TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ዩናይትድ ኪንግደም /UK/ የ4,419 ሰዎችን ሞት ሪፖርት አድርጋለች፤ ዛሬ ሪፖርት ከተደረገው ውስጥ 765 ሰዎች (ባለፉት 24 ሰዓት) በሆስፒታል የሞቱ ናቸው። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26,097 ደርሷል። UK ከአሜሪካና ከጣልያን ቀጥላ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የሞተባት ሀገር ሆና ተመዝግባለች።

- በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ወደ ሆስፒታል ካቀኑ የዩናይትድ ኪንግደም ህመምተኞች መካከል አንድ ሶስተኛው መሞታቸውን አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል - #BBC

- ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች፤ አምስቱ (5) ከውጭ የገቡ ናቸው። ሀገሪቱ ከ15 በታች ኬዝ ስታስመዘግብ 11ኛ ቀኗ ነው።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ427 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል።

- የጁቬንቱሱ አጥቂ ፓውሎ ዲባላ በ6 ሳምንታት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ #ፖዘቲቭ ሆኖ ተገኝቷል።

- የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት 4.8 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። እአአ 2014 ላይ ከታየው ውድቀት ወዲህ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። ዛሬ የወጣ አሀዝ እንደሚያሳየው፤ ከ26 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሥራ አጥ ሆነዋል። በአሜሪካ ታሪክ ንግድ የተቀዛቀዘበት ወቅት መሆኑም ተመልክቷል። የአገሪቱ እድገት 30 በመቶ ወይም ከዛ በላይም ሊገታ እንደሚችል ተገምቷል - #BBC

- በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 225 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 13 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል 3 ሰዎች አገግመዋል፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 98 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE (ሀላባ ዞን አስተዳደር) በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸው ግለሰቦችን በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡ በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 25/2012 ዓ/ም) በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንኪኪ እንደነበራቸው የተጠረጠሩ እስካሁን 40 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ…
#UPDATE

(ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር)

በሞያሌ የአስገዳጅ ማቆያ የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎለት #ፖዘቲቭ መሆኑ የተረጋገጠና ከእሱ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 7 ተጠርጣሪዎች ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የተደረገ መሆኑ ይታወሳል።

ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የ3ቱ የምርመራ ውጤት #ኔጌቲቭ ሆኗል። የተጠርጣሪዎቹ የናሙና ውጤት በአሁኑ ምርመራ ኔጌቲቭ ቢሆንም የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን ዝቅተኛውን ስታንዳርድ 14 ቀን መጠበቁ የግድ በመሆኑ 14 ቀን እስኪሆናቸው ድረስ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ይቆያሉ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የከተማው ነዋሪ በዚህ መልካም ዜና #ሳይዘናጋ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ ኃላፊነት በተሞላ መልኩ የመከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በትግራይ ክልል 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት የተደረገው የ4 ሰዎች #ፖዘቲቭ ኬዝ ጥዋት በፌደራል ደረጃ በጤና ሚኒስቴር ከተገለፀው ውጭ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ #አረጋግጠውልናል

በትግራይ ክልል ስልተገኙት 4 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የክልሉን ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይን አነጋግረን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማንቂያ ደውል ይሁነን!

ከዚህ ቀደም ከሞያሌ መምጣቱ የተገለፀው ግለሰብ የሀላባ ዞን ባዘጋጀዉ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ዉስጥ ሀኪም ተመድቦለት ተገቢዉን ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው ገልፀዋል።

ግለሰቡ #ፖዘቲቭ ሆኖም እስከአሁን መደበኛ 'ምልክቶችን አለማሳየቱ' ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል 'ማንቂያ ደወል' ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከዚሁ ግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ እንዳላቸዉ የተጠረጠሩ 37 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸዉ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የምርመራ ዉጤታቸዉ የበፊቱን ሁኔታ ብቻ የሚገልፅ በመሆኑ 15 ቀን ሲሞላቸዉ ሁለተኛ ዙር ምርመራ ተደርጎላቸዉ ዉጤታቸዉ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል የሚገለፅ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የዞኑ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የማንቂያ ደውል ይሁነን! ከዚህ ቀደም ከሞያሌ መምጣቱ የተገለፀው ግለሰብ የሀላባ ዞን ባዘጋጀዉ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ዉስጥ ሀኪም ተመድቦለት ተገቢዉን ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው ገልፀዋል። ግለሰቡ #ፖዘቲቭ ሆኖም እስከአሁን መደበኛ 'ምልክቶችን አለማሳየቱ' ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል 'ማንቂያ ደወል' ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። ከዚሁ ግለሰቡ ጋር…
የማንቂያ ደውል ይሁነን!

"ሳል፣ ትኩሳት፣ ለመተንፈስ መቸገርና የራስ ህመም የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክቶች ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ #ፖዘቲቭ ሊሆኑና ወደ ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ዕድል ሊኖራቸዉ ስለሚችል ምልክቶች ታዩም አልታዩ የሚደረጉ መሰረታዊ የጥንቃቄ መመሪያዎችን መተግበር አማራጭ የሌለዉ ተግባር ነው" - አቶ አለማየሁ ጌታቸው (የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዩጋንዳ ምን ታስተምረን ይሆን ?

ዩጋንዳ ወደሀገሯ የሚገቡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ክትትልና ምርመራ እናደረገች ትገኛለች። የባለፉት 3 ቀናት ምርመራን በአጭሩ እንመልከት!

ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም የተደረገ ምርመራ ፦

• 3,091 የላብራቶሪ ምርመራ በከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ - 1 ሰው #ፖዘቲቭ
• 718 የላብራቶሪ ምርመራ ከማህበረሰቡ - ሁሉም #ነፃ
• አጠቃላይ የተደረገ ምርመራ - 3,809

ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም የተደረገ ምርመራ ፦

• 2,421 የላብራቶሪ ምርመራ በከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ - 13 ሰዎች #ፖዘቲቭ
• 740 የላብራቶሪ ምርመራ ከማህበረሰቡ - ሁሉም #ነፃ
• አጠቃላይ የተደረገ ምርመራ - 3,161

ግንቦት 1/2012 ዓ/ም የተደረገ ምርመራ ፦

• 1,913 የላብራቶሪ ምርመራ በከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ - 2 ሰዎች #ፖዘቲቭ
• 652 የላብራቶሪ ምርመራ ከማህበረሰቡ - ሁሉም #ነፃ
• አጠቃላይ የተደረገ ምርመራ - 2,565

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የእኔ ውጤት #ኔጌቲቭ ነው!" - ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ውጤታቸው #ፖዘቲቭ ነው ተብሎ በሚዲያዎች ላይ መነገሩ ሀሰት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ "በትላንትናው ዕለት የደቡብ ሱዳን ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ እንዳረጋገጠልኝ የናሙና ውጤቴ #ኔጌቲቭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ…
#TikvahEthiopia

ዛሬ በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 4 ሰዎች መካከል ሁለቱ (2) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና መጥተው በተደረገው ምርመራ የተገኙ ናቸው።

አጭር መረጃ ፦

- ሁለቱም በ50ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው።

- አንደኛው ታማሚ ማክሰኞ ከሰዓት ነው ወደ ሆስፒታል የመጡት፤ ሌላኛው ታማሚ ደግሞ እሮብ ጥዋት ነው ወደ ሆስፒታል የመጡት።

- የምርመራው ውጤቱ ትላንት ነው የወጣው፤ የሁለቱም (2) ናሙና #ፖዘቲቭ ሆኖ ነው የተገኘው።

- በሆስፒታሉ የመተንፈሻ አካላት እና ተዛማጅ በሽታዎች ያለባቸውን ታማሚዎች የመርመር ስራ እየተሰራ በመሆኑ ነው እኚህ የኮቪድ-19 ታማሚዎች የተገኙት።

- በሆስፒታሉ ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን በሙሉ ኳራንታይ እንዲደረጉ ተደርጓል (የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ማንኛውም ሆስፒታል ውስጥ ያሉና ግንኙነት የነበራቸው)

- ከሆስፒታል ውጭ ደግሞ ከመጡበት አካባቢ ጀምሮ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመፈለጉ እና ኳራንትይን እንዲገቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው።

- አንደኛው ታማሚ ባህር ዳር ሄደው ነው የመጡት የከተማ አስተዳደሩ ከታማሚው ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ ሰዎችን ኳራንታይ የማድረግ ስራ እየሰራ ነው አሁንም ኳራንታይን የተደረጉ አሉ።

- ሁለተኛው ታማሚ ከጯሂት ነው የመጡት መጀመሪያ ያከሟቸው ሃኪምን ጨምሮ ኳራንታይ ተደርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia