TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ማካሄድ ጀምሯል። በዋነኛነት የኦሮሞን ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ለማጥናት የተቋቋመው ኦሳ፤ ላለፊት 32 ዓመታት ጉባኤውን ከኢትዮጵያ ውጪ ሲያካሄድ ነበር።

ዛሬ በተጀመረውና ለሦስት ቀን በሚቆየው ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዘዳንት ኩለኒ ጃለታ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ስለ ኦሮሞ ታሪክ ያለውን የተዛባ ትርክት ለማስተካከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ከኦሮሞ ቋንቋ እና ባህል ውጪ ስለሌሎች ብሔረሰቦች ታሪክ በማጥናት ጽሁፎች ያዘጋጃል። በዚህም የተቀረው ዓለም ስለነዚህ ማህበረሰቦች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ፕሬዘዳንቷ ተናግረዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ እስካሁን የጥናት ተቋሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በፖለቲካ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ተገዶ የነበረው የጥናት ተቋምና ደጋፊዎቹ "አሸንፈዋል" ብለዋል። "ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ ልጆቻችሁ እንኳን ተመለሱላችሁ" ብለዋል አቶ ሽመልስ በንግግራቸው።

አሁን ያለው ትውልድ የገዳ ሥርዓት እንዲጠነክር እየተካሄደ ያለው ጥናትና ምርምር እንዲቀጥልበት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጥሪ አስተላልፈዋል። "ተሳታፊዎች በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል የጀመረው 'የዜግነት አገልግሎት' ሥራ ላይ እንደውል ሊደግፉ ይገባል" ብለዋል።

የኦሳ ፕሬዘዳንት፤ የጥናት ተቋሙ የጥናት ማዕከል ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ፍኖተ ካርታ ማሳየት አለበት ብለዋል። በጉባኤው ላይ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ምሁራን ይታደማሉ።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA_2019

ታዋቂው ባለሃብት አቶ ድንቁ ደያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የOSA conference ላይ ተገኝተው ለታዋቂው ምሁር ዶ/ር #ገመቹ_መገርሳና ለባለቤታቸው ዶ/ር አኒሳ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክተዋል። በተጨማሪም ለታዋቂው ምሁርና የገዳ ተመራማሪ ፕሮፌሰር #አስመሮም_ለገሰ የ200,000 ብር ስጦታ አበርክተዋል።

Via THE FINFINNE INTERCEPT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛው ጉባኤ ዛሬ ለ3ኛ ቀን በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

Photo: OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA #ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ #BBC👇
https://telegra.ph/OSA-07-28