TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዲሲ ከንቲባ በቅርቡ አዲስ አበባን ይጎበኛሉ!

የዋሺንግተን ከንቲባ ሙሪል ቦውዘር አዲስ አበባን በቅርቡ እንደሚጎበኙ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ። አምባሳደር ፍጹም እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግሥት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል። በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የአሜሪካ መንግሥት ለአፍሪካ በከፈተው “አፍሪካን ማበልጸግ” አዲስ ፖሊሲ  ተጠቃሚ ለመሆን እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

"ሰበር ዜና፣ አፈትልኮ የወጣ መረጃ፣ አሁን የደረሰን ውስጣዊ መረጃ" ብለው ብዙ መቶ ሺዎች የሚከተሏቸው ገፆች ትናንት "ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ጥሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ ቤት ይገኛሉ" ብለው የፆፉት የሀሰት መረጃ ነው። ከጠ/ሚር ቢሮም፣ ከፓትርያርኩ ፅ/ቤትም በተገኘው መረጃ ይህ ውሸት እንደሆነ እና ፓትርያርኩ ፈፅሞ በጠ/ሚሩ ቢሮ እንዳልተገኙ ይጠቁማል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኑ ትውልድ እንገንባ!

💫አዲስ አበባ
Yonas G/Meskel 0970514616
Meba 0924140293

💫ሰበታ
Yared Lemma 0932540523
Yeabsera Kassa 0921421493

💫ጅማ
Assefa 0911670454

💫ድሬዳዋ
Mehari 0915034762

💫አዳማ
Selam 0949377735

💫ቡታጅራ
Yab 0910899212

💫አምቦ
Haymanot +251943806689

የመማሪያ መፅሃፍት ይለግሱ!
እስካሁን 90 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል!

በደቡብ አፍሪቃ የውጭ ሃገራት ነዋሪዎች ጥቃት ጋር በተያያዘ ፖሊስ ከ90 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ዐስታወቀ። በመዲናዪቱ ፕሪቶሪያ፤ ጆሀንስበርግ እና በርካታ አጎራባች ሥፍራዎች የውጭ ሃገራት ነዋሪዎች ጥላቻ በቀሰቀሰው ጥቃት በርካታ መደብሮች ተመዝብረው በእሳት መቀጣጠላቸው ተገልጧል። የመደብሮቹ ባለቤቶችም ለሕይወታቸው በመስጋት ወደተመዘበሩት መደብሮቻቸው ከመሄድ ተቆጥበዋል። የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት በሀገሪቱ ኹከትና ዝርፊያው የተቀሰቀሰው በአንዳንድ ጥቅመኛ እና የተደራጁ ወንጀለኞች ነው እንጂ በውጭ ሃገራት ነዋሪዎች ጥላቻ አይደለም ብሏል። የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ኹከቱን እና ዝርፊያውን አውግዘዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰት ነው!

በኢትዮ ቴሌኮም ስም በተከፈተ ቻናል ሀሰተኛ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ በመሆናቸው ጥንቃቄ አድርጉ። ኢትዮ ቴሌኮም ነፃ የኢንተርኔት እና የድምፅ አገልግሎት ይሰጣል ይህን ተቀላቀሉ ለሌሎችም አጋሩ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በአንድ ቀን በደቡብ ሱዳን የተሾሙ የብሪታኒያ፣ የጀርመን፣ የሳዑዲ አረቢያ፣ የጣልያን፣ የኖርዌይ፣ የጆርጂያ፣ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደሮችን ተቀብለዋል። አገራቱ ከሪየክ ማቻር በተጀመረው ዕርቅ ቁልፍ ሚና ያላቸው ናቸው።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ-ከተማው ሲዘረፍ አድሯል⬆️

ናይጄሪያውያን በደቡብ አፍሪካ ለተፈፀመውን ጥቃት ምላሽ በሚመስል መልኩ ትላንት የደቡብ አፍሪካ ዜጎች የሚሰሩባቸውን የንግድ ተቋማት ሲዘርፉ አድረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ SHOPRITE ሲወድምና ሲዘረፍ⬆️

በናይጄሪያ የሚገኘው Shoprite በተቆጡ #ናይጄሪያውያን ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል። በርካታ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ይሰሩባቸዋል ይኖሩባቸዋል የሚባሉ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ የጥቃት ሰለባዎች ሆነዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኲሓ የሚገኘው የመቐለ ዩኒቨርስቲ መለስ ካምፓስ በ2012 ዓ/ም ስራ ይጀምራል!

ኲሓ የሚገኘው ስድስተኛው የመቐለ ዩኒቨርስቲ መለስ ካምፓስ በ2012 ዓ/ም ስራ ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ሂደት ለማሳለጥ በዩኒቨርስቲ ደረጃ ዓብይ ኮሚቴ በማቋቋም የተማሪዎች መማርያ ክፍሎች ፣የመኝታ ክፍሎች፣ካፌ፣ ህክምና፣ ውሃና መብራት፡ኢንተርኔት፣ትራንስፖርት እንዲሁም ፀጥታና ደህንነት የሚመለከቱ ስራዎችን ለይት ተቀን በመስራትና በመከታተል አስፈላጊውን ዝግጅት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የዩኒቨርስቲ የበላይ አመራሮች ለኲሓ እና አከባቢው ማሕበረሰብ የካምፓሱ ስራ መጀመር ለማብሰር እና የተማሪዎች ደማቅ አቀባበል ለማድረግ በቀጣይ ሳምንት ውይይት ያካሂዳል ፡፡ አዲሱ መለስ ካምፓስ በ2012 ዓ/ም አዲስ የሚመደቡ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ተቀብሎ ያስተናግዳል፡፡

ምንጭ፦ መቐለ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እብነ በረዱ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ እንዲሰጠው ተጠየቀ!

ለጌጥ ተብሎ የተለጠፈው እብነ በረድ እየወደቀ በመሆኑ ወደ ህንጻው በሚገቡና በሚወጡ ተገልጋዮችና ሠራተኞች ላይ ወድቆ አደጋ ሊያደርስ ስለሚችል ፈጣን መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ የአራዳ ክፍለ ከተማና ሠራተኞቹ አሳሰቡ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አበባ እሸቴ በተለይ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደገለጹት፤ ለኮንስትራክሽን ቢሮና ለፐብሊክ ሰርቪስ ጽህፈት ቤት ከተገነባው ህንጻ በሚወድቀው እብነ በረድ ምክንያት ጉዳት እንዳይከሰት የማረሚያ ሥራ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አፋጣኝ ምላሽ አልተሰጣቸውም።

ህንጻውን በበጋ ወቅት ስለተረከቡ በወቅቱ ፍሳሽ እንዳልነበረ የተናገሩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አበባ ፤ ክረምት ላይ ፍሳሽ መኖሩን መመልከታቸውን ገልጸው፤ የህንጻውን የፍሳሽ ችግሮች የማስተካከል ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች ቦምባስ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ በጉምሩክ ፈታሾች እና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

ከሽጉጦቹ ጋር ሁለት የሽጉጥ ሰደፍና 11 ካርታ የተያዘ ሲሆን ህገ-ወጥ መሳሪያው ኮድ3-30513 የሰሌዳ ቁጥር ባለው አይሱዙ ተሸከርካሪ ትናንት ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ ህገ-ወጥ መሳሪያው የጫነው ተሽከርካሪ ወደ ሐረር መስመር እየተጓዘ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ፦የገቢዎች ሚንስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ከቀረጥ ነጻ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን

የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በተመጣጠነ ዋጋ እንዲቀርብ እንዲሁም ተደራሽነቱ እንዲሰፋ ምርቶቹ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እንደማንኛውም መድኃኒት እና የህክምና አገልግሎት መስጫ መሣሪያ ተመርቶ እንዲሰራጭ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘም ተናግረዋል፡፡

"በግሌና እንደ ጤና ጥበቃ ሚንስትርነቴም፤ የንፅህና መጠበቂያ ማግኘት የእያንዳንዷ ሴት መብት መሆኑን አምናለሁ" ያሉት ዶ/ር አሚን፤ መንግሥት ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ

የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል።

የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።
የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።

በተመሳሳይ ዜና...

ታዋቂው የናይጄሪያ ድምፃዊ ቡራን ቦይ በዘርኝነት ጥቃቱ ምክንያት በጭራሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ እንደማይፈልግ ተናግሯል።
ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።

አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።
የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት በበኩላቸው በደቡብ አፍሪካ ባሉ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎችን ኢላማ አድርጎ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አውግዘዋል።

ሊቀ መንበሩ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት በንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ንብረት መዝረፍ እና ማውደምን ጨምሮ ሌሎች እየፈፀሙ ያሉ ድርጊቶችን ክፉኛ ኮንነዋል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመራቸውንም ሊቀ መንበሩ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።

Via #EBC
@tikvahethiopia
#update የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በውጭ ዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለውን ንብረት መዝረፍ እና የዘር ጥቃት አወገዘ፡፡ ሚንስቴር መስሪያቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ድርጊቱን ማውገዛቸው የሚበረታታ መሆኑን አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ MiT ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች⬆️

Via EDALE CHALEW/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Urgent Notice!!!

Adigrat University, the Department of Architecture has launched a vacancy for 15 Assistance Lecture and Lecturer positions.

Requirements:

⁃ Minimum GPA 3.0 for female and 3.25 for male candidates
⁃ Original or temporary Degree/MSc
⁃ Application letter
⁃ CV
⁃ Recommendation Letter
⁃ 0 year experience
⁃ BSc. and above in Architecture or Architecture and Urban Planning
⁃ Deadline is within 3 days until Friday 06-09-2019

Priority will be given for Masters Degrees holders.

For further information please contact:
Cell phone: +251914013344 or +251914723178
E-mail: [email protected]
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎችን ኢላማ ባደረገ መልኩ የተፈጸመውን ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ በፅኑ ያወግዛል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ክቡር ሰርል ራሞፎሳ ድርጊቱን በማውገዝ በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንደሚያቀርቡ የገቡት ቃል አበረታች በመሆኑ መ/ቤታችን አድናቆቱን ይገልጻል። ፕሬዝዳንቱ በገቡት ቃል መሰረትም በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ እንደሚያቀርቡ መ/ቤታችን ያምናል።

ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ አጋጣሚ በየደደረጃው የሚገኙ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ጠንካራ ክትትል በማድረግ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር እንዲያውሉና ለህግ እንዲያቀርቡ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ሚኒስቴር መ/ቤታችን ጥሪውን ያቀርባል።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲም ከሚመለከታቸው የአገሪቱ ባለስልጣናት እና ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጋር ሁኔታውን ለማረጋጋት በቅርበትና በትብብር እየሰራ መሆኑንና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ይገልጻል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል። የትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት፣ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤጀንሲውና አምስት የሥራ ኃላፊዎቹ በ174 ሚሊዮን ብር ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እንዲሁም አምስት የሥራ ኃላፊዎቹ በድርጅቱ ላይ ላደረሱትና ለሚደርሰው ጉዳት የ174 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር ተከፍሎ እስከሚያልቅ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ክስ እንዳቀረበባቸውና ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ኤ ቢ ኤች (ጥምረት ለተሻለ ጤና) ሰርቪስስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣእንደገለጹት፤ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከማምራቱ በፊት ኤጀንሲው የድርጅቱን መልካም ሥምና ዝናን በማጠልሸቱ ይቅርታ እንዲጠይቅና ችግሩን እንዲያርም ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህም ድርጅቱ ነሐሴ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትሐብሔር ስድስተኛ ምድብ ችሎት የመዝገብ ቁጥር 241863 ክስ ለመመስረት ተገድዷል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ አምስት የሥራ ኃላፊዎችም ተከስሰዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው።

በበዓለ ሲመቱ ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖትን ጨምሮ የየአገረ ስብከቱ ሊቀጳጳሳትና የየአጥቢያው አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል። በዓለ ሲመቱ እየተከበረ ያለው በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ነው።

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ላለፉት 20 ዓመታት አሜሪካን አገር የሚገኘውን ‘ስደተኛ ሲኖዶስ’ እየተባለ የሚጠራውን መንበር ሲመሩ እንደነበርና በቅርቡም በተፈጠረው እርቀ ሰላም ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia