TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AAWSA

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለመስቀል በዓል የውሃ ችግር አይኖርም ብሏል። ባለሰልጣኑ የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢፈጠር አፋጣኝ መልስ ለመስጠት በ16 ውሃ ማጠራቀሚያዎች ውሃ ማከማቸቱን አስታውቋል።

ይህንኑ የዝግጅት ስራ ንፋስ ስልክ፣ አራዳ፣ መካኒሳ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኙ 16 የእሳትና ድንገተኛ ግብዓት ማከማቻዎች በአግባቡ መስራታቸውን ፈትሼ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ ቅርንጫፎቹም ደመራው በሚለኮስበት መስቀል አደባባይ በአንድ ኪ.ሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እና ችግሩ ቢከሰት በፍጥነት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት በሚያስችል ፍጥነት ተደራሽ የሚሆኑ ናቸው፡፡

በዕለቱ በ16ቱም ማጠራቀሚያ ጣቢያዎች ውሃ አቅርቦቱ እንዳይስተጓጎል ብሎም የተሻለ ግፊት እንዲኖረው የሚቆጣጠር ኮሚቴ መቋቋሙንም አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ ባደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ ሦስት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ማጠራቀሚያዎችን ጠግኖ ለስራ ዝግጁ አድርጊያለሁ ብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAWSA

አዲስ አባባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን “ውኃ በተሽከርካሪ እናቀርባለን“ የሚሉ ግለሰቦችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንፁህ የመጠጥ ውኃ አምርቶ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት የአገልግሎት ክፍያ እንደሚሰበስብ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ስልጣን ያልተሰጣቸው ግለሰቦች “ውኃ እናቀርባለን” በሚል ጥራቱ ያልተጠበቀ እና ከየት እንደተቀዳ የማይታወቅ የውኃ ሽያጭ እያካሄዱ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ህብረተሰቡም ከባለስልጣኑ ዕውቅና ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ውኃ የጥራት ደረጃው ያልተረጋገጠ ከመሆኑም ባለፈ ለጤና ጠንቅ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ ያለፍቃድ ውሃ በመሸጥ ላይ የተሰማሩ አካላትም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን ማሳሰቢያ በቸልታ ያለፈ እና በተግባሩ የቀጠለን ግለሰብ በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethioia
#AAWSA

በቀን 40 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚያመርተው የለገዳዲ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት ከትናንት ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቦሌ አራብሳ፣ ቦሌ አያት (1፣ 2፣ 3፣ እና 4)፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ አያት፣ የካ አባዶ፣ የካ ጣፎ እና ኮተቤ ገብርዔል አካባቢ ላሉ ደንበኞቹ ውሃ ማሰራጨት አለመቻሉን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት መሪ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

የኢ/ኤ/ አ ለተፈጠረው የትራንስፎርመር ችግር መፍትሄ ለመስጠት እየሰራሁ ነው ቢልም እስካሁን ለችግሩ እልባት መስጠት አለመቻሉን የተናገሩት ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ በዚህ ወር በተደጋጋሚ የተከሰተ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAWSA

አዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውኃ አገልግሎት መቋረጡን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።

በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ ምክንያት 700 ሚሊሜትር ስፋት ያለው የውሃ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ ነው ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት የተቋረጠው።

የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ግንባታን እያከናወነ ያለው የቻይናው #ሲሲሲሲ ስራ ተቋራጭ ለውሃ መስመሩ ጥንቃቄ ሳያደርግ የግንባታ ስራ ሲያከናውን ነው ውሃ በሚያስተላልፈው የውኃ መስመር ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

በዚህም ጋንዲ ሆስፒታል ፣ አምባሳደር አካባቢ ፣ ቦሌ ሮድ እስከ ደንበል በአጠቃላይ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት ተቋርጣል፡፡

መስመሩን ጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጾ ደንበኞች በትግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT