TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SEKOTA

በሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና በጎንደር አካባቢዎች የደመራ በዓል በመስቀል ዕለት ነው የሚከወነው፡፡ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ዛሬ የደመራ መለኮስ መርሀ ግብር እየተካደ ነው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Sekota

" ችግሩ እልባት የሚያገኘው ወደ ቀያችን ስንመለስ ብቻ ነው " - ተፈናቃዮች

በሰቆጣ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የፃግብጂ ወረዳ ተፈናቃዮች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እየደረሰ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ተፈናቃዮች ህፃናትና እናቶች በመጠለያ ችግር ለበሽታ እየተጋለጡ መሆኑን በመግለፅ የመጠለያ ችግር እንዲቀረፍ ፣ የህክምና አገልግሎት እንዲመቻች ከምንም በላይ ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ቀን ሩቅ እንዳይሆን ሲሉ ነው ጥይቄ ያቀረቡት።

" የተጋረጠብን ችግር ወቅቱ ያመጣው ቢሆንም ችግሩ እልባት የሚያገኘው ደግሞ ወደ ቀያችን ስንመለስ ብቻ ነው " ሲሉም ገልፀዋል።

" የፀጥታ ሀይሉ ፃግብጂን ነፃ ሊያወጣ ይገባል። " ያሉት ተፈናቃዮች " ይህ ካልሆነ የተፈናቃዮች ቁጥር አሁን ካለው ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ህዝቡን ለከፋ ርሃብና ችግር ይዳርጋል " ብለዋል።

የፃግብጂ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የት/ት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ደሳለኝ ተፈናቃዮቹ ባነሱት ጥያቄ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኃላፊው፥ " የእናንተ ጥያቄ የኛም ጥያቄ ነው። በተለይ የፃግብጂ ህዝብ ወደ አካባቢው እንዲመለስና ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖር ደጋግመን ጠይቀናል። የፃግብጂን ህዝብ ጥያቄ ችላ ያልንበት አግባብ የለም " ብለዋል።

ከመጠለያ ችግር ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ የመጠለያ ችግር እንዲፈታ የክልሉን መንግስት የጠየቅን ሲሆን የመጠለያ ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

ለተፈናቃዮች የመጣን ማንኛውም ዓይነት ድጋፍ ያለአግባብ የተጠቀመ አካል ካለ ህዝቡ እንዲጠቁምና ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረው እስከ አሁን 11 ሺ 136 ተፈናቃዮች ድጋፍ እንደሚሹ ለክልልና ፌደራል መንግስት ማሳወቃቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Sekota📍

በሰቆጣ ከተማ እንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ጥብቅ ውሳኔዎች ተላለፉ።

የሰቆጣ ከተማ የጸጥታ ም/ቤት ከከተማው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈ ሲሆን ፤ ከውሳኔዎቹ መካከልም ፦

➡️ የትኛውም ተሽከርካሪ ከተፈቀደለት እና ስምሪት ከተሰጠው ውጭ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11:30 መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

➡️ ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ እና ከንጋቱ 11:30 በፊት ከተፈቀደለት አካል ውጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

➡️ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ስምሪት ከተፈቀደለት የጸጥታ አካል ውጭ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

➡️ የጸጥታ መዋቅሩ በሚያከናውኗቸው ህግን የማስከበር ስራዎች ተባባሪ የማይሆን ለማደናቀፍ የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

➡️ ከከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ አካላት ውጭ የመንግስትም ሆነ የግል ታጣቂዎች በከተማዋ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

➡️ መጠጥ ቤቶች ፣ ግሮሰሪዎች የትኛውም የመዝናኛ ድርጅት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።

➡️ በከተማው በ4ቱ ቀበሌ በህገ ወጥ የመሬት ወረራየተሳተፉ እስከ 12/09/2014 ዓ/ም ድረስ እራሳቸው አፍርሰው እንዲቆዩ ይህን ካልሆነ የጸጥታ መዋቅሩ እርምጃ ይወስዳል።

➡️ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት፣ የግለሰቦችን ሰብዕና የሚያጎድፍ እንዲሁም የጸጥታ መዋቅሩን ስም ማጠልሸት ተከልክለዋል ... የሚሉት ይገኙበታል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia