#AddisAbeba
የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ጥዋት ከነበረው አንፃር በአሁን ሰዓት አንፃራዊ መረጋጋት እየታየበት ይገኛል። እንቅስቃሴዎች የተቀዛቀዙ ቢሆንም ሁኔታዎች መረጋጋት ጀምረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Harar በተመሳሳይ በሀረር ከተማ ጥዋት የነበረው ከፍተኛ ውጥረት ረገብ እያለ የመጣ ይመስላል፤ የቲክቫህ ሀረር ቤተሰቦች ሁኔታዎች ከጥዋቱ አንፃር መሻሻል ማሳየታቸውን ገልፀው ወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ ተማፅነዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እና አደጋ አሁንም እየቀጠለ መሆኑንፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተናገሩ። ፓትርያርኩ ዛሬ የተጀመረውን የአመቱን የሲኖዶሱን ምልአተ ጉባኤ ሲከፍቱ እንዳሉት «በሃገራችን በተፈጠረው ያለመረጋጋት አብያተ ክርስትያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል አሁንም ስጋቱ እንዳለ ከቀረበልን የአህጉረ ስብከት ሪፖርት ሰምተናል በአይናችንም አይተናል» ብለዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA በድሬዳዋ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ የሚገልፁ ሪፖርቶች ቢኖሩም፤ ጥዋት ከነበረው ሁኔታ አንፃር አሁን ላይ የተሻለ መረጋጋት እንደሚታይ የቲክቫህ ድሬዳዋ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ሰላም ለሀገራችን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ለሀገራችን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ የቲክቫህ ቤተሰቦች...
"ዛሬ በጅማ ከፍተኛ ተቃውሞ ነበር፤ አክቲቪስትና የOMN ዳይሬክተር ጀዋር መሀመድ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ነው በሚል የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ደምፃቸውን #በሰላማዊ መንገድ ነው ያሰሙት። በአሁን ሰዓት በከተማው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ይታያል።"

#MOJO | በሞጆ ከተማ ጥዋት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነበር። ወደ አ/አ የሚወስደው መንገድም አሁንም እንደተዘጋ ነው። በአሁን ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነው ከተማይቱ የምትገኘው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RUSSIA
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ መርሆችን በመተግበር በመጪዎቹ አስር አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አምስት ቀዳሚ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እየተሰራ ነው ብለዋል። በበሀገሪቱ እየተካሄደ ስላለው ሪፎርም ገለፃ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ ባደረገችው ጦርነት ሩሲያ ለነበራት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በበኩላቸው በኢጋድ መሪነት ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን፥ በተባበሩት መንግስታት ባለብዙ ዘርፍ መድረኮች ሀገራቱ አብረው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። መሪዎቹ በመከላከያ፣ ትምህርት፣ የኒዩክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ግልጋሎት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታላይ በማተኮር ውይይት አድርገዋል፡፡
Via FBC

#attention
በአሰላ ከተማ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦችን ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋጉ ገልፀዋል። በከተማይቱ የተፈጠረውን ችግር ወደሌላ የመቀየር ጥረቶች ይታያሉ የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት ትኩረት ይስጠው ሲሉ አሳስበዋል።
PHOTO: GET/አሰላ ቲክቫህ ቤተሰብ/

#GELAN ገላን ከተማ ከጠዋቱ የተሻለ መረጋጋት ቢኖርም አሁንም በርካታ ጎማዎች እየነደዱ ነው፤ ወጣቱ ተቋሞውን አሰምቶ ወደ ቤት ተመልሷል። ምንም ጉዳት አልደረሰም።
/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking
"#ጃዋር_መሀመድ በሚቀጥለው ምርጫ እንደሚሳተፍ/እንደሚወዳደር ከደቂቃዎች በፊት ሰምቻለሁ።" ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/Associated Press/

#MOJO | በሞጆ ከተማ አንፃራዊ #ሰላም በመስፈኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በከፊል ተጀምሯል፤ የፀጥታ ኃይሎች አስፓልት ላይ የተደረደሩ ድንጋዮችን እያነሱ ነው።
Via Bek/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Bek/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA
በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እንዳይሸከረከር በሞተር ሳይክል ላይ የተጣለው የሰዓት ገደብ ተነሳ!
በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እንዳይሸከረከር በሞተር ሳይክል ላይ የተጣለው የሰዓት ገደብ መነሳቱን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኢዮብ አቢቶ በሰጡት መረጃ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ እንዳይሽከረከር የተጣለው የሰዓት ገደብ ተነስቶ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት መፈቀዱ ተገልፃል፡፡
የሞተር ሳይክል ተጠቃሚ ህብረተሰብ በተለያየ መድረክ የተጣለው የሰዓት ገደብ እንዲነሳ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበረ ኮማንደሩ ገልፀው የሀዋሳ ከተማ በዚህ ወቅት የተሻለ ሰላም መሰፈኑን ተከትሎ ከኮማንድ ፖስት ጋር በመናበብ መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ የሶስት እግር ተሸከርካሪን ጨምሮ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር እንደማይቻል ገልጸው መንጃ ፍቃድ ፣ሰሌዳና ሶስተኛ ወገን ባለጠፉ ተሸከርካሪዎች ላይ ሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናከሮ እንሚቀጥል ኮማንደር ኢዮብ አቢቶ ተናገረዋል፡፡
ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል። በኢትዮጵያ እና በሩስያ መካከል ሥላለው የንግድ ግንኙነት፣ በሀጋራቱ የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ከ35 በላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በሚሳተፉበት የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለመሳተፉ ነው ወደ ሩሲያ ያቀኑት፡፡
Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትናንት ምሽት በአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ላይ የተፈጸመው ተግባር ተቀባይነት የሌለውና ስህተት ነው" – አቶ ሽመልስ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-
• ትናንት ማታ የተፈጸመው ድርጊት ስህተት ነው፤ ስህተቱን ማን እንደፈጸመው፣ ለምን ጉዳዩን ምሽት ላይ ማድረግ እንደተፈለገ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
• ዛሬ ለሞቱት ወገኖች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
• ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡
• እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
• የተለያዩ አካላት ለውጡ ዘላቂነት እንዳይኖረው የተለያዩ ሙከራዎች ሲያደርጉ ነበር፡፡
• ዛሬ የተፈጸመው መሆን የሌለበት ነገር ነው፡፡
• መንግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ነው ለወንድማችን ጀዋርና ለሌሎች ከውጭ ለገቡ ሰዎች ጥበቃ የሚያደርገው፡፡
👉https://telegra.ph/ETH-10-23-7

#ADAMA
ዛሬ ነውጥ ካስተናገዱ ከተሞች አንዷ አዳማ ስትሆን የ2 ሰው ህይወት አልፏል። በንብረት ላይም ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ንብረትነቱ የAfrica PLC. የሆነ የምግብ ነክ ምርቶች ፋብሪካ ጉዳት ደርሶበታል። የብራዘርስ ብስኩት ፋብሪካም ጉዳት ደርሶበታል።
Via ELU

#BATI
ከአማራ ክልል በባቲ ወረዳ የተሰባሰቡ 92 ታዳጊ ህጻናትና ወጣቶችን በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር ለማስወጣት የሞከሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
በፌዴራል ፖሊስ የ3ኛ ሻምበል ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ሞገስ ከበደ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎቹን ጭነው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለማሸጋገር ሲሞክሩ ነው።
በወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉም፤ ኅብረተሰቡ ባደረገው ትብብር ዋና አዘዋዋሪውና ረዳት አሽከርካሪው መያዛቸውን ተናግረዋል።
መንገደኞቹ የተሰባሰቡት ከሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግ ኸምራ ብሄረሰብና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኖች መሆኑንም አስረድተዋል። ወጣቶቹ ሲጓጓዙ የነበሩት የጅቡቲ ሰሌዳ 844 ዲ64 የጭነት መኪና እንደነበርም ዋና አዛዡ ገልጸዋል።
Via ENA

Activist #Jawar_Mohammed tells Al Jazeera English he is seriously considering running in May election.
Via Robyn Lee Kriel
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Robyn Lee Kriel
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የደህንነት ኃይሎች በአጽንኦት የተናገሩት 'ብዙ ባላንጣዎች ስላለህ ጥቃት ቢሰነዘርብህ በሃገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ስለዚህ የደህንነት ጥበቃ ሊኖርህ ይገባል' ነው የተባልኩት..." ጃዋር መሃመድ
.
.
ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሯል።
ጀዋር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በመኖሪያ ቤቱ ተፈጽሟል ስላለው ጉዳይ እና ምልከታውን ለቢቢሲ አጋርቷል።
ጃዋር እኩለ ሊሊት ላይ የተፈጸመውን ሲያስረዳ "ተኝቼ ነበር፤ በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩት ጠባቂዎች 'በአስቸኳይ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ' ተባሉ። ይህ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ" ይላል።
ድንጋጤ የፈጠረበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ "አንደኛ እኩለ ለሊት ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ጀዋር ሳይሰማ ውጡ' ነው የተባሉት። በዚያ ላይ የሚተኩ ጠባቂዎች የሉም" ይላል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-23-9
Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
.
.
ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሯል።
ጀዋር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በመኖሪያ ቤቱ ተፈጽሟል ስላለው ጉዳይ እና ምልከታውን ለቢቢሲ አጋርቷል።
ጃዋር እኩለ ሊሊት ላይ የተፈጸመውን ሲያስረዳ "ተኝቼ ነበር፤ በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩት ጠባቂዎች 'በአስቸኳይ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ' ተባሉ። ይህ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ" ይላል።
ድንጋጤ የፈጠረበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ "አንደኛ እኩለ ለሊት ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ጀዋር ሳይሰማ ውጡ' ነው የተባሉት። በዚያ ላይ የሚተኩ ጠባቂዎች የሉም" ይላል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-23-9
Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BBC | "እኔን #ማሰረ ከተፈለገ በፈለጋቸው ጊዜ ቢጠሩኝ የምገኝላቸው ሰው ነኝ። 'ና ታሰር' ቢሉኝ እንኳ ክሱ አሳማኝ እስከሆነ ድረስ እምቢ የምልበት ምክያት የለም፤ በውድቅት ለሊት በጣም አጣራጣሪ በሆነ መልኩ የተሞከረው ምን እንደሆነ አልገባኝም። የእስርም አይመስለኝም። ከውስጥ እንደምሰማው ሰሞኑን የነበረን ክርክር እየጦፈ ስለመጣ ሴኪሪቲውን በማስነሳት እንዲፈራ እና እንዲሸማቀቅ እናደርጋለን' የሚል የውስጥ ንግግር እንደነበረ፤ ከዚያም በገፋ መልኩ በዱርዬዎች ቤቴ ላይ ጥቃት በማድረስ ለማሳበብ እንደታሰበ ነው ያሉኝ መረጃዎች የሚያሰዩት" አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ
📹11 MB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
📹11 MB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«በጸሎት ሁሉም ቢደግፍ ጥሩ ነው። ዋናው ግን የመንግሥት ሥራ ነው» ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል
የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ባነሱት ነጥብ የክልሉ መንግስት የተጀመረው የሰላም ሂደት ምሉእ እንዲሆን እንደሚሻ ገልፀዋል፡፡ የትግራይ ክልል መንግስት «ተከበናል የሚል መንፈስ በህዝብ ዘንድ እየፈጠረ፣ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው የሚሉ ጉዳዮች ይነሱበታል» ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ዶክተር ደብረፅዮን ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
📹3.3 MB
Via DW

ጅማ እንዴት አመሸች?
ጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት ከተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ለተወሰነ ሰዓት ቆሞ ነበር፤ የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጦ እንደነበር ቅድም ገልፀንላችኃል፤ አመሻሹን ግን ከተማዋ ወደ መረጋጋት በመመለሷ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል።