኦሮሚያ ክልል እና 5 ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 217 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot