TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎርብስ አፍሪካ በመስከረም እትሙ ኢትዮጵያ ላይ አተኩሯል!

ፎርብስ አፍሪካ በመስከረም እትሙ ኢትዮጵያ ላይ አተኩሮ "ኢትዮጵያ- የአፍሪካ ኩራት" በሚል አብይ ርእስ ሰፋ ያሉ ዘገባዎችን ይዞ ወጥቷል። መጽሄቱ በዚህ እትሙም ከኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ዶ/ር ይናገር እና ወ/ሮ ዳግማዊት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅን ይዟል። በተጨማሪም ሌሎች ሚኒስትሮችና የተቋማት ሃላፊዎችን አነጋግሮ ዘርዘር ያለ ዘገባን አካቷል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
3 ሰዎች በወንዝ ውሃ ተወስደው ህይወታቸው አለፈ!

በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ሶስት ሰዎች የየኪ በተባለው የወንዝ ውሃ ተወስደው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የሰዎቹ ህይወት ያለፈው ከሚዛን አማን ከተማ ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ ሞልቶ በነበረው ወንዝ ለመሻገር ሲሞክሩ ከመሸጋገሪያው ድልድይ ጋር አብረው በመወሰዳቸው ነው፡፡

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ኢንተለጀንስ ስራ ሂደት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ውብሸት ካሳ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ነሐሴ 27/2011ዓ.ም ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ነው። በዚህም ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች ናቸው።

የሟቾቹ አስከሬንም ትናንት በፍለጋ መገኘቱንና በሚዛን ቴፒ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎ ቤተሰብ እንዲረከብ መደረጉን ኢንስፔክተር ውብሸት አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እስካሁን ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል። #ደቡብ_አፍሪካ #SouthAfrica
ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል!

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚነስቴር አስታወቀ፡፡ የአውሮፕላን ነዳጅ በነሐሴ ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 25.16 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 40 ሳንቲም በመጨመር በሊትር ብር 25.56 እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ!

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የ2011 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ፡፡

በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው አለመረጋጋት ለፈተና ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል በርካታ ተማሪዎች ያቋረጡ ቢኖርም በአሁን ጊዜ በመደበኛ፣ በማታና በግል በአጠቃላይ 340 ሺህ 85 ከተመዘገበው 331 ሺህ በፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከተመቀመጡት ውስጥ 70 በመቶ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃለፊ አቶ ተሰማ ዲማ ገልፀዋል፡፡
የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ በጥሬ ማርክ ለወንዶች 45 ለሴቶች 43 እና ለዓይነ ስውራን 40 እንዲሆን በተደረገው ውሳኔ በክልሉ በመደበኛ፣ በማታ እና በግል በአጠቃላይ ፈተና ላይ ከተቀመጡት 331 ሺህ ተማሪዎች ወስጥ 230 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደሚቀጥለው 9ኛ ክፍል ማለፋቸውንም ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!! ETHIO-FM 107.8 -- 2ኛ አመት!!
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ፈተናዎች ብቻ ይወሰናል ተባለ!

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት የሚወሰነው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ፈተናዎች ብቻ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በ12ኛ ክፍል ፈተና እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተሰጡ ፈተናዎች ብቻ ይወሰናል ተብሏል። በዚህም እንግሊዝኛ፣ አፕቲቲውድ፣ ሂሳብ፣ ጂኦግራፊ እና ፊዚክስ ውጤቶች የተማሪዎቹን መግቢያ ይወስናሉ ተብሏል። ይህ የሆነው ደግሞ በቀሪዎቹ ሁለት ቀናት የተሰጡት ፈተናዎች የውጤት መጋሸብ ስለታየባቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ምንጭ፦ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት ዓይነቶች ውጤት ብቻ ይወሰናል።

የትምህርት ዓይነቶች፦

•እንግሊዝኛ፣
•ሒሳብ፣
•አፕቲቲዩድ እና ፊዚክስ በተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም ጂኦግራፊን ጨምሮ በማህበራዊ ሳይንስ ነው የተወሰነው።

ይህ የተደረገው በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የውጤት #ግሽበት በመታየቱ ነው! በቀጣይ ደግሞ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይወሰናል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነታሪኩ ለማ ላይ የዋስትና እግዱን አጸና!

#የደቡብ_ክልል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የዋስትና እግድ እንዲጸና ወሰነ። የስር ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪዎቹ የፈቀደውን የ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲታገድ የጠየቀው ጉዳያቸውን እየመረመረ የሚገኘው ፖሊስ ነው።

በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች እጃቸው አለበት በሚል በእስር ላይ የሚገኙ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችን ዋስትና ፈቅዶ የነበረው የሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር። መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብትን የሚከለክል ከመሆኑም በላይ «በዋስ ከወጡ መረጃዎችን ሊያጠፉ፣ ምስክሮችን ሊያባብሉ ይችላሉ» በማለት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእግድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወቃል።

https://telegra.ph/ETH-09-04
የፓለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ያቀረቡበት የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች ህግ አስፈላጊው ውይይት እንደተካሄደበት ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ቡርቱካን ሜዴቅሳ ጉዳዩን አስመልክተው በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

https://telegra.ph/ETH-09-04-2
ተማሪዎች ሲያቀርቡት ለነበረው ቅሬታ ከተሰጣቸው መልሶች መካከል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤትን የተመለከተ መግለጫ!

የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ምክትል ዳይሬክተሮች ዶ/ር ዘሪሁን ዱሬሳ እና አቶ መሳይ ደምሴ፣ እንዲሁም የየክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ጋረደው የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ይልቃል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተከታታይ #ውጤቱን በተመለከተ በጋራ በተላለፈው #ውሳኔ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁም መሰረት በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያጋጠመ ችግር መኖሩን በተለይ በደንብ ጥሰት ዙሪያ #በማረጋገጫ የተያዘባቸው ተማሪዎች ውጤት መሰረዙ እና በደንብ ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በየደረጃው ተጠያቂ የሆኑበት ሁኔታን እንዳለ ሆኖ፤ ፈተናዎቹ ከሰጡባቸው ቀናት ሀሙስና አርብ ማለትም በ6 እና 7/10/2011ዓ.ም ከተሰጡት ፈተና ውጤቶች በተለየ ከቅዳሜና እሁድ በኋላ ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም በ10 እና 11 10/2011ዓ.ም በተሰጡት ፈተናዎች በግልጽ የታየ የውጤት ግሽበት መኖሩ በመረጋገጡ የዩንቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በአራቱ የትምህርት ዓይነቶች ላይ መሰረት ያደረገ እንደሚሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ እነዚህም እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ፊዚክስ ለተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድና ጂኦግራፊ ለማህበራዊ ሳይንስ ይሆናሉ፡፡

ይህም ሲሆን ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ሊገነዘቡ የሚገባቸው ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመምህርነት ሙያ ለመማር ከመረጡ ተማሪዎች ውጪ ለዩንቨርስቲ መግቢያ ብቻ የሚያገለግልና የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተብለው ዩንቨርስቲ እንደሚገቡና ከአንድ ዓመት የፍሬሽማን ኮርሶች በኋላም በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት የፈለጉትን የትምህርት ፊልድ መርጠው መማር የሚችሉ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የተከሰተውን #ግሽበት በተመለከተም የማጣራት ሂደቱን የሚያካሂድ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ያሳወቁ ሲሆን ተጠያቂው አካል አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በመግለጫው ማጠቃለያም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ እንደገለጹት የመቁረጫ ነጥቡን በተመለከተ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ችግር የነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚታይላቸው መሆኑንና በጥቂት ቀናት ውስጥ በኤጀንሲው የሚገለጽ መሆኑን እንዲሁም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት የተያዙት የተማሪዎች ውጤቶች #እንደሚለቀቅ ጨምረው አሳውቀዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር 14 እጩ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረጉ!

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ 14 የካቢኔ እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በእጩ ካቢኔ አባላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሹመት ቀርበዋል፤ የዓለም ባንክ የቀድሞው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ደግሞ ለገንዘብ ሚኒስትርነት ቀርበዋል።

አስማ አብደላህ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እጩ ሲሆኑ ኢብራሂም ኤልባዳዊ ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትርነቱን እንዲመሩ በነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ለሹመት ተጠቁመዋል።

የገንዘብ ሚኒስትርነቱን የሚረከቡት ኢብራሂም ኤልባዳዊ፤ በቀውስ ላይ የሚገኘውን የሱዳን ምጣኔ ሀብት እንዲያገግም የማድረግ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል ተብሏል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈም ለሌሎች 12 መስሪያ ቤቶች ሚኒስትር ለመሾም እጩዎች ይፋ መሆናቸው ነው የተነገረው።

እንደ መረጃ ምንጮች ከሆነ አደል ኢብራሂም የኢነርጅና የማዕድን ሚኒስትር፣ ጀኔራል ጀማል አለዲን ኦማር የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ሙሉ የካቢኔ አባላትን በ48 ሰዓታት ውስጥ ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን ካቢኔው የሱዳንን ሦስት የሽግግር ዓመታት የመንግሥት ስራዎችን ያስፈፅማል።

ሃምዶክ የካቢኔ አባላቱ ከመላው ሱዳን የተውጣጡ እና የሴት ተሿሚዎች ቁጥርም ተመጣጣኝ እንዲሆን ማቀዳቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው አል ጄዚራ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia

ለተፈናቀሉ ሰዎች ለምርጫ 2012 የተለየ የምርጫ ጣብያ እንደሚያዘጋጀ ቦርዱ አስታወቀ!

ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች በምርጭ 2012 መሳተፍ እንዲችሉየተለየ የምርጫ ጠቢያዎችን ሊያዘጋጅ እንደሆነ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ቦርዱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ላይ ሰብስቢዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንደተናገሩት፤ በአገር አቀፍ ደረጃ በቀጣዩ አመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ህብረተሰቦች የተለየ የምርጫ ጠብያዎች ለማዘጋጀት ተዘጋጅቷል።

ለክልል የምርጫ ጽ/ቤት ቅርንጫፎች በሃላፊነት ለመወዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማሟላት ያለበትን መስፈርቶችም በመግለጫው ላይ ተብራርተዋል።

Via #EPA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
የመጽሓፍ አዉደ ርዕይ በ6 ኪሎ የካቲት 12 አደባባይ ለተደራሲን ክፍት ሆነ!

ንባብን ባህል እናድርግ በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ያዘጋጀዉ የመጽሓፍ አዉደ ርዕይ በ6 ኪሎ የካቲት 12 አደባባይ ትላንት ተከፍታል፡፡

አዉደ ርዕዩን የቢሮው ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ መርቀዉ የከፈቱት ሲሆን በቢሮዉ የስነ-ጥበባት ዘርፍ ም/ቤት ኃላፊ አቶ ሰርጸ ፍሬ ስብሃት እና የደራሲን ማኅበር ስራ አስኪያጅ ተወካይ ወ/ሮ የዝና ወርቁ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር፡፡

በዚሁ አዉደ ርዕይ የአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች ጨምሮ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ቤተ መጽሓፍትና ቤተ መዛግብት ኤጄንሲ እና የግል መጽሓፍት መደብሮች ተሳትፈዋል፡፡

አዉደ ርዕዩ በርካታ ወጣት ተደራሲያንና ጸሓፍት የተገኙ ሲሆን የልቦለድና ኢልቦለድ መጽሓፍቶች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ ይህ የመጽሓፍት አዉደ ርዕይ እስከ ጳጉሜ 1/2011 ድረስ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡

Via #etv
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው በሶስት ጉዳዮች ላይ ይወያያል ተብላል!

በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በሦሰት ዐበይት ጉዳዮች ጥልቀት ያለው ውይይት አድርጎ የመፍትሄ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለዋዜማ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያ የሚያየው አጀንዳ ሕዝቡንና ቤተ ክርስቲያናን የመጠበቅ ሓላፊነት ስላለበት ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይመለከተዋል ብለዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እንዳሉት መግለጫውን የሰጡት አካላት ጉዳዩ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንንም አይወክልም፡፡ ምክንያቱም መግለጫ ሰጭዎች የራሳቸውን አሳብ ይዘው ነው የተነሡት፡፡ አሳቡ በራሱ የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር የሚጻረር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያን እስከወዲያኛው እንደማትደግፋቸው አበክረው ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው አጀንዳ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ ከመንግሥት ጋር እንዴት መቀጠል እንዳለባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይወያያል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስቲያን ጥያቄዎች መንግሥት በቀጣይ በምን አግባብ መመለስ እንዳለበት እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን በኩል ደግሞ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚወያይባቸው ተገልጿል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አያይዘውም መንግሥት በልዩ ልዩ ችግሮች የተወጠረ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን ትረዳለች ብለዋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-05

@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
በህገወጥ መንገድ 700 ኩንታል ማሾ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጓዝ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ!

በባሌ ዞን በህገ ወጥ መንገድ 700 ኩንታል ማሾ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ ደርሼባቸዋለው ያላቸውን ስድስት ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘው ይሄው ምርት ሲጓጓዝ የተገኘው ህጋዊ ፍቃድ ሆነ ማስረጃ እንደሌለው ተመልክቷል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ባለሙያ ኮማንደር ናስር ኡመር እንደገለጹት ግለሰቦቹ ማሾውን ከባሌ አልፈው በሶማሌ ክልል በኩል ወደ ውጭ ለማስወጣት አስበው ህብረተሰቡ ለመዳወላቡ ወረዳ ፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መያዝ ተችሏል።

ግለሰቦቹ ከነማሾው የተያዙት ነሐሴ 26/ 2011 ዓ.ም በተለያያ ሰዓት በአራት የጭነት ተሽከርካሪዎች  በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ነው።

በህገ ወጥ መልኩ ማሾውን ጭነው የነበሩት ተሽከርካሪዎች የታርጋ ቁጥራቸው ኤፌሰር  ኮድ 3- 99109 አ አ፣ ሲኖ ኮድ 3- 82093 ኢት፣ ሲኖ ኮድ 3- 95488 ኢት እና ሲኖ ኮድ 3 -90019 ኢት ናቸው።

ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረውን ማሾ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ገቢ ማድረጉን የጠቆሙት ኮማንደሩ አራቱም ተሽከርካሪዎችና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንዳለቸው የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

Via #ENA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
“መደበኛ ምርጫ አይሆንም” - ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወደፊት የሚያካሂደው ምርጫ በሃገሪቱ ከዚህ ቀደም ከተለመዱት ምርጫዎች ፍፁም የተለየ ይሆናል” ሲሉ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሳ ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

“በዋናው መሥሪያ ቤት የተጀመረው የቦርዱ የውስጥ የአደረጃጀት ለውጥም በአገርአቀፍ ደረጃም ይቀጥላል” ብለዋል። ቦርዱ ከየትኛውም ወገን የሚመጣን ተፅዕኖ እንደማይቀበልም ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል።

Via #VOA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
“አዲሱን ዓመት #ነጭ ለብሰን እንደምንቀበለው ሁሉ እኛም ውስጣችንን ከቂምና ከበቀል አጽድተን እንደ አዲሱ ዓመት አዲስ ሆነን መቀበል ይገባናል” ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ አሳሰቡ።

መጪው አዲስ ዓመት ቤተክርስቲያኒቱን ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያ ችግሮች ይወገዱ ዘንድ ቤተክርስቲያን ፀሎት እንደምታደርግም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-09-05-2
ከጎንደር...

"የክረምቱን በጎ ተግባር ከእናንተ ገፅ ባገኘነው ልምድ መሠረት እኛ የደቡብ ጎንደር የነፍስ መውጫ ተወላጆችና ደጋፊዎቻችን ደጋፊ ሌላቸው 500 ተማሪዎች 6,000 ደብተር እና 1000 እስክብሪቶ አሰባስበን ለመጭው መስከረም 3 /2012 ለቤተሰቦቻቸው ለማስረከብ ቀጠሮ ላይ እንገኛለን፡፡" #BIRHANU

@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር!

እየተከለሰ ያለው የኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት በተመረጡ የትምህርት ክፍሎች በ2013 ዓ.ም መተግበር እንደሚጀምር የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አገር ዓቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናት ጉባኤ ከትላንት ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ በ2001 ዓ.ም የተሻሻለው ስርዓተ ትምህርትን የዳሰሰ ጥናት ቀርቧል።

የዳሰሳ ጥናቱ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ድጋፍ በካምብሪጅ ኢንተርናሽናል አሰስመንት የተካሄደ ነው። በጉባኤው ላይ እንደተገለፀው፤ የአገሪቱን ስርዓተ ትምህርት ለመከለስ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው ስራ ትግበራ አምስት አመታትን የሚፈጅ ነው።

የሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አስፋው እንዳሉት፤ ዩኒሴፍ በአጠቃላይ ለስርዓተ ትምህርቱ ክለሳ የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ ቃል ገብቷል። ጥናቱ በስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያሉ ጥንካሬና ድክመቶችን በመለየት ለትምህርት ጥራት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA