TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቅሬታ #ምላሽ

“ ... ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኞች ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ የባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው ” - የኪ ሃውሲንግ የቤት ዕጣ ቆጠቢ

“ ... ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ጽፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ” - አቶ ቸርነት መንግስቱ (ከድርጅቱ)

ከሰሞኑን " Key Housing Finance Solution " የተሰኘ ተቋም የቤት ባለቤት ለመሆን ሲቆጥቡ ለነበሩ ሰዎች ዕጣ አውጥቶ ነበር።

ከተለያዩ ሴክተሮች በሚገኙ ልምድ ባላቸው አካላት ተዋቅሯል የተባለው " Key Housing Finance Solution " ከ15,000 በላይ ለሆኑ የቤት ቆጣቢ ተመዝጋቢዎች መካከል ለ60 ቆጣቢዎች / የቤት ዕድለኞች የመጀመሪያ ዙር ዕጣ አውጥቶላቸዋል።

ድርጅቱ በ77,280 ብር ቅድመ ቁጠባ ሰዎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሞዴል ፕሮጀክት እንዳለው በገለጸው እና በተለያዩ መንገዶች ባስተዋወቀው መሰረት ነው ከ15,000 በላይ ቤት ፈላጊ ቆጣቢዎች ውስጥ #ለ60_ቆጣቢዎች / #ባለዕድለኞች ዕጣ ያወጣላቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ “Key housing Finanance Solution” የቤት ዕጣ ቆጣቢ፣ “ኪ ሃውሲንግን በተመለከተ እጣ አወጣጡ ላይ ስህተቶች የተሰሩ በመሆኑ ማብራሪያና እርማት ብንጠይቅም በሶሻል ሚድያም ሆነ በሌላ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም” የሚል ቅሬታ ደርሶታል።

ከተመዝጋቢዎቹ መካከል አንዷ በሰጡን ቃል፣ “ ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ ለዚሁም ብለን ' አትላስ ' በሚገኘው ዋና ቢሯቸው ማብራሪያ ለማግኘት ከአንዴም ሁለቴ ብንሄድም #በsystem ምክንያት ዕጣ አወጣጡ ላይ ችግር ያለበት መሆኑን ከማመን የዘለለ በቂ ምላሽ አልሰጡንም ” ሲሉ ድርጅቱን ወቅሰዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረቡ ቅሬታዎች በዝርዝር ምን ይላሉ ?

- ዕጣው የደረሳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ካደረጉ በኋላ ቼክ በምናደርግበት ጊዜ ልዩነት አለው። 

- ልዩነት የተፈጠረው ባለ 3 ፣ ባለ 2 እና ባለ 1 መኝታ ቤት ነው ያዘጋጁት። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ካለው ዝርዝር ጋር ስናስተያየው ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብኞቹ ባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው።

- ከተመዝጋቢዎች ብዛት አንፃር #ባለ_3_መኝታ_ቤት ለ30 ሰዎች (50%)፣ ባለ 2 መኝታ ቤት ለ21 ሰዎች (35%)፣ ባለ 1 መኝታ ቤት ለዘጠኝ ሰዎች (15%) እንደሚወጣ ነበር ዕጣውን ከማውጣታቸው በፊት ሲገልጹ የነበረው።

- ባለ 3 መኝታ #ለ30_ሰዎች ብለው ካሰቡት ውስጥ ለ21 ሰዎች ነው የወጣው። የባለ 2 ደግሞ ለ21 ሰዎች ብለው ከገለጹት ለ29 ሰዎች ነው የወጣው። ባለ 1 መኝታ ቤት ደግሞ ለ9 ሰዎች ብለው ካሰቡት ለ10 ሰዎች ነው የወጣው። ይህ ማለት ይፋ ካደረጉት ፐርሰንቴጂ ጋር ግልፅ የሆነ ልዩነት አለው።

- በተጨማሪም ፤ ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የታቀደው ፕላን በፐርሰት 50 በመቶ ባለ 3 መኝታ ቤት ፣ 35 በመቶ ባለ 2 መኝታ ቤት እንዲሁም ፣ 15 በመቶ ለባለ 1 መኝታ ቤት ብለው ነበር ያስቀመጡት። አክቹአል ሲወጣ ግን ወደ 35፣ 48፣ እና 17 ፐርሰቶች ተቀያይሯል።

- ከ15,000 በላይ ተመዝጋቢዎች 60 እደለኞች ብቻ መመረጣቸው ሳያንስ ይኸውም የ60 ሰዎች ዕጣ አወጣጥ ትክክል ያልሆነና ተዓማኒነት የጎደለው ነው።

- ሌላ ያስተዋልው የተመዝጋቢዎች ስም ዝርዝር ተብሎ የተመዘገበው ላይ እስከ አያት ድረስ በተመሳሳይ ደብል የሆኑ ስሞች አሉ” የሚሉ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፤ የተነሳውን #ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የብሉዞን ማርኬቲንግ ማናጀርና የኪ ሃውሲነሰግ ቦርድ ሜምበር አቶ ቸርነት መንግስቴን አነጋግሯቸዋል።

እሳቸው ምን አሉ ?

ወደ ሲስተም ሲሞላ የታይኘ ኢረር ይኖረዋል። ባለ 2 የተመዘገበን ሰው ባለ 1 ብለህ ልትጽፍ ትችላለህ፣ ባለ 1 የተመዘገበን ባለ 3 ትላለህ። 

ይኼ ከሆነ ምናልባት ደንበኛው ራሱ ደግሞ ዕጣ ውስጥ ' መካተት ፤ አለመካተቱን ' እንዲያረጋግጥ ፣ እንዲህ አይነት የታይፕ ስህተቶች ተፈጥረው ከሆነ ታይቶ እንዲነገረን ፖስት አድርገንላቸዋል። 

በቴሌግራም ላይ ፖስት ካደረግን በኋላ ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ፅፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ። እሱን ከውሉ ጋር ወዲያው ከሀርድ ኮፒው እናመሳክራለን። ሲስተሙ ላይ ይስተካከልላቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ሲስተም ነው። መሞከሪያም ነው መስተካከል አለበት።

ፓስት ያደረግነው ቁጥር ሁሉም ማለት አይደለም የተወሰኑ ሰዎች ‘እንዲህ አስተካክሉልን’ ብለውናል። አስተካክለንላቸዋል። ‘አስተካክሉልን’ ያሉን ሰዎች ከተስተካከለላቸው በኋላ በቀጥታ ሰነዱን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ያስረክብነው የተስተካከለውን። 

ቴሌግራም ላይ ፖስት የተደረገው ያልተስተካከለው የመጀመሪያው (አስተያዬት ለመሰብሰብ ፓስት የተደረገው) ነው። ዕጣ ከወጣ በኋላ ሰዎች ሂደው ሲያመሳክሩ ያን ያዩታል። ግን እነዛ ሰዎች እዚጋ እንዲስተካከልላቸው ሆኗል። ራሳቸው ባቀረቡት መሠረት ማለት ነው።

እንዲህ ካደረጋችሁ ፥ በተመዝጋቢዎች በኩል ብዥታ እንዳይፈጠር ለምን የተስተካከለውን በድጋሚ ፖስት አላደረጋችሁላቸውም ? ብሎ ቲክቫህ ጠይቋቸዋል።

ምላሻቸውም ፤ " ካለፈ በኋላ ፓስት ማድረግ እንችል ነበረ " ብለዋል።

ዕጣው ከመውጣቱ በፊት #የተስተካከለውን ሰነድ ፓስት ያላደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ፤ " የተጣራው ለአዲስ አበባ የምንሰጠው ሰነድ ነው። የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ Soft ware ከሰራበት በኋላ ነው እንጂ ኦዲት የምናደርገው ቀድመን ምን ይደረግ የሚለውን አናውቅም። ዜሮ፣ ዜሮ መሆኑን ብቻ ነው የምናየው " ሲሉ ተናግርዋል።

በተጨማሪ ...

ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው ዕጣ የወጣላቸው ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ፤ ተብሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ይህ #እውነት_አይደለም። ምክንያቱም ባለ 2 ተመዝግበው ባለ 3 እንዴት ይደርሳቸዋል ? የደረሰውስ እንዴት ይቀበላል ? የማይሆን ነገር ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ዕጣ ከማውጣቱ በፊት ለባለ 3 ፣ ለባለ 2 እንዲሁም ለባለ 1 የቤት ዕድለኞች ያቀዱት ፐርሰንቴጂ ዕጣው ከወጣ በኋላ ተቀያይሯል ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ቤቱን ገና አላስተላለፍንላቸውም። ገና በ18 ነው ቤቱን የሚረከቡት።

የሚረከቡትም በተባለው መሠረት ባለ 1 መኝታ ቤት ዘጠኝ ሰዎች፣ ባለ 2 መኝታ ቤት 21 ሰዎች፣ ባለ 3 መኝታ ቤት 30 ሰዎች ናቸው። ባልተዘጋጁ ቤቶች ዕጣ አናወጣም። ከየትስ እናመጣዋለን " ከሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ድርጅቱ ማብራሪያ ሊሰጥ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ተወካይ ነን ብለው ለመጡ አባላቶች (የምር ተወካይ አይደሉም፤ የተወካይ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም) ፤ ግን ነገሩ መልካም ስለሆነ ቢሮ ለእያንዳዱ ሰነድ ጭምር እያሳዬን ማብራሪያ ሰጥተናል ” ሲሉ መልሰዋል።

በተመሳሳይ ስም የተጠቀሱ " ዳብል " ተመዝጋቢዎች መኖራቸው ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ... እንድ ተመዝጋቢ #ለብዙ_ሰዎች መመዝገብ ይችላል፣ ኮዱም ቢሆን ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።

በአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ።

@tikvahethiopia