TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ጌታቸው አሰፋ‼️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ያደርጋል። አራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም ከድርጅታዊ ጉባኤው በፊት የፓርቲዎቻቸውን ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የማዕከላዊ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን አካሂደዋል።

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያውን ወደ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በተመሳሳይ መልኩ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ደግሞ ወደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መቀየራቸው ይታወሳል። ሁለቱ ፓርቲዎች ከስማቸው ባሻገር የአርማ ለውጥም አድርገዋል። በሌላ በኩል ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የቀድሞ ስማቸውን እና አርማቸውን ይዘው ቀጥለዋል።

ኦዴፓ፣ አዴፓ እና ዴኢህዴን በርካታ የቀድሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በአዲስ እና ወጣት አባሎች ተክተዋል። ይህ በእንዲህ
እንዳለ ህውሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ የመረጣቸው ግለሰቦች ነባር እና ከሞላ ጎደል የድርጅቱ ታጋዮች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

በተለይ ደግሞ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ከዐሥራ አንዱ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎች ህወሓት #ከለውጡ ራሱን ገሽሽ እያደረገ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማሳያ አድርገው ወስደውታል።

ለመኾኑ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሥራ አስፈጻሚ መምጣታቸው አሁን ባለው የለውጥ አውድ ምን ፖለቲካዊ ትርጉም ይሰጣል?

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የህወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ #ጌታቸው_ረዳን እንዲህ ብለዋል፦

''ጌታቸው አሰፋ #ጎበዝ መሪ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ኢህአዴግ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ #ህወሓት መሆኑን አውቃለሁ። ህወሓት ሲወስን በሚዲያ #ሃሜት ላይ ተመሥርቶ አይደለም የሚወስነው'' በማለት በቀድሞው የደኅንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የሚቀርቡ ወቀሳዎችን አጣጥለዋል።

አቶ ጌታቸው ጨምረውም ''ይፋዊ መግለጫ ሳይኖር ሚዲያዎች ሃሜት ሲያወሩ ነበር። ሃሜት ላይ ተወስነን ውሳኔ የምናስተላልፍ ቢሆን ኖሮ ሃገር #ይጠፋል። ክስ ስለመመስረቱም የማውቀው ነገር የለም። አቶ ጌታቸው አሰፋን ፈልጎ ህውሓት ጋር የመጣ አካል የለም።'' በማለት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ አለመመሥረቱን አመላክተዋል።

አቶ ጌታቸው አያይዘው እንደሚሉት ከሆነ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ የመመረጥ ፍላጎት አልነበራቸውም።

''ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መግባትም አልፈለገም፤ ሲሪየስሊ [አጥብቆ] ነው የተከራከረው። ጉባኤው ግን ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንዲገባ ወሰነ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ውስጥ መግባት አለበት ብሎ ወሰነ።'' ይላሉ አቶ ጌታቸው ረዳ።

"አቶ ጌታቸው አሰፋ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀዋሳ ይሄዳሉ ወይ?" ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ጌታቸው ረዳ ሲመልሱ ''የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በጉባኤው እንዲሳተፍ ይጠበቃል። እንደማንኛው የኮሚቴ አባል ሀዋሳ ላይ ልታይዋቸው ትችላላችሁ።

እንደማንኛውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተሳትፎ ማድረግ ስላለብን አንዳንዶቻችን ያው መንገድ ላይ ነን። ለምሳሌ አውሮፕላን ካመለጠኝ ልቀር እችላለሁ'' ብለዋል።

ይህ አገላለጽ 'አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይገኙ ይችላሉ' የሚለውን ያመላክት እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣"እኔ የእያንዳንዱ ሰው ስኬጁል አላወጣም። ሁላችንም ተበትነን ነው ወደ ሀዋሳ እየሄድን ያለነው፤ ጌታቸውም በራሱ ጊዜ ስኬጁሉን አሬንጅ ያደርጋል፤ ካገኘሁት እነግራችኋለሁ" ሲሉ በቀልድ የታጀበ ምላሽ ሰጥተዋል።

ነገ በሚጀመረው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማን ሊሆን ይችላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ''አሁን ያሉት ሊቀ መንበር ላለፉት 5 ወይም 6 ወራት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። እስካሁን የሠሩት ሥራ ተገምግሞ ለውጥ ማድረግ ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው የጉባኤው ውሳኔ ነው የሚሆነው'' በማለት መልሰዋል።

ህወሓት ማንን በእጩነት ለማቅረብ እንደተሰናዳ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲዎች እንደማይመርጡ አስረድተዋል። ''ህወሓት፣ ብአዴን
ወይም ኦህዴድ ዕጩዎችን አያቀርቡም። ፓርቲዎች አይደሉም ዕጩዎችን የሚጠቁሙት። ከ180ዎቹ የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ግለሰቦችን ለሊቀ መንበርነት ለጉባኤው ጥቆማዎችን ይሰጣሉ። ከዚያም ምርጫ ይካሄዳል። ድምጽ ያገኘ ያሸንፋል።'' ብለዋል።

በግንባሩ ጉባኤ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አፈጻጸም ላይ መቀዛቀዝ ይታያል።

ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እሱን እንዴት አድርገን ነው በፍጥነት የምናስቀጥለው የሚለው ትልቁ አጀንዳ ነው። ወደ ሃገር እንዲገቡ የተደረጉ ተፎካካሪ፣ ተቃዋሚ የሚባሉ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ከገቡ በኋላ አንዳንዱ 'አሸንፌ ነው የመጣሁት' ይላል። ሌላኛው 'ወደሽ ሳይሆን ተገደሽ ነው የተቀበልሺኝ' ይላል። ይህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥረው #የሰላም እና #የመረጋጋት ዝብርቅርቅ አለ። ይህን ለመሰሉ ጉዳዮች ጉባኤው #ምላሽ ይሰጣል። ይህ የሁላችንም አጀንዳ ነው'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንተርኖች👆

ተመራቂ #የህክምና_ተማሪዎች እየጠየቅን ላለነው #ጥያቄ አሁንም ትክክለኛ #ምላሽ_እያገኘን አይደለም ብለዋል። #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
JiT👆

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የዓመቱ የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥብት ቀን #ይራዘምልን በማለት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ ፦ "ፊርማ አሰባስበን የፈተናው ቀን እንዲራዘም ብንጠይቅም ተቋሙ ጥያቄያችንን ወደኃላ በማለት በአቋሙ ፀንቷል፤ ብዙ portion ያልጨረስን በመሆኑ ተማሪውን ከግቢ #ለማባረር የተጠነሰሰ ሴራ ነው" ብለን እናምናለን ሲሉ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከJiT አመራሮች የሚሰጥ #ምላሽ ካለ ተከታትዬ የማቀርብላችሁ ይሆናል። #JiT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደራ_ወረዳ #ትኩረት

በደራ ወረዳ ያለው የፀጥታ ችግር አሁንም #አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ፣ የሰዎች ህይወት እያለፈ ፣ ንብረትም እየወደመ መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል የልጆቻቸው እናት የሆነች ሚስታቸውን ከ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች ጋር በመወገን ገድለዋል ብለዋል።

አንድ ቃላቸውን ለ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' የሰጡ የሟች የቅርብ ቤተሰብ ነኝ ያሉ ግለሰብ ፤ " በደራ ጁሩ የተባለ አካባቢ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል የፓሊስ አባል ከኦነግ ሸኔ ጋር በመወገን የአራት ልጆቹን እናትና የ5 ወር ነፍሰጡር ሚስቱን ገድሏል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የሟች የቅርብ ቤተሰብ ይህ ግድያ በጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ፤ " ጁሩ " የተባለ አካባቢ ላይ እንደትፈጸመ አስረድተው፣ " የሟቿን እናት ጨምሮ ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል። እኛም ልባችን ተሰብሮ አለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛው የዓይን እማኝ #ጥቅምት_9 በገለጹት መሠረት፣ በደራ ወረዳ " ቆሮ ግንደ በርበሬ " ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ጦር አካባቢውን እና መንደሩን ካቃጠለ 2 ሴቶችን እና አንድ ወንድ ገድሏል ሲሉ ከሰዋል።

እንደ ነዋሪው ገለፃ ን በታጣቂ ቡድኑ የተገደሉት ፀጋ እምነት፣ ጌታው አቤቱ እና ለግዜው ስሟን ያላወቁት ሴት ናቸው።

እኚሁ እማኝ ፤ " በመንግሥት ይሁንታ #የደራ_ህዝብ ከፍተኛ የዘር የፍጅት እየደረሰበት ነው " ብለዋል።

ይኸው ዘገባ እየተዘጋጀበት እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ታጣቂ ቡድኑ ያለበትን ሁኔታ ሲያስሩዱም፣ " አሁንም በተለያዩ ቀበሌዎች እንደቀጠለ ነው። መንግሥት ምንም እርምጃ አልወሰደም። አድማሱን እያሰፋ ይገኛል " ነው ያሉት።

እኚሁን ምንጭ ጨምሮ ሌሎች የኦሮሚያ እና የአማራ ተወላጅ የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣  አሙማ ገንዶ፣ ኢሉ ጎደ ጨፌ ፣ ሀርቡ ደሶ ፣ ዴኙ ወቤንሶ ፣ ጁሩ ዳዳ፣ ሀቼ ኩሳዬ፣ ካራ፣ ጎዲማ ሶስት ዋርካ፣ ጊሊ ወዲሳ፣  ቆሮ ግንደ በርበሬ፣ በዮ ኖኖ፣ ደንቢ ብርጄ፣ ባቡ ድሬ፣ ወሬ ገበሮ፣ መንቃታ፣ የተባሉና ላሎችም ቀበሌዎች እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) በታጣቂ ቡድኑ ስር ናቸው ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ቃላቸውን በስልክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ፣ መከላከያ በአካባቢው እንዳለ፣ እንደ አጠቃላይ ግን ነዋሪው የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደሆነ አስረድተው ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል።

ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው ፤ " ፋኖ ታጣቂዎችም አልፎ አልፎ ጥቃት እያደረሱ  ነው። በመካከል እየተጎዳ ያለው ንጹሐኑ ነው። መንግሥት እርምጃ ቢወስድ ምን አለ ? " ሲሉ ተይቀው ተጨማሪ ሀሳብ ለመስጠት ተቆጥበዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ባለፉት ሳምንታት በርካታ ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ እንደታገቱ ፣ ከእገታ ለመለቀቅም ከ500 እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እየተጠየቀባቸው እንደነበር፣ በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ፣ በርካታ ቤቶች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት እንደተቃጠሉ መግለፃቸው ይታወሳል።

የኦሮሚያ ተወላጆችም ፤ " የፋኖ ታጣቂዎች በርካታ ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎችን ገድለዋል " ማለታቸው አይዘነጋም።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ በሚጠራው የታጣቂ ቡድን ታገቱ የተባሉ ሰዎች ከምን እንደደረሱ፣ የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ፣ የቤት ቃጠሎ ጥቃቱ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር የከፈሉ ተለቀዋል፣ ያልከፈሉትን ገድሏል " ብለዋል ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ታማኝ ምንጭ።

ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚሰነዝሩትን ግድያ፣ ቃጠሎ፣ እገታ እንዳላቆሙ የሟቾችን ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደተገደሉ አስረድተው፣ ይህን ልጓም ያጣ ጥቃት መንግሥት ቸል ብሎታል የዓለም መንግሥታት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይወቁልን ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ደረሰ እና አልቆምመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአቶ ሺበሺን በስልክና በአጭር ጽሑፍ እንዲያብራሩ ጥያቄ ቢያቀርብም #ምላሽ_ለመስጠት_ፈቃደኛ_አልሆኑም

አቶ ሺበሺ ከዚህ በፊት ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ችግሩን ለመቅረፍ የጸጥታ ኃይል እጥረት እንዳለ አስረድተው ነበር።

በተጨማሪ ከዞኑ አስተዳደር፣ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ የተደረገው ተመሳሳይ ሙከራ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በደራ ስላለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ያነጋገረ ሲሆን " ክትትል ተጀምሯል ግን ገና አላለቀም " የሚል አጭር ምላሽ አግኝቷል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ይቅርታ የጠየቀን የለም ፤ ለምን በረራው እንደተሰረዘ ያሳወቀንም አካል የለም " - መንገደኞች ዛሬ ከሰዓት ወደ ደሴ - ኮምቦልቻ ሊደረግ የነበረ የአየር በረራ መንገደኞች ወደ አውሮፕላኑ ከገቡ በኃላ እንደተሰረዘ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እንደደረሰባቸው መንገደኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ለበረራው መሰረዝ ዝርዝር ምክንያት እንዳልተነገረቸው የገለፁት መንገደኞቹ "…
#ምላሽ

በረራው ለምን ተሰረዘ ?

ዛሬ ከሰዓት በኃላ ወደ ደሴ ኮምቦልቻ በረራ ለማድረግ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱ በኃላ " በረራው ተሰርዟል " የተባሉ መንገደኞች ለምን በረራው እንደተሰረዘ በአግባቡ እንዳልተነገራቸውና ይቅርታም ባለመጠየቃቸው ምክንያት እንዳዘኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚመለከተው ክፍል ቅሬታውን አቅርቦ ምላሽ ጠይቋል።

አየር መንገዱ በሰጠው መረጃ መሰረት ቀን ላይ ወደ ደሴ - ኮምቦልቻ በረራዎች መደረጉን ገልጿል።

የምሽቱ በረራ ግን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መግባት ስለማይችል (በተለምዶ "SunSet" በመድረሱ) መሰረዙ አመልክቷል።

የኮንቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ በምሽት የሚደረጉ በረራዎችን ማስተናገድ ባለመቻሉ በረራው ከመደረጉ በፊት በረራ ከመጀመሩ በፊት የሚነሳበት ሰዓት፣ የሚደርስበት እና የሚመለስበት ሰዓት ተሰልቶ በረራው መደረግ አለመደረጉ ይወሰናል ብሏል።

ይህ ተሰልቶ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት የማይደርስ ከሆነ በረራው ከወዲሁ የሚሰረዝ እንደሆነ ማብራሪያ የሰጠን አየር መንገዱ ወቅቱም ቀኑ አጭር በመሆኑ ቶሎ በመምሸቱ ይህ ማጋጠሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#የመምህራን_ቅሬታ #ምላሽ

ለ487 ' የአዲአርቃይ ወረዳ ' መምህራን የ22 ወራት የደረጃ ዕድገት ደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ማሳደሩን የሰሜን ጎንደር ዞን መምህራን ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፤ " በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን "  የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።

የሰሜን ጎንደር ዞን የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሀብታሙ አቸነፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- የመምህራንን #የመልካም_አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ የሆነ የፖለቲካ የመንግሥት አመራር ባለመፈጠሩ ምክንያት 487 የአዲአርቃይ ወረዳ መምህራን ከጥር 1/2014 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ በጊዜ ቆይታ የደረጃ እድገት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ይህ በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የቅሬታ ምንጭ ሆኖብናል።

- ለመምህራን ከጥር 01/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የደረጃ እድገታቸው እንደሚያድግና ለእድገታቸው የሚሆን በጀት ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሥማቸው ተይዞ ነበር። ይህንን በጀት ' አዘዋውረን ለሰላም ማስከበር አውለነዋል' ነው የሚለው የአስተዳደር ምክር ቤቱ።

- ጥያቄያችንን #በተደጋጋሚ አቅርበን ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት አካል አላገኘንም።

- ባለፈው ዓመት በወረዳው ላይ በነበረ አንድ ጉባኤ ' የመምህራን ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፣ በአዲሱ በጀት ዓመት ጥያቄውን እመልሳለሁ ' የሚል ምላሽን ሰጠ #አስተዳዳሪው። በዚህ ዓመት ደግሞ ፦
* ሀምሌ፣
* መስከረም፣
* ጥቅምት ወራት ላይ ተጠየቀ አሁን የመጨረሻው ውሳኔ ' እኔ በጀቱን አላውቅም ፣ በወቅቱ የነበረውን አስተዳዳሪ በጠየቃችሁ ፣ እኔ አሁን የምከፍልበት ኮንዲሽን የለም ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው ፤ በዚህ መምህራን በጣም #ተበሳጭተው ነው ያሉት።

- መምህራን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለመጠየቅ ሲሄዱ 'እናስራችኋለን፣ እንመታችኋለን' የሚል ተፅእኖ አለ።

- በወቅቱ የነበረው ችግር የሁላችንም ችግር ቢሆንም ደመወዝ ቀጥታ ተከፋይን አንስቶ ' ለሰላም ማስከበር ' በሚል ላለአስፈላጊ ጥቅም ማዋል ተገቢ አይደለም። ላለአስፈላጊ ጥቅም ነው የዋለበት ያልኩት ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኮማንድ ፖስት የትዕዛዝ አቅጣጫ ተሰጥቶ የነበረው ሁሉም ደመወዝ ለሰላም ማስከበር ይሆናል የሚል ሳይሆን፣ 'የሥራ ማስኬጃ 40%ን ተጠቀሙ' የሚል ስለነበር ነው።

- እንደ 'ሰሜን ጎንደር ዞን' ብዙ ወረዳዎች ተሳትፈዋል በጦርነቱ። ጠለምት ተሳትፏል፣ ዳባት ተሳትፏል ነገር ግን አንድም ከበጀት ጋር የተያያዘ ደመወዝ የተነሳበት ወረዳ የለም። በዞናችን አሥር ወረዳዎች አሉ ሙሉ በሙሉ የደረጃ ዕድገታቸውን እየከፈሉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። #አዲአርቃይ ግን እንዲህ አይነት ችግር ገጥሞናል።

- ያልተከፈለውን የደረጃ እድገት ምን ያህል እንደሆነ አላሰላሁትም፣ ግን ቢያንስ ለ487 መምህራን ዝቅተኛ 800፣ ከፍተኛ እስከ 2,000 ብር የደረጃ እድገት ያገኛሉ። ነገር ግን ይኸው እንግዲህ አሁን ጥር ወር ሲገባ 2 ዓመታት ሊሆነው ነው ሳይከፈል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ " የመምህራኑን #የደረጃ_እድገት ደመወዝ ለምን እስካሁን ድረስ አልተከፈለም ? " ሲል የአዲአርቃይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ ጆርጌ ጠይቋል።

አቶ አረቡ ጆርጌ " አሁን ያለበት ሁኔታ በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " መምህራኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እንዳልተከፈላቸው፣ በመጨረሻም በጀቱ ለሌላ ጥቅም እንደዋለ " እንደገለፁለት ለኃላፊው #በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪ ፦

* ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለምን ገንዘቡን አልከፈላችሁም ?

* አሁን ለመክፈልስ ምን የታሰበ ነገር አለ ? ብለን ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው " ኦሬዲ ጠይቀዋል በጀት ተይዞ እንደሚከፈል ብቻ ነው የነገርናቸው እንጂ ለዚህ የተመደበ #ለሌላ ጥቅም የዋለ ገንዘብ የለም " ብለዋል።

" መከፈሉ ግዴታ ነው፣ እንደ ተቋም እንደ አስተዳደር ምክር ቤትም ' አይከፈልም ' የሚል ማስተባበያ አይኖረንም ምክንያቱም ደመወዝ ስለሆነ " ያሉት ኃላፊው፣ " ለሁለት ዓመታት ያክል የገቢ መሰብሰብ ችግር ስለነበር በጦርነቱ ምክንያት በጀቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነው ያሳደረው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስለዚህ እኛም አሁን የያዝነው ፕሮግራም ሙሉውን እንኳ ባይከፈል እየተከፈለ (የአመቱን ወደ 6 ወራት፣ የ6 ወራቱን ወደ ሦስት ወራት እየተደረገ በጀት እየያዝን እንከፍላለን እንጂ አይከፈልም የሚል አቋም የለም። ተገቢነትም የለውም " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሶማሊላንድ ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ።

የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዜዳንት አብዲራህማን ሳይሊች የሶማሊላንድን ካቢኔ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።

ይኸው የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ በሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ እና የፌዴራል ምክር ቤቶች ለተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ #ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ንግድ እና ቱሪዝም ሚኒስትር አብዲረሺድ ኢብራሂም ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ ስብሰባው በሶማሊያ መንግሥት እየተፈፀመ ስለሚገኘው ቅስቀሳ ግልፅ በሆነ መንገድ በጥልቀት ይመከርበታል የሚል መረጃ ማግኘት ተችሏል።

አስቸኳይ ስብሰባው በፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት ነገ ጥዋት ይካሄዳል።

በሌላ በኩል፤ ዛሬ ምሽት በሶማሊላንድ ሃርጌሳ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ ወጥተው ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሲደግፉ ነበር ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ቅሬታ #ምላሽ

“ ... ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኞች ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ የባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው ” - የኪ ሃውሲንግ የቤት ዕጣ ቆጠቢ

“ ... ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ጽፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ” - አቶ ቸርነት መንግስቱ (ከድርጅቱ)

ከሰሞኑን " Key Housing Finance Solution " የተሰኘ ተቋም የቤት ባለቤት ለመሆን ሲቆጥቡ ለነበሩ ሰዎች ዕጣ አውጥቶ ነበር።

ከተለያዩ ሴክተሮች በሚገኙ ልምድ ባላቸው አካላት ተዋቅሯል የተባለው " Key Housing Finance Solution " ከ15,000 በላይ ለሆኑ የቤት ቆጣቢ ተመዝጋቢዎች መካከል ለ60 ቆጣቢዎች / የቤት ዕድለኞች የመጀመሪያ ዙር ዕጣ አውጥቶላቸዋል።

ድርጅቱ በ77,280 ብር ቅድመ ቁጠባ ሰዎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሞዴል ፕሮጀክት እንዳለው በገለጸው እና በተለያዩ መንገዶች ባስተዋወቀው መሰረት ነው ከ15,000 በላይ ቤት ፈላጊ ቆጣቢዎች ውስጥ #ለ60_ቆጣቢዎች / #ባለዕድለኞች ዕጣ ያወጣላቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ “Key housing Finanance Solution” የቤት ዕጣ ቆጣቢ፣ “ኪ ሃውሲንግን በተመለከተ እጣ አወጣጡ ላይ ስህተቶች የተሰሩ በመሆኑ ማብራሪያና እርማት ብንጠይቅም በሶሻል ሚድያም ሆነ በሌላ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም” የሚል ቅሬታ ደርሶታል።

ከተመዝጋቢዎቹ መካከል አንዷ በሰጡን ቃል፣ “ ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ ለዚሁም ብለን ' አትላስ ' በሚገኘው ዋና ቢሯቸው ማብራሪያ ለማግኘት ከአንዴም ሁለቴ ብንሄድም #በsystem ምክንያት ዕጣ አወጣጡ ላይ ችግር ያለበት መሆኑን ከማመን የዘለለ በቂ ምላሽ አልሰጡንም ” ሲሉ ድርጅቱን ወቅሰዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረቡ ቅሬታዎች በዝርዝር ምን ይላሉ ?

- ዕጣው የደረሳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ካደረጉ በኋላ ቼክ በምናደርግበት ጊዜ ልዩነት አለው። 

- ልዩነት የተፈጠረው ባለ 3 ፣ ባለ 2 እና ባለ 1 መኝታ ቤት ነው ያዘጋጁት። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ካለው ዝርዝር ጋር ስናስተያየው ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብኞቹ ባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው።

- ከተመዝጋቢዎች ብዛት አንፃር #ባለ_3_መኝታ_ቤት ለ30 ሰዎች (50%)፣ ባለ 2 መኝታ ቤት ለ21 ሰዎች (35%)፣ ባለ 1 መኝታ ቤት ለዘጠኝ ሰዎች (15%) እንደሚወጣ ነበር ዕጣውን ከማውጣታቸው በፊት ሲገልጹ የነበረው።

- ባለ 3 መኝታ #ለ30_ሰዎች ብለው ካሰቡት ውስጥ ለ21 ሰዎች ነው የወጣው። የባለ 2 ደግሞ ለ21 ሰዎች ብለው ከገለጹት ለ29 ሰዎች ነው የወጣው። ባለ 1 መኝታ ቤት ደግሞ ለ9 ሰዎች ብለው ካሰቡት ለ10 ሰዎች ነው የወጣው። ይህ ማለት ይፋ ካደረጉት ፐርሰንቴጂ ጋር ግልፅ የሆነ ልዩነት አለው።

- በተጨማሪም ፤ ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የታቀደው ፕላን በፐርሰት 50 በመቶ ባለ 3 መኝታ ቤት ፣ 35 በመቶ ባለ 2 መኝታ ቤት እንዲሁም ፣ 15 በመቶ ለባለ 1 መኝታ ቤት ብለው ነበር ያስቀመጡት። አክቹአል ሲወጣ ግን ወደ 35፣ 48፣ እና 17 ፐርሰቶች ተቀያይሯል።

- ከ15,000 በላይ ተመዝጋቢዎች 60 እደለኞች ብቻ መመረጣቸው ሳያንስ ይኸውም የ60 ሰዎች ዕጣ አወጣጥ ትክክል ያልሆነና ተዓማኒነት የጎደለው ነው።

- ሌላ ያስተዋልው የተመዝጋቢዎች ስም ዝርዝር ተብሎ የተመዘገበው ላይ እስከ አያት ድረስ በተመሳሳይ ደብል የሆኑ ስሞች አሉ” የሚሉ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፤ የተነሳውን #ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የብሉዞን ማርኬቲንግ ማናጀርና የኪ ሃውሲነሰግ ቦርድ ሜምበር አቶ ቸርነት መንግስቴን አነጋግሯቸዋል።

እሳቸው ምን አሉ ?

ወደ ሲስተም ሲሞላ የታይኘ ኢረር ይኖረዋል። ባለ 2 የተመዘገበን ሰው ባለ 1 ብለህ ልትጽፍ ትችላለህ፣ ባለ 1 የተመዘገበን ባለ 3 ትላለህ። 

ይኼ ከሆነ ምናልባት ደንበኛው ራሱ ደግሞ ዕጣ ውስጥ ' መካተት ፤ አለመካተቱን ' እንዲያረጋግጥ ፣ እንዲህ አይነት የታይፕ ስህተቶች ተፈጥረው ከሆነ ታይቶ እንዲነገረን ፖስት አድርገንላቸዋል። 

በቴሌግራም ላይ ፖስት ካደረግን በኋላ ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ፅፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ። እሱን ከውሉ ጋር ወዲያው ከሀርድ ኮፒው እናመሳክራለን። ሲስተሙ ላይ ይስተካከልላቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ሲስተም ነው። መሞከሪያም ነው መስተካከል አለበት።

ፓስት ያደረግነው ቁጥር ሁሉም ማለት አይደለም የተወሰኑ ሰዎች ‘እንዲህ አስተካክሉልን’ ብለውናል። አስተካክለንላቸዋል። ‘አስተካክሉልን’ ያሉን ሰዎች ከተስተካከለላቸው በኋላ በቀጥታ ሰነዱን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ያስረክብነው የተስተካከለውን። 

ቴሌግራም ላይ ፖስት የተደረገው ያልተስተካከለው የመጀመሪያው (አስተያዬት ለመሰብሰብ ፓስት የተደረገው) ነው። ዕጣ ከወጣ በኋላ ሰዎች ሂደው ሲያመሳክሩ ያን ያዩታል። ግን እነዛ ሰዎች እዚጋ እንዲስተካከልላቸው ሆኗል። ራሳቸው ባቀረቡት መሠረት ማለት ነው።

እንዲህ ካደረጋችሁ ፥ በተመዝጋቢዎች በኩል ብዥታ እንዳይፈጠር ለምን የተስተካከለውን በድጋሚ ፖስት አላደረጋችሁላቸውም ? ብሎ ቲክቫህ ጠይቋቸዋል።

ምላሻቸውም ፤ " ካለፈ በኋላ ፓስት ማድረግ እንችል ነበረ " ብለዋል።

ዕጣው ከመውጣቱ በፊት #የተስተካከለውን ሰነድ ፓስት ያላደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ፤ " የተጣራው ለአዲስ አበባ የምንሰጠው ሰነድ ነው። የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ Soft ware ከሰራበት በኋላ ነው እንጂ ኦዲት የምናደርገው ቀድመን ምን ይደረግ የሚለውን አናውቅም። ዜሮ፣ ዜሮ መሆኑን ብቻ ነው የምናየው " ሲሉ ተናግርዋል።

በተጨማሪ ...

ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው ዕጣ የወጣላቸው ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ፤ ተብሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ይህ #እውነት_አይደለም። ምክንያቱም ባለ 2 ተመዝግበው ባለ 3 እንዴት ይደርሳቸዋል ? የደረሰውስ እንዴት ይቀበላል ? የማይሆን ነገር ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ዕጣ ከማውጣቱ በፊት ለባለ 3 ፣ ለባለ 2 እንዲሁም ለባለ 1 የቤት ዕድለኞች ያቀዱት ፐርሰንቴጂ ዕጣው ከወጣ በኋላ ተቀያይሯል ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ቤቱን ገና አላስተላለፍንላቸውም። ገና በ18 ነው ቤቱን የሚረከቡት።

የሚረከቡትም በተባለው መሠረት ባለ 1 መኝታ ቤት ዘጠኝ ሰዎች፣ ባለ 2 መኝታ ቤት 21 ሰዎች፣ ባለ 3 መኝታ ቤት 30 ሰዎች ናቸው። ባልተዘጋጁ ቤቶች ዕጣ አናወጣም። ከየትስ እናመጣዋለን " ከሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ድርጅቱ ማብራሪያ ሊሰጥ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ተወካይ ነን ብለው ለመጡ አባላቶች (የምር ተወካይ አይደሉም፤ የተወካይ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም) ፤ ግን ነገሩ መልካም ስለሆነ ቢሮ ለእያንዳዱ ሰነድ ጭምር እያሳዬን ማብራሪያ ሰጥተናል ” ሲሉ መልሰዋል።

በተመሳሳይ ስም የተጠቀሱ " ዳብል " ተመዝጋቢዎች መኖራቸው ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ... እንድ ተመዝጋቢ #ለብዙ_ሰዎች መመዝገብ ይችላል፣ ኮዱም ቢሆን ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።

በአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ።

@tikvahethiopia