TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን #የዋስትና ጥያቄ #ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የፈቀደው።

በዚህም መሰረት የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ለመስከረንም 4/ 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ⬇️

ፖሊስ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር #አብዲ_መሐመድ ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ 14 ቀን የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ተፈቀደለት።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በተጠርጣሪዎች የቀረቡትን አቤቱታ ሰምቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እይጠየቀን አይደለም ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም የሚል #ቅሬታ በጠበቆቻቸው በኩል እቅርበዋል።

መዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። የዋስትና መብታቸውም እንዲከበር እንዲሁ። ፍርድቤቱ የቀረቡት ጉዳዮችን በተመለከተ ፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማየሰጣቸው ይህን ጥያቄ #ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በመሆኑም ቀጣይ የቀጠሮ ጊዜ መስከረም 18 እንደሚሆን ፍርድቤቱ ወስኗል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባህር ዳር ከተማ በአምስተኛ ሳምንት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር እንዲደረግ የወጣው መርሐ ግብር እንዲራዘም ያቀረበውን ጥያቄ #ውድቅ አድርጎታል።

©SoccerEthiopia
@tsegawolde @tikvahethiopia
#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር#ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፍርድ ቤት ዛሬ የሰኔ 16ቱ ቦንብ ጥቃት ተጠርጣሪዎቹን ጌቱ ግርማንና ሌሎች 4 ተከሳሾችን ክሳችሁን ተከላከሉ እንዳላቸው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል፡፡ ሌሎቹ በቀጥታ ወንጀል አድራጊነት የተከሰሱት ብርሃኑ ጃፋርጥላሁን ጌታቸውና ባህሩ ቶላ ናቸው፡፡ ተከሳሾች “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም” በማለት ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመገናኘት የመስቀል አደባባዩን የድጋፍ ሰልፍ ለመበተን ሲሉ ቦንብ ጥቃት አድርሰው 2 ንጹሃን ሞተዋል፤ ከ160 በላይ የሚሆኑትን ደሞ #በማቁሰል ሽብር ፈጽመዋል- ይላል ክሱ፡፡ ዐቃቤ ሕግም ምስክሮቹን ለችሎቱ አሰምቷል፤ ማስረጃዎቹንም አቅርቧል፡፡ ተከሳሾች በበኩላቸው ፖሊስ ምርመራ ያደረገው በማናውቀው መንገድ ነው፤ ያለ አስተርጓሚ #ምርመራ ተደርጎብናል ብለው ያቀረቡት አቤቱታ #ውድቅ ሆኖባቸዋል፡፡ የተከሳሾች መከላከያ ምስክሮች ሰኔ 25 ይሰማል፡፡

Via wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

#የባሕር_ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የእነ ብርጋዴየር ጀነራል #ተፈራ_ማሞን ጉዳይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተመልክቷል፡፡ መርማሪ ፖሊስ #ተጨማሪ_መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚል 14 ቀናት ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን #ውድቅ አድርጎታል፡፡ እስከ ነሀሴ 13/2011 ዓ.ም ድረስ ክስ እንዲሰመርትም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•ባዮሎጂ፣
•ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም

በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•የታሪክ (History)፤
•ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች #ውድቅ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ባለፈው ሰኔ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል በእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ እና አፕቲቲዩድ ውጤቶቻቸው ይለካሉ።

ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፊዚክስ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ የጂኦግራፊ ፈተናዎች ለመመዘኛነት ተመርጠዋል።

ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ «ተማሪዎችንም ፍትኃዊ በሆነ መልክ ሊያወዳድር እና ከእነሱ ችሎታ ባሻገር ምንም መበላለጥን ሊያስከትል የማይችል ሆኖ ስላገኘንው እነዚህን ተጠቅመን ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መመደብ እና የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ወስነናል» ብለዋል።

ከ322 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የተቀመጡበት ይኸው ፈተና ችግር እንደነበረበት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚዓብሔር «ሰኔ 6 እና 7 የተፈተኑት ፈተና ትክክለኛ ይዘት አለው። ሰኔ 10 እና 12 [የተፈተኑት ፈተናዎች ውጤት] ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ሲታይ የመጨመር ባሕሪ ሲያሳይ የተወሰነ ቦታ ላይ ግን ከሚጠበቀው በላይ ጋሽቦ ሔዷል» ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ «መቁረጫ ነጥቡ የት ይሆናል የሚለውን ኤጀንሲው ለተማሪዎች እና ለወላጆች፤ ለዩኒቨርሲቲዎች ግልፅ የሚያደርግ ይሆናል» ብለዋል።

የመንግሥት ባለስልጣናቱ ውሳኔ ቀድሞም ቀውስ ውስጥ በገባው የትምህርት ዘርፍ ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆኗል። ለመመዘኛነት አያገለግሉም ተብለው ውድቅ የተደረጉት የፈተና ውጤቶች ችግሮች ምንድናቸው? በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምን አይነት ችግሮች ተፈጠሩ? #ተጠያቂውስ ማነው ለሚሉ ጥያቄዎች ባለሥልጣናቱ በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሚመሩት አጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩ ይመረመራል ተብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...የአውሮፓ ህብረት ለቀጣዩ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል" - ጆሴፍ ቦሬል የአውሮፓ ሕብረት ከመንግሥት ጋር ስምምነት ባለመደረሱ የምርጫ ታዛቢ የመላክ እቅዱን መሰረዙን ገልጿል። የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻለሁ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ትላንት ይፋ አደርጓል። የሕብረቱ የውጪ ጉዳዮች…
አምባሳደር ዲና ስለአውሮፓ ህብረት :

የአውሮፓ ህብረት በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን አልክም ማለቱ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን የሚጻረር አካሄድን አልቀበልም በማለቷ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያ ውጪ የራሴን ይዤ ልግባ ማለቱን አንስተው ለመግለጫው አንዱ ምክንያት ይህ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከምርጫው ጋር በተገናኘ የምርጫ ቦርድን ተግባር እንዲሁም ኃላፊነት የሚጸረር ጥያቄ አቅርቦ #ውድቅ ተደርጎበተል ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ ቀድሜ ይፋ ላድርግ የሚሉት ፋላጎቶቹ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለሚፈታተን እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ነው ህብረቱ ለስድስተኛው የሀገራዊ ምርጫ ታዛቢዎችን አልክም ያለው ብለዋል። ~ ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UNSC

ትላንትና ሌሊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሩሲያ በዩክሬን ላይ " ወረራ " ፈፅማለች በሚል ለማውገዝ በምዕራባውያን የሚመራ የውሳኔ ሃሳብ ቢቀርብም ሩስያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን [ veto power ] በመጠቀም #ውድቅ አድርጋዋለች።

ቻይናም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ድምፅ ከመስጠት ታቅባለች።

የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እነማን ደገፉት ? ማን ተቃወመ ? እነማን ድምፃቸው አቀቡ ?

#የደገፉ_ሀገራት

🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇮🇪 አይርላድ
🇦🇱 አልባኒያ
🇬🇦 ጋቦን
🇲🇽 ሜክስኮ
🇧🇷 ብራዚል
🇬🇭 ጋና
🇰🇪 ኬንያ

#የተቃወሙ

🇷🇺 ሩስያ

#ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ

🇨🇳 ቻይና
🇮🇳 ሕንድ
🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UN #ETHIOPIA

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈፅመዋል ለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲያጣራ ባቋቋመው ገለልተኛ ዓለማቀፍ መርማሪ ኮሚሽን ዙሪያ የውሳኔ ሃሳብ አቅርባ ድምጽ እንዲሰጥ አድርጋለች።

ኢትዮጵያ ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ላቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ጠቅላላ ጉባዔው የስራ ማስኬጃ በጀት #እንዳይፈቅድ የሚጠይቅ ነው።

በዚህም ዛሬ ምሽት በ193 አባል ሀገራት ባሉት የጠቅላላ ጉባኤው በጀት ኮሚቴ ድምፅ የተሰጠ ሲሆን ፦

👉 27 ሀገራት ደግፈዋል።

👉 66 ሀገራት ተቃውመዋል።

👉 39 ሀገራት ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል።

በአብላጫ ድምፅ የውሳኔ ሃሳቡ [ ኢትዮጵያ የጠየቀችው የስራ ማስኬጃ በጀት እንዳይፈቀድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ] #ውድቅ ሊሆን ችሏል።

የኢትዮጵያን የውሳኔ ሀሳብ ደግፈው ከቆሙ ሀገራት መካከል ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ ፣ኩባ ፣ ቻይና ፣ ሌሴቶ፣ ማሊ፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኡጋንዳ ፣ ብሩንዲ፣ ሩስያ ፣ ኢራን ይገኙበታል።

ተቃውሞ ካደረጉት መካከል ደግሞ አሜሪካ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኖርዌይ፣ ኒውዝላንድ ፣ ፖላንድ ፣ ሮማኒያ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ፊንለንድ ፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን፣ ጃፓን ፣ ጣልያን፣ ሞናኮ፣ ሜክሲኮ ፣ ካናዳ ይገኙበታል።

ድምፀ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ቦትስዋና ፣ ግብፅ ፣ ኮትዲቯር ፣ ኩዌት ፣ ሌባኖስ ፣ማሌዥያ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ ፣ ሞሮኮ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ ሴኔጋል ፣ ደ/አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ቶጎ፣ ሲንጋፖር፣ ዩናትድ አረብ ኤሜሬትስ ይገኙበታል።

ቱርክ ፣ ሱማሊያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሩዋንዳ ፣ ጋምቢያ ... ሌሎችም በርካታ ሀገራት ሙሉ በሙሉ በድምፅ አሰጣጡ አልተሳተፉም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል። የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው…
#ተጨማሪ

" መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል።

የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን #ብቸኛው ሆኗል።

ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። 

ፎቶ ፦ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት " በሚል ወደ ኤርትራ፣ አስመራ መጓዛቸው ተሰምቷል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " በሁለቱ ወንድማማች አገራት " የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመምክር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ብሏል። በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር…
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነትን ውድቅ የሚያደርግ ሕግ ፈርመው አፅድቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ሕጉ " አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እንዲሁም የግዛት አንድነታችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው " ማለታቸው ተነግሯል።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ግን የሶማሊያ መንግሥት እንቅስቃሴዎችን ውድቅ በማድረግ ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን እየገለፀች ትገኛለች።

ሶማሊያ እያቀረበች ያለው ይገባኛል ሀሰት መሆኑን ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት አመታት መቆጠራቸውን፣ የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዬጵያ ጋር የተደረገው ስምምነት (MoU) ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲተረጎም የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለው እያሳወቀች ነው።

በሌላ መረጃ ፤ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ኤርትራ፣ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል። ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል። ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል። የሶማሊያው…
#Update

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የሁለትዮሽ ስምምነት ለማድረግ " የሶማሊያ ፍቃድ "አያስፈልገኝም ፤ አልጠይቅምም " አለች።

ከሶማሊያ ተነጥላ ሶስት አስርት ዓመታት እንደሆናት የገለፀችው ሶማሌላንድ፤ ሶማሊያ የምታቀርበው " የኔ አካል ናት " የሚለው የባለቤትነት ጥያቄ ፍፁም ሀሰት ነው ስትል ገልጻለች።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን በሶማሊላንድ የወደብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት አንድ ሀገር ከሌላ ሀገር ጋር ከሚደርገው #የሊዝ_ኮንትራቶች የተለየ አለመሆኑን አመልክታለች።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፤ ሶማሊያ የመግባቢያ ስምምነቱን በተመለከተ ያየዘችውን አቋም እና ያወጣቻቸውን መግለጫዎች ሁሉ #ውድቅ አድርጋለች።

ከዚህ ባለፈ ሶማሌላንድ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማድረግ የሶማሊያን ፈቃድ ትፈልጋለች የሚባል ማንኛውም ሀሳብ ፍፁም ውሸት ነው ስትል ገልጻለች።

ሶማሊላንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር የራሷን ነጻ የሆነ ግንኙነት ስታደርግ እንደነበርና አሁንም የምትቀጥል መሆኑን ገልጻ ከአሁኑ የመግባቢያ ስምምነት በፊት በርካታ ዓለም አቀፍ እና የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተሳካ ሁኔታ መፈፀሟን አስታውሳለች።

ከእነዚህ ከተፈፀሙ ዓለም አቀፍ እና የሁለትዮች ስምምነቶች መካከል አንዳቸውም ከሶማሊያ ፈቃድ አልተጠየቁም ወይም አልተቀበሉም ብላለች።

ሶማሌላንድ ባለፉት 33 ዓመታት የሶማሌላንድ እና የሶማሊያ #ተቃራኒ ሁኔታዎችን ብዙ ይናገራሉ ስትልም ገልጻለች።

ሶማሌላንድ ፤ በአፍሪካ ቀንድ የበለፀገ ዲሞክራሲ እና የመረጋጋት ምልክት ሆና የውስጥ ጉዳዮቿን፣ አስተዳደሯን እና ምርጫዋን ያለአለም አቀፍ ድጋፍ በብቃት በመምራት ላይ እንደሆነች አመልክታችለች።

" ሀገራችን እና የባህር ዳርቻዋ ያለማቋረጥ / በወጥነት ከዘረፋ፣ ከሽብርተኝነት እና ከሽፍታነት የፀዱ ናቸው። " ስትል አክላለች።

በአንፃሩ ሶማሊያ ላለፉት 33 ዓመታት ከውስጥ ሽኩቻ፣ ሙስና እና ሽብርተኝነት ጋር ስትታገል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በተደጋጋሚ " የወደቀች / የከሸፈች ሀገር " ስትባል እንደነበር እና ለራሷ ጥበቃ የዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሃይል ያስፈለጋት ሀገር መሆኗን ሶማሌላንድ ገልጻለች።

" ሶማሊያ ብዙ ጊዜ ' ብርቅዬ አፍሪካዊ ተአምር ' እየተባለች በሚነገርላት በሶማሌላንድ ላይ ያልተገባ አረዳድ እንዲኖር ከማድረግና መሠረተ ቢስ የባለቤትነት ጥያቄ ከማቅረብ ይልቅ፣ የራሷን ቤት ብታስተካክል ይመረጣል " ብላለች።

" እርግጥ ነው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ከፍተኛ ልዩነት ይገነዘባል " ያለችው ሶማሌላንድ " እኛ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት የምናደርገውን አስተዋጽኦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደንቀው ነው " ስትል ገልጻለች።

ሶማሌላንድ እንደፈለገችው በነፃነት ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመመሥረት ሉዓላዊ መብቷን ከማስጠበቅ ወደ ኋላ ባትልም፣ ከሶማሊያ ጋር እንደ #ጎረቤት ገንቢ ውይይት ለማድረግና ሰላማዊ በሆነ መንገድ አብሮ ለመኖር ቁርጠኛ ነኝ ብላለች።

ሶማሊያ ፤ እንደ አንድ የራሷ ግዛት በምትቆጥራት ሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈረመውን ስምምነት " ዋጋቢስ " በማለት ውድቅ ያደረገች ሲሆን የኢትዮጵያ ድርጊት ሉዓላዊነቴን ፣ ግዛታዊ አንድነቴ የሚዳፈር ነው ብላለች።

የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድም ስምምነቱን ተከትሎ ወደ ተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር በመደወል ውይይት አድርገዋል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲም ወደ ግብፅ መጥተው የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia