TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
37 ሺህ ዩሮ ለባለቤቱ የመለሰው ወታደር!

ወድቆ ያገኘውን 37 ሺህ ዩሮ ለባለቤቱ የመለሰው ወታደር የሁለት ማዕረግ እድገት ተሰጠው። ታማኙ የናይጄሪያ አየር ኃይል አባል የሆነው በሺር ኡመር ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን በሰሜናዊቷ ካኖ ግዛት አውሮፕላን ማረፊያ ቅኝት በማድረግ ላይ ነበሩ። በቅኝቱ ወቅት በሺር ኡመር በካርቱን ተጠቅልሎ የወደቀ 37 ሺህ ዩሮ (41 ሺህ 500 ዶላር) ያገኛል።

በገንዘቡ መጠቅለያ ላይ የተጻፈው ስልክ ላይ በመደወል ለባለቤቱ መልሷል። የአየር ኃይል አባሉ በሺር ኡመር በዚህ የታማኝነት ተግባሩ ለማሳካት 10 ዓመት የሚወስድበትን የሁለት ማዕረግ እድገት ከተቋሙ ተችሮታል። የምስጋና ወረቀት በተቋሙ እንደተጠሰውም ነው የተነገረው።

ትናንት ምሽት በነበረው ስነ ስርዓት የአየር ኃይል አዛዡ ማርሻል ሳዲቅ አቡበከር “ኡመር ወድቆ ያገኘውን ገንዘብ ለባለቤቱ በመመለስ ሀቀኝነትን በተግባር አሳይቶናል” ብለዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ ክልል ዝግጅቴን አጠናቅቂያለሁ ብሏል!
#ሃምሌ22

በአንድ ጀምበር 200 ሚሊየን ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል በተያዘው እቅድ መሰረት የአማራ ክልል በአንድ ቀን 100 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ የመስኖ ግንባታና የተፈጥሮ ሃብት ምክትል ሃላፊ አቶ ማርቆስ ወንዴ፥ ሃምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ በክልል ደረጃ 100 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ለዚሁ ተግባር ችግኞች ወደ መትከያ ቦታዎች መጓጓዛቸውን በመግለጽ በእለቱ በየችግኝ መትከያ ቦታዎች ድጋፍ የሚያደርጉ የዘርፉ ሙያተኞች መመደባቸውን አንስተዋል፡፡

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ማህበረሰቡ ለዚሁ ተልዕኮ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም ምክትል ሃላፊው ገልጸዋል፡፡ በእለቱ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በዚሁ ፕሮግራም ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው አቶ ማርቆስ የተናገሩት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቁልቢ #ሀዋሳ #ሀምሌ19

በቁልቢ እና በሐዋሳ ከተሞች በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረው የገብርኤል አመታዊ ንግሥ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ተከናወነ። የክብረ በዓሉ ታዳሚዎች ቁጥር በቁልቢ ሲጨምር በሐዋሳ በግማሽ ገደማ መቀነሱን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁልቢ ከተማ የተካሔደው የዛሬው የበዓል አከባበር ምንም እክል እንዳልገጠመው የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ሱልጣን አወል ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

https://telegra.ph/HAMLE19-07-26
#update የአሜሪካ መንግስት ከ16 አመት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ የሞት ቅጣት መወሰኑ ተነገረ፡፡ ከፈረንጆቹ 2003 በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ የሞት ቅጣት መወሰኑን የአሜሪካ ፌዴራል መንግስት ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው 5 ሰዎች በህፃናት ላይ በፈጸሙት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለሞት ቅጣት ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል ተብሏል ፣ የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቀን ታህሳስ 2019 እና ጥር 2020 እንደሆነም በዘገባው ተካቷል፡፡ በአሜሪካ የሚገኙ የመብት ተሟጋች ቡድኖች የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምበት ቀን በጣም ቅርብ ስለሆነ ሊታሰብበት ይገባል ፣ በቅጣቱ ፍትሃዊነት ላይም ትኩረት ይሰጥ ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው..."

ከሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ በሜድትራኒያን #ባሕር ላይ በትናንትናው ዕለት በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከታደጓቸው ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አንድ ከፍተኛ የሊቢያ ባለሥልጣን አስታወቁ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) በበኩሉ በጀልባ የሜድትራኒያን ባሕርን ለማቋረጥ ከሞከሩ 300 ስደተኞች ውስጥ #147ቱ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የአፍሪካ እና የሜድትራኒያን ቃል-አቀባይ ቻርሊ ያክስሊ ዛሬ እንደተናገሩት ኾምስ ከተባለችው የሊቢያ ከተማ ከተነሱት ስደተኞች ውስጥ 150 ያክል በባሕር ላይ ሞተዋል የሚል መረጃ በሊቢያ ከሚገኙ ባልደረቦቻቸው ደርሷቸዋል።

የሊቢያ የባሕር ኃይል ቃል-አቀባይ ጄኔራል አዩብ ቃሲም በበኩላቸው ከኾምስ 100 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ከሚገኘው የባሕሩ ክፍል በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ አስከሬኖች እና 134 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ተናግረዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችልም ትንብያዉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና #እንዲጠነቀቅ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በአብዛኛዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጥሩ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ትንበያዉ የሚያመለክት ሲሆን ይህም ለግብርናዉ የስራ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ታምኖበታል፡፡ ቀድመዉ የተዘሩ እና በእድገት ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የሚገኘዉ እርጥበት በጎ ሚና አለዉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ለቋሚ ተክሎች የዉሓ ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላለቸዉና ለአርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች የግጦሽ እና የመጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

በቀጣይ የሚኖረዉ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተፋሰሶች ላይ ለዉጥ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ በአብዛኛዉ የተከዜ፣ የኦሞ ጊቤ የአባይ፤ የላይኛዉና የመካከለኛዉ አዋሽ እና አፋር ደናክል ተፋሳሾች ከፍተኛ እርጥበት ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
ፎቶ: ፋይል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል ዝግጅቱ ተጠናቋል!
#ሃምሌ22

በኦሮሚያ ክልል የተዘጋጁ ችግኞች #ወደሚተከሉበት ስፍራ እየተጓጓዙ መሆኑ ተገለጸ። በክልሉ ባሉ 3 ሺህ 92 የችግኝ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ችግኞች ወደሚተከሉበት ቦታ እየተጓጓዙ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በየዓመቱ ሐምሌ 19 ቀን የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ዛሬ በቁልቢና በሐዋሳ ከተሞች ተከበረ።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች እንደገለጹት በከተሞቹ በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰላም ተከብሯል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለጹት በዓሉ በቁልቢ ከተማ የተከበረው ያለአላንዳች የጸጥታ ችግር ነበር።

ለዚህም የጸጥታ አካላት ባደረጉት የወንጀል መከላከል ሥራና ኅብረተሰቡ ያደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ በዓሉን በሰላም ለማክበር  እንዳስቻለ ገልጸዋል።

በዓሉ ላይ በስርቆት ተሰማርተው እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሰባት ተጠርጣሪዎችን በሥፍራው የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ከስምንት ወር በሚደርስ እስራት  መቀጣታቸውን  ኮማንደር ስዩም ኣስታውቀዋል።

በተመሳሳይ በሐዋሳ ከተማ ዓመታዊው የንግሥ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃዋሳ #ሃምሌ19

በሐዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት የተከበረው ዓመታዊው የገብርኤል የንግሥ በዓል ሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #መስፍን_ዴቢሶ ገልፀዋል። 

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከአባቶቻችን የተቀበልናትን ከተማ ለቀጣዩ ትውልድ ምቹ እና አረንጓዴ አድርገን የማስተላለፍ ግዴታ አለብን፡፡" ኢ/ር ታከለ ኡማ

ዛሬ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መድረክ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን ጨምሮ ዶ/ር ፍቃዱ ሙሉጌታ እና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ንግግር አድርገዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ለተማሪዎች ዩኒፎርምን እና የት/ት ቁሳቁስን ማቅረብም ሆነ የከተማዋን ልምላሜ ዳግም ለመመለስ ችግኝን የመትከል ስራ በዋነኛነት ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ከተማን ለማስተላለፍ አላማ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ተፈጥሮን መንከባከብ ለራሳችን ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከአባቶቻችን በክብር የተቀበልናትን ከተማ ለቀጣዩ ትውልድ ምቹ እና አረንጓዴ አድርገን የማስተላለፍ ግዴታ አለብንም ብለዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራቸው ባሉ የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ዙሪያም ለተሰብሳቢው ሰፊ ማብራሪያ አድርገዋል፡፡

ከተለያዩ ተቋማት እና የህብረተሰብ ክፍሎች የመጡ ተወካዮች ከኢ/ር ታከለ ኡማ እጅ ችግኝ ተረክበዋል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ ለከተማቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር እንዲያሳዩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴልኮም ማጭበርበር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፦

ተከሳሽ #ኤልያስ_አብዱርቃድር የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በህገ-ወጥ መንገድ ዓለም አቀፍ ጥሪ በማስተላለፍ የኢትዮ ቴሌኮምን ከ518 ሺ ብር በላይ እንዲያጣ በማድረጉ በፈፀመው ወንጀል በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ #የቴሌኮም መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ዉስጥ ለማስገባትና ለመጠቀም ብሎም የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በኮልፌ ቀራኒዎ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ቤት በመከራየት የዲንስታር ጌትዌይ የስልክ መደወያና ቲፒ ሊንክ የሚባል የቴሌኮም መሳሪያዎችን በመጠቀም የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት ከሐምሌ 2010 እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ 95,378.73 ደቂቃ ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን በማስተላለፍ ኢትዮ ቴሌኮም ያገኝ የነበረዉን 18,121.96 ዶላር ወይም 518,568.70 ብር እንዲያጣ በማድረጉ በቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀፅ 9 (1ለ) ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመተላለፍ የተከሰሰ መሆኑን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡ ዐቃቤ ሕግም የሰው ምስክሮች፣ የሰነድና የኢግዚቢት ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ የወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ፣ ተከሳሽን በፈፀመው ወንጀል ጥፋተኛ በማለት ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ500 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

እነ ብርጋዴዬር ጀነራል ተፈራ ፍርድ ቤት ቀረቡ!

ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተሞከረ ከተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ ተጠርጥተው ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ተይዘው የነበሩት ብርጋዲዬር ጀነራል ተፈራ ማሞና ኮሎኔል አማረ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ለሦስት ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ሞት ምክንያት ከሆነው የባህር ዳሩ ክስተት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የቆዩት ሁለቱ ሰዎች በክልሉ የጸጥታ ተቋም ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ከአንድ ወር በላይ በምርመራ ላይ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፤ ይህም ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ምርመራውን እያደረገ ያለው ፖሊስ በአጠቃላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የዘጠና ሰዎችን ቃል መስማቱን ለፍርድ ቤቱ ገልፆ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ አስር ቀን ፈቅዷል።

በዚህም መሰረት በእነ ብርጋዴዬር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ለመመልከት ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 29/2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ ወጣቶች፦

ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ ብስራተ ገብረኤል ት/ቤት እና በእመቤታችን ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በመሰረቱት የሽልማት እና የድጋፍ ማህበር በአይነቱ ልዩ የሆነ ውድ እና አንጋፋ መምህራኖቻችንን የምንሸልምበት እና የምንዘክርበትን የመጪው ታዳጊ ልጆቻችን እና የድሬ ተስፋዎችን በርቱ ጠንክሩ የምንልበት የሽልማት እና የድጋፍ መርሃግብር ቅዳሜ ሐምሌ 20, 2011ዓ/ም በብስራተ ገብርኤል ት/ቤት ለማከናወን ዝግጅቱን ጨርሶ ታዳሚዎቹን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። የማይቀር የማይታለፍ መርሀ ግብር! ከእናንተው ልጆች ለእናንተ ልጆች!
#ሀምሌ21 #2_ቀን_ቀርቶናል!

የዚህ ገፅ #ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ ይህ የናተ ቀን ነውና እሁድ ሃምሌ 21 ከቀኑ በ6:00 ሰዓት በአበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያና ልማት ድርጅት እንድትገኙ ከታላቅ አክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንገናኝ #ሀምሌ21

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡

Google Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡
#update የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በለጠ ካሳ መታሰሩን ንቅናቄው አስታውቋል፡፡ በለጠ የታሰረው ፖሊስ ትፈለጋለህ ብሎት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከሄደ በኋላ ነው፡፡

በተጨማሪ፦

1. አቶ አንተነህ ስለሺ የአብን የአዲስ አበባ የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እና
2. አቶ ንጉሴ ይልቃል የአብን የየካ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ በአዲስ አበባ 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አብን አስታውቋል። ለአቶ አነተነህ እስር ፓሊስ ያቀረበው ምክንያት የአሰምነውን ፎቶ በኪሱ ይዞ ተገኝቷል የሚል ነው ሲልም ንቅናቄው በፌስቡክ ገፁ አሰራጭቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updatesport በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ከጅቡቲ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ በአስቻለው ታመነ ጎል 1-0 አሸንፋለች፡፡ የመልሱ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ በቀጣ ሳምንት ይደረጋል፡፡

IVia Soccer Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ማካሄድ ጀምሯል። በዋነኛነት የኦሮሞን ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ለማጥናት የተቋቋመው ኦሳ፤ ላለፊት 32 ዓመታት ጉባኤውን ከኢትዮጵያ ውጪ ሲያካሄድ ነበር።

ዛሬ በተጀመረውና ለሦስት ቀን በሚቆየው ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዘዳንት ኩለኒ ጃለታ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ስለ ኦሮሞ ታሪክ ያለውን የተዛባ ትርክት ለማስተካከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ከኦሮሞ ቋንቋ እና ባህል ውጪ ስለሌሎች ብሔረሰቦች ታሪክ በማጥናት ጽሁፎች ያዘጋጃል። በዚህም የተቀረው ዓለም ስለነዚህ ማህበረሰቦች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ፕሬዘዳንቷ ተናግረዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ እስካሁን የጥናት ተቋሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በፖለቲካ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ተገዶ የነበረው የጥናት ተቋምና ደጋፊዎቹ "አሸንፈዋል" ብለዋል። "ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ ልጆቻችሁ እንኳን ተመለሱላችሁ" ብለዋል አቶ ሽመልስ በንግግራቸው።

አሁን ያለው ትውልድ የገዳ ሥርዓት እንዲጠነክር እየተካሄደ ያለው ጥናትና ምርምር እንዲቀጥልበት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጥሪ አስተላልፈዋል። "ተሳታፊዎች በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል የጀመረው 'የዜግነት አገልግሎት' ሥራ ላይ እንደውል ሊደግፉ ይገባል" ብለዋል።

የኦሳ ፕሬዘዳንት፤ የጥናት ተቋሙ የጥናት ማዕከል ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ፍኖተ ካርታ ማሳየት አለበት ብለዋል። በጉባኤው ላይ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ምሁራን ይታደማሉ።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በወረብ ቆላ ጽዮን አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላልቅሎ በጣለ ዝናብ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። ሐምሌ 18 ቀን 2011ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ አውሎ ነፋስ እና በረዶ ቀላለቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል። ሐምሌ 18/ 2011 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰው ውሽንፍር የቀላቀለ ዝናብ በርካታ ቤቶች የቆርቆሮ ክዳናቸውን አጥተዋል። ከቤቶቹ በተጨማሪ በጣለው በረዶ ሰብል ላይም ጉዳት ደርሷል። ነዋሪዎቹ የተነቀለው ቆርቆሮ ከአካባቢው እንደጠፋ እና ድጋፍ እንደሚሹም ተናግረዋል። የወረብ ቆላ ጽዮን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ጥጋቡ በለጠ እንደተናገሩት ከ300 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እገዛችንን ከፈለገ ከጎኑ እንቆማን አለ፡፡
.
“የደርግ ሰራዊት” የሚለው የበፊት መጠሪያው “የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት” በሚል ተቀይሮ ከመንግስት እውቅና እንደተሰጣቸውም የማህበሩ መሪዎች ተናግረዋል፡፡ “አሁንም የኢትዮጵያን #አንድነት ለማስጠበቅ ከቆመ መንግስት ጋር አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡

በመላው አገሪቱ 53 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ የማህበሩ ሀላፊዎች በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት ማለታቸውን ከጋዜጣዊ መግለጫው ሰምተናል፡፡ ማህበሩ ከቀድሞዎቹ ሚሊሺያዎች እስከ ከፍተኛ የጦር መኮንንነት የደረሱ አባላት እንዳሉት ተነግሯል፡፡

ምንጭ - ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሐምሌ 22 ቀን የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት👇
https://telegra.ph/PMO-07-26

#አረንጓዴአሻራ
#PMOEthiopia