TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ⬇️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ባቀረቡት #የዋስትና ጥያቄ ላይ ለመወሰን #ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው እለት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ፥ ወይዘሮ ራሃማ መሐመድ፣ አቶ አብድራዛቅ ሰህኒ እና አቶ ሱልጣን መሐመድ፥ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ የወንጀል ችሎት መቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህ ወቅትም የተለያየ የጤና እክል እንዳለባቸው በመጥቀስ፥ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የዋስትና ጥያቄ ይፈቀድልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄውን በመቃወም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሚያካሂደው ምርመራ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ #ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን #የዋስትና ጥያቄ #ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የፈቀደው።

በዚህም መሰረት የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ለመስከረንም 4/ 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን⬇️

በኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን በስራ ማቆም አድማ የተጠረጠሩት 9 ግለሰቦች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከ70 ሚሊየን 944 ሺህ ብር በላይ #ከሲራ ማድረሳቸውን መርማሪ ፓሊስ አስታወቀ።

መርማሪ ፓሊስ ቀሩኝ ያላቸውን ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

በዛሬው ዕለት በፌዴራል የመጀመሪያው ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የወንጀል ችሎት በባለፈው ቀጠሮ ለፓሊስ በሰጠው የስምንት ቀን የምርመራ ጊዜ መነሻ በማድረግ የተሰሩ የምርመራ ስራዎችን፣ ቀሪ ምርመራዎችንና የተጠርጣሪዎችን አስተያየት አድምጧል።

በዚህ ወቅት መርማሪ ፓሊስ በተሰጠው ጊዜ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን በመጥቀስ በአየር መንገዱ ላይ የ70 ሚሊየን 944 ሺህ ብር ኪሰራ እንደደረሰም መረጃ መሰብሰቡን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

ፓሊስ ተጠርጣሪዎቹ አድማውን በተመለከተ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች ጋር የተለዋወጧቸው መልዕክቶችን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ማግኘቱንና በክልል ከሚገኙ ቅርንጫፍ ሰራተኞች የምስክር ቃል መቀበል መጀመሩን ገልጿል።

የቀሩትን የክልል ምስክሮች ቃል ለመቀበል፣ የደረሰውን ኪሳራ መነሻ ያደረጉ ሰፊ የምርመራዎችን ለማድረግ 14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ፓሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣረዎች በጠበቃቸው በኩልና በራሳቸው አንደበት የአየር መንገዱ ሰራተኛ እንዳልሆኑና የጠየቅነው መብትና ጥቅማችን ነው ፓሊስ ከዚህ ውጭ በማያያዝ በእስር ሊያቆየን ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የሌሎችን ፊርማ አስመስሎ መፈረም በሌላ ወንጀል የሚያስጠይቅና ከዚህ ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ከዚህ በላፈ ቤተሰቦቻቸው በችግር ላይ እንደሆኑና ደመወዛቸው መታገዱን በመግለፅ ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት በማስገባት በዋስ እንዲለቃቸውና በስራ ላይ ሆነው ምርመራውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

መርማሪ ፓሊስ በበኩሉ አየር መንገዱና ሲቪል አቬሽን ተመጋጋቢ መስሪያ ቤት መሆናቸውን በመግለፅ በምርመራው ከስራ ማቆሙ በስተጀርባ ሌሎች ጉዳዮች መኖራቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ሰፊ ምርመራ ያስፈልጋል ብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ የሀገሪቱ ሲቪል አቬሽን የአየር ክልል ለአደጋ የተጋለጠ መሆኑን ለተለያዩ ሀገራት መልዕክት ሲልኩ እንደነበረና ይህም በምርመራ የተገኘ መሆኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ግለሰቦች በዋስ ቢወጡ ምስክር የሚያሸሹና ምርመራውን የሚያደናቅፉ በመሆናቸው ዋስትናውን ተቃውሟል።

የሁለቱን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎችን #የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፓሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የሰባት ቀን ጊዜ በመስጠት ለመስከረም 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " - ፕ/ር መስፍን አርአያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

አሁንም " ወደ ምክክር መድረኩ ኑ " ያለው ኮሚሽኑ ፤ ለታጠቁ አካላት ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና በኮሚሽኑ እንደሚያመቻች ገልጿል።

ይህ የተሰማው በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክልል ማህበረሰብ ተወካዮች የማጠቃለያ ልየታ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

" በትጥቅ ትግል ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ #ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ " የሚያዋጣን ይሄ ነው ፤ በየታች ድረስ ሄደን ያገኘነው ህዝባችን ሰላምን እንደሚፈልግ ነው የገለጸለን  " ብለዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው ፥ እንዲህ አይነት ምክክር ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።

" ይህን አጋጣሚ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት ይገባል " ብለዋል።

" በተለይ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት ወደ መድረኩ ሊመጡና ሀሳባቸውን ሊገልጹ ይገባል ፤ እነሱ መጥተው በሚሳተፉበት ጊዜ ኮሚሽኑ ተገቢውን #የዋስትና_ጥበቃ /safe space/ የሚያመቻች ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼቨለ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia