TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፖሊስ አንድን ወጣት #ሲደበድብ የሚታይበት የዛሬው ቪዲዮ በበርካቶች ዘንድ #መነጋገሪያ ሆኗል!
ትላንት በተሰራጨው ቪድዮ ላይ ድብደባ ሲፈፅም የነበረው ፖሊስና ባልደረባው በቁጥጥር ስር ውለዋል!

ትናንት ጎፋ አካባቢ ድብደባ ፈፀመ የተባለው ፖሊስ እና የስራ አጋሩ ሌላ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኮማንደር ፋሲካ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለምህንድስና ተማሪዎችና በልምድ ለሚሠሩ ባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው!

•ስልጠናው ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ይካሄዳል

ከዩኒቨርስቲ #ለሚመረቁ የምህንድስና ተማሪዎችና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ዉስጥ በልምድ እየሠሩ ላሉ ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙያዊ ብቃት እንዲኖራቸዉ የሚያስችል ፕሮጀክት በጀርመን የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማህበር መተግበር ጀመረ።

ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ጋር በትብብር ዳብሮ አሁን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመግባት ላይ መሆኑን የጀርመን የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማህበር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ሔንዝ ሪትማን ተናግረዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27
TIKVAH-ETHIOPIA
ትላንት በተሰራጨው ቪድዮ ላይ ድብደባ ሲፈፅም የነበረው ፖሊስና ባልደረባው በቁጥጥር ስር ውለዋል! ትናንት ጎፋ አካባቢ ድብደባ ፈፀመ የተባለው ፖሊስ እና የስራ አጋሩ ሌላ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኮማንደር ፋሲካ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #በትናንትናው እለት ሁለት የፖሊስ አባላቱ በቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ የፈፀሙትን ድርጊት እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ትናንት ረፋድ ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ በድለላ ስራ ላይ በተሰማሩ ሁለት ቡድኖች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሷል።

ይህን ተከትሎም የተፈጠረውን አለመግባባት ለመዳኘት ወደ ስፍራው ያቀኑ ሁለት የፖሊስ አባላት፥ አለመግባባት የፈጠሩት የቡድን አባላት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄዱ በጠየቁበት ወቅት አለመግባባቱ ተካሮ የፖሊስ አባላቱ በግለሰቦች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን እና ጥይት መተኮሱን ጠቅሷል። የፖሊስ አባላቱ አዲስ እና በቅርቡ ሰራዊቱን የተቀላቀሉ መሆናቸውን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፥ የፈፀሙት ድርጊት ግን ተገቢነትም ሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ገልጿል። አሁን ላይም ጉዳያቸው በወንጀልና በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እየተጣራ መሆኑን ጠቅሶ፥ ጉዳዩን አጣርቶ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ አሳውቃለሁ ብሏል። ህብረተሰቡም መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች የማሳወቅ ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቁን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ ጊሎ ወንዝ ሞልቶ ነዋሪዎችን አፈናቀለ!

በጋምቤላ ክልል አኝዋሃ ዞን ጆር ወረዳ የጊሎ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰስ ከ400 በላይ ነዋሪዎችን ማፈላቀሉን የዞኑ አስተዳደሪ ገለፁ።

የዞኑ አስተዳደሪ አቶ ኡጉላ ኡጁሉ እንደገለጹት ነሐሴ 18 ቀን 2011 ምሽት ላይ ወንዙ ሞልቶ በመፍሰሱ በወረዳው ኡንጎጂ ከተማ  ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። በወንዙ ሙላት 30 ፍየሎችና ሁለት የቀንድ ከብቶች ከመሞታቸው በስተቀር በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አላደረሰም ብለዋል።

ከጊሎ ወንዝ በተጨማሪ የአኮቦ ወንዝ በተመሳሰይ ጊዜ ሞልቶ በመፍሰሱ በዚሁ ወረዳ በሚገኙ 15 ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አጋጥሟል።

በቀበሌዎች በሰብልና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ባለሙያዎች መሰማራታቸውንም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ተፈናቃዮች በአካባቢው በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢዎች እንዲጠለሉ ተደርጓል።

ለተፈናቃዮች ድጋፍ  የተወሰነ ገንዘብ የተመደበ መሆኑንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል። በተጨማሪም ከጎርፉ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለማከላከልም የሚመለከታቸው አካላት የተካተቱበት ኮሚቴ በቅርቡ ይቋቋማል ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኮርያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ፕሬዝዳንት ጋር ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ ተወያዩ። ኮይካ በኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በውሃና ግብርና ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን የልማት ድጋፍ አድንቀዋል። በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው የኮይካ ኃላፊዎች መግለፃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ የተፃፈ አዲስ መፅሃፍ በቀጣዩ ሳምንት ይመረቃል!! #TIKVAH_ETHIOPIA
ፖሊስ?

ይህ ቪድዮ ከሳምንት በፊት ነው የተቀረፀው፤ መሰል ድርጊቶች በፖሊስ አባላት በየሰፈሩ፣ በየመንደሩ ይፈፀማሉ። ሰዎች ወንጀል ሰርተው ከሆነ ሊጠየቁ የሚገባው በህጉና በስርዓቱ ሆኖ ሳለ እንዲህ አይነት ድርጊቶች በየአደባባዩ ዩኒፎርም በለበሱና ህግን እናስከብራለን ባሉ የፖሊስ አባላት ሲፈፀም መመልከቱ የሚያስዝን ነው፤ የሚያሳዝን ብቻ አይደለም የፖሊስ ስራ ላይ ጥያቄን የሚያስነሳ ነውና መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ቪድዮ: Dada/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሁለት የተከፈሉት የሲአን አመራሮች ውዝግብ! የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) "ህጋዊ አመራሮች ነን" በሚሉ ሁለት ወገኖች መካከል አለመግባባት መከሰቱ ተሰማ። በዶክተር ሚሊዮን ቱማቶ የሚመራው ቡድን የሲአን ህጋዊ አመራር መሆኑን በመግለጽ የንቅናቄውን የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ማካሄዱን አስታውቋል። በአቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመራው ሲአን በበኩሉ፣ ሌላኛውን ቡድን "የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በከባድ የስነ…
ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ፦

በሲዳማ ህዝብናድርጅታችን ላይ የተከፈተው የማጠልሸት ዘመቻ መሠረተ ቢስ ነው!

የሲዳማ ህዝብ ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘመናዊውን ቅርጽ ከያዘችበት ጊዜ ጀምሮ ለግንባታ ሂደትና እንደ ሀገርም ለመቀጠል እንደሌሎች ሀገርቷ ህዝቦች ሁሉ የበኩሉን አሻራ ያኖረና ህይወቱንና ንብረቱን የገበረ ህዝብ እንደሆን የአደባባይ ምስጥር ነው፡፡ ይህንን እውነት መቀበል የማይፈልጉና ለህዝብ ክብር የሌላቸው የውስጥና የውጭ ቡድኖች እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የሲዳማን ህዝብ ሀገር አፍራሽ እንደሆነ አድርገው ከማቅረባቸውም ባሻገር ሀገርን የማዳን ተግባር በእነሱ ትከሻ ብቻ እንደወደቀ አድርገው እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ጨቋኝ ፀረ-ዴሞክራት ኃይሎችና በንዋይ ያበዱ ጥቂት የብሔሩ ተወላጆቸ ህዝባችን ለዘመናት ሲታገልለት፣ሲሰደድለትና ሲሞትለት የቆየውን ራስ በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እንዲደናቀፍም በግልጽ መስራት ከመጀመራቸውም ባሻገር ይህ ፀረ-ህዝብ ተግባር በሀገራችን ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ከቅርብ ጊዜ ታሪክ መማር የሚፈልጉም አይመስሉም፡፡

በሌላ በኩል የህዝባችንን የታፈነ ድምጽ አስተባብሮ የሚሰራ ድርጅታችንን ለግል ጥቅም ለማዋል የሚፈልጉ አካላት ከፀረ-ህዝብ ኃይሎች ጋር በመተባበር ከድርጅቱ ፍቃድ ውጭ የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ እንዳሉ ለመገንዘብ ችለናል፡፡ እነዚህ ቡድኖች በሲዳማ የነፃነት ትግል ውስጥ አዲስ ክስተት ባይሆኑም ቅሉ ህዝባችን ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ እና ሊትገነባ የሚፈልጋት ፌደራላዊት ዴሞክራሲያዊ ሀገር እውን መሆን የሚያደርገውን መስዋዕትነት በየትኛውም ኃይል መቀልበስ በማይቻልበት ጊዜ መሞከራቸው በእጅጉ የሚያስታዝባቸዉ ከመሆኑም ባሻገር በሲዳማ ትግል ታሪክ ጥቁር አሻራ ያስቀመጡ የመጨረሻዎቹ መሆናቸዉ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

በተጨማሪም ሐምሌ11 ቀን 2011ዓ.ም በሲዳማ የተፈጠረውን መጠነኛ አለመረጋጋት መነሻ በማድረግ በዜጎች ላይ የተከፈተ የማሳደድ፣ የማሰርና የማሰቃየት ዘመቻ ተባብሶ ቀጥሏል፣ ትምህርት ቤቶች በአስነዋሪ ሁኔታ ወደ እስር ቤትነት ተቀይረዋል፣ የፍትህ ስርዓት በፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ነጻነቱን አጥቷል፤ ወጣቶችን እያፈኑ ወዳልታወቀ ስፍራ መዉሰድም የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን ይሀንን አሳሳቢና አስጊ ተግባር አጥብቆ እያወገዘ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡-

1ኛ. ህዝባችን ለዘመናት የወደቀለትን የመብት ጥያቄን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ለዉጥ ቀልባሽና ፖለቲካ ደላሎች የዘመናት መስዋእት የተከፈለበትን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ለማስተጓጎል እየተራወጡ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችን ድርጅታች እጅግ አጥብቆ እያወገዘ ከዚህ እኩይ ተግባራቸዉ እንዲትቆጠቡ አጥብቆ ያስጠነቅቃል፡፡

2ኛ. በድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከባድ የድሲፒሊን ግድፈት ታይቶባቸዉ በድርጅቱ የበላይ አካል በሆነዉ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዉሳኔ ከድርጅታችን አመራርነትና አባልነት የተሰናበቱ ግለሰቦች በሲአን ስም የሚያስተላልፉት ማንኛውም አይነት መልዕክቶች ድርጅታችንን የማይወክሉና የህዝብን ታሪካዊ ጥያቄ ከፀረ-ሲዳማ ኃይሎች ጋር በመተባበር ለማደናቀፍ የተማማሉ ግለሰቦች ተግባር እንደሆነ እያሳወቅን እነዚህ ግለሰቦችም ከዚህ ፀረ-ህዝብ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ አጥብቀን እናስጠነቅቃለን፤

3ኛ. ድርጅታችን በከባድ የዲሲፒሊን ግድፈት ከድርጅቱ አመራርነትና አባልነት ያሰናበታቸዉን ግለሰቦች ለሁሉም የሚዲያ አካላት በጽሁፍ ያስተላለፈ ቢሆንም አንዳንድ ሚዲያዎች ከነኝህ ግለሰቦች ጋር በድርጅታችን ስም የሚያደርጉት የሚዲያ ግኑኝነት ህዝባችንን ለማዋከብ ዓይነተኛ መሳሪያ ስለሆነ ሁሉም ሚዲያዎች ህጋዊነትን እንዲከተሉ በዚህ አጋጣሚ በድጋሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

4ኛ. የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የሌለበት የፍትህ ስርዓት መስፈኑ ለዴሞክራሲ ማበብና ለሀገራችን ሰላምና አንድነት አማራጭ የሌለው እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል፡፡ በመሆኑም አሁንም በሀገራችን እየታየ ያለው የፍትህ ተቋማት በፖለቲካ ፍላጎት የሚመሩ መሆኑ ሀገራችንን ዳግም ለችግር እንዳይዳርግ መንግስት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደረግ እናሳስባለን፤

5ኛ. የክልሉ መንግስትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሲዳማ ህዝብ ጥያቄን በህዝቤ- ውሳኔ ለማረጋገጥ የተደረሰበትን ደረጃ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም የተከበራችሁ የሲዳማ ህዝብና አብሮ ነዋሪ የሆናችሁ ህዝቦች ከጥንት ጀምሮ የመጣዉን አብሮ የመኖር ባህልና እሴት አስጠብቃችሁ ለሀገራችን ሰላምና አንድነት መጠናከር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንዲታደርጉ እያሳሰብን በሌላ በኩል ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ለዘመናት ሲያነሳ የነበረዉን ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ለማደናቀፍ ከፀረ-ህዝብ ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለዉ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ጭፍን ግለሰቦችንና ቡድኖችን በንቃት በመከታተል እንድትታገሏቸዉ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

ሲዳማ አርነት ንቅናቄ
ነሐሴ 21 ቀን 2011ዓ.ም
ሐዋሳ፣ ሲዳማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአክሱም...

"ኣገር ኣቀፍ የተማሪዎች ህብረት #በመቐለ የነበረው ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ ኣሁን ደግሞ ከ14 ዩንቨርስቲዎች የተውጣጣ ቡድን ትናንት ነጃሺ ታሪካዊ መስጊድ ዛሬ ደግሞ በኣክሱም ጉብኝት እያደረግን እንገኛለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲአን ትክክለኛው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፌስቡክ ገፅ ይህ 5,740 like ያለው ነው። ከዚህ ቀደም ዋዜማ ሬድዮና ሌሎች ስለሀዋሳው የቀድሞ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ መረጃ አገኘን ብለው ያሰራጩት ከዚህ ትክክለኛ ገፅ የተወሰደ አይደለም። በሌላ አገላለፅ #በሀሰተኛ ገፅ ተታለው ነበር።

የሲአን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 5,740 like ያለው ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‘አፋር ኡጉጉሞ” ወደ አገሩ ገባ!

በኤርትራ በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ የነበረው ”አፋር ኡጉጉሞ” የተባለው ድርጅት አመራሮች ትናንት በሰመራ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው። የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ (አብዴፓ)ሊቀመንበር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳስታወቁት ድርጅቱ ከኤርትራ ወደ አገሩ የተመለሰው በመጋቢት 2011 በተደረገ ስምምነት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-2

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ አህመድ🛫ወደ ጃፓን አቅንተዋል!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ጃፓን አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ነው ወደ ጃፓን ያቀኑት።

በጃፓን ቆይታቸውም በጃፓኗ ዮኮሃማ ከተማ በሚካሄደው 7ኛው የጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል። ከጉባዔው ጎብ ለጎንም ከጃፓን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጃፓን-አፍሪካ የልማት ፎረም (የቲካድ ) ላይ እንዲሳተፉ እና ከጉባዔው ቀደም ብሎም በጃፓን ጉብኝት እንዲያደርጉ በጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጥቂ ቀርቦላቸው እንደበረ ይታወሳል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጉራጌ ልማት ማህበር ከህብረተሰቡ ተወላጆች ያሰባሰበውን 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከጉራጌ ልማት ማህበር እና ከህብረተሰቡ ተወላጆች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጉራጌ ልማት ማህበር ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላደረገው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሶማሌ ክልል ለስድስት ቀናት በዘመቻ በተሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ647 ሺህ በላይ ህፃናት መከተባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት መማክርት ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናገሩ።

https://telegra.ph/ET-08-27

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተውን የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ከፌዴራል መንግስት ድጋፍ ሊደረግለት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገለጸ። ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በኬሚካል የተነከረ የአጎበር አቅርቦት ድጋፍ ሊደረግለት መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር ተናግረዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ቺኩንጉንያ ቫይረስ ምንድነው? ቺኩንጉንያ ቫይረስ (ቺክቭ) በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ቺክቭ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህምምን ያስከትላል። ቺክቭ አብዛኛው ጊዜ ሞትን አያስከትልም፣ ነገር ግን የሚወልዳቸው የጤና እክሎች ነገሮችን ከመስራት እስከማገድ የሚደርሱ ሆነው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ለከባድ ተጨማሪ በሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ቫይረሱን እና ኢንፈክሽኑ የምንከላከልባቸው መንገዶችን የተመለከተ እውቀት መጨበጥ ወሳኝ ነው። የሚወስዷቸው ጥንቃቄዎች ከሌሎች በትንኞች የሚመጡ በሽታዎችም ይከላከልልዎታል።

#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
 በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
 ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
 ራስ ምታት
 የጡንቻ ህመም
 የጀርባ ህመም
 ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)

በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
 ህጻናት (<1 ዓመት)
 አረጋውያን (>65 ዓመት)
 እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።

*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*

ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም

#DCSSH

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
 በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
 ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
 ራስ ምታት
 የጡንቻ ህመም
 የጀርባ ህመም
 ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)

በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
 ህጻናት (<1 ዓመት)
 አረጋውያን (>65 ዓመት)
 እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።

*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*

ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም

#DCSSH

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በቺክቭ ተጠቂቻለሁ የሚል ጥርጣሬ ካደረብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ትኩሳት እና የመገጣጠሚያ ህመም ለመቀነስ መድሀኒቶችን መጠቀም ጥቅም ሊኖረው ይችላል። ሐኪም ያማክሩ።

ቺክቭ ይዞኝ ሉሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ካደረብዎ፦
 የታይብዎ ምልክቶችን መዝግበው በመያዝ ወደ ሐኪም ይሂዱ።
 ራስዎን ተጨማሪ በትንኝ ከመነከስ ይከላከሉ።
 በቺክቭ ከተያዙ በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ እራስዎን ከትንኝ ንክሻ መከላከል ይኖርብዎታል።

ምን ማድረግ አለብኝ?

#ይልበሱ
ረዥም፣ ቀለል ያለ እና ቀላል ቀለም ያለው ልብስ ይልበሱ።

#ፈሳሽ_ማድረቅ
እቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ያለ ማንኛውም ያቆረ ውሃ ያስወግዱ።

#ማታ እና #ጠዋት
ማታና ጠዋት ትንኞች በብዛት የሚንቀሳቅሱበት ጊዜ በመሆኑ በተቻለ መጠን ከቤት አይውጡ።

#DCSSH

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia