TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ለወላጆቻቸዉ አዲስ ያወጣዉ ደንብ ባለሙያዎችን እያከራከረ ነዉ!

የየሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ለወላጆቻቸዉ አዲስ ያወጣዉ ደንብ ባለሙያዎችን እያከራከረ ነዉ። የሳይንስና የከፍተኛ ትምሕርት ሚንስቴር «የተማሪዎች፣ የወላጆችና የትምሕርት ፅፈት ቤቶች ዉል» ያለዉ ደንብ የመማር ማስተማሩን ሒደት ከተጠያቂነት ጋር ለማያያዝ ያለመ እንደሆነ አስታዉቆ ነበር።

በመማር ማስተማር ሒደት ላይ ጥናት የሚያደርጉ ሙሕራን  ግን ደንቡ በልጆችና ወላጆች መሐል አለመተማመንን የሚፈጥር፣ አጠራጣሪና ግልፅነት የጎደለዉ በማለት ደንቡን ነቅፈዉታል። ሌሎች ምሁራን ግን ደንቡ በየዩኒቨርቲዎቹ የሚነሱ የጎሳ ግጭቶችና ሁከቶች መንግስትን እንዳሳሰቡት ጠቋሚ ነዉ ይላሉ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DV2021 🛫 የ2021 ዲቪ ሎተሪ ምዝገባ በፈረጆቹ ጥቅምት 2 ይጀምራል ህዳር 5 ከምሽቱ 8 ሰዓት ላይ ምዝገባው ይጠናቀቃል፡፡ ማመልከቻው በዚህ ድረገፅ ብቻ ነው https://dvlottery.state.gov/ መቅረብ አለበት። ማንኛውም አይነት የወረቀት ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም ተብሏል። የDV ሎተሪ ምዝገባን በተመለከተ በዚህ ዓመት የፖሊሲ ለውጥ እንደተደረገ የተነገረ ሲሆን ዲቪ 2021 ለማመልከት ትክክለኛ እና ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖርዎት ይገባል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎች እና መመሪያዎች በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👉https://bit.ly/2lHBngk

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ74 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቷ በአማርኛ ባደረጉት ንግግራቸው በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት በበርካታ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝደንቷ በ74ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር አንኳር የሆኑትን ነጥቦች በዚህ ማንበብ ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-09-26-6

ጥሩ የኤንተርኔት ግንኙነት ካላችሁ ደግሞ በዚህ የዩትዩብ አድራሻ ገብታችሁ የፕሬዘደንቷን ሙሉ ንግግር ማድመጥ ትችላላችሁ👇
https://youtu.be/eTeYouXvOw0
አርቲስት አቡሽ ዘለቀ በሐሰተኛ የፌስቡክ አካውንት መልካም ስሙ እየጎደፈ መሆኑን አስታወቀ!

አርቲስት አቡሽ ዘለቀ በሐሰተኛ ፌስቡክ መልካም ስምና ዝናውን የሚጎዳ መረጃ እየተለቀቀበት መሆኑን ለድሬቲዩብ አስታወቀ፡፡ አርቲስቱ የፌስቡክ ተጠቃሚ መሆኑን ገልጾ በራሱ ስም (Abush Zeleke) በሚል 37 ሺ ገደማ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገጽ በተጨማሪም 23 ሺ ተከታይ ያለው የላይክ ፔጅ እንዳለው ጠቅሶ፤ ሐሰተኛው ግን በቁቤ የተፃፈ (Abbush zallaqaa) የሚል ስም የያዘ ነው ብሏል፡፡

አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክትም "የጥበብ አፍቃሪያንና አድናቂዎቹ (Abbush zallaqaa) የሚል ሐሰተኛ አካውንት ከ98 ሺ በላይ ላይክ እንዳለው እና በእኔ ስምና ፎቶግራፍ በመጠቀም የሚጽፈውም ሕዝብና ሕዝብን የሚያጋጭ እና እኔን ጨርሶ የማይገልጽ መሆኑ ይታወቅልኝ" ብሏል፡፡

Via DireTube
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

መንግስት በቅርቡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ላነሳቻቸው ጥያቄዎች ከፍተኛ ትኩረትና አፅንዖት በመስጠት ከአስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በሰላማዊ መንገድ በፌደራልና በክልል አውንታዊ ምላሽ መስጠት ጀምሯል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት ጉዳዩ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ባለበት በዚህ ወቅት የቤተ-ክርስቲያን ጥያቄን ሽፋን በማድረግ አንዳንድ አካላት ጥያቄውን መስመር በማሳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማሳሳትና የእምነቱ ወግና ስርዓት ከሚፈቅደው ውጪ ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ ለማስኬድ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳለ ፖሊስ ደርሶበታል፡፡

በተጨማሪም የሃገራችን ወጣቶች የደመራ በዓል ለማክበር በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ ምዕመናኑ ሲሄዱ በሰላም ወደ ክብረ በዓሉ እንዲደርሱና የደመራ በዓሉ በሰላምና በደስታ እንዲያከብሩና አምላካቸውን የሚያመሰግኑበትን ተግባራት ሲፈፅሙ የሚታወቁበት እንጂ የተለያዩ አጀንዳዎች የሚያሰሙበት እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባገኘው መረጃ መሰረት በዓሉ በሰላም እንዳይጠናቀቅ የተለያዩ የግል አጀንዳዎችን አንግበው የበዓሉን ስነ-ስርዓት #ለማወክ የተዘጋጁ ሃይሎች እንዳሉ ደርሶበታል፡፡

በዚሁ መሰረት ከበዓሉ ስነ-ስርዓት ውጪ፣ ግጭት ቀስቃሽ ፅሁፎች፣ አንዱን የሚያሞግስ ሌላውን የሚያንቆሽሽ ፅሁፍ፣ ብዙሀነታችንን የማይገልፁ ፅሁፎች በማንኛውም መንገድ ይዞ መገኘት ፣ በህገ መንግስቱ ከተፈቀደው ሰንደቅ ዓላማ ውጪ እና የተለያዩ አርማዎችን ይዞ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ መምጣት የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስታውቃል።

ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሌላ በኩል...

በአዲስ አበባና በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት የነበራቸው የአልሸባብና አይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድኖች አባላት በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስመልክቶ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የፀጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተከትሎ የሽብር ቡድኖቹን ያስከፋቸው በመሆኑ አሁንም አፀፋዊ የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አመቺውን ሁኔታ ሁሉ ለመጠቀም እንደሚፈልጉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚሁ መሰረት በያላችሁበት አካባቢ በዓሉን ስታከብሩ የተለየ እንቅስቃሴ ስትመለከቱ በአካባቢው ላሉ የፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብራችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የኢትዮጲያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dire Dawa Administration Police Commission

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሚከበረው የደመራ እና መስቀል በዓል አስመልከቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርጎ ቅድመ ዝግጀቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡ የተለየ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲገጥመው በተለመደው የስልክ ቁጥሮች መረጃ እንዲያደርሱት ለህ/ቡ መልእክቱን አስተላልፎል፡፡

የፖሊስ የመረጃ ስልክ ቁጥሮች፦

•ፖሊስ ኮሚሽን 025 111-16-00/ 025 111-52-11
•መልካ ጀብዱ ፖ/ጣቢያ 025116-01-76
•ሳቢያን ----------------- 025-111-39-57
•ጎሮ------------------- 025-111-70-15
•ሀሎሌ/ጀርባ/--------- 025-211-23-24
•ከዚራ----------------- 025-111-17-13
•ገንደ ቆሬ------------- 025-111-15-36
•አዲስ ከተማ--------- 025-111-16-20
•መጋላ -------------------025-111-05-97
•አፈተ-ኢሳ------------- 025-111-17-96
•ለገሀሬ---------------- 025-112-61-10
•ፖሊስ መሬት----------025-112-60-35

Dire Dawa Administration Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በድሬዳዋ በሚገኙ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ሃሳብ አመንጪነት የደመራ በዓል የሚከበርበት የለገሃር አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች ተፀድቷል። የፅዳት ዘመቻው ሰሞኑን በድሬዳዋ ተከስቶ የነበረውን ግጭትና ውጥረት ለማርገብ ተምሳሌት የሆነ ነው ተብሏል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Vacancy at Ethio telecom!

Click the respective links to apply for the job openings below before the closing dates.

Graphics Design Specialist: https://bit.ly/2mBoa94
Band Management Specialist: https://bit.ly/2mD7M7Y
POS Engineer: https://bit.ly/2lvymQr
#አርሲ_ሮቤ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ሮቤ ከተማ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በተከሰተው የሰላም ችግር ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት ተካሂዷል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተፈጠረው የሰላም ችግር የሃይማኖት አይደለም ብለዋል።

ከዚህ በፊትም ከአሁንም፤ ከዚህ በኃላም እኛ አንድላይ ነው የምንኖረው፤ ስለዚህ እምነትን ምክንያት በማድረግ የፖለቲካ አመለካከትን ሲያንፀባርቁ የነበሩ አካላት በህግ ይጠየቁልን ሲሉ ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ የተገኙት የODP ሃላፊ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ የተካሄደውና የተፈፀመው ነገር ሆን ተብሎ እንደሆነና፤ በዓሉን የሚያከብሩ ሰዎች ህጋዊ ባንዲራዎችን በመጠቀም በዓሉን ማክበር እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ውጪ ግን ሌሎች ያልተፈቀዱ እና እውቅና የሌላቸው ባንዲራዎችን መጠቀም ተገቢ አይደለም የተከለከለም ነው ሲሉ አሳስበዋል። እምነትን ተገን አድርገው የማህበረሰቡን ሰላም የሚበጠብጡ አካላትን ለህግ እናቀርባለን ብለዋል የODP ተወካዩ። የኦሮሞ ህዝብም ከብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለውን ሰላም እንዲጠብቅም መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ እምነት ተከታዮች ጋር በመሆን መስቀል አደባባይን አፀዱ። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ የከተማ ነዋሪዎች በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ እንዲያፀዱ ምክትል ከንቲባው ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል አንዳንድ ከተሞች በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ያለአግባብ የተያዙ መሬቶችን በመያዝ ማስመለስ መቻሉን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችንና መሬቶችን ማስመለሱን ቢሮው ገልጿል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዘርፉ በህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ የነበነራቸውን አመራሮችና ሠራተኞች ላይም እርምጃ መውሰዱን ቢሮው በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2012 የስራ ዘመን የዕቅድ ዝግጅት የግምገማ መድረክ ላይ ገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ የሚዘጉ መንገዶች!

በአዲስ አበባ ለደመራ በዓል አከባበር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች፦ ዛሬ በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከረፋዱ 4 ሰአት ጀምሮ ተከታዮቹ መንገዶች ዝግ ይሆናሉ፦

• ከኦሎፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአምባሳደር ቲያትር ቤት ወደ መስቀል አደባባይ

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ፣ 6727 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚስን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA በጅማ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሰከረም 17 የመስቀል ክብረ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ ዛሬ በማፅዳት ዝግጁ አደረጉ። በከተማው በዓሉ በሚከበርበት “ሚኒ ሁለገብ ስታዲየም” በተካሄደው የጽዳት ሥራ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላትና የወጣት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለጊፋታ እሮጣለሁ " በሚል የተዘጋጀ እሩጫ በወላይታ ከተማ ተካሄደ!

የወላይተ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለጊፋታ እሮጣለሁ በሚል የተዘገጀ የ3ኪሎ ሚትር እሩጫ ውድድር ተካሄዷል። ሩጫውን ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩንቤ እና የዞኑ ባህል ቱሪዝምና እስፖርት መምሪያ ኅላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን ሲሆኑ፤ በሩጫውም በርካታ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ

የወላይታን የዘመን መለዋጫ የጊፋታ በዓል #በዩኔስኮ የማስመዝገብ ጥረት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደገለጹት፤ የጊፋታን በዓል በዩኔስኮ የማስመዝገብ እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ ነው ብለዋል፡፡ ከመስከረም 14 እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረው የወላይታ ዘመን መለዋጫ ትርጓሜ ታላቅና የመጀመሪያ ማለት እንደመሆኑ በበዓሉ ያለውን እውነታ በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረውን ጥረት ከፍ እንደሚያደርገው አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#AAWSA

አዲስ አባባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን “ውኃ በተሽከርካሪ እናቀርባለን“ የሚሉ ግለሰቦችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንፁህ የመጠጥ ውኃ አምርቶ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት የአገልግሎት ክፍያ እንደሚሰበስብ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ስልጣን ያልተሰጣቸው ግለሰቦች “ውኃ እናቀርባለን” በሚል ጥራቱ ያልተጠበቀ እና ከየት እንደተቀዳ የማይታወቅ የውኃ ሽያጭ እያካሄዱ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ህብረተሰቡም ከባለስልጣኑ ዕውቅና ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ውኃ የጥራት ደረጃው ያልተረጋገጠ ከመሆኑም ባለፈ ለጤና ጠንቅ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ ያለፍቃድ ውሃ በመሸጥ ላይ የተሰማሩ አካላትም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን ማሳሰቢያ በቸልታ ያለፈ እና በተግባሩ የቀጠለን ግለሰብ በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethioia
#HARAR የደመራና የመስቀል በዓል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#update የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ተሰጠ። ማብራሪያውን የሰጡት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ናቸው፡፡

https://telegra.ph/TIKVAH-09-27

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethioia
#DEBRE_MARKOS

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን የንጉሥ ተክለሃይማኖት አደባባይ አካባቢን አፅድተዋል።

በበጎ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethioia