#መቐለ
የመስቀል ደመራ በዓል በመቀለ ጮምአ ተራራ በሚባል ስፍራ ዛሬ በድምቀት ተከበረ። በበዓሉ ላይ አቡነ ኢሳያስ እንደተናገሩት የመስቀል በዓል የህዝቡ ሰላምና አንድነት የሚሰበክበት እለት ነው፤ በመሆኑም በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በየጊዜው የሚከበሩ ሃይማኖታዊ በአላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ ለሰላምና ልማት ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ዶክተር ደብረጽዮን ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ ከእምነቱ ባለፈ ለአካባቢው ሰላምና እድገት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። “በተለይም የወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በዚህ አመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል። ለዚሁ ዕቅድ ተግባራዊነት ደግሞ ሁሉም የመንግስት ሴክተሮች በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበው አመቱ የሰላምና የልማት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። በበዓሉ ላይ የሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የመቀሌ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና ህዝበ ክርስቲያኑ ተሳታፊ ሆነዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethioia

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የደመራ በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተከብሯል፡፡
https://telegra.ph/ETH-09-27-2
https://telegra.ph/ETH-09-27-2
#ቢሾፍቱ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ደመራ እንዳልተደመረ ገልፀዋል። ለምን? የሚለውን በቦታው የነበሩ የቤተሰባችንን አባላት ያዩትን ተናግረዋል ይቀርባል። የሚመለከታቸውን አካላት ለማናገርም ጥረት እናደርጋለን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ...
"የደመራ በዓል በድሬዳዋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ በሆነና በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት ተከብሯል። የደመራው ስነ ስርዓት ተጠናቆ ምዕመናኑ በጋራ መዝሙሮች እየዘመሩ ወደዬ መኖሪያ አካበቢያቸው አቅንተዋል። በሰላም እንድጠናቀቅ ደፍ ቀና ላሉ አካላት አመስግኑልን። መልካም በዓል!"

ከቢሾፍቱ የአይን እማኝ...
"ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ ስንደርስ ያልተፈቀደ አርማ ያለበትን ልብስ ለብሳችኃል/ይዛችኃል/ በሚል አታልፉም አሉን/የፀጥታ አካላት/። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የለበሱም ነበሩ እሱን እንዲህ ሆነን ማለፍ እንደማንችል ተነገረን። መዘምራንም ጭምር። ይሄን አርማ ይዛችሁ እና ለብሳችሁ ማለፍ አትችሉም አሉን። እዛው የነበርነው ሰዎች እንደዛ ከሆነ እዛው ኪዳነ ምህረት እናበራለን ብለን ተመለስን። ወደኪዳነ ምህረት ስንመለስ ወደአዳባባይ የሄዱት ሰዎች አንድ ደብር ጎሎ #አናበራም ብለው ሁሉም ተሰብስቦ ወደ ኪዳነ ምህረት እየተመለሰ ነበር #አደባባይ ያለውን ሳያበሩ ቀርተው። ግማሹ ኪዳነ ምህረት ከሄደ በኃላ እላይ ያለውን ወደታች እንዳይወርድ ታች ያለውን ወደ ላይ እንዳይወጣ ከለከሉ። ሰዎች ወደቤት አንሄድም አሉ። ሰዎችን አሳምነውም ወደአደባባይ ለመውሰድ እና ደመራው እንዲበራ ለማድረግ ጥረት አድርገው ነበር ግን ሰው አልተስማማ። እየዘመርን ወደቤታች እንመለሳለን ብሎ እኛ ወደቤታችን ሄደናል።"
ቢሾፍቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር አልተሳካም። #BISHOFTU #ቢሾፍቱ

#UPDATE የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የደመራ በዓል በሰላም መከበሩን አስታወቀ፡፡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የኃይማኖቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ጎብኝዎች የታደሙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር
የመስቀል በዓል ዘር፣ ቋንቋና ሃይማኖት ሳይለዩን በጋራ ተግባብተን መኖርን የተማርንበት ዕለት በመሆኑ በድምቀትና ታላቅ ኩራት ልናከብረው ይገባል ሲሉ የባህርዳር ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ አብርሃም ገለጹ።
በየዓመቱ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓልን አስመልክቶ የሚካሄደው የደመራ ስነ-ስርዓት በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናንና የውጭ አገራት ቱሪስቶች በተገኙበት በባህርዳርና በሌሎች ከተሞችም በድምቀት ተከብሯል።
አቡነ አብርሃም በበዓሉ ላይ ለምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት ወቅቱ የመስቀሉ ባለቤት የሆኑ ክርስቲያኖች ፈተና የበዛበት በመሆኑ ይህን አስከፊ ጊዜ በትዕግስት ዕንጂ ጥፋትን በጥፋት በመመለስ መሆን እንደማይገባው ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-27-3

#update በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ትግበራ ይገባል። ትራንስፎርሜሽኑን በሚመለከትም የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም ለኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኪራይ ቤት ይኖሩ የነበሩት የቶምቦላ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ አሸናፊ የቤት ቁልፋቸውን ተረከቡ!
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለ2011 ዓ.ም ያዘጋጀውን የቶምቦላ ሎተሪ ለአዲስበ አበባ ከተማ ነዋሪ ለሆኑት አቶ በቀለ ካሳ ወጥቷል፡፡ዕድለኛው በመንግስት ኪራይ ቤቶች ተከራይተው ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩ ሲሆን ዘ-ሉሲ በሚባለው የታክሲ ማህበር የትራንስፖርት አገለግሎት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዕድለኛው ገና በ27 አመት እድሜቸው ሎተሪን በመቁረጥ እንደጀመሩ የተናገሩ ሲሆን በ25 ብር በገዟት የቶምቦላ ሎተሪ ቲኬት አሸናፊ ሆነው ባለ 3 መኝታ አፓርታማ የመኖሪያ ቤት ከሙሉ የቤት ዕቃው ጋር ተሸልመዋል፡፡
Via የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር

ድሬዳዋ⬆️በዛሬው ዕለት #በድሬዳዋ_ከተማ በነበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለክርስቲያን ወንድምና እህቶቻቸው ውሃ ሲያቀርቡ ነበር።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ!
በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ። መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።
ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች 'የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል'፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም' የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል። አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ። በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።
Via #BBC

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
"ፌስቡክ ላይ የሚለቀቁ አሉባልታዎችና ወቀሳዎች ስራዬ ብሎ የሚከታተል ሰው አዕምሮው ቀስ በቀስ የመፍጠር አቅሙን እያጣ ይመጣል አብዛኞቹ ዜናዎቻችን ተስፋ የሚያስቆርጡ ናቸው። አንድ ሰው ለ30 ደቂቃ ያህል ዜና ሲያይ ካመሸ እንቅልፉ ሰላማዊ አይሆንም። ይደብረዋል፤ ይህ ሂደት ሲደጋገም ቀስ በቀስም ተስፋ ወደ መቁረጥ ይሄዳል።" ዳዊት ድሪምስ የአስተሳሰብ ለውጥ ባለሙያ | #EPA
እጅግ የምናከብራችሁ እና የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን ሀሳቡ እንዴት አገኛችሁት? #TIKVAH_ETHIOPIA
✅ትክክል
❌ትክክል አይደለም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እጅግ የምናከብራችሁ እና የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን ሀሳቡ እንዴት አገኛችሁት? #TIKVAH_ETHIOPIA
✅ትክክል
❌ትክክል አይደለም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውጤታችሁና ምደባችሁ ይፋ ተድርጓል - ASTU & AASTU!
ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ይፋ ተደርጓል። በዚህ https://portal.neaea.gov.et/Home/Student ድረገፅ በመግባት የመፈተኛ ቁጥራችሁ እያስገባችሁ ውጤታችሁን እንዲሁም በየትኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደባችሁ መመልከት ትችላላችሁ።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ይፋ ተደርጓል። በዚህ https://portal.neaea.gov.et/Home/Student ድረገፅ በመግባት የመፈተኛ ቁጥራችሁ እያስገባችሁ ውጤታችሁን እንዲሁም በየትኛው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደባችሁ መመልከት ትችላላችሁ።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ASTU & AASTU ትናንት ምሽቱን ተማሪዎች ውጤታቸው እየተመለከቱ እንደነበር በእኛ በኩል በርከት ያሉ ተማሪዎችን ውጤት እና ምደባ ለማየት ብንችልም ዌብሳይቱ ከለሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ እየሰራ እንዳልሆነ ተመልክተናል። የተፈጠረውን ለማጣራት ጥረት እናደርጋለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት እና የበረከት ይሁንላችሁ!
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GONDAR
የመስቀል ደመራ በዓል በጎንደር ከተማ መከበር ጀምሯል፡፡ ጧት ላይ በየቤቱ የተጀመረው የደመራ መለኮስ ሥነ ስርዓት ረፋድ ላይ ደግሞ በመስቀል አደባባይ በድምቀት በከተማ ደረጃ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል፡፡
Via #AMMA

#SEKOTA
በሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና በጎንደር አካባቢዎች የደመራ በዓል በመስቀል ዕለት ነው የሚከወነው፡፡ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ዛሬ የደመራ መለኮስ መርሀ ግብር እየተካደ ነው፡፡

#DOHA
ሁሉም አትሌቶቻችን ውድድር ሲያቋርጡ፤ ሮዛ ህመም አጋጥሟት ሆስፒታል ተወስዳለች!
መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁሉም አቋርጠዋል፡፡
አንደኛዋ ተወዳዳሪ ሮዛ ደምሴ ህመም ያጋጠማትና ሙቀቱን ልትቋቋም ባለመቻሏ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች፡፡ ሮዛን ተከትላ ያቋረጠችው ደግሞ ሩቲ አጋ ስትሆን መጀመሪያ አካባቢ የነበራት አቅምና ፊቷ ላይ ይነበብ የነበረው የውድድር መንፈስ በጣም ጥሩ ቢሆንም ከ15 ኪ.ሜ በኋላ ግን መቀጠል አልቻለችም ሲል ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
ሙቀቱን በከፍተኛ እልህ ለመቋቋም የሞከረችው ሶስተኛዋ ተወዳዳሪ ሹሬ ደምሴም ከነ ሩቲ በኋላ አቋርጣለች፡፡ በእለቱ የነበረው ሙቀት መጠን 32 እና ከዚያ በላይ ዲግሪ ሴንቲግሬድ መድረሱ ተገልጿል፡፡
Via #EPA
PHOTO: #AryatRyan

ሰራተኞች በመገደላቸው ፋብሪካው ስራ እንዳቆም ተሰምቷል!
በኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ ላይ በተገነቡት ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት ሰራተኞች በስራ ላይ እያሉ መገደላቸውና ሰራተኞች የፀጥታ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ፋብሪካው ስራ እንዳቆመ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሰራተኞች ማህበር አስታወቀ።
በአካባቢው ላይ ያለው የእርስ በእርስ ግጭትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋሻው አይችልሁም ተናግረዋል።
የስኳር ኮርፖሬሽን መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር ጋዲሳ ደሳለኝ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በፋብሪካ ሰራተኞች ላይ የሚፈፅሙት የግድያ ጥቃት እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል። እንደ ሊቀ መንበሩ ገለፃ ታጣቂዎቹ ሰሞኑን ብቻ በተከታታይ በፈፀሙት ጥቃት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሹፌርን ጨምሮ በሸንኮራ ማሳ ላይ የተሰማሩ በርካታ ወዛደሮች ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል ሲሉ ገልፀዋል። ለዚህም ግጭት መነሻ የሆነው የአካባቢው አርብቶ አደሮች አርስ በእርስ በመጋጨታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
በወቅቱ በፋብሪካው ለሚሰሩ ሰራተኞች ምግብ የሚመጣው ከጂንካ ከተማ ቢሆንም በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በርካታ ሰራተኞች ስራቸውን ለቀዋል።
ምንጭ፦ መሰረት አበጀ/Addis Maleda/

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል ሲያደርገ የቆየውን ዝግጅት አጠናቆ ተማሪዎችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችም ትላንት መስከረም 16/2012 ዓ.ም የተማሪዎቹን አገልግሎት መስጫ ማዕከላት (የተማሪዎች ማደሪያ፣ መመገቢያ አዳራሾችን እና የመዝናኛ ቦታዎችን) ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱም የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች እና የተቋማት ዳይሬክተሮች ተማሪዎቻቸው የሚያርፉባቸውን ማደሪያ ክፍሎችና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተማሪዎቹን መግባት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ