TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው..."

ከሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ በሜድትራኒያን #ባሕር ላይ በትናንትናው ዕለት በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከታደጓቸው ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አንድ ከፍተኛ የሊቢያ ባለሥልጣን አስታወቁ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) በበኩሉ በጀልባ የሜድትራኒያን ባሕርን ለማቋረጥ ከሞከሩ 300 ስደተኞች ውስጥ #147ቱ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የአፍሪካ እና የሜድትራኒያን ቃል-አቀባይ ቻርሊ ያክስሊ ዛሬ እንደተናገሩት ኾምስ ከተባለችው የሊቢያ ከተማ ከተነሱት ስደተኞች ውስጥ 150 ያክል በባሕር ላይ ሞተዋል የሚል መረጃ በሊቢያ ከሚገኙ ባልደረቦቻቸው ደርሷቸዋል።

የሊቢያ የባሕር ኃይል ቃል-አቀባይ ጄኔራል አዩብ ቃሲም በበኩላቸው ከኾምስ 100 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ከሚገኘው የባሕሩ ክፍል በመስጠም ላይ ከነበረ ጀልባ አስከሬኖች እና 134 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ተናግረዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia