TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረሪ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 175 የላቦራቶሪ ምርመራ ነው 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ደርሷል፡፡

የእለቱ ታማሚዎች ተጋላጭነት ሁኔታ ከታወቀ ታማሚ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እና የውጪ ጉዞም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ወንድ ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌለው

ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ወንድ ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌለው

ታማሚ 3 - የ35 ዓመት ሴት ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌላት

የላቦራቶሪ ምርመራው የተደረገው በሀረማያ ዩኒቨርሲቲና በሀረሪ ክልል ላቦራቶሪ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 233 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሃያ ሁለት (22) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው 20 ሰዎች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ22-44 ውስጥ ይገኛል።

ሁለቱ (2) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #የሌላቸው ሲሆኑ የሁለቱ ሰዎች የእድሜ ክልል ከ17-31 ውስጥ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከላካቸው የኮቪድ-19 ናሙናዎች መካከል ዛሬ ሁለቱ (2) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ሁለቱ ሰዎች አንደኛው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ሲሆን ሌላኛው በለይቶ ማቆያ የሚገኝ የጅቡቲ ተመላሽ ነው።

(ወ/ሮ ለምለም በዛብህ - የቢሮው ኃላፊ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Djibouti

በጅቡቲ በተደረገው 1,109 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ ሰማንያ (280) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 3,194 ደርሰዋል።

በተጨማሪ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር ሃያ ሁለት (22) ደርሷል።

በሌላ በኩል አርባ አምስት (45) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,286 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አፋር ክልል !

በአፋር ክልል በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዙን የተረገጠውን አንድ (1) ሰው ጨምሮ በአጠቃላይ 31 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና #አገግመዋል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
COVID-19 Ethiopia.apk
6.6 MB
Debo (3).apk
3 MB
#COVID19Ethiopia

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሁለት የሞባይል መተግበርያ (አፕሊኬሽኖችን) አገልግሎት ላይ ማዋሉን አስታውቋል።

ከሞባይል መትግበርያዎቹ የአንደኛው የጤና ባለሞያዎችን እውቀት ለማሳድግ የሚያስችል ሲሆን ሌላው ኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መለየት የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በማዳጋስካር 60 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል!

የማዳጋስካር ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ ስልሳ (60) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውና የአንድ (1) ሰው ህይወት ማልፉን ሪፖርት አድርጓል።

በሀገሪቱ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ከቀን ወደቀን እየጨመር መጥቷል። እስካሁን 758 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የስድስት (6) ሰዎች ህይወት አልፏል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 165 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ ተጨማሪ 143 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው መረጋገጡን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,888 ደርሷል።

በሌላ በኩል 26 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አራት መቶ ስልሳ አራት (464) ደርሰዋል። እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓት የ1 ሰው ህይወት በማለፉ የሟቾች ቁጥር ወደ 63 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
 #DrYohannesChala 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 22/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 717 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከነዚህ ውስጥ ሶስት መቶ ስልሳ ስምንት (368) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሃምሳ ስድስት (56) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 12 ሰዎች
• ልደታ - 6 ሰዎች
• ጉለሌ - 17 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 3 ሰዎች
• ቦሌ - 1 ሰው
• የካ - 1 ሰው
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 1 ሰው
• አራዳ- 5 ሰዎች
• ቂርቆስ- 1 ሰው
• አቃቂ ቃሊት - 0
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 9 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰባት መቶ አስራ ሰባት (717) ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 171 ሰዎች
• ልደታ - 143 ሰዎች
• ጉለሌ - 103 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 69 ሰዎች
• ቦሌ - 64 ሰዎች
• የካ - 32 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 31 ሰዎች
• አራዳ - 28 ሰዎች
• ቂርቆስ - 23 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 13 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 40 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 95 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,034 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና አምስት (95) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,063 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 71 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ15 እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 94 ሰዎች…
#AtoAknawKawza

በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 8 መሆናቸው ተገልጿል!

ባለፉት 24 ሰዓት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት 100 ያህል የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል። በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ስምንት (8) ነው።

አንድ ግለሰብ ከአዲስ አበባ ቤት ለቤት በተደረገው ምርመራ ፖዘቲቭ ሆኖ ወደ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ከገባ በኃላ ሲያዝ በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስቴር አዲስ በቫይረሱ መያዛቸውን ካረጋገጠው 95 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በንሳ ወረዳ ላይ ተይዞ በይርጋለም ለይቶ ማቆያ እንዲቆይ ተደርጓል።

ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው እና አብረውት ከአዲስ አበባ ወደ በንሳ የመጡ 14 እና 20 ሰዎች ደግሞ ከተጠርጣሪውና ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ተለይተው በድምሩ 34 ሰዎች ንክኪ ያላቸው #በይርጋለም ለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተሳሳቱ መረጃዎች እንዳትደናገሩ!

በጤና ሚኒስቴር ከተገለፀው ውጭ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የለም። የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት ያደረገው ከ95ቱ ሰዎች አንደኛው ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ የገባን ታማሚ ነው።

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው እንዳለ አድርገው የተለያዩ ያልተረጋገጡና በጤና ሚኒስቴር ያልተሰጡ መረጃዎችች እያሰራጩ እንደሆን ተመልክተናል። #በተሳሳቱ መረጃዎች እንዳትደናገሩ።

ዛሬ ግንቦት 22/2012 ዓ/ም #ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አምስት (95) ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SOMALIA

የሱማሊያ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተጨማሪ 88 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,916 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል አስራ ሰባት (17) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከበሽታው #ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 327 ደርሷል። እንዲሁም አንድ ሰው ህይወቱ በማለፉ የሟቾች ቁጥር ወደ 73 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CoronaVac

በቻይና የኮቪድ-19 ክትባት እያዘጋጁ የሚገኙት ሳንቲስቶች (ከሶኖቫክ ባዮቴክ) ክትባቱ 99% ውጤታማ እንደሚሆን #ለSkyNews ተግረዋል።

በአሁን ሰዓት ክትባቱ በሁለተኛ ደረጃ የሙከራ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ሶስተኛው ደረጃ የሙከራ ሂደት በዩይትድ ኪንግደም እንደሚደረግ ሳይንቲስቶቹ ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን አሁን ያለው ሙከራ ሂደት ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ቢገኝም ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ሙከራው ተጠናቆ በስፋት ለሰዎች እስኪቀርብ ድረስ ወራትን ይፈጃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የ1 ሰው ህይወት አለፈ!

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 45 ሰዎች መካከል የአንዲት ሴት ህይወት ማለፉን (ከማይካድራ) የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትግራይ!

ዛሬ በትግራይ ክልል (ከማይካድራ) በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወቷ እንዳለፈ የተነገረን ሴት ተጓዳኝ ህመም (የኩላሊት ህመም) ነበረባት። በሁመራ ካህሳይ አበራ ሆስፒታል (ICU) ውስጥ እያለች ነው ህይወቷ ያለፈው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ ሱዳን ሌላኛው ምክትል ፕሬዝዳንት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀምስ ዋኒ ኢጋ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን #አረጋግጠዋል

ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀምስ ዋኒ ኢጋ ከዚህ ቅደም በቫይረሱ የተያዙትን ዶክተር ሬክ ማቻር (ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት) ፣ ሁሴን አብድልበጊ አኮል (ምክትል ፕሬዘዳንት) ፣ አንጅሊና ቴኒ (የመከላከያ ሚኒስትር) እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀላቅለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሱዳን ውስጥ በ2 ቀን 279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ባወጣው የሁለት ቀን ሪፖርት (ግንቦት 20 እና ግንቦት 21) ተጨማሪ 279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል።

እንዲሁም በሁለቱ ቀናት 29 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 457 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሱዳን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 4,800 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ262 ሰዎች ህይወት አልፏል። 1,272 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot