TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና~ሞያሌ‼️

ትናንት #በሞያሌ_ከተማ 13 ሰዎች ተገድለው፣ 12 መቁሰላቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ከሟቾቹ መካከል 8ቱ በቀለ ሞላ ሆቴል ውስጥ የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የገደሏቸው ተብሏል፡፡ ሰዎቹ የተገደሉት የኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል እና የፌደራል ጸጥታ ሃላፊዎች እንዲሁም የቦረና ኦሮሞ እና ጋሪ ሱማሌ ጎሳ ተወካዮች ሆቴሉ ውስጥ የጋራ ምክክር ላይ ሳሉ ነው፡፡ መከላከያ ሚንስቴር እስካሁን ስለ ክስተቱ መግለጫ አልሰጠም፡፡ በከተማዋ ዛሬም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ(በዋዜማ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መካከል ነገ #በሞያሌ ከተማ ለሚካሄደው የሠላም ኮንፈረንስ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተነግሯል፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ ለመሳፍ የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የፀጥታ እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ኡጋዞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ሞያሌ ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 912 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ #ከኬንያ የተመለሰና #በሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከፑንትላንድ የተመለሰና በጅግጅጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰባት (7) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ስድስት (66) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia