TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MOJO | በሞጆ ከተማ ጥዋት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነበር። ወደ አ/አ የሚወስደው መንገድም አሁንም እንደተዘጋ ነው። በአሁን ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነው ከተማይቱ የምትገኘው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MOJO | በሞጆ ከተማ አንፃራዊ #ሰላም በመስፈኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በከፊል ተጀምሯል፤ የፀጥታ ኃይሎች አስፓልት ላይ የተደረደሩ ድንጋዮችን እያነሱ ነው።

Via Bek/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MOJO

ትላንት ለሊት 10:00 በሞጆ ከተማ ገበያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር። የሞጆ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ ለሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት መረጃው ባይኖራቸውም በንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱን በስፍራው ተገኝተው አረጋግጠዋል። እሳቱን ከሰዓታት በፊት ነው መቆጥጠር የተቻለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ADAMA #BAHIRDAR ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል። ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል። የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች…
#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል።

ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

#ቢሾፍቱ 📍

በቢሾፍቱ ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ከኦዳ ነቤ ሆቴል ጎን እና ከመዘጋጃው ፊትለፊት)፤

#ሞጆ📍

በሞጆ አንድ መናኸሪያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር፤

#ደብረብርሃን 📍

ከዘርዕ ያዕቆብ አደባባይ ወረድ ብሎ ባለው ኖክ ማደያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት መሆኑን ገልጿል።

በቢሾፍቱ፣ በሞጆ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia