TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ADDISABEBA "የአሸንዳ በዓል #የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ሰላም በማጠናከር ጉልህ ሚና አለው" የበዓሉ ተሳታፊዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ፦

እኛ በየደረጃው የምንገኝ የአዲስ አበባ አዴፓ አመራሮች ከነሐሴ 25 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በ2011ዓ.ም መደበኛ የድርጅትና የፖለቲካ ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም በከተማዋ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እንቅስቅሴ ዙሪያ የከተማችንን ህዝብና ወጣት መሰረታዊ ፍላጎቶች ለመመለስ፣ ባከናወናቸው ተግባራት የነበሩንን ጠንካሬና ጉድለቶች በዝርዝር ገምግመናል፡፡

#AddisAbebaEPRDF

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01-5
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ #አልተደረገም፤ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲም መቼ ይፋ እንደሚደረግ #አላሳወቅም። በተመሳሳይ ስለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ የሚዋራው ሀሰት ነው። መቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም።

ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በተለያዩ ሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ! ተማሪዎች እና ወላጆች አጠቃላይ ስለፈተናችሁና ውጤታችሁ ትክክለኛ መረጃን ልታገኙ የምትችሉት በዚህ መንገድ ብቻ ነው፦

1. https://m.facebook.com/neaea.nae/ ይህ ትክክለኛው የኤጀንሲው የፌስቡክ ገፅ ነው። አዲስ መረጃ ካለ በዚህ በኩል ይገልጻሉ።

2. https://app.neaea.gov.et/ ይህ የኤጀንሲው ድረገፅ ነው። አዲስ መረጃ ካለ በዚህ በኩል ይገልጻሉ።

3. በተለያዩ የመንግስትና የግል የቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያዎች በኤጀንሲው በኩል የሚሰጠውን መረጃ ብቻ ተከታተሉ።

4. ህጋዊ በሆኑና በቴሌቪዥንና በሬድዮ ጣቢያዎች ቁጥጥር ስር ባሉ ህጋዊ✔️የፌስቡክ ገፆች ላይ ስለውጤታችሁ የሚወጣ መረጃ ካለ #ተመልከቱ፤ አረጋግጡ።

📌ከዚህ ውጪ በትኛውም አይነት መንገድ የሚሰራጩ መረጃዎች #እንዳታምኑ። በሚሰራጩ ሀሰት ወሬዎችም #እንዳትጨነቁ። የምታዩትን ነገር ሁሉ ሼር እንዳታደርጉ በቅድሚያ አረጋግጡ!!

💫ኤጀንሲው ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የለውም! ሁሉም በኤጀንሲው ስምና በትምህርት ሚኒስቴር ስም የተከፈቱት ቻናሎች ህጋዊ እውቅና የሌላቸው ናቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዋጋ ንረት ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር እየተወያየ ነው። ውይይቱ በዋናነት በአገልግሎት እና በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ በሚታየው የዋጋ ንረት ላይ ነው እየመከረ ያለው። በመድረኩ የዋጋ ንረትን እና ህገ ወጥነትን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት አግባብ ዙሪያም ምክክር እየተደረገ ነው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
💫በአዲስ አበባ የአርሰናል ደጋፊዎች ትላንት አርሰናል ከቶትነሀም ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨወታ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተገኝተው የታደሙ ሲሆን በጎ አላማ ያለውን ስራንም አሳክተዋል፡፡ ደጋፊዎቹ ከ10:00 ሰአት ጀምሮ ችግርተኛ ተማሪዎችን ለመርዳት ከበርካታ ተመልካች የመማሪያ ደብተር እና ቁሳቁስ ለመለገስ የመሰብሰብ ስራን ሰርተዋል መልካም ተግባር ፈፅመዋል፡፡

Via Teddy Soccer
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ስራን ሰርተን እንለፈ!

"እኛ እዚህ አዲስ አበባ የምንኖር የተወሰንን የጭሮ ተወላጆች በ26/12/2011 ዓ.ም. በጭሮ ከተማ የሚገኝ ቁጥር 4 ት/ቤት አቅም ላነሳቸው ተማሪዎች የደብተር፣ የብእርና አርሳስ እርዳታ በቦታው በመገኘት አድርገናል። ይህንን አስመልክቶ ከወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ተሰቶናል። ለቀጣም አጠናክረን እንቀጥላለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለ10 ቀናት ሥራ ማቆሙ ተገለጸ!

የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት አስር ቀናት ያህል ሥራ የተቋረጠ ሲሆን አንድ ድርጅት የጄነሬተር ኃይል በመጠቀም ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል።

የፓርኩ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ መሐመድ ሃጂ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ፓርኩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኘው ከአዋሽ መልካሳ የኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ለፓርኩ ኃይል የሚያቀብለው ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ምክንያት ሥራቸው መስተጓጎሉን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሰኞ ነሐሴ 20/2011 አዲስ ትራንስፎርመር ተገዝቶ ወደ አዋሽ መልካሳ መላኩን የነገሩን መሐመድ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥገናው ተጠናቆ የኃይሉ ችግር እንደሚቀረፍ ተናግረዋል።

በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ አለመሆኑን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኮንን ኃይሉ ገልጸዋል። ብዙዎቹ ፓርኮች ሥራቸውን ባቀዱት መጠን እንዳይሠሩ የኃይል መቆራረጡ እቅፋት እንደሆነባቸውም ኃላፊው ተናግረዋል።

#AddisMaleda

https://telegra.ph/ETH-09-02
ከበዓል በፊት ደሞዛችን ይከፈለን!

ከአደረጃጀት ጋር በተያያዘ የኛ #የዶክተሮች ክፍያ አልተፈፀመም ሲሉ በቀድሞው የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን "ሰገን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል" የሚሰሩ ዶክተሮች ቅሬታ አቅርበዋል። የህክምና ባለሞያዎች ለሰሩበት እና ላገለገሉበት ክፍያ ካልተፈፀመላቸው ለምን መጥተው ያገለግላሉ ሲሉም ይጠይቃሉ? ከአደረጃጀት ጋር በሚያያዙ ጥያቄዎች የኛ ለሁለት ወር የደሞዝ አለመከፈል እጅጉን ቅሬታ ፈጥሮብናል፤ ይህ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ጤና መግባት የለበትም ያሉት ዶክተሮቹ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ከላይ ያሉት አመራሮች ትኩረት ሰጥተውበት እንዲሰሩ ጠይቀዋል አዲሱ ዐመት ከመግባቱም በፊት ተገቢው ክፍያ እንዲከፈላቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ...

የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ የሆኑት ዶክተሮቹ በአሁን ሰዓት የሚገኙት በጉማይደ/ሰገን/ ከተማ ሲሆን አከባቢው #በወታደር ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢዜማ በደሴ ከተማ ውይይት አደረገ!

ለኢትዮጰያ ጠንካራ አንድነት፣ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት አበክሮ እንደሚሰራ የኢትዮጰያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ገለፀ ። ኢዜማ ከደሴና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር በለውጡና በቀጣይ የሰራ እቅዶቹ ዙሪያ ትናንት መክሯል፡፡

የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ የአገሩን ዳር ድንበር አስከብሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሉ ክፉ ደጉን አሳልፏል፡፡ ይህን ከአባቶች የተገኘውን የረጅም ዘመን አንድነት፣ ሰላምና የመቻቻል ባህልና እሴት ለማጎልበት ኢዜማ አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ከተደቀነባት አደጋ ለማውጣት በየደረጃው ጠንካራ መሪና ህዝብ ያስፈልጋታል ያሉት አቶ አንዷለም ከዚህ ችግር እንድትወጣ ከመንግስትና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓሪቲዎች ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አንዷለም ገለጻ ከማንኛዉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በፊት አገር፣አንድነትና ሰላም መቅደም እንዳለበትም አብራርተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-02-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደህና መጣችሁ!

በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ ገብቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

በአቀባበል ስነ-ስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ ስፖር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን የተውጣጡ አካላት ተሳታፊ ናቸው፡፡

የስፖርት ልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባበት ሰአት ለአቀባበል ምቹ ስላልነበረ የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለዛሬ መተላለፉ ተገልጿል፡፡ 250 አባላትን የያዘው የስፖርት ልኡካን ቡድኑ በሞሮው መድረክ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 12 የነሃስ ሜዳሊያዎች በማስመዝብ ከአፍሪካ 9ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

Via ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ🛬አዲስ አበባ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ሃገራት ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድቬንቱስ ሰራተኞች የ3 ወር ደሞዝ አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል!

"ሰላም ጤና ይስጥልኝ! የdVentus Technologies (www.dventus.com) ሰራተኛ ነኝ፤ ደሞዝ በፈረንጆቹ በ27 ነበር ሚገባልን 3 ወር ሙሉ ሳይከፈለን ይኸው ዛሬ የአራተኛው ወር 6 ቀን ሆኖታል። የድርጅቱ ሼር ሆልደሮች አቶ ዳንኤል ግዛው እና ጥረት ኮርፖሬሽን ሲሆኑ፣ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና ትልቁን ሼር የያዘው አቶ ዳንኤል ግዛው ማረሚያ ቤት ይገኛል። ሌሎች ይመለከታቸዋል ያልናቸውን የድርጅቱ አመራሮች ብንጠይቅም መፍትሔ ሚሰጠን አጣን። ወዴት አቤት እንበል?"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ

"በትላንትናው ዕለት የአምባ ፋርማሲዩቲካልና አኳርየስ አቪየሽን በመተባበር ለ2ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ሀይቅ ዳርቻ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር ዝናቡ ሳያመልጠን ችግኞች ስንተክል፤ የዛሬ ወር ገደማ የተከልናቸውንም ስንንከባከብ ዉለናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየመን በሶስት ዓመታት ብቻ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል!

በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ኃይል በየመን በፈጸመው የአየር ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።

ቀይ መስቀል እንዳለው ከሆነ በተደጋጋሚ በተፈጸመው የአየር ጥቃት የተገደሉት በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው የነበሩ ሰዎች ናቸው።

ከአየር ጥቃቱ በህይወት መትረፍ የቻሉ 40 ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው በመሆኑም ተነግሯል። የአየር ጥቃቱ ቢያንስ ስድስት ጊዜ መፈጸሙን ከአየር ጥቃቱ የተረፉት እና በአከባቢው የሚኖሩ ሰዎች ተናግረዋል።

#BBC

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/ETH-09-02-3
#update ቱርክ ለዓለም ገበያ ምታቀርባቸውን ምርቶች በተመረጡ 17 አገራት ላይ በአምስት ዘርፍ የምትልካቸውን ምርቶች እጥፍ ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋለች። ከተመረጡት አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካን እና ኬንያን ጨምሮ ሦስት አገራት መሆናቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዳቦ ቤቶች የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በህገወጥ መንገድ እስከ መሸጥ መድረሳቸው ተነገረ!

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበራት ጋር እያካሄደው ባለው የውይይት መድረክ ላይ በከተማዋ ያሉ ዳቦ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ለውይይት በወቀረበው ሰነድ ላይ እንደተገለፀው መንግስት ለህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ሲል የአንድ ዳቦ ዋጋ በ1 ብር 30 ሳንቲም ተምኖ ለዚህ የሚውል ስንዴን በድጎማ በ550 ብር እያቀረበ ይገኛል፡፡

ሆኖም ዳቦ ቤቶች ስንዴውን ገበያ በማውጣትና ‘ልዩ ስንዴ’ በማለት በ2 ሺህ ብር እየሸጡ 1 ብር 30 ሳንቲም የነበረ የዳቦ ዋጋ 3 ብር ድረስ ሲሸጥ እንደተደረሰበት በሰነዱ ላይ ቀርቧል፡፡

ከዚህ ባለፈ ዳቦ ቤቶች የተፈቀደላቸው ዳቦ እንዲያቀርቡ ቢሆንም ኩኪስ፣ዶናት፣ ኬክና መሰል ምርቶችን በድጎማው ስንዴ አምርተው በመሸጥ ላይ እንደሚገኙም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

በዚህ መሰረት ቁጥጥር ሲደረግ በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት ሲሰሩ የነበሩ ዳቦ ቤቶች አርበኞች፤ ሮዛ፤አፍሪካ እና ምስራቅ ዳቦ ቤቶች ብቻ መሆናቸውም ተያይዞ ተገልጿል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሰኔ 15 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ የብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ደስታ አሰፋ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል መዝገብ ችሎቱ ተጨማሪ 28 ቀን ለፖሊስ ምርመራ ፈቅዷል፡፡

ዛሬ ፖሊስ በዚህ መዝገብ የተካተቱ 7 ተጠርጣሪዎችን ከዚህ በፊት ጠርጥሪያለው ብሎ ከነበረበት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተሳትፎ ባለፈ በቤንሻንጉል መተከል ከተፈጠረው ግድያ ጋር በተያያዘም እጃቸው እንዳለበት ጠርጥሪያለው ሲል ለችሎቱ አስረድቷል።

የብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ሚስት የታሰሩት የእሱ ሚስት በመሆናቸው ብቻ መሆኑን ጠበቃቸው ለችሎቱ ያስረዱ ቢሆንም ፖሊስ ከመኖርያ ቤታቸው ያገኘው 60 ጥይት እንዳገኘ በመግለፅ ለምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል።

ጠበቃቸው ግን ሟች መንግስት ያስታጠቃቸውን መሳሪያ በመኖሪያ ቤታቸው ማስቀመጣቸው ባለቤታቸውን ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ጋር ያገናኛቸዋል ማለት አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል።

Via ሳምራዊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ዱራ በተባለው አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ። በትራፊክ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።

አደጋው ከሽረ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ተሸከርካሪ ከሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑን የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። አደጋው ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተከሰተ እንደሆነም የፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

አሽካርካሪዎች ከዚህ አደጋ ትምህርት በመውሰድ ፍጥነት በመቀነስ በሰው ህይወት እና ንብራት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀነሱ የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቺክቭ የተጠቁ ሰዎች 20 ሺህ ደርሷል!

በድሬዳዋ በችኩንጉኒያ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ማሻቀቡ ተገለጸ፡፡ ችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ችኩንጉኒያ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ ህመም ነው፡፡

የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ የተከሰቱ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥር ባሳለፍነው ሳምንት ከደረሰበት 15 ሺህ አሁን ላይ ወደ 20 ሺህ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ህብረትሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡ በወረሽኙ እስከ አሁን ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

እስካሁን በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ 86 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች ወረርሽኙን የሚያስተላልፈው ትንኝ እጭ እንደተገኝባቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቃል፡፡ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች የተውጣጣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታው በመገኘት የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ወረርሽኙን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃል ተቋቁሞ በቅንጅት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የቤት ለቤት ርጭት፣ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የህክምና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማቶች እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ቺኩንጉንያ ቫይረስ ምንድነው? ቺኩንጉንያ ቫይረስ (ቺክቭ) በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ቺክቭ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህምምን ያስከትላል። ቺክቭ አብዛኛው ጊዜ ሞትን አያስከትልም፣ ነገር ግን የሚወልዳቸው የጤና እክሎች ነገሮችን ከመስራት እስከማገድ የሚደርሱ ሆነው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ለከባድ ተጨማሪ በሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ቫይረሱን እና ኢንፈክሽኑ የምንከላከልባቸው መንገዶችን የተመለከተ እውቀት መጨበጥ ወሳኝ ነው። የሚወስዷቸው ጥንቃቄዎች ከሌሎች በትንኞች የሚመጡ በሽታዎችም ይከላከልልዎታል።

#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia