TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrGurmeessaaHinkoosaa

ህብረተሰቡ በኮሮና ስርጭት ላይ #መዘናጋት እንደሌለበት የጤና ባለሞያው ዶክተር ጉርሜሳ ሂንኮሳ አሳስበዋል። ዶክተር ጉርሜሳ ከOMN ጋር በነበራቸው ቆይታ የአሜሪካን ሁኔታ እንደማሳያ አስተዋል።

በአሜሪካ በ49 የመጀመሪያው ቀናት በበሽታድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 987 እንደነበር አስታውሰው ከዚያ ቀጥሎ ባሉት 16 ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ከ100,000 መብለጡን ገልፀዋል።

ይህ የሚያሳየው በሽታው በአንዴ መስፋፋት እንደሚችል ነው ያሉት ዶክተር ጉርሜሳ ህብረተሰቡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቁጥር አይቶ መዘናጋት የለበትም ብለዋል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን ምክር መከተል እና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

#DrGurmeessaaHinkoosaa #OMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia