TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.3K photos
1.58K videos
216 files
4.32K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 71ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2012 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikavhethiopia
#update ሱዳን ውስጥ ሁለት የአማፂያን መሪዎች እና አንድ የተቃዋሚው መሪ በፀጥታ ኃይላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተቃዋሚ ኃይሎች ገለፁ። ይህ የሆነው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ወታደራዊው ምክር ቤት እና ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር ሱዳን መዲና ካርቱም ላይ ከተወያዩ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ዓርብ ዕለት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሰሜን ሱዳን ህዝብ የነፃነት ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ ኢስማኤል ጃላብ እና የታጠቀው ቡድን ቃል አቀባይ ሙባራክ አርዶል በቁጥጥር ስር የዋሉት ከስብሰባው ጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደሆነ ተዘግቦአል። የተቃዋሚው መሪ ሞሀመድ ኤስማት እና የአማፂያን መሪዎቹ አባላት የት እንደታሰሩ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሃገሪቱ የታየዉ ኃይል የቀላቀለ ብጥብጥ እንዲያበቃ እና ሀገሪቱም ወደ ትክክለኛው የዲሞክራሲ መንገድ እንድታመራ ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣኑን በሲቪል ለሚመራ ኃይል እንዲያስረክብ ግፊት አድርገዋል። ካለፈው ሰኞ አንስቶ በከተማዋ በነበሩ ግጭቶች ቢያንስ የ60 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ...

ዛሬ በተጨዋች ወንደሰን ዮሐንስ መኖሪያ ቤት የሰፈሩ ልጆች እና ጓደኞቹ የሻማ ማብራት እና ፀሎት ፕሮግራም እያካሄዱ ይገኛሉ። ወንደሰን ከቀናት በፊት ነቀምት ከተማ ውስጥ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉ አይዘነጋም።

በድጋሚ ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት እንመኛለን!!

Via Yitba
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዉ በመንግስት የፀጥታ አካላት የተከለከለ መግለጫ አለመኖሩን ገለፀ፡፡

ጌት አማካሪዎች የንግድና ኢንቨስትመንት የተባለ ድርጅት ግን በዚህ ሳምንት ለሁለት ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳልሰጥ ተከልክያለሁ ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢቲቪ እንደተናገሩት አዲስ የሚቋቋምን የቴሌቭዥን ጣቢያ አስመልክቶ ትናንት በሂልተን ሆቴል ሊሰጥ የነበረዉ መግለጫ በሆቴሉ የፀጥታ ሀላፊ በኩል መግለጫዉ በመንግስት አካላት ስለመከልከሉ ተነግሮናል ብለዋል፡፡

የሂልተን አዲስ ሆቴል በበኩሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉ የተከለከለዉ ከሆቴሉ ጋር ውል የሌላቸዉ ግለሰቦች መግለጫዉን እንሰጣለን በማለታቸዉ ነዉ ብሏል፡፡

የሆቴሉ ጊዜአዊ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ስለሺ ተሰማ መግለጫዉ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚሰጥ የተፈፀመ ዉል እንደሌላቸዉ ለአዲስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብሎክ 21 የተማሪዎች ህንፃ ላይ ድንገተኛ እሳት እንደተነሳ ተማሪዎች ጠቁመዋል። የሚመለከታችሁ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታሰርጉ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋን ኦሮሞ በሃያ ትምህርት ቤት ሊሰጥ ነው...

በቀጣዩ ዓመት አፋን ኦሮሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በሃያ ትምህርት ቤት ለመስጠት መታቀዱን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናገሩ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቁጥሩ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ህዝብ እንደሚኖር የተናገሩት ዶክተር ግርማ፣ በዚህ ዓመት በሃያ ትምህርት ቤት ይሰጣል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም፤ ከሰላም መደፍረስ የተነሳ አስር ትምህርት ቤት ብቻ እንዲወሰን መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ይህን ቁጥር በቀጣዩ ዓመት ከፍ በማድረግ ወደሃያ ለማድረስ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና ቤኒሽንጉል ጉምዝ አማካይነት የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ እንዲቋቋም በመደረጉ በኦሮሚያ በኩል የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው በአፋን ኦሮሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ ያስቻለ በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

በዚህ ዓመት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በአስር ትምህርት ቤት በአፋን ኦሮሞ ትምህርት እንዲሰጥ መደረጉ እንደ ትልቅ ስኬት እንደሆነም ዶክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ባለፈው በሁለቱ ክልልች የተደረገው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ወቅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመሆን ተዘዋውረው ትምህርት ቤቶቹን ማየታቸውን የገለፁት ዶከተር ግርማ፣ የረጅም ጊዜ የነበረው ጥያቄ ተመልሶ ማየት መቻላቸውን ጠቅሰው፤ ትምህርት ቤቱን ያዘጋጁት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆኑን ተናግረው፤ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ መምህራኑን ወስዶና አሰልጥኖ እንዲያስተምሩ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና...

በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዮካራ በተባለ ቀበሌ ዛሬ ረፋዱ ላይ ከቀኑ 4 ሰዓት በደረሰ የመሬት ናዳ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የወረዳዉ ዋና አስተዳደሪ አቶ እንግዳወርቅ ገነቱ ለfbc እንደገለፁት፥ ሰባት የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ሸክላ ለመስራት የሚሆን አፈር ለማዉጣት አፈር በመቆፈር ላይ ሳሉ ነው ናዳው የደረሰው አንዲት ወጣትም ከአደጋው ህይወቷ መትረፉንም ነው ያመለከቱት። ሟቾች ሁሉም ሴቶች ሲሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸዉ።

በህይወት የተረፈችዉ ወጣት በአሁኑ ሰዓት በአረካ ከተማ በሚገኘዉ ዱቦ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለች ትገኛለች።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ...

"የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነርሲንግ ማስተባበሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ምንችል ታምር ለጎ/ዩ/አጠ/ሰፔ/ሆ/ል/ጤ/ሙ/ማህበር እንደገለፁት በአለም አቀፍ እና በሀገራችን ደረጃ የሚከበረውን “የነርሰ ቀንን “ ሰኔ 4/2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ይከበራል፡፡ ቀኑም የሚከበረው “የሞያ ትስስር ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ነው፡፡የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች ማህበር ለሁሉም የሀገራችን ነርሶች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።"

Via Endal Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብሎክ 21 የተማሪዎች ህንፃ ላይ ድንገተኛ እሳት እንደተነሳ ተማሪዎች ጠቁመዋል። እስካሁን የደረሰ አካል እንደሌለ እየሰማን ነው። የሚመለከታችሁ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታድርጉ በድጋሚ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

አርባምንጭ ከተማ 03 ሰልባጅ ተራ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተነስቷል። የሚመለከታችሁ አካላት ጥቆማው ይድረሳችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የእሳት አደጋ ደረሰ። በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የደረሰው የእሳት አደጋ ዛሬ ሰኔ 1/2011 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ አካባቢ ጀምሮ ነው።

በወንድ ተማሪዎች መኝታ ቤት አካባቢ በቁጥር 21 እና 27 በሚል ተለይተው የሚታወቁ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎች በእሳቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ በስልክ የገለፁት የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመድ መሃመድ በተማሪዎች ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተናግረዋል።

እሳቱን ለማጥፋት ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርና ከሃበሻ ቢራ ፋብሪካ በትብብር በተገኙ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች በመታገዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የነገሩን አቶ አህመድ ወደ ሌሎች ህንፃዎች ሳይሸጋገር ለመቆጣጠር እንዲቻል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። ዳይሬክተሩ የቃጠሎው ምክንያት በውል እንዳልታወቀና እንደሚጣራ አስታውቀዋል።

ሰሞኑን መጠነኛ የተማሪ ግጭቶችን ያስተናገደው ዩኒቨርስቲው በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው ባላቸው 58 ተማሪዎችን በስንብት በእገዳና በማስጠንቀቂያ መቅጣቱ የሚታወስ ነው።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ~ሲቀላ ገበያ👆

በአርባ ምንጭ ከተማ ሲቀላ ገበያ የተነሳው የእሳት አደጋ የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ የእሳቱ ኃይል እየቀነሰ እና እየተዳከመ ይገኛል።

Via Bonke's
Photo: Lij
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባምንጭ ከተማ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል። የደረሰውን የጉዳት መጠን በተመለከት በነገው ዕለት አጣርቼ ወደእናተ አደርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
/#ሼር/#Share/

"አጠገባችሁ ያለው ተማሪ ወንድማችሁ እንደናንተው ከምስኪን ቤተሰብ የተገኘ ፣ ጭራሮ ለቅማ፣ ጠላ ሽጣ፣ ግፋ ቢል በጉሊት ችርቻሮ ወይም በመንግሥት ስራ ከእጅ ወደአፍ ኑሮ የምትኖር የአንተንው እናት የምትመስል እናት/ ሀርሜ አለቺው። እንዳንተው በእርሻ ፣ በመለስተኛ ንግድ ወይም በመንግሥት ስራ የሚተዳደር አባት፣ እንዳንተው ነገ ተመርቀህ ለራስህና ለኔ ተሳልፍልኛለህ ብሎ ተስፋ ያሚጥልበትና የሚያዝንለት ወገን ያለው ወገንህ ነዉ። እናም ማንም ከየትም ሆኖ በሚፈጥርልህ በዉል እንኳ ተለይቶ በማይታወቅ ምክንያት ውንድምህን አታጥቃው። እመነኝ በዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ትርፍ አልባ ግጭት ደም ገብረህ፣ ወንድምህን ገድለህ በፀፀት አለንጋ እየተገረፍህ እድሜህን ትማቅቃለህ። አሊያም ራስህ ሰለባ ሆናህ የራስህንና የወገንህን ህልም ተጨልማለህ። ባይሆንስ ምንም ውስጥ ከሌለበት ወንድምህ #ተባልተህ ትርፉ ምንድነው? ይሉቁንስ በዚህ የማይደገመውን የካምፓስ ህይወት አጋጣሚ በጋራ በመሆን #ለሀገራችሁ ችግር መፍትሔ ፈልጉ። እመነኝ አንድ ሆነህ ከቆምህ ከፊትህ ብሩህ ተስፋ አለ!!"

Via ዶክተር ታደሰ ቀነአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በገዛ ሰራተኞቹ ወሊሶ ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰ ተድርጎ በሀሰተኛ ዶክመንት 47,000 ብር የካሳ ክፍያ ተወስዶብኛል አለ። 7 ሰራተኞቹም የፖሊስ ምርመራ ላይ ናቸው።

Via Tesfaye Getnet/ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ ሰኔ 3 ቀን 2011ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያ ይጀመራል፤ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

በፈተና ጊዜ የፈተና #ትዕዛዛትን በማክበር ከጭንቀት ራስን ነፃ ማድረግ እንደሚቻል የሥነ-ልቦና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ በፈተና ጊዜ የፈተና ሕግና ደንብን መጣስ በፈታኙ ‹‹ታየሁ-አልታየሁ›› የሚል ጭንቀት ውስጥ ስለሚከትት የፈታኞችን ትዕዛዝ ማክበር በነፃ አዕምሮ ጥያቄችን ለመመለስ ያስችላል፡፡

ፈተና መምህራን ተማሪ ለመጣል የሚያዘጋጁት መሰናክል ሳይሆን አንድ ተማሪ ያለበትን የክፍል ደረጃ አጠናቅቆ ለቀጣዩ እርከን ብቁ መሆን አለመሆኑ የሚመዘንበት ነው፡፡ ስለሆነም በክፍል ደረጃው አንድ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኝ ተማሪ ሊመልሳቸው የሚችሉና ከአጠቃላይ የትምህርቱ ዓለማ የሚመዘዙ የፈተና ጥያቄዎች ስለሚዘጋጁ ተማሪዎች ሊሰጉ አይገባም፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁ የፈተና ጥያቄዎች በክፍል መምህራን ከሚዘጋጁ ጥያቄዎች የተሻለ ለብዙዎቹ ተማሪዎች የሚቀልሉ እንደሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ምክንያቱም በብዙ ጥንቃቄና በበርካታ ሰዎች የሚዘጋጁና የሚገመገሙ በመሆናቸው ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሰዋስውና የፊደል ግድፈታቸው የቀነሰ፣ አብዛኞቹ ተማሪዎች ሊረዷቸው በሚችሉ ቋንቋዎች የሚዘጋጁ፣ ከጥቅል የትምህርቶቹ ዓላማ አንጻር የሚዘጋጁ በመሆናቸው ነው፡፡

ተማሪዎች ተረጋግተው ለመሥራት እንዲችሉ ወደ ትምህርት ቤት ለፈተና ሲሄዱ በአግባቡ የተቀረጹ እርሳሶች፣ መቅረጫ፣ መታወቂያ፣ የፈተና መግቢያ (አድሚሽን) ካርድ ይዘውና የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ለብሰው ስለሆነ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተው መሆን አለበት፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሱዳን ባለስልጣናት የተቃዋሚ መሪዎችን እያሰሩ ነው...

በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ ሱዳን ካርቱም ደርሰው ከተመለሱ በኋላ የሱዳን የደህንነት ኃይሎች ተቃዋሚዎችን ማሰር መጀመራቸው ተሰማ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሱዳን አቅንተው የነበረው ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለውን የወታደራዊ ምክር ቤት ባለስልጣናትንና ተቃዋሚዎችን ለማሸማገል ነበር።

ነገር ግን የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪው መሐመድ ኢስማት አርብ እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተገናኙ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

ዛሬ ማለዳም ኢስማኤል ጃላብ እና ቃል አቀባዩ ሙባረክ አርዶል የተሰኙ የተቃዋሚ ቡድን መሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ተቃዋሚዎቹ የበርካቶች ደም ከፈሰሰ በኋላ የሚደረጉ ውይይቶችን ስለማያስተማምኑ አንቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል።

የወታደራዊ ምክር ቤት የሲቪል አስተዳደር ለመመስረት ቢስማማም ነገር ግን ተቃዋሚዎች የጊዜ ገደቡ ላይ ባለመስማማታቸውና በአድማው በመቀጠላቸው ግጭቶች ተፈትረው ከመቶ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በፀጥታ ኃይሉ ተገድለዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት ማታ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ለሊት 8:00 መጥፋቱ ተረጋግጧል። ትናንት ሰኔ 01/2011 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ነበር እስካሁን ምክንያቱ #ያልታወቀው የእሳት ቃጠሎ የተከሰተው። በግቢው ውስጥ በሁለት ህንፃዎች ላይም ጉዳት አድርሷል። በእሳት ማጥፊያ መኪና እና የልዩ ኃይል እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ጨምሮ በሰው ኃይል ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ጥረት ተደርጎ ነበር፤ ነገር ግን እሳቱ የህንፃዎቹን የመጨሻ ክፍል ሙሉ በሙሉ ካወደመ በኋላ ሌሊት 8:00 አካባቢ መጥፋቱን ተሰምቷል፡፡
የተቃጠሉት ህንፃዎች የተማሪዎች መኖሪያ ነበሩ። በሰው ህይወትም ሆነ አካል ላይ ጉዳት እንዳልደረሰም ታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...

"ይሄ ነው እንግዲ የተነሳው እሳት ያደረሰው እልቂት። እሳቱ ከተነሳ ከሁለት ሰዓታት በኋል የደረሰው የከተማው የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና በውስጡ ውሃ ይያዝ አይያያዝ ባይታወቅም ከ10 ደቂቃዎች በላይ እሳቱን ለማጥፋት እርዳታ ማድረግ አልቻለም። ይሁን እንጂ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቦቴዎች እንዲሁም ግዙፍ የሆነው የኤርፖርት የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና እሳቱን ለማጥፋት ህይወቱን መሰዋእት ካደረገው ከአባባቢው ወጣቶች በመቀጠል የአንበሳውን ድርሻ ወስዳል።" ፀጋዘአብ ከአርባ ምንጭ

@tsegabwolde @tikvahethiopia