TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ👆
/StopHateSpeech/

የጅማ ዩኒቨርስቲ የTIKVAH ቤተሰቦች በመጀመሪያው ጉዟቸው ትልቁን #ኃላፊነት በተወጡበት እና ትልቅ ስራዎችን በሰሩበት የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ቆይታ #በጥላቻ_ንግግሮች ዙሪያ ልዩ የግንዛቤ መስጫ ማድረክ ተዘጋጅቶ ነበር።

ምስጋና፦

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች
ለወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች
ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች
ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች
ለኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አመራሮች

ረጃጅም ርቀቶችን በብቃት ላሽከረከሩ፦ ሁሉም ሹፌሮች!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: የቀድሞው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ/OBN/ ዋና ዳይሬክተር መሃመድ አዴሞ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጋር #ሃረማያ_ዩኒቨርስቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ፦ TIKVAH-ETH ከየትኛውም የመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ጋር ግንኙነት የለውም። TIKVAH-ETH ትክክለኛ የኢትዮጵያን ቀለም የያያዙ #የጀግና ሀገር ወዳድ ወጣቶች ስብስብ ነው።

በተለይ የStopHateSpeech ጉዞ ከየትኛውም ወገን ድጋፍ የለውም፦ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡን #መኪና ብቻ ነው። አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቸው ለጉዞ የሚሆን ጥቂት ገንዘብ/ለድንገተኛ ጉዳዮች/ የሚሰጡት ካልሆነ ምንም አይነት አበል የለውም/እስካሁን የተሰጠውንም በቀጣይ ሳምንት ይፋ አደርጋለሁ/። ተማሪዎች የሚመገቡት በዩኒቨርሲቲ ካፌ ነው። "አበላችን እና ክፍያችን #ፍቅር ነው" ይህ ነው ቃላቸው!!

ሌላው፦
√በራሪ ወረቀት፣ ባነር የሚያሳትምልን ድርጅት ባለመኖሩ በራሳችን ወጪ ነው የምንሰራው።
√ተማሪው በጉዞ መሃል ለሚያፈልግው ወጪ ከራሱ ከኪሱ ነው የሚጠቀመው።
√ቢታመም እንኳን ገንዘብ ሳይኖረው ነው ለእናት ሀገር ሰላም የሚጓዘው።

ወጣቶቹ ትምህርታቸውን ጥለው፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች ተጎድተው፣ ተንገላተው፣ ተርበው፣ ለፍተው እየዞሩ ያሉት ለፍቅር ነው፤ ለትውልዱ ሰርቶ ለማለፍ ነው፤ ሀገር ሲበጠበጥ ቁጭ ብሎ ላለማውራት ነው፤ ከህሊና እዳ ነፃ ለመሆን ነው፤ ለሀገሬ ምን ልስራላት በማለት ነው፤ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መምጣት ከወጣቶች ውጪ አማራጭ ስለሌለ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን #ወጣቶች የሚያስታውስበት ቀን እሩቅ አይደለም፤ ለምን እንደሚዞሩም የሚረዳበት ቀን ሩቅ አይሆንም፤ በሀገራችን ለተፈጠሩ እና እየተፈጠሩ ላሉ ግጭቶች ዋነኛው መንስኤ የጥላቻ ንግግር እና ጥላቻ ነው።

•ኦሮሚያ
•ትግራይ
•አማራ
•ደቡብ በፍቅር አቅፍችሁ #ስለተቀበላችሁን እናመሰግናለን!!

ኑ ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde
TIKVAH-ETH በቀጣይ ስራዎች ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እና ያለውን ጠንካራ ጎን ይዞ እንዲሄድ የእናተ አስተያየት ወሳኝ ነው። በቻናሉ ስራዎች ላይ ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት እና ሃሳብ በጨዋ ደንብ ላኩልኝ። ምን አጠፋን?? ምን ይስተካከል?? ምን ጥሩ ጎን አያችሁ?? @tsegabwolde /0919743630

በተጨማሪ እኚህ አዳዲሶቹ ቻናሎች ናቸው፦

TIKVAH-ETH/Sport/👇

https://t.iss.one/tikvahethsport

TIKVAH-ETH/AFAAN OROMOO/👇

@tikvahethAFAANOROMOO
አክሱም ዩኒቨርሲቲ👆

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቋሙ ወደየመጡበት እንዲሸኛቸው በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ ይገኛሉ። በግቢው ውስጥ ከተፈጠረው አለመረጋጋት በኃላ ተማሪዎቹ ላለፉት ቀናት በአዳራሽ ውስጥ እያደሩ እንደሚገኙ ገልፀው፤ የደህንነት ስጋት ስላለባቸው እና አሁን ባለው ሁኔታ ትምህርት መቀጠል እንደማይችሉ በማስገንዘብ ግቢው እንዲለቃቸው ጠይቀዋል።

ለሁለት ጊዜ ውይይት የተደረገ ቢሆንም ከአመራሮች ጋር ስምምነት ላይ ሊደርስ አልቻለም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሪ ቤተሰቦች...

"ፀግሽ አክሱም ዩንቨርስቲ እስካሁን መፍትሄ አላገኘም ልጆቻችን በርሀብ ሊያልቁ ነው። በር ተዘግቶባቼው ነው ያሉት ቤተሰብ #ተጨንቀናል ምን እንደምናረግ አናውቅም ፀግሽ መፍትሄ ካለህ..."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-SPORT
#update በትግራይ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የወረዳዎች፣ የከተሞችና ክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት ተጠናቋል።

@tikvahethsport
#update ሀገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ፈተናዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ መላኩ መሃሪ እንደተናገሩት የዚህ ዓመት ፈተና በተሳካ መልኩ እንዲፈፀም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል።

ለሥራው መሳካት የሚያግዙ የጸጥታ አካላት እና ተሽከርካሪዎችም ተመድበዋል ነው ያሉት መምሪያ ኃላፊው።

የክልል አቀፍም ሆነ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ደርሰው ተገቢ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነም ታውቋል።

በዞኑ የተመደቡ ሁሉም የፈተና ተጠሪዎች እና ተቆጣጣሪዎች ወደ ተመደቡበት ቦታ እየገቡ ለተማሪዎች ማብራሪያ እና ማስገንዘቢያ በመሰጠት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል በመደበኛና በግል 15 ሺህ 443 ተማሪዎች፣10ኛ ክፍል 36 ሺህ 174 ተማሪዎች እንዲሁም 8ኛ ክፍል በመደበኛ፣በማታና በግል 46 ሺህ558 ተማሪዎች በ556 ትምህርት ቤቶች እንደሚፈተኑ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት #መፍትሄ ይስጠን...
/የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች/

√በርካታ ተማሪዎች ከዶርማችን ውጪ ላለፉት ቀናት በአዳራሽ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ እያደርን ነው ግቢው በሩን ከፍቶ በሰላም ይሸኘን ሲሉ ተማሪዎች #በሰላማዊ_ሰልፍ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ምላሽ ካገኘሁ ወደናተ አደርሳለሁ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"National Exams will be administered for grade 10 from Sene 3-5,grade 12 on Sene 6,7,10 & 11 & grade 8 from 12-14/2011E.C. Good luck!" Araya G/Egziabher D/G NEAEA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት 8 ዕጩ አባላትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው መጋቢ ዘሪሁን ደጉ መንግስቴን፣ አቶ መላኩ ስብሀት በዳኔን፣ አቶ ውብሸት አየለ ጌጤን፣ አቶ ብርሀነ ሞገስ ፍቅርን፣ አቶ ደመወዜ ማሞን፣ ወ/ሮ ብዙወርቅ ከተተን፣ ዶ/ር ጌታሁን ካሳን እና አቶ አበራ ደገፉ ነገዎን እንዲሁም አንድ ተጠባባቂን በዕጩነት መርጧል፡፡

የመልማይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ እንደተናገሩት 8ቱን ዕጩ አባላት ለመምረጥ በስልክ፣ በፋክስ እና በኢሜል የቀረቡት 200 ገደማ ተጠቋሚዎች በ3 የማጣሪያ ምዕራፎች እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡

ዕጩዎቹ በህግ፣ በፖለቲካ ሳይንስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ከምርጫ ጋር ተያያዥ በሆኑ መስኮች ስለመማራቸው በመጀመሪያው የማጣሪያ ምዕራፍ ታይቷል፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴው የመረጣቸውን 8 አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚልክና ለቦታው የሚፈለጉት የመጨረሻዎቹ 4 ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚለዩ ተገልጿል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላም እና የልማት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎችን ከሰኔ 3/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉበሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች ተረጋግተው በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የተማሪዎችን ስነ-ልቦና የሚያጠናክሩ ሥራዎችን በመከወን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርኣያ ገ/እግዚአብሄር የዘንድሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 03/2011ዓ.ም እስከ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10 እና 11/2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸው ለ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 1,277,533 እና ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 322,317 ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የፈተና ህትመትና ሌሎችን ጨምሮ እስከ ሥርጭት ያሉ ሥራዎች ከዚህ በፊት ከነበሩት ዓመታት በተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዘገባ ያመለክታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
YOU DON'T NEED TO BE
A DOCTOR TO SAVE LIVES
GIVE THE
GRACIOUS GIFT OF LIFE.
JUNE 09/2019 Sunday / ሰኔ 02/2011እሁድ[4:00pm-7:00pm]
#update በዱባይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ከመንገድ ምልክት ጋር በመጋጨቱ በደረሰ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ለጉዳት ተዳርገዋል። ሟቾቹ የተለያየ አገራት ዜጎች እንደሆኑም ታውቋል።

መለያ ቁጥሩ በኦማን የተመዘገበው ተሽከርካሪው አደጋ ሲደርስበት 31 ሰዎችን አሳፍሮ በሸክ መሐመድ ዛይድ ጎዳና ላይ እየተጓዘ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።

ከሟቾቹ መካከልም ስምንቱ የሕንድ ዜጎች መሆናቸውን የሕንድ ባለሥልጣናት አረጋግጠናል ብለዋል።

በዱባይ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ የሟቾቹን ሕንዳውያን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸውም አሳውቀዋል፤ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሕንዳውያንም ህክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

የ50 ዓመቱ የአውቶብሱ አሽከርካሪ ቀላል ጉዳት ያጋጠመው ሲሆን ሕክምና እየተደረገለት ይገኛል።

የዱባይ ፖሊስ በይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ በተፈጠረው አደጋ ማዘኑንና ለተጎጅ ቤተሰቦችም መፅናናትን እንደሚመኝ አስፍሯል።

የፖሊስ ኃላፊው ማጅ አብዱላህ ካሊፋ አል ማሪ "አንዳንድ ጊዜ ተራ ስህተት አሊያም ግድ የለሽነት እንዲህ ዓይነት አስከፊ አደጋዎችን ያስከትላሉ" ብለዋል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ሲሆን ስለ አደጋው ዝርዝር ሁኔታ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ አሽከርካሪው የመንገድ ምልክትን በመጣሱ በድንገት መንገድ ለመቀየር ሲል አደጋው እንዳጋጠመው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የኦማን የአውቶቡስ አምራች ምዋሳላት " በአደጋው የተሰማቸውን ሃዘን የገለፁ ሲሆን ከሙስካት ዱባይ የሚሰጡትን አገልግሎት ለጊዜው ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ...

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ማዕከል /UNESCO/ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ 12 ቱ የኢትዮጵያ የፅሁፍ ቅርሶች ''ግዕዝና ስነ ፈውስ'' በሚል መሪ ቃል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው አምስተኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባዔ ላይ ከቀረበ አውደ ርዕይ የተወሰደ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ለመለየትና ለመመልመል የተቋቋመው ኮሚቴ የሥራ ሂደትን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ውሳኔ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት እና ተማሪዎች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia