TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE (ሀላባ ዞን አስተዳደር) በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸው ግለሰቦችን በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡ በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 25/2012 ዓ/ም) በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንኪኪ እንደነበራቸው የተጠረጠሩ እስካሁን 40 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ…
#UPDATE

(ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር)

በሞያሌ የአስገዳጅ ማቆያ የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎለት #ፖዘቲቭ መሆኑ የተረጋገጠና ከእሱ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 7 ተጠርጣሪዎች ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የተደረገ መሆኑ ይታወሳል።

ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ የ3ቱ የምርመራ ውጤት #ኔጌቲቭ ሆኗል። የተጠርጣሪዎቹ የናሙና ውጤት በአሁኑ ምርመራ ኔጌቲቭ ቢሆንም የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን ዝቅተኛውን ስታንዳርድ 14 ቀን መጠበቁ የግድ በመሆኑ 14 ቀን እስኪሆናቸው ድረስ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ይቆያሉ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የከተማው ነዋሪ በዚህ መልካም ዜና #ሳይዘናጋ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ ኃላፊነት በተሞላ መልኩ የመከላከል ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የእኔ ውጤት #ኔጌቲቭ ነው!" - ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ውጤታቸው #ፖዘቲቭ ነው ተብሎ በሚዲያዎች ላይ መነገሩ ሀሰት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ "በትላንትናው ዕለት የደቡብ ሱዳን ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ እንዳረጋገጠልኝ የናሙና ውጤቴ #ኔጌቲቭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia