TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንጠንቀቅ!

ዘግናኝ የሆኑ ተንቀሳቀሽ የቪዲዮ ምስሎች በተለያየ ብሄር ሙዚቃዎች እየታጀቡ በማህበራዊ ድረገፆች በስፋት እየተለቀቁ እንደሆነ እየተመለከትን ነው።

እንጠንቀቅ…

ስሜታዊ ሆኖ ሼር ከማድረግ በፊት እነዚህ ምስሎችን በደንብ መመልከት፣ አላማቸው ምን እንደሆነ ማወቅ፣ ከምስሎቹ ጀርባ ለሀገራችን ምን እየታሰበ እንደሆነ መረዳት ሁላችንም ግድ ይለናል።

Via ሸገር ታይምስ መፅሄት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በትምህርት ዘመኑ ከትግራይ ክልል 45 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መዝግበን እያስተማርን ነው!" የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አህመድ ሞሀመድ
.
.
የአማራ ሕዝብ ሰላም ወዳድ እና አቃፊ መሆኑን ከትግራይ ክልል የመጡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናግረዋል።

ህይዎት ሀለፎምና ትርሀስ ገብረ እግዚአብሄር የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት በዩኒቨርሲቲው እና በአካባቢው በነበራቸው ቆይታ ምንም የደኅንነት ስጋት እንዳላጋጠማቸው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

ለተግባር ልምምድ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው እንደነበር የተናገሩት ተማሪዎቹ በቆይታቸው የአማራ ሕዝብ ሰላም ወዳድ እና እንግዳ ተቀባይ መሆኑን እንደታዘቡ ነው ያረጋገጡት፡፡

ከኤርትራ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመጡት ሔርሞን ገዛኢ እና ክብሮም አክሊሉ በእነ ህይዎት ሀሳብ ይስማማሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-3

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመሚለከታችሁ አካላት፦

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 15 ልዪ ስሙ አወሊያ መስጊድ አከባቢ አንድ ጭነት የጫነ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪክ ገመድ በጥሶ ባስከተለው ችግር ምክንያት ከ40 በላይ ቤቶች ከአርብ 7:00 ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል። የአከባቢው ህብረተሰብ ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቅም እስካሁን መፍትሔ ባለማግኘቱ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረገ ይገኛል።

Via Yosef Fikadu/TIKVAH ETH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIGRAY

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የክልሉን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ማንነት በማስተዋወቅ ትልቅ አስተዋፀኦ አበርክተዋል ላላቸው ሶስት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ትናንት የገንዘብ ሽልማትና እውቅና ሰጠ። እውቅና የተሰጣቸው የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የትግራይ ህዝብ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላትና ታሪካዊ ስፍራዎችን በተለያዩ ሚድያዎች በማስተዋወቅ የላቀ ድርሻ የተወጡ መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል።

እንዲሁም የህዝቡ ባህልና ወግ፤ፍቅርና አንድነት የሚገልፁ ባህላዊና ዘመናዊ ዘፈኖችን በማቅረብ አርአያነታቸውን የተወጡ ሲሆን ለእያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ሽልማትና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶአቸዋል።

በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አማካኝነት ትናንት ማምሻውን በዓዲግራት ከተማ በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ እውቅና የተሰጣቸው የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋዜጠኛና ደራሲ ደስታ ካህሳይ፤በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ህመም ምክንያት የአልጋ ቁራኛ የሆነችው ዝነኛዋ የትግርኛ ዘፋኝ ንግስቲ ሐየሎምና የኪነ ጥበብ ባለሙያ የሆነው ታደሰ ደስታ ናቸው።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ፓሪስ በማቅናት ከፈረንሳይ የግሉ ዘርፍ ኮንፌዴሬሽን የአፍሪካ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከባለሃብቶቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የኢቨስትመንት ድባቡን አስመልክቶ የተከናወኑ ማሻሻያዎች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-21-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#METU

የኦሮምያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለጉብኝት ኢሉባቦር ዞን መቱ ከተማ የመጡ ሲሆን መቱ ዪኒቨርሲቲ ግቢ አደራሽ ዉስጥ በመገኘት ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዪ ይገኛሉ።

Via Wonde Tilaye/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል! በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ። ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ…
#RIDE #ZayRide

ራይድ ትራንፖርት የቅርብ ተወዳዳሪው ዛይ ራይድ ታክሲ ላይ አቅርቦት የነበረው ከስያሜ እና ከንግድ ምልክት ባለቤትነት ጋር የተያያዘ አቤቱታ ለክስ የሚያበቃ ምክንያት የለውም በማለት የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ውድቅ አደረገው።

ሁለቱ ተቋማት የትራንስፖርት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተጠቃሚዎችን እና ደንበኞችን በስልክ መተግበሪያዎች በማገናኘት የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሲሆን ከንግድ ስያሜ እና ከባለቤትነት መብት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ወዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባና ዙሩያዋ ሰላም እና ፀጥታ ካለፈው ሳምንት ወዲህ አጠያያቂ ሆኖ ቀጥሏል!

ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በለቡ፣ ጀሞ፣ አስኮ፣ በአቃቂ ክ/ከተማ የተለያዩ አካባዎች፣ ኮየ ፈጬ እና በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተደራጁ ወጣቶች ምክንያት ሰላም ደፍርሷል፤ ህብረተሰቡም ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡

የተደራጁ ወጣቶቹ ከየት መጡ ሳይባል መንገድ ይዘጋሉ፣ የጥላቻ ንግግሮችን በአደባባይ ያስተላልፋሉ፣ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዜጎችን ያስፈራራሉ ንብረትም ያወደሙ እንዳልጠፉ ለማወቅ ችለናል፡፡

በማህበራዊ ድህረገፆች ደግሞ መንገድ በድንጋይ ከመዝጋት ጀምሮ የተለያዩ የድርጅቶች ማስታወቂያዎችን እና አርማዎችን ሲያወርዱ፣መንገድ ዘግተው በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ተመልክተናል፡፡ የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ አካላት ህግ ከማስከበር ይልቅ ቆመው ሲታዘቡ ለማየትም ችለናል፡፡

ጉዳዩ በጊዜ ካልተቀረፈ ስጋቱ ወደ መሀል ከተማ የማይመጣበት ምክንያት የለም እና ቆሞ ከመታዘብ ውጪ የፀጥታ ሀይሎች ህግ እንዲያስከብሩ የየአካባቢው ነዋሪዎች ሀሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ በአዲስ አበባ የተፈጠረው የሰላም እጦት አሁንም ቀጥሏል፤ ይህ ሁሉ ሲፈጠር ለመሆኑ ፖሊስ ቆሞ መታዘቡን ይቀጥላል፣ ወይስ ሰላም ያስከብራል በሚለው ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡

Via Ethio FM/ጋዜጠኛ ትግስት ዘላለም/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስራ ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ለሚያካሂደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ሲሆን በዚሁ ስራ ይረዳ ዘንድ ለአጭር ጊዜ የፕሮጄክት አስተባባሪ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

•የስራ መደቡ መጠሪያ - የፕሮጄክት አስተባባሪ

•የስራ ጊዜው - የአጭር ጊዜ ማስተባበር (21 ቀናት)

የስራ መደቡ ዋና ዋና ሃላፊነቶች፦

-ለሲዳማ ሪፈረንደም አፈጻጸም ፕሮጄክት ስራ የማስተባበር ድጋፍ መስጠት

-ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር የምርጫ ዝግጅቱን እና ሂደቱን ማገዝ

-አስፈላጊ ከሆኑ የተለያዩ አካላት ጋር ግንኙነቶችን ማድረግና ስራዎች በእቅድ መሰረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ

-የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የሚመለከቱ ውይይቶችን እና ሁነቶችን ማዘጋጀት፣ ማስተባበር

-አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከቦርዱ የሚፈለጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መስጠትና በተመሳሳይም ለቦርዱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማጠናከር

-የስራውን ሂደት እና ውጤት አስመልክቶ ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር ሪፓርት ማጠናከር

ተፈላጊ ችሎታ፦

-የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪ

-ቢያንስ ለ5 አመት ያህል የማስተባበር ስራ ልምድ

-የምርጫ እና ተያያዥ ሂደቶችን በሚገባ የሚረዳ/የምትረዳ

-በፍጥነት ችግሮችን የመፍታት ክህሎት ያለው/ያላት

-በአጭር ጊዜ የማስተባበር ስራዎችን የመስራት ልምድ ያለው/ያላት

-መረጃዎችን መሰብሰብና ሪፓርት ማጠናቀር ልምድና ችሎታ ያለው/ያላት

-የፌደራሉን የስራ ቋንቋ በሚገባ መጻፍና መናገር የሚችል/የምትችል፣ (ተጨማሪ ቋንቋ ማወቅ ይበረታታል)
ክፍያ - በስምምነት

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-5
#attention

ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከሰዓታት በፊት የፀጥታ ችግር እንደተፈጠረ በአካባቢው የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል። ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙም እንደሆነ ተናግረዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ትኩረት እንዲጥም አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HPR

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኝ መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፀጥታ ችግሩ መነሻ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የተናገሩት በአካባቢው የሚኖሩ የቤተሰባችን አባላት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሆነ፣ ወጣቶች ተደራጅተውና ዱላ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደተመለከቱ፣ የፀጥታ ሃይሎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር በአካባቢው እንደተሰማሩ፣ የአምቡላንስ ድምፅ በአካባቢው እንደሚሰማ ገልፀዋል።

#video: Hils/የቲክቫህ ቤተሰብ ከቦሌ ቡልቡላ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Addis Abeba Police Commission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በአዲስ አበባ እና ዙርያዋ ስለተከሰቱ ችግሮች ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት የተናገሩት፦ "ምንም ነገር የለም! የሆኑ ሰዎች ኮየ ፈጬ ትናንት ተጣልተው ነበር። በዚህ ምክንያት የተፈጠረ ነገር ነው እንጂ ሌላ የጎላ ነገር የለም። ቦሌ ቡልቡላ ላይ ደግሞ የሆኑ ሰዎች መያዝ፣ አለመያዝ ጉዳይ ነበር። በዛ ምክንያት ጥይት ተተኩሶ ነበር። አቃቂ ግን ምንም የለም!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BoleBulbula "የፖሊስ ኮሚሽኑ መግለጫ #የሚያሳፍር እና ሀላፊነት የጎደለው መግለጫ ነው፡፡ ይኼ ማድበስበስ ማንንም አይጠቅም። ቦሌ ቡል ቡላ ነበርኩ Almost ወደ 4:10 ገደማ ወጣቶቹ መንገድ ዘግተው እየጨፈሩ ቀበሌ ወደሚባለው ቦታ እየሄዱ ነበር።" T/የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከቦሌ ቡልቡላ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦሌ ቡልቡላ...

"ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ነው ያለሁት። አሁን ባንኮች ሁሉ ዝግ ናቸው፤ ትራንስፖርትም የለም። ከሰዓት በፊት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ አልተቀረፈም። ጉዳት የደረሰባቸው የፀጥታ አካላት በአምቡላስ ሲወሰዱም ነበር። አሁን ላይ በአካባቢው የአ/አ ፖሊስ እና ፌደራሎች አሉ።" Dere/ቲክቫህ ቤተሰብ/

PHOTO: MA/ቲክቫህ ቤተሰብ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የቀሪ ዕዳ ጉዳይን በቅርቡ ለመፍታት ስምምነት ላይ ሊደርሱ መሆኑን ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ!

ኢትዮጵያ ያለባትን ቀሪ ዕዳ ጉዳይ በቅርቡ ለመፍታት ሞስኮ ከሀገሪቱ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ማቀዷን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሩሲያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት በሶቪየት ዩኒየን ዘመን የተበደሩትን 20 ቢሊዮን ዶላር ሩሲያ በድህረ ሶቪየት ዘመን እንደሰረዘች የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ይህም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እነዚህን ዕዳዎች የመቋቋም አቅም ስላልነበራቸው ነው ብለዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-21-7

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠየቁ!

በኦሮሚያ ክልል የቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች በአካባቢያቸውን የሚታየውን የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠየቁ። የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግስት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች በልማት በኩል ያሉባቸውን ችግሮች በመገንዘብ ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የቡኖ በደሌ ወረዳ ነዋሪዎች የልማት ጥያቄአቸውን ያቀረቡት ትናንት ከክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የክልሉ መንግስት ያሉባቸውን የልማት ችግሮች    እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-21-6

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba | የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በአዲስ አበባ መሰጠት ተጀመረ፡፡ ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 14 ይቀጥላል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩና እድሜአቸው 14 አመት ለሆናቸው ታዳጊ ሴቶች ክትባቱ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡ ከትምህርት ቤት ውጪ ያሉና በዚሁ የእድሜ ክልል የሚገኙ ታዳጊ ሴቶችን በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በኩል በመለየት ክትባቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ እና አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ረቡዕ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ ይገናኛሉ!

ግብፅ በዚህ ሳምንት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ በሚደረገው ድርድር የውጭ አሸማጋይ ጣልቃ እንዲገባ ግፊት እንደምታደርግ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከነገ በስቲያ ረቡዕ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ በሚጀመረው የሩሲያ እና አፍሪካ ጉባኤ ጎን በጉዳዩ ላይ ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሬውተርስ ዘግቧል።

“በዚህ ስብሰባ በድርድሩ አራተኛ ወገን እንዲሳተፍ ከስምምነት እንደርሳለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ አንድ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ “በሚቀጥሉት ሳምንታት ከአንዳች ቀመር ላይ እንስማማለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

https://telegra.ph/DW-10-21

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ የሚለው የሀገሪቱ መንግስት እንዲህ ያሉ መሰል ትንንሽ የሚመስሉ ያልተገቡ ድርጊቶችን ማስቆም ካልቻለ ሀገሪቱ ወደሌላ ትርምስ ውስጥ ሊትገባ የምትችልበትን በር ይከፍታልና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ። ከሰሞኑን በየአካባቢው የሚስተዋለው ያልተባ ድርጊት ውጤቱ ጥሩ አይመጣም። ሁኔታዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ከሆኑ ሀገሪቱ የማያባራ ቀውስ ውስጥ ዳግም መግባቷ ስለማይቀር ተገቢው ትኩረት እና ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ህዝብ የሚከተላችሁ ሰዎችም እንደዚህ ያለው ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን ለትውልዱ ልታስተምሩ ይገባል። ሁሉም ነገር ሰላምና ሀገር ሲኖር ነው የሚያምረው!

#የቲክቫህ_ቤተሰቦች_መልዕክት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ687 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለፀ!

ባለፈው ሩብ ዓመት ግምታዊ ዋጋቸው 687ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው መካከል የጦር መሳሪያዎች ፣የተለያዩ አገራት ገንዘቦች፣ መድሃኒቶች ፣አደንዛዥ እፆች ፣ምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦች ፣ኤሌክትሮኒክስና ልዩ ልዩ መለዋዎጫ እቃዎች እንዲሁም ልባሽና አዳዲስ ጨርቆች ፣ወደ አገር እንዳይገቡ ክልከላና ገደብ የተደረገባቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ይገኙበታል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-21-9

@tsegabwolde @tikvahethiopia