TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለOMN ጋዜጠኞች ከጃዋር መሀመድ የተፃፈ...

(ከEyasped Tesfaye)

ይህ ዛሬ #OMN ውስጥ ከሚሰራ ወዳጄ ያገኘሁት መረጃ ነው። ጃዋር መሀመድ በትናንትናው ዕለት ለ OMN staff የፃፈው ደብዳቤ ሲሆን ፤ ለ internal consumption ብቻ ይውል የነበረ ቢሆንም ለሌሎች ሚዲያዎችም ትምህርት እንዲሆን እና መንገዳቸውን መርምረው አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ ይረዳል ብዬ ስላመንኩ ለጥፌዋለሁ።
.
-ማንኛውንም ብሄር #በመጥፎ መልኩ የሚገልፁ ወይም የሚያቀርቡ ዜናዎችም ሆነ ፕሮግራሞች እንዳይኖሩ

-ግጭትን እና ፀብን የሚያነሳሳ ይዘት ያላቸው የሚመስሉ ማንኛውም ፕሮግራሞች #እንዳይቀርቡ

-እንዲሁም ሰላምን መቻቻልን እና መረዳዳትን ብቻ መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ.....ወዘተ ይገልፃል ደብዳቤው።

(ሙሉ ደብዳቤው በምስል ከላይ ተያይዟል)

Via Eyasped Tesfaye
@tsegabwolde @tikvahethiopi
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል መባሉን አስተባበሉ!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጉዳዩን አስመልክተው ለኦ ኤም ኤን በሰጡት አስተያየት፤ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መሰረተቢስ ወሬ ነው ብለዋል፡፡አቶ ሽመልስ ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን በዉይይት እንዲፈቱ ነው የተናገርኩት ነው ያሉት፡፡

"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም በማለት ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል” ሲል የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ዘግቧል የተባለውን ምክትል ፕሬዝዳንቱ የማደናገሪያ ወሬ ነውም ብለዋል፡፡

መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ገብቶ በስብሰባ ላይ ተሳተፉ ተብለው ለተጠየቁ ጥያቄም መልስ ሲሰጡ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘው እንደሆነ ገልፀው፤ ምክረሀሳብ ከማቅረብ የዘለለ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ያሉት፤ ምእመናን በቋንቋቸው እንዲያመልኩ ላመስቻል ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የቤተክህነቱ መቋቋም በቤተክርስትያኗ ውስጥ ስር የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል ይላሉ፡፡አላማችን ሌላ ስኖዶስ ማቋቋም አይደለምም በማለት በተደጋጋም ተናግረዋል፡፡ይሁንና የቤተክህነቱን መቋቋም በአዎንታዊነት ያልተቀበሉ አካላት እርምጃውን ተቀውመዋል፡፡

Via #OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ''ጊፋታ'' ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ብሄር የባህል ፤ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል።

Via #OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በቃል ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ደውዬ እነግራለሁ ብለውናል!

"በምላሹ ምን ያህል እረካችሁ ለሚለው፤ ማለት ምፈልገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት ነገር አለ፤ የህዝቡ ፍላጎት ይሄ የሚሆን ከሆነ በህግ እና በህገ መንግስታዊ ስርዓት መሰረት እንዲጠናቀቅ አደርጋለሁ። ቃል በቃል ደግሞ ለምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ደውዬ እነግራለሁ ነው ያሉት። ይሄን ያሉት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የቀድሞ የደኢህዴን ሊቀ መንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ባሉበት ነው።" አክቲቪስ ወርቅነህ ገበየሁ (እሁድ የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ከተሳተፉት መካከል አንዱ)

#OMN (ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#OMN

ከሰሞኑን ኦ ኤም ኤን በተባለ መቀመጫነቱን አዲስ አበባ ባደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት ባደረገ ዝግጅት ዙሪያ እየተሰራጨ በሚገኝ የቀጥታ ስርጭት ወቅት አንዲት ሴት የተናገረችው ንግግር ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮ፣ ብዙዎችን አስቆጥቶ በመንግስት ደረጃም ግብረ መልስ ተሰጥቶበታል።

ንግግሩ በተላለፈ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያው ቪድዮውን ከማህበራዊ ገፁ ላይ ያነሳ ሲሆን በእንስቷ ያልተገባ ንግግር ለተከፉ የቴሌቪዥኑ ተመልካቾች በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

መንግስት በበኩሉ በህዝባዊ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በሃገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ እንደሚደቅኑ ገልጾ በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቀዋል።

More https://telegra.ph/OMN-03-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰሞኑን በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ OMN የተላለፈውን አንድ መልዕክት ሰምተናል
<unknown>
#OMN

ሰሞኑን በOMN በተላልፈው መልዕክት በቀጥታ ሲከታተሉ የነበሩት የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ኦፌኮ ሊቀመንበሩር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዴት እንደተረዱት እንዲያስረዱ በሸገር ኤፍ ኤም ተጠይቀው ነበር።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የንግግሩ ችግር አይታየኝም፣ ማንኛውም ዜጋ የሚናገረውን ለመቆጣጠር ፍላጎቱ የለንም ብለዋል፡፡

ሬድዮ ጣቢያው ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሕግ ምሁር እና የብሮድካስት ባለስልጣንንም ጠይቋል፡፡ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለመከላከል በቅርቡ በጥቁር እና በነጭ ተፅፎ የፀደቀው ሕግስ እንዴት እየተተረጎመ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrGurmeessaaHinkoosaa

ህብረተሰቡ በኮሮና ስርጭት ላይ #መዘናጋት እንደሌለበት የጤና ባለሞያው ዶክተር ጉርሜሳ ሂንኮሳ አሳስበዋል። ዶክተር ጉርሜሳ ከOMN ጋር በነበራቸው ቆይታ የአሜሪካን ሁኔታ እንደማሳያ አስተዋል።

በአሜሪካ በ49 የመጀመሪያው ቀናት በበሽታድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 987 እንደነበር አስታውሰው ከዚያ ቀጥሎ ባሉት 16 ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ከ100,000 መብለጡን ገልፀዋል።

ይህ የሚያሳየው በሽታው በአንዴ መስፋፋት እንደሚችል ነው ያሉት ዶክተር ጉርሜሳ ህብረተሰቡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቁጥር አይቶ መዘናጋት የለበትም ብለዋል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን ምክር መከተል እና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

#DrGurmeessaaHinkoosaa #OMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF 🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ መንግስት በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው ” ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ወቀሰ። ፓርቲው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል። በዚህም በወቅታዊ እና በአገራዊ ጉዳዮች እንደ ፓርቲ ያለውን ግምገማና የመፍትሄ ሀሳብ አጋርቷል። Q. ስለ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፓርቲው ግምገማ ምንድን ነው ? ኦነግ ፦ የአገራዊ ምክክር…
ፎቶ ፦ ባለፉት አራት አመታት እስር ላይ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ተለቀዋል።
➡️ አብዲ ረጋሳ፣
➡️ ሚካኤል ቦረን፣
➡️ ኬነሳ አያና፣
➡️ ለሚ ቤኛ፣
➡️ ዶክተር ገዳ ኦልጅረ፣
➡️ ገዳ ገቢሳና ዳዊት አብደታ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ቤት በዋስ መለቀቃቸውን የግንባሩ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ለሚ ገመቹ ለኦኤምኤንገልፀዋል።

#OMN

@tikvahethiopia