ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል መንግሥት ላይ በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሕይወታቸው ያለፉ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ሥርዓተ ቀብር ትላንት በባሕር ዳር ተፈፅሟል።
በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀብር ሥነ-ስርዓት ትላንት በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ገብርኤል ተከናውኗል፡፡
የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ከመከናወኑ በፊት ደግሞ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጄር ጄኔራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።
የቀብር ስነ ስርዓቱ በመቐለ ከተማ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሰዋታቸው ይታወሳል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀብር ስነ ስርዓቱ በመቐለ ከተማ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሰዋታቸው ይታወሳል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም" አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)
በጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመካፈል ወደ መቀሌ ያቀኑት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር( ትዴት) መሪ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) "የወጣቶች መንጋ" ባሏቸው ሰዎች ጥቃት እንደተሞከረባቸው ተናግረዋል፡፡ ቢሆንም ግን "አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም" ብለዋል።
የቀብር ስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት የሰማእታት ሃውልት ደጃፍ ላይ ሲደርሱ ከውስጥና ከውጭ የነበሩት ወጣቶች "መግባት የለበትም" ብለው በመቃወማቸውና ጥቃት ለማድረስ በመሞከራቸው የክልሉ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ሊታደጋቸው እንደቻለ ገልፀዋል።
ይህን ተከትሎ ግርግር በመፈጠሩ ወጣቶቹ በወረወሩት ድንጋይ የፖሊስ ኣባላት ላይ እንዲሁም መኪኖች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡
ፖሊስ ግርግሩን ለመቆጣጠርም አስለቃሽ ጭስ ለመጠቀም ተገዶም ነበር ተብሏል። ከግርግሩ በኋላ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) ወደ ዞኑ የፖሊስ ጽህፈት ቤት የተወሰዱ ሲሆን፤ ማምሻውን በእንግዳ ማረፍያ ማሳለፋቸውንም ተናግረዋል።
'ባዶ ስድስት' የሚባል እስር ቤት ውስጥ ታስረዋል የተባለው ስህተት እንደሆነና ዛሬ ጧት ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ እንደሆነም ገልጸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት በዓይደር ሆስፒታል ህክምና እያገኙ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ

አሳዛኝ ዜና‼️
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ከ30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲል ሀሰን ለቢቢሲ ገለፁ።
ጥቃቱ የደረሰው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ 11 ሰዓት ላይ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በጥቃቱ ወደ 16 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀው ወደ 66 ቤቶች በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት በአማራ ክልል የሚኖሩ የጉሙዝ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ያኔም ለቁጥር መግለፅ ከባድ ያሉት ሰው መሞቱን ተናግረዋል።
ጥቃት አድራሾቹ 'ከአማራ ክልል መምጣታቸውን' የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በቁጥጥር የዋለ መሳሪያና ሰው ቢኖርም ምን ያህል እንደሆነ ግን የተጠናከረ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።
በስፍራው አሁንም ስጋት መኖሩን የተናገሩት አቶ አሻድሊ ሀሰን ጉዳዩን ለመፍታት ከመከላከያና ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር እየሰሩ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል።
በጉዳቱ የቆሰሉ ሰዎች በፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልፀዋል።
Via #BBC

#ባህር_ዳር
መንግስት #በባህርዳር ከተማ ተሞከረ ባለው መፈንቅለ መንግስት ክስተቶችን ያስተናገዱ ዋና ዋና ቦታዎችን በካርታዎቹ ላይ መመልከት ይቻላል። ካርታውን ያይን እማኞች ነን ያሉ ግለሰቦችና የመንግስት ባለስልጣናት የተናገሩትን መሰረት ያደረገ ነው።
Via #elu

ዶክተር አምባቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው የተገደሉበት የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት በከተማ ማህል የሚገኝ ባለ 3 ፎቅ ህንጻ ሲሆን ዘወትር ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለታል።

ብርጋዴር ጄነራል #አሳምነው የሚኖሩበትና ትዕዛዝ ሲሰጡበት ነበር የተባለው 'ገስት ሀውስ' በጣና ዳርቻ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት በጫካ የተከበበ ባለ 2 ፎቅ ህንጻ ነው። ይህ ህንጻ ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት 1 ፌርማታ ይርቃል።

የክልሉ ም/ደህንነት ሀላፊና የፕሬዝደንቱ ሹፌር ታገቱበት የተባለውና "መፈንቅለ መንግስት" አድራጊዎች እንደካምፕ የተጠቀሙበት የአማራ ስራ አመራር ተቋም ከገስት ሀውሱ በ3 ፌርማታ እርቀት ይገኛል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ና በአባይ ወንዝ ይዋሰናል።

ከግድያው ቀደም ብሎ የክልሉ የጸጥታና የደህንነት ሀላፊዎች ተሰበሰቡበት፣ ቀጥሎም እገታ ተፈጸመባቸው የተባለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስርያቤት ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ቢያንስ በ3 ወይም በ4 ፌርማታ ይርቃል። በዚሁ ህንጻ በጸጥታ ሀይሎች መካከል ለሰዐታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ የአማራ ቴሌቪዥንና ራዲዮን ጨምሮ አብዛኞቹ የክልሉ መንግስት ቢሮዎች ይገኛሉ።

በቅዳሜ ከፍተኛ ጥቃት ካስተናገዱ የከተማው አካባቢዎች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚኖሩበት ቀበሌ ሶስት የሚገኝ በአጥር የተከለለ የመኖሪያ መንደር (gated community) አንዱ ነው። በፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግቢውን ከሚጠብቁ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ቢያንስ 6 ተገለዋል። በግቢው ከሚኖሩ ባለስልጣናት ጋርም የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የተገደሉባት #ዘንዘልማ 'ከገስት ሀውሱ' በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ 'ሳተላይት' ከተማ ናት። በከተማዋ የግብርና ኮሌጅ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በአብዛኛው ጫት በማምረት የሚተዳደሩ ናቸው። አካባቢውም በጫት ማሳ የተሸፈነ ነው። በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ የኢ.መ.ሠ ምዕራብ ዕዝ ዋና መስሪያቤትና የኢ.አ.ሀ ሰሜን ምድብ ዋና ጣቢያን ጨምሮ የወታደርና የፌ. ፖሊስ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን፣ ቃል አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት በክልሉ ም/ፕሬዝደንት ግብዣ ወደ ከተማው እንዲገቡ ሆኗል። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም።

ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል የአዴፓ ጽህፈት ቤት፣ የክልሉ ምክርቤት እና የአማራ መገናኛ ብዙሐን ኤጀንሲ የሚገኙበት ሲሆን፣ "መፈንቅለ መንግስት" ሞካሪ የተባሉ ሀይሎች የአዴፓን ጽህፈት ቤት መቆጣጠር ችለው ነበር።

#update የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት መታሰራቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርትያን ታደለ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ክርስትያን እንደተናገሩት በትንሹ 56 የፓርቲው አባላት በአዲስ አበባ መታሰራቸውን አስታውቀዋል።
Via #bbc
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #bbc
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ተመራቂ ተማሪዎች የተራቆቱ ቦታዎች ላይ ችግኝ ተክለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ተመራቂ ተማሪዎች ችግኞቹን የተከሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ ይህ የችግኝ ተከላ የተካሄደው በመቱ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሲሆን፣ በዚህ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የዩኒቨርሲተው የበላይ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የ2011 ዓ.ም. የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በተያያዘ ዜና በመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ድጋፍ ስድስት ለሚሆኑ አባወራዎች የመኖሪያ ቤት እተሰራላቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቤቱ የሚሰራላቸውም በሚኖሩበት ቀበሌ በኩል የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ምንም ገቢ የሌላቸው መሆናቸው የተረጋገጠ ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ:- የመቱ ዩኒቨርሲቲ
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ:- የመቱ ዩኒቨርሲቲ
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ ‹‹አሁን ያለው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሠላማዊ፤ ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳን የፀጥታ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ማዋል በሚችልበት ደረጃ ላይ ነው›› ብለዋል፡፡
አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ስጋቶችና ችግሮች አጠቃላይ የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ እንደማይገልጹ ያመለከቱት ኮሚሽነር ሰዒድ ‹‹የተፈጠረው ችግር ድንገተኛነትና ያልተለመደ መሆን በኅብረተሰቡ ሥነ-ልቡና ላይ ችግር የፈጠረ ቢሆንም ሕዝቡ አመዛዛኝ በመሆኑ በፍጥነት ከችግሩ መውጣት ተችሏል›› ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ሕዝብ ለአካባቢው ሠላም ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጫቸው ያነሱት ኮሚሽነር ሰዒድ ‹‹በተለይም ወጣቱ ትናንት የነበረውን የክልሉን ከፍተኛ መሪዎች የቀብር ሥነ- ስርዓት በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያደረገው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ምሥጋና ያቀርባል›› ብለዋል፡፡
Via #AMMA

#update የአማራ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ፣ አራት የክልሉ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ለአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ድርጅት እንደገለጹት፣ የልዩ ኃይሉ ዋና አዛዥ ጨምሮ ሌሎች በስም ያልተገለጹ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ታስረው በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡
አመራሮቹ በክልሉ ፕሬዚዳንት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እና በሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው እዘዝ ዋሴ፣ እንዲሁም በክልሉ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር ግንኙነት ይኑራቸው ወይም አይኑራቸው የሚለውን ለማጣራት መታሰራቸውን ኮሚሽነር አበረ አስታውቀዋል፡፡
ኮሚሽነሩ እንዳሉት በግድያና በተቀነባበረው ሴራ በመሳተፍ ከተጠረጠሩ 190 የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መካከል፣ ከ170 በላይ የሚሆኑት በፈቃደኝነት እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በሰጡት ማሳሰቢያ በቅርቡ የተመለመሉ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትም ሆኑ ነባሮቹ፣ ዋና ኃላፊነታቸው የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ እንደሆነና ከግለሰቦች አምላኪነት መውጣት አለባቸው ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ሕዝብም የልዩ ኃይሉ የፖሊስ አባላትን በእኩል ዓይን እንዲመለከት አሳስበዋል፡፡
ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በባህር ዳር ከተማ በርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እና የአደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ ሲገደሉ፣ የክልሉ ዓቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ሕክምና ሲከታተሉ ቆይተው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
የሦስቱም የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሥርዓተ ቀብር በባህር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ረቡዕ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚፈጸም፣ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡
Via #ሪፖርተር

ጄነራሎቹን ገድሏል ስለተባለው የግል ጠባቂ...
ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ምሽት ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ሰዓረ መኮንን ከአጋራቸው ጄነራል ገዛዒ አበራ ጋር በገዛ ጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።
በቀጣዩ ቀን የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ ጄኔራሉን እና ወዳጃቸውን በጥይት መትቶ #ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ አስታውቆ ነበር።
ሰኞ ከሰዓት ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ጄኔራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱን ተናገሩ። ሰኞ ምሽቱን ደግሞ ፌደራል ፖሊስ ቀደም ሲል ራሱ የሰጠውን መግለጫ አስተባብሎ ጠባቂው በሕይወት እንደሚገኝ አስታውቀ።
እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች እንዴት ሊወጡ ቻሉ? ጄነራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂስ አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል? የጠቅላይ ሚንሰትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉስ ጥላሁን፦
''በአዲስ አበባም ይሁን በባህር ዳር የተፈጠረው ችግር ድንገተኛ ነው፤ አደናግጧል፤ አደናብሯል። ሁሉም መረጃ በአንድ ግዜ አይገኝም። በወቅቱ የሚደርሱ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሃን ሲሰጡ ነበረ። መረጃዎች የሚስተካከል፤ የሚታረም ነገር ሊኖራቸው ይችላል። ሰው ነው የሚሰራው፤ ሰው ነው የሚናገረው። መረጃው ደግሞ ታቅዶ፣ ተደራጅቶ፣ ተገምግሞ የሚሰጥ ዓይነት መረጃ አይደለም። እንደዚህ አስቸኳይ በሆነበት ሰዓት፣ ሕብረተሰቡ መረጃ በሚፈልግበት ሰዓት፣ መገናኛ ብዙሃን በሚያጣድፉበት ሰዓት እንዲህ ዓይነት ስህተቶች አያጋጥሙም ማለት አይደለም'' ይላሉ።
ተጠርጣሪው እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደዋለ እና አሁን ስለሚገኝበት ሁኔታ የተጠየቁት አቶ ንጉሱ፤ ''የግል ጠባቂው በጄነራሎቹ ላይ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ተታኩሶ ነበረ። በዚህም የተኩስ ልውውጥ እሱም ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት እና ወደ ህክምና ሥፍራ ተወስዶ ጥበቃ እየተደረገለትና የጤና ክትትል እያደረገ ነው'' ነው ሲሉ መልሰዋል።
''የጤንነቱን ጉዳይ ሃኪሞች፤ የጥበቃውን ሁኔታ ደግሞ የጸጥታ መዋቅሩ እየሰሩ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ወደፊት የሚጠሩ ይሆናሉ'' በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል...
የአማራ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ፣ አራት የክልሉ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ፣ አራት የክልሉ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ170 በላይ የሚሆኑት እጃቸውን ሰጥተዋል...
ባለፈው ቅዳሜ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በግድያና በተቀነባበረው ሴራ በመሳተፍ ከተጠረጠሩ 190 የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መካከል፣ ከ170 በላይ የሚሆኑት በፈቃደኝነት እጃቸውን ሰጥተዋል ተብሏል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው ቅዳሜ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በግድያና በተቀነባበረው ሴራ በመሳተፍ ከተጠረጠሩ 190 የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መካከል፣ ከ170 በላይ የሚሆኑት በፈቃደኝነት እጃቸውን ሰጥተዋል ተብሏል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጄኔራሎቹ ገዳይ...
''የግል ጠባቂው በጄነራሎቹ ላይ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ተታኩሶ ነበረ። በዚህም የተኩስ ልውውጥ እሱም ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት እና ወደ ህክምና ሥፍራ ተወስዶ ጥበቃ እየተደረገለትና የጤና ክትትል እያደረገ ነው። የጤንነቱን ጉዳይ ሃኪሞች፤ የጥበቃውን ሁኔታ ደግሞ የጸጥታ መዋቅሩ እየሰሩ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ወደፊት የሚጠሩ ይሆናሉ'' አቶ #ንጉሱ_ጥላሁን ለBBC የተናገሩት

በርካቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው...
ፖሊስ በአዲስ አበባ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር እያዋለ መሆኑን DW የከተማይቱን ነዋሪዎች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብንና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ/አዜማ አባላት እንደታሰሩም ተጠቁሟል፡፡ ጸጥታ ሃይሎች በከተማዋ #ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሆነ የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
Via #dw/#wazema