TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ ዓመት ስጦታ በሽ በሽ ለባለ እድል!!
መጭውን አዲስ ዓመት በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ያውም ኩራትና ክብራችን በሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆቴል ስናከብር የአዲስ ዓመት ስጦታ በሽ በሽ ነው!!

1. ለጥንዶች የአውሮፕላን ደርሶ መልስ ነፃ ትኬት
2. ለአንድ ሰው የአውሮፕላን ደርሶ መልስ ነፃ ትኬት
3. 20 ቅንጡ የመኝታ ክፍሎች ለጥንዶች
4. ነፃ የቢዝነስ ክላስ አፕግሬድ
5. 1 ተጨማሪ ሻንጣ ነፃ ማጓጓዣ
6. የአውሮፕላን ትኬት ለገዙ መንገደኞች የአዲስ አበባ ኤርፖርት ቢዝነስ ክላስ ላውንጅ መግቢያ
7. ለጥንዶች በባህላዊ ሬስቶራንታችን የእራት ግብዣ
8. ለጥንዶች በቻይና ሬስቶራንታችን የእራት ግብዣ
9. ለጥንዶች በግራንድ ኪችን ሬስቶራንታችን የእራት ግብዣ
10. ለጥንዶች የኤግዜኪውቲቭ ላውንጅ መግቢያ

እርስዎ ብቻ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ምሽትዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ! 1500 የተመረጡ ቪአይፒዎች ብቻ የሚስተናገዱበት ታላቁ የእራትና የሙዚቃ ምሽት 6 ቀናት ብቻ ቀሩት! ከልብ ወዳጅዎ ጋር ያሻዎትን እየተጎነጩ ደረጃዎን፣ ክብርና ዝናዎን በሚመጥነው ባለ 5 ኮከቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል የ2012 መልካም ምኞትዎን ይግለጹ! እርስዎ የምሽቱ የክብር ንጉስ/ንግስት ነዎት! እኛ ደግሞ ምሽትዎ ያማረና ብሩህ ተስፋ የሞላበት፣ ደስታዎን የሚያጣጥሙበትን ምሽት እፁብ ድንቅ ልናደርግልዎት ዝግጅታችንን ጨርስናል!

ዻጉሜ 6 - የአዲስ ዓመት ዋዜማ
ልብ ይበሉ ሁሉም ትኪቶች ቪአይፒ ናቸው!
ኑ አዲሱን ዓመት አብረን እንቀበል!
ታድያ ለምን ይጠብቃሉ? አሁኑኑ ትኬትዎን ይግዙ! እርስዎ ይደውሉ እኛ ያሉበት ድረስ እንመጣለን!

መረጃ እና ትኬቶችን በ 0904 05 03 21 ማግኘት ይችላሉ!
የነሃሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 17.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግባል!

የነሐሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 17 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ። ግሽበቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በዋና ዋና እህል ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ለአጠቃላይ ግሽበቱ ከሚጠቀሱት ምክንያቶች መካከል ነው። ይኸው ጭማሪ ያለማቋረጥ መቀጠሉንም ኤጀንሲው አመልክቷል።

ለምግብነት ተፈላጊ የሆኑ አንዳንድ የአትክልት ዓይነቶች በተለይም ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት በአንድ ወር ውስጥ የተጋነነ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ይህም የዋጋ ግሽበቱ ከፍ እንዲል እንዳደረገው ነው የኤጀንሲው መግለጫ የጠቆመው። ሆኖም በአንዳንድ የአገሪቱ ክልሎች የስንዴ፣ ሩዝና ዳቦ ዋጋ የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑንም አመልክቷል።

የልብስና መጫሚያ፣  የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ትራንስፖርት፣ ከሰል እና የማገዶ እንጨት በወሩ ውስጥ ጭማሪ አሳይተዋል።

Via #ENA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETH ለመላው የኢትዮ ኤፍ ኤም አድማጮች፣ ሠራተኞች እና አመራሮች በሙሉ እንኳን ለ2ኛ አመታችሁ አደረሣችሁ ለማለት ይወዳል! መጪው ጊዜም የስኬት እንዲሆንላችሁ ይመኛል!

#TIKVAH_ETHIOPIA
#በጎፈቃኞችን_እንፈልጋለን!

የትምህርት ሚኒስቴር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እየሰራችሁት ላለው ትልቅ ስራ ምስጋና ይገባችኀል፡፡ የዚህ ሥራ ዋጋ እንዲህ በቀላሉ የሚተመን ሳይሆን ለበርካታ አቅም ላጠራቸው ቤተሰቦች እረፍትን የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም የታቀደለትን ግብ እንዲመታ ሁላችንም መረባረብ ይጠበቅብናል፡፡ በጎፈቃደኞቹ እነዚህን የትምህርት ቁሳቁሶች ወደ መኪና ጭነው ወደተፈለገው ቦታ ለማድረስ ከፍተኛ የሰው ኃይል ያስፈልጋቸዋልና እናግዛቸው፡፡
ማገዝ ለምትፈልጉ
📞+251911485705 /+251944260072
ደውላችሁ መረጃ በመጠየቅ በዚህ ሀገራዊ ሥራ ላይ የበኩላችሁን አሻራ አኑሩ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ማስከበር ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ማሰከበር የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ዋና ኃላፊው አቶ አህመድ መሐመድ እና ምክትል ኃላፊው አቶ አብዱልዋህድ አብዱላህ ናቸው በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የተገለጸው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው ከህገ ወጥ የኮንትረባንድ ዝውውር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩት የሥራ ኃላፊዎቹ በከባድ የሙስና ወንጀል ነው ዛሬ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

Via #AMMA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•ባዮሎጂ፣
•ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም

በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•የታሪክ (History)፤
•ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች #ውድቅ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ባለፈው ሰኔ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል በእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ እና አፕቲቲዩድ ውጤቶቻቸው ይለካሉ።

ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፊዚክስ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ የጂኦግራፊ ፈተናዎች ለመመዘኛነት ተመርጠዋል።

ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ «ተማሪዎችንም ፍትኃዊ በሆነ መልክ ሊያወዳድር እና ከእነሱ ችሎታ ባሻገር ምንም መበላለጥን ሊያስከትል የማይችል ሆኖ ስላገኘንው እነዚህን ተጠቅመን ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መመደብ እና የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ወስነናል» ብለዋል።

ከ322 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የተቀመጡበት ይኸው ፈተና ችግር እንደነበረበት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚዓብሔር «ሰኔ 6 እና 7 የተፈተኑት ፈተና ትክክለኛ ይዘት አለው። ሰኔ 10 እና 12 [የተፈተኑት ፈተናዎች ውጤት] ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ሲታይ የመጨመር ባሕሪ ሲያሳይ የተወሰነ ቦታ ላይ ግን ከሚጠበቀው በላይ ጋሽቦ ሔዷል» ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ «መቁረጫ ነጥቡ የት ይሆናል የሚለውን ኤጀንሲው ለተማሪዎች እና ለወላጆች፤ ለዩኒቨርሲቲዎች ግልፅ የሚያደርግ ይሆናል» ብለዋል።

የመንግሥት ባለስልጣናቱ ውሳኔ ቀድሞም ቀውስ ውስጥ በገባው የትምህርት ዘርፍ ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆኗል። ለመመዘኛነት አያገለግሉም ተብለው ውድቅ የተደረጉት የፈተና ውጤቶች ችግሮች ምንድናቸው? በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምን አይነት ችግሮች ተፈጠሩ? #ተጠያቂውስ ማነው ለሚሉ ጥያቄዎች ባለሥልጣናቱ በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሚመሩት አጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩ ይመረመራል ተብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የ2012 ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ/የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ እየተባለ የሚሠራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
#የአምቦ_ህብረት -- ደብተር ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ቤተሰብ ልጆች የደብተር ማሠባሰብ ሥራ እየተሠራ ነው። በአምቦ የምትገኙ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በዚህ ሥራ ላይ እንድትሣተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
📌በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ማስታወቂያ ተመሳሥሎ የተሠራ ነው!

"ሰላም ፀጋ የUnity University ማስታወቂያ ተመሳስሎ የተሰራጨው ማስታወቂያ #በphotoshop ተቀነባብሮ የተሰራ መሆኑን የግቢው አስተዳደር አረጋግጦልኛል" #YABU

ተመሳስሎ የተሰራበትን ማስታወቂያ👇
#Photoshop የተሰራበት ትክክለኛው ማስታወቂያ ይህ ሲሆን ለማረጋገጥ ቀኑን, ቁጥሩን እንዲሁም የተሰኩበትን መርፌዎች ቀለም ተመሳሳይነት መመልከት ይቻላል።

Via #YABU/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የተላለፈላችሁ መልዕክት!

ለዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ሆኖም በቴሌግራም የተሣሣተ መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ደርሠንበታል። ስለሆነም የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ተገንዝባችሁ ለአላስፈላጊ ቅጣትና መጉላላት እንዳትዳረጉ እያሳሰብን ዩኒቨርሲቲው ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት #ክፍያችሁን እንድታከናውና እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናስታውቃለን።

#ሼር

@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
👆ይህን መልዕክት በTIKVAH-ETH ተመልክታችሁ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጋችሁ ላሳወቃችሁን አካላት ከልብ እያመሰገንን የትኛውም ድርጅት ስለተቋሙ እንዲሁም ግለሠቦች በማህበራዊ ሚዲዎች የሚናፈሱ መረጃችን ለማክሰም እና ህብረተሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ በዚህ መልዕክት መላክ ይቻላል @tsegabtikvah
በመጪው ዓመት ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ከ50 ሚሊየን በላይ መራጭን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት ተደርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌደራል ፖሊስ ባለፈው አንድ አመት ሰላምን ለማስከበር ላበረከተው አስተወጽኦ የምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ የሰለም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፌደራል ፖሊስ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ በማድረግ ሂደት ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሀሰት ነው!

በኢትዮ ቴሌኮም ስም በተከፈተ ቻናል ሀሰተኛ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ በመሆናቸው ጥንቃቄ አድርጉ። ኢትዮ ቴሌኮም ነፃ የኢንተርኔት እና የድምፅ አገልግሎት ይሰጣል ይህን ተቀላቀሉ ለሌሎችም አጋሩ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ከተለያየ የዓለም ክፍል የተወጣጡ እና በተባበሩት መንግሥታት መሪነት አዲስ አበባ ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ የአፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሁለት ሠዎች ተገደሉ!

በጋምቤላ ክልል በዛሬው ዕለት ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የአይን እማኞች እና የክልሉ መንግሥት ሰራተኛ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በጋምቤላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኛ የሆኑ አንድ የአይን እማኝ እንዳሉት ሰራተኞቹ የተገደሉት “ዊኜል” ከተባለ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ነው።

ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉት የተ.መ.ድ. ሰራተኛ «ዛሬ በኢታንግ መስመር ዊኜል ወደተባለ [መጠለያ] ሲሔዱ፤ ሁለት ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ተገድለዋል። እኛው ጋ የሚሰሩ የሌላ ተቋም ሰራተኞች ማለት ነው» ሲሉ ተናግረዋል።

አክሽን አጌይንስት ኸንገር (Action Against Hunger) የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ተቀጣሪ ናቸው የተባሉት ሁለት ሰዎች «ወደ ኢታንግ ከሚወስደው መንገድ ተገንጥለው ወደ ስደተኞች መጠለያለው ለመግባት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው» በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኙ አብራርተዋል።

የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪ ባለሙያ በበኩላቸው በአካባቢው አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ንብረት የሆነ ተሽከርካሪ ጥቃት እንደተፈጸመበት አረጋግጠዋል። «የሆነ መኪና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መኪና ተመቷል። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የሚባል አለ። ሁለት ሰው ሞቷል» ያሉት የጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪ ባልደረባ አንድ አሽከርካሪ እና የመስክ ሰራተኛ መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስልመና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበረው የአሹራ በዓል የፊታችን ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአልነጃሺ መስጊድ በድምቀት ይከበራል። በዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮችና ሃይማኖት መሪዎች በተገኙበት የሚከበር መሆኑ ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አንድ ሐገር-ቢያ ቶኮ"

በተለይ ኤቶዮጵ በተሰኘው መፅሐፉ ብዙ አንባቢዎችን ያስደመመው ደራሲና ሐኪም ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ አዲስ መፅሐፍ "አንድ ሐገር-ቢያ ቶኮ" ነገ ለአንባቢያን ይቀርባል። መፅሐፉ ነገ ጷግሜ 1 ከ11 ሰኣት ጀምሮ በሐገር ፍቅር ቲያትር ቤት የሚመረቅ ሲሆን ዋጋው 100 ብር ብቻ ነው። ከቅዳሜ ጀምሮ በሁሉም የአዲስ አበባ መፅሐፍት ቤቶችና አዟሪዎች እጅ ላይ ያገኙታል። ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ አንባብያን ከእሁድ ጀምሮ እንደሚሰራጭና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንደሚዳረስ ደራሲው አሳውቆናል።

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia