TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ይቅርታ ጠየቀ!

የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በ2 አባላቱ ለተፈጠረው ድርጊት ኅብረተሰቡን ይቅርታ ጠየቀ!

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ነሐሴ 20 ቀን 2011 ላይ ‘ሕጋዊ የኮሚሽን ሥራ እንሠራለን’በሚሉ እና ‘እኛም ሰፈራችን ስለሆነ እንሠራለን’ በሚሉ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ የፖሊስ አባላት የወሰዱት እርምጃ አነጋጋሪ ሆኗል።

በአካባቢው የነበሩት ፖሊሶች ፀብ ውስጥ የነበሩትን ግለሰቦች ‘ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሔዳችሁ ዳኝነት ታገኛላችሁ’ ቢሉም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አለመግባባት ተፈጥሮ የፖሊስ አባላቱ የተወሰኑ ሰዎችን መደብደባቸውን የአ.አ. ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽን እና የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢቲቪ አራት ማዕዘን ዝግጅት ክፍል አረጋግጠዋል።

ፖሊሶቹም ራሳቸው ደንብ ልብሳቸውን ለብሰው፣ ሥራ ላይ ተሰማርተው እያሉ፣ አንደኛው ላይ ከእነ ልብሱ ፖሊሱን በማነቁ፣ ሌላኛው ላይ ደግሞ መሣሪያ ጭምር ለመቀማት እና የመተናነቅ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል።

በዚህም የተነሣ ፖሊሶቹ ነገሩን ለማብረድ ጥይት ተተኩሰዋል፣ድብደባም ተፈጽሟል በማለት ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

የተፈጠረውን ድርጊት ተከትሎ የፖሊስ አባላቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ማጣራት እያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። ሆኖም ለድርጊቱ የአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡን ይቅርታ ይጠይቃል ብለዋል።

https://telegra.ph/ETH-08-27-3
ሰኔ 15 ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌን አጓጉዤያችኋለሁ ያሉ ምስክር ቃላቸውን ሰጡ!

የሰኔ 15ቱን የባህር ዳር ጥቃት #ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌን ወደ ጎንደር መስመር አጓጉዤያቸዋለሁ ያሉ ሹፌርን የምስክርነት ቃል አደመጠ። በጥይት ቆስለው ሆስፒታል የሚገኙት ሹፌሩ ፍርድ ቤት የቀረቡት በተሽከርካሪ ወንበር ነው።

የሹፌሩን የምክርነት ቃል ዛሬ ረፋዱን በነበረው ችሎት ያደመጠው በእነ ብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠረጠሩ 48 ሰዎችን ቅድመ ክስ እየተመለከተ የሚገኘው የባህር ዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት ነው። ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን 17 ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በችሎት የቀረቡት ሁለቱ ብቻ ናቸው። 

ሁለቱም ምስክሮች የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት በባህር ዳር በተገደሉበት ዕለት መኪና የማሽከርከር የስራ ስምሪት እንደተሰጣቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። በሰኔ 15 ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነውን በመኪናቸው ማጓጓዛቸውን የተናገሩት አንደኛው ሹፌር ከዚያ አስቀድሞ ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተናግረዋል።

#DW

ይህን ይጫኑና ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-4
የኦነግ ወታደራዊ ዩኒፎም ተያዘ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው!

በወልዲያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ የተያዘው ወታደራዊ ዩኒፎርም መሰል አልባሳት የእኔ ነው ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ መነሻዉን መቐለ ያደረገ አይሱዙ ወልዲያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ሲደርስ በፍተሸ ጣቢያ ሰራተኞች ተይዞ ፍተሻ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ምክንያቱ ደግሞ የጫነዉ አልባሳትን ምንነት ለማረጋገጥ ነዉ ተብሏል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰለሞን ወርቁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ መኪናዉን ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ቁጥጥርና ጥበቃ ሰራተኞች /ስካዉት/ የሚለብሱት ዩኒፎርም ነበር ብለዉናል፡፡ መኪናዉም 3 ሺህ የዩኒፎርም አልባሳትና 170 ጃኬቶችን ጭኖ ከመቀሌ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ እንደነበረም ነዉ የተናገሩት፡፡

አልባሳቱ #የተጫነዉ በግል መኪና መሆኑና አልባሳቱ የኛ መሆኑን የሚያመለክት ደብዳቤ በአሽከርካሪዉ እጅ አለመገኘቱ ለጥርጣሬዉ መነሻ እንደሆነም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተነጋግረን ማረጋገጫ ደብዳቤ እንድንጽፍ በጠየቁን መሰረት ደብዳቤ ጽፈናል፤በነገዉ እለትም መኪናዉ ወደ አዲስ አበባ ይንቃቀሳል ብለን እንጠብቃልን ነዉ ያሉት፡፡

ከዚህ ባሻገር ግን አልባሳቱ የኦነግ ነዉ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰዉ ወሬ #ከእዉነት_የራቀ_ነዉ፤ አልባሳቱ የኛ ነዉ፤ ለዱር እንስሳት ጥበቃ ለመተማሩ ሰራተኞች የተዘጋጀ ዩኒፎርም ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በፌደራል ደረጃ በሚተዳደሩ 13 ብሄራዊ ፓርኮች 790 ስካዉቶች በስራ ላይ ተሰማርተዉ ይገኛሉ፡፡

Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ2011 በጀት አመት ሊሰወር እና ሊጭበረበር የነበረ 50 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ከሂሳብ እና ከኦዲት ባለሙያዎች ጋር ውይይት በአዲስ አበባ እያደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ሸዋ ዞን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰስ ያስከተለው ጎርፍ 3ሺህ 500 ሄክታር የእርሻ ማሳ ላይ የተዘራ ሰብልን ከጥቅም ውጪ ማድረጉን የዞኑ ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጉታ ቡልቻ ለኢዜአ እንደገለጹት ጎርፉ ያደረሰው ጉዳት ኤጀርሳለፎ እና ኤጄሬ በተባሉ ወረዳዎች በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ውስጥ ነው። በዚህም በ3ሺህ 500 ሄክታር ማሳ በመጥለቀለቁ ተዘርቶ የነበረ የስንዴ፣ የበቆሎ፣የማሽላና ሌላም ሰብል ከጥቅም ውጭ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነሐሴ 24 ጀምሮ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ። ምከር ቤቱ በቆይታዉ የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ምክር ቤቱ የክልሉን የጠቀላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስራ ቤትን ሪፖረትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና...

የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አሰቀድመው በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሀዋሳ ከተማ ላይ እየመከሩ ነው። ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚላውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎች የሚመለከት ሁላት አንኳር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ መድረኩን የመሩት በሚንስትር መዓረግ የዲሞክራሲ ማዕከል ምክትል ዋና አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ እንዳሉት የምክር ቤቱ አባላት በሀገራዊና ክልላዊ ነበራዊ ሁኔታ ላይ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ የመስፈጸም አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማስቻል የታሰበ ነው። በክልል ደረጃ በተነሳዉ የአደረጃጀት ጥያቄ በምሁራን የጠናው ጥናት ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ምክክር የሚደረግበት እደሆነም ተናግረዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱዳናውያን ሴቶች አደባባይ ወጡ!

ሱዳናዊያን ሴቶች በሽግግር መንግስቱ ምስረታ የሴቶች ተሳትፎ #አልተረጋገጠም ሲሉ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ሱዳንን ለሦስት አስርት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዑመር ሃሰን አል-በሽር በሕዝባዊ ተቃውሞ ባለፈው ሚያዝያ ላይ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላም ሱዳን ሰላም አልነበራትም፡፡

ከበርካታ ግጭቶች እና ተቃውሞዎች በኋላ ከሦስት ቀናት በፊት ለሚቀጥሉት 21 ወራት ሀገሪቱን የሚመሩ የሽግግር መንግስት አባላት ተሰይመዋል፡፡ የሽግግር መንግስቱ ከተቋቋመ እና ቃለ መሃላ ከፈፀመ በኋላ ትናንት ሰኞ በሱዳን ኦምዱርማን ሴቶች ‹‹በሽግግር መንግስቱ መስረታ በውሳኔ ሰጪነት ቦታ ላይ የሴቶች ተሳትፎ የለም›› በሚል ለተቃውሞ ጎዳና ወጥተዋል፡፡

በኡማ ፓርቲ መቀመጫ ኦምዱርማን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሰልፈኞቹ ‹‹ትግላችን ለሴቶች እኩልነት፣ ፍትሃዊነት እና የሴቶችን ነፃነት እስኪረጋገጥ ድረስ ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡ ሴቶች እንደማንኛውም የተፎካካሪ ፓርቲ ተደራጅተን ለመብታችን እንከራከራለን ወይም ደግሞ በሽግግር መንግስቱ አባላት ውስጥ ሴቶች በውክልና ሳይሆን 50 በመቶ የሚሆነውን ቦታ ሊሸፍኑ ይገባል ብለዋል፡፡ የውክልና መብታቸው እስኪረጋገጥ ድረስም ተቃውሞው እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካ ኒውስ/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በቀጣዩ ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚወዳደር አስታውቋል። በምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ገና ያልጨረሰው ኦነግ ፤ በመላ ሃገሪቱ ምርጫ መወዳደር የሚያስችል ቁመና አለኝ ብሏል። ከምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሰርተፍኬት የማግኘት ሂደቱን ከጨረሰ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-08-27-5

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎች ድርጅቶች መካከል በትብብር የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የታገደበት ዋና ዋና ምክንያቶች፦

1. በትብብር ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት ባልተዘረጋበትና ተቋማት ተገምግመው ብቁ መሆናቸው ባልተረጋጠበት ሁኔታ እየተሰጠ ያለው ትምህርት ህጋዊና አግባብነት የሌለው እንዲሆን የሚያደርጉት ጉዳዮች ፡-

1.1. ዩኒቨርስቲዎች በትብብር የሚያስተምሩት ከኤጀንሲው እውቅና ከተሰጣቸው የግል ከፍተኛ ት/ተቋማትጋር ከሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቅና ባገኙበት ግብዓት ላይ ተጨማሪ ተማሪ ማስተማር ህገወጥ ከመሆኑም በላይ በጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር በመሆኑ፤

1.2. ዩኒቨርስቲዎች በትብብር የሚያስተምሩት ከኤጀንሲው እውቅና ካልተሰጣቸው ለሌላ አገልግሎት ከተመሰረቱ ተቋማት ጋር ከሆነ ትምህርቱ የሚሰጥበት ሁኔታ አነስተኛ የጥራት መለኪያ መስፈርቶችን ስለማሟላታው ባለመረጋገጡ የሚሰጠው ትምህርት ጥራት ያለውና አግባብ መሆኑ ስለማይታወቅ፤

1.3. ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት የሚሰጡት በመጀመሪያ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃት ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎችን በመከራየት ከሆነ ተማሪዎች ምንም አይነት የቤተ-መጸሀፍት፣ የዲሞኒስትሬሽን፣ የላቦራቶሪና የኮምፒዩተር ማእከልና ሌሎች ለትምህርቱ አጋዥ የሆኑ አገልግሎቶች በሌሉበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ ለከፍተኛ የጥራት መጓደል የሚዳርግ በመሆኑ፤

****

2. የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከተቋማቸው (እውቅና ከተሰጣቸው ካምፓሶች) ብዙ ኪሎ-ሜትር በመራቅ እውቅና ባላገኙበት ካምፓስ (የማስተማሪያ ቦታ) ማስተማራቸው

2.1. ዩኒቨርስቲዎች መደበኛ ስራቸው ላይ እንዳያተኩሩ ችግር ከመፍጠሩም በላይ ከተሰጧቸው ዋና ዋና ተልእኮዎች መካከል ጥናትና ምርምርንና የማህበረሰብ አገልግሎትን በአጥጋቢ ሁኔታ እንዳያከናውኑ የሚያደርጋቸው በመሆኑ፣

2.2. መምህራን በተደጋጋሚ ከተቋማቸው ውጭ ስለሚንቀሳቀሱና ለረጅም ጊዜ ከተቋማቸው ርቀው ስለሚቆዩ መደበኛ ተማሪዎች በቂ ትምህርትና እገዛ እንዳያገኙ ስለሚያደርግ፤

2.3. የመንግስትን ሀብትና ንብረት ላልታለመለት አላማ እንዲያውሉ መደረጉ፤

****

3. አብዛኞቹ የትብብር ትምህርቶች የሚሰጡት ተባባሪ ተቋማት ከማስተማር የሚሰበሰበውን ፋይናንስ እንዲያስተዳድሩ በማድረግ በመሆኑ፣

3.1. ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ዩኒቨርስቲዎች ከመንግስት የፋይናንስ ስርዓት ውጭ የመንግስትን ሀብትና ንብረት አላግባብ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ አጋጣሚ ስለሚፈጥርና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስርዓትን በማዘጋጀት በሚነስትሮች ም/ቤት በማጸደቅ ተግባራዊ ያደረገውን አሠራር ስለሚጥስ፣

3.2. ተባባሪ ተቋማትን የሚመርጡበት የማወዳደሪያ መስፈርት ሂደትና የገቢ ክፍፍል ሁኔታ ግልጸኝነት የጎደለውና የመንግስትን መመሪያና ስርዓት ያልተከተለና ለኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር የተጋለጠ በመሆኑ፤
በአጠቃላይ በሀገራችን የትምህርት ጥራት ያለበት ሁኔታ ማንንም ቅን አሳቢ ዜጋ የሚያስጨንቅ በሆነበትና መንግሥትም ከመቹውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ በሚሰራበት ወቅት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሀገርን ጥቅም በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ጥራትና አግባብነት ላይ በማተኮር በክፍለ አሀጉር፣ በአሀጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሚያደርጋቸው ሥራ ላይ ከማተኮር ይልቅ እሴት በማይጨምርና በተቋማቸው ከሚሰጡት ትምህርት በባሰ መልኩ ብቃቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ትምህርት መስጠቱ አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ ወደፊት ጥናት ላይ ተመስርቶ ሥርዓት እስኪበጅ ድረስ የትብብር ትምህርት የታገደ መሆኑን በድጋሚ እናስታውቃለን፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ወደ አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ለመግባት የሚያስፈልጉ የመመዝገቢያ መስፈርቶች ይፋ ተደርጓል እየተባለ በአንዳንድ የማዕበራዊ ሚዲያዎች የሚወራው ውሸት ነው። ASTU/AASTU የመመዝገቢያ መስፈርት ገና ይፋ አልተደረገም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለአፍሪካውያን ሴት የሥራ ፈጣሪዎች የቡድን 7 አባል ሃገራት 251 ሚሊየን ዶላር መመደባቸው አስታውቀዋል።

Via #CGTN/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎች ድርጅቶች መካከል በትብብር የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የታገደበት ዋና ዋና ምክንያቶች፦ 1. በትብብር ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት ባልተዘረጋበትና ተቋማት ተገምግመው ብቁ መሆናቸው ባልተረጋጠበት ሁኔታ እየተሰጠ ያለው ትምህርት ህጋዊና አግባብነት የሌለው እንዲሆን የሚያደርጉት ጉዳዮች ፡- 1.1. ዩኒቨርስቲዎች በትብብር የሚያስተምሩት…
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ የሚሰጠው ስልጠና ዕውቅና የለውም ተባለ!

ዩኒቨርስቲው ከየካቲት 2007 እስከ ጥር 2010 ድረስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን በመመዝገብ እንዲያስተምር ዕውቅና ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ከትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ውጪ አሁንም ድረስ እያስተማረ በመገኘቱ ከዕውቅና ውጪ መሆኑ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ከትምህርት ሚኒስቴር በወጣ መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ጳጉሜ 4/2007 ዩኒቨርስቲው እንዲያስተምር የተሰጠውን ዕውቅና እንደተሻረና የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች እንዲያስጨርስ ደብዳቤ ተፅፎለት ነበር። ይሁን አንጂ ዩኒቨርስቲው አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መገኘቱ በኤጀንሲው በተጨባጭ ታይቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ሰኔ 27/2011 የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኹሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። ነገር ግን ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የርቀትና ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ መርሃግብር እያካሔደ እንደሚገኝ ታውቋል። ይህም ከኤጀንሲው ዕውቅና ያልተሰጠው ስለሆነ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅና ከሚኒስቴሩ ጋር በመመካከር አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድበትም ተገልጿል።

Via #AddisMalda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ #በድርቅ ለተጠቁ አራት ሃገራት የሚውል የ55.9 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያስተባበረ መሆኑን ዘ-ኢስት አፍሪካ ዘገበ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድ እሽግ 12 ደብተር፣ 2 እስክሪብቶ፣ 2 እርሳስ፣ 2 ላጲስ ፣ 2 መቅረጫን የሚያካትት ሲሆን ቤተሰባችን በየዓመቱ በእርስ በእርስ ትውውቅ፣ በቤተሰባዊነት፣ በጓደኝነትና በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚፈጠሩ ትስስሮች በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ እሽጎችን እየሰበሰበ በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለተቸገሩ ህጻናት እያደረሰ ይገኛል፡ እነሆ ዘንድሮ 8ኛ አመቱን ሲያከብር ለ 13,000 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ተነስተናልና እናንተም ከጎናችን በመሆን እሁድ ነሃሴ 26 በ Getfam Hotel ተገኝተው አስደሳች የክረምት ጊዜን ከቤተሰባችን ጋር እንድታሳልፉ በአክብሮት እንጋብዛለን

#onepackforonechild #summerfun #gooddead #onecanreallymakeadifference
ከሰሞኑ በሰደድ እሳት እየነደደ ስለሚገኘው የአማዞን ደን አንዳንድ መረጃዎች፦

• አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡

•ጥቅጥቅ ደኑ 9 ሃገራት ላይ የሚያርፍ ሲሆን 2/3ተኛው ወይም 60 በመቶው የአማዞን ክፍል የሚገኘው ብራዚል ነው፡፡

•ስፋቱ የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡

•አማዞን ሃገር ቢሆን ኖሮ የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር፡፡

•በደኑ ውስጥ ከ30ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ ከነዚህ ውስጥ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ እና 2ሺህ አባላት ያላቸው 350 ነባር ጎሳዎች ይገኙበታል፡፡

•ከ350 ነባር ጎሳዎች መካከል 100 ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው አያውቁም፡፡

•አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡

•በየሁለት ቀናት ልዩነት አዳዲስ የእጽዋት ወይም የእንስሳት ዝርያዎች በአማዞን ይፈጠራሉ፡፡

•40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ።

•በጥቅጥቅ ደኑ 400 ቢሊዮን ዛፎች ይገኛሉ፡፡

•የአለማችን 20 በመቶ ኦክስጅን የሚመረተው በአማዞን ደን በመሆኑ “የፕላኔታችን ሳንባ ” በመባልም ይታወቃል፡፡

•አማዞን ከ90 እስከ 140 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን በውስጡ በመያዝ የካርቦን ልቀቱን ይቆጣጠራል፡፡

•80 በመቶ የአላማችን ምግብ በአማዞን የበቀለ ነው፡፡

•120 የሚጠጉ የመድሃኒት አይነቶች የሚገኙት ከዚሁ ደን ነው፡፡

•አናኮንዳን የመሳሰሉ አደገኛ የእንስሳት ዝርያዎች የሚገኙት እዚሁ አማዞን ጫካ ውስጥ ነው፡፡

•ደኑ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ እጽዋቱ ጸሃይ የሚያገኙት ከ2 እስከ 5 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ምንጭ፡ አዲስ ቴሊቪዥን/ሲ ኤን ኤን እና የተለያዩ ድረ ገጾች/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኑ ትውልድ እንገንባ!

ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የመማሪያ መፅሃፍትን ይለግሱ!

#መቐለ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት በተለይም የዘንድሮ ተፈታኞች የመማሪያ መፅሃፍትን ለመለገስ የምትፈልጉ👉ኤርሚያስ ደጀኔ/0912178520/፣ ፊራኦል መስፍን/0923602445/

#ራያ_ቆቦ እና አካባቢው የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት በተለይም የዘንድሮ ተፈታኞች የመማሪያ መፅሃፍትን ለመለገስ የምትፈልጉ👉ሉላይ/+251949256094/

#ወላይታ_ሶዶና አካባቢዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት በተለይም የዘንድሮ ተፈታኞች የመማሪያ መፅሃፍትን ለመለገስ የምትፈልጉ👇
+251913776084/Aso/
0926172318/Beza/
0926172318/Gedi/
+251936455130/Bereket/
0968787670 /Zegeye/

በሁሉም ክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰቢያ ዘመቻ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ዜጎች ወደ ውጭ ሃገራት በህጋዊ መንገድ የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ ከሌሎች ሃገራት ጋር የተደረሱ ስምምነቶች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በውጭ ሃራት በአስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ውስጥም ከ140ሽህ በላይ የሚደርሱትን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ለአዲስ ቴሌቪዥን አስታውቀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው የፌደራል ስርአቱን የማይንድ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው የፌደራል ስርአቱን የማይንድ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት አለው በሚል ከህብረተሰቡ ሰፊ አስተያየት መሰጠቱን መግለጫው ተመልክቷል፡፡

የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በሰጡት ማብራሪያ በሁሉም ት/ቤቶች ቢያንስ ለ1 አመት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሰጥ አስገዳጅ መሆኑ ፍኖተ ካርታውን ከዚህ ቀደሙ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አዲሱ ፍኖተ ካርታ የተሟላ የትምህርት ስርአትን ይከተላል ያሉት ሚንስትሩ እንደ ጆኦግራፊ እና ታሪክ ያሉ የትምህርት አይነቶች በአገር በቀል እውቀት እንዲቃኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ የሚፈቅድ ሲሆን የፌደራል የስራ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ በፍኖተ ካርታው ምክረ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ይህ በክልሎች ስልጣን የሚወሰን መሆኑን የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ገረመው ሁሉቃ ገልፀዋል፡፡ ፍኖተ ካርታው 36 የተለያዩ ነጥቦች ያሉት ሲሆን ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዘመናዊ ህክምናን ከመንፈሳዊ ህክምና ጋር በማስተሳሰር ለህሙማን የተሻለ ፈውስ ማምጣት የሚቻል በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለፀ። የሃይማኖት መሪዎችና መንፈሳዊ አባቶች በአለርት ህክምና ማዕከል የሚገኙ ህሙማንን ጎብኝተዋል፤ ለህሙማኑም መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥተዋል።

ማዕከሉ የህክምና አሰጣጡን ከመንፈሳዊው ጋር ማስተሳሰር የሚያስችል ሳምንት “አብሮነት፣ ርህራሄና ስነ-ምግባርን በተላበሰ የህክምና አገልግሎት መስጠት” በሚል መሪ ሐሳብ ሁለተኛ የጉብኝት ሳምንት ዛሬ ጀምሯል።

የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና እና የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የኃይማኖት አባቶች በጉብኝቱ የተገኙ ሲሆን ፅኑ የህሙማን መታከሚያ የድንገተኛ አደጋ ክፍልን፣ የማዋለጃና የቀዶ ጥገና ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

አባቶቹ በጉብኝቱ ወቅት ህሙማንን አፅናንተዋል፣ እንደየዕምነታቸው የቡራኬና የፀሎት አገልግሎትም ሰጥተዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኑ ትውልድ እንገንባ!

#ሰበታ የምትገኙ 0932540523/ያሬድ ለማ/ ፣ 0921421493/ያብስራ ካሳ/

#አዲስ_አበባ የምትገኙ 0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/፣ 0924140293/መባ/

#ድሬዳዋ የምትገኙ 0915034762/መሃሪ/

#አዳማ የምተገኙ 0949377735/ሰላም/

#ሀዋሳ የምትገኙ +251926429534/ተስፋ/፣ +251935932153/ብስራት/

በሁሉም የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630

የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች በትልቁ አሻራችሁን እንደምታሳርፉ ምንም አንጠራጠርም!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰቢያ ዘመቻ!